የ«ኢጋድ»እና የ«ኤስ ፒ ኤል ኤም» ውይይት
ለደቡብ ሱዳን ውዝግብ መፍትሔ የማፈላለጉ ጥረት ከእስር የተፈቱት 11 የመንግሥቱ የቀድሞ ባለሥልጣናትም የአጠቃላዩ የሰላም ድርድርሩ አባል መሆን እንዳለባቸው በመታመኑ ተቀናቃኝ ወገኖችን ለማስታረቅ የሽምግልና ጥረት ከጀመረው የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ፣ ኢጋድ ተወካዮች ጋ ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት ጀመሩ።
ለደቡብ ሱዳን ውዝግብ መፍትሔ የማፈላለጉ ጥረት ከእስር የተፈቱት 11 የመንግሥቱ የቀድሞ ባለሥልጣናትም የአጠቃላዩ የሰላም ድርድርሩ አባል መሆን እንዳለባቸው በመታመኑ ተቀናቃኝ ወገኖችን ለማስታረቅ የሽምግልና ጥረት ከጀመረው የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ፣ ኢጋድ ተወካዮች ጋ ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት ጀመሩ።
ኤርትራዊው ደራሲ ሰለሞን ፀሓዬ በትግርኛ ቋንቋ በቃል የሚነገሩትን ባህላዊ አባባሎች እና ትውፊቶችን በማጥናት በመጽሐፍ መልክ አሳትመዋል።
የመጀመሪያ የህክምና ርዳታ ሰዎች በየትኛዉም አጋጣሚ የሚደርስባቸዉ አደጋ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል የሚሰጥ ጊዜያዊ ርዳታ ነዉ።
በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ዘንድሮ እንደ ሊቨርፑል ልቡ የተሰበረ ቡድን የለም። 24 ዓመታት ጠብቀውም ዋንጫ የመጨበጥ ህልማቸው እንደ ጉም በኗል። ማንቸስተር ሲቲ በሦስት ተከታታይ የጨዋታ ዘመን ለ2ኛ ጊዜ ዋንጫውን ማን ደፍሮ ከእጄ ሊነጥቅ ብሏል። የፕሬሚየር ሊግ ጨዋታዎች፣ የጀርመኑ ቡንደስ ሊጋ፣ የስፔን ላሊጋና የጣሊያን ሴሪኣ ቅኝት ተደርጎባቸዋል።
በምሥራቅ ዩክሬይን 2 ግዛቶች ውሳኔ ሕዝብ አካሂደው እንደተነገረው 89 ከመቶ የሚሆነው ድምፅ ሰጪ ከኪቭ የተለየ አቋም እንዳለው አሳይቷል።ውጤቱ ፤ በአንድ በኩል ቅራኔውን አባብሶ ፤ አገሪቱ ከ2 እንድትከፈል አለያም፤ ተጨባጩን እውነት በመቀበል፤ ምዕራባው
ባለፈዉ ታሕሳስ አጋማሽ የተጀመረዉ ጦርነት አንዳድ ግምቶች እንደሚጠቁሙት በአስር ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ገድሏል።ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ አፈናቅሏል።ወይም አሰድዷል።ከሰወስት ሚሊዮን የሚበልጥ ለረሐብ አጋልጧል።ጦርነቱ እስከ መጪዉ የዝናብ ወቅት ከቀጠለ ደግሞ—–
የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መ ኢ አ ድ) በደቡብ መስተዳድርጎፋ ልዩ ዞን፤ ሳውላ ወረዳ ትናንት ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደ። ከአዲስ አበባ ዘጋቢአችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የ ሰልፉን አዘጋጂዎች ቃል ጠቅሶ እንዳብራራው፤ የፀጥታ ኃይሎች፤ ለማደናቀፍ
ማስተር ፕላን የኦሮምያ ክልልን ጥቅም ያስቀራል የአካባቢውን ገበሪ ያፈናቅላል የሚሉና የመሳሰሉ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩበት ነው ። መንግሥት ግን ማስተር ፕላኑ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮምያ ልዩ ዞን ከተሞችም ከአዲስ አበባ ጋር አብረው እንዲያድጉ ታስቦ ነው ይላል ።
የደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነት ሁለት ቀንም ሳይሞላው ዛሬ ሳይጣስ እንዳልቀረ ተነገረ። የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት መሪዎች ፕሬዚዳንት ሣልቫ ኪርና ሪኤክ ማቸር ተኩስ ለማቆም ከትናንት በስተያ ነበር አዲስ አበባ ውስጥ የተፈራረሙት። የተኩስ አቁም ስምምነቱ ስለመጣሱ የመንግሥትና የተፋላሚ ወገኖች እየተወነጃጀሉ ናቸዉ።
ናይጀሪያ መዲና አቡጃ ካለፈው ረቡዕ እስከ ትናንት ድረስ በተካሄደው ያካባቢው የዓለም የኤኮኖሚ መድረክ ላይ የተሳተፉት እንግዶች በሀገሪቱ አክራሪው የሙሥሊሞች ቡድን ቦኮ ሀራም ባስፋፋው ሽብር እና በፀጥታ አጠባበቁን አስተማማኝ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ መወያየት ግድ ነበር የሆነባቸው።
የዓለም ዜና
በደቡብ ሱዳን ለወራቶች ከዘለቀ ከፍተኛ ግጭትና ጦርነት በኋላ፤ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳል ቫኪርና ተቀናቃኛቸዉ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪኤክ ማቸር የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረሙ። ይህ ትናንት ምሽት የተደረሰዉ ስምምነት፤ በተፈረመ በ24 ሰዓታት ዉስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልፆአል።
ካራቱሪ የተባለዉ የህንድ ኩባንያ ጋምቤላ ዉስጥ ለእርሻ ሥራ የተሰጠዉን አንድ መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ማልማትን ትቶ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ማሽኖችን በማከራየት ሥራ መጠመዱን ሠራተኞች አመለከቱ።
በኦሮምያ ክልል ለአዲስ አበባና ለኦሮምያ ልዩ ዞኖች የተዘጋጀውን ማስተር ፕላን በመቃወም ባለፈው ሳምንት ሰልፍ በወጡ በተለያዩ የኦሮምያ ክልልየሚገኙ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ዛሬ ጠዋት በርሊን ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።
ሁለት በጀርመን የሚኖሩ ወጣቶች በተለይ ኢትዮጵያ ለሚገኙ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሆን አንድ የትምህርት መማሪያ ድረ ገፅ ሰርተዋል።ስለዚህ የትምህርት ድረ ገፅ አላማ እና አጠቃቀም መስራቾቹ በዛሬው የወጣቶች ዓለም ይገልፁልናል።
የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ለዛሬ እንደተቀጠረዉ ለፊት ለፊቱ ዉይይት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ዛሬ ከቀትር በፊት መድረሳቸዉ ሲገለፅ፤ የቀድሞ ምክትላቸዉና የአማፅያኑ መሪ ሪክ ማቻር ደግሞ ትናንት ማምሻዉን ነዉ አዲስ አበባ ገብተዉ ያደሩት።
ዋና ጽ/ቤቱ በሰሜን ጀርመን በገኧቲንገን ከተማ የሚገኘው በዓለም ዙሪያ በጭንቅ ላይ ለሚገኙ ሕዝቦች ተቆርቋሪ መሆኑ የሚነገርለት ማሕበር(GFBF) በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የሰብአዊ መብት ይዞታ አስመልክቶ ትናንት ጋዜጣዊ መግለጫ አወጣ።
ናይጀሪያ ውስጥ ፤ እስላማዊው አክራሪ ቡድን ቦኮ ሃራም፤ ከምንጊዜውም የበለጠ አሁን ተጠናክሮ ይገኛል። በሳምንቱ መግቢያ ላይ አገሪቱን ከካሜሩን ጋር በሚያዋስነው ድንበር፣ እንደገና አንድ መንደር ከቦ ጥቃት ማድረሱ ታውቋል።
በደቡብ ሱዳን ካለፈው ታህሳስ ወር ወዲህ በመንግሥቱ ጦር እና በዓማፅያኑ መካከል በቀጠለው ውጊያ ስቃይ ውስጥ ያለው ተፈናቃዩ ሲቭል ሕዝብ ወደ የማሳው በመለስ ዘር እንዲዘራ እና ወደ ዕለታዊ ተግባሩ እንዲመለስ ለማስቻል በምሥራቅ
የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን ትናንት በሞስኮ ከአውሮጳ የፀጥታ እና ትብብር ድርጅት ሊቀመንበር ዲድየ ቡርክሀልተር ጋ ስለ ዩክሬይን ውዝግብ ከመከሩ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በምሥራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩስያ ቡድኖች
ሚያዝያ 27፤ 73ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች በዓል በአራት ኪሎ የድል አደባባይ በደማቅ ስነ- ስርዓት ተከብሯል። በተለይ በብሄራዊ ትያትር አባት አርበኞች፤ ህጻናት ቲያትረኞች፤ ሙዚቀኞች የተሳተፉበት ሥነ-ስርዓት እጅግ የደመቀና ታሪክና ባህልን ያካተተ መሆኑ ተነግሮለታል።
የኢትዮጵያ ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት ፣ ፖሊስ ከ10 ቀናት በፊት በታሰሩት በ6 ድረገጽ ጸሐፍት ጉዳይ ላይ ዛሬ የጠየቀውን የ15 ቀናት የምርመራ ጊዜ ወደ 10 ቀናት ዝቅ አደርጓል።
የመረጃ ፤ የዕውቀት ማካማቻውና ማከፋፈያው ጋን ከተከፈተ ከጥቂት ዐሠርተ ዓመታት ወዲህ፤ የምርምር ውጤቶቻቸውን በኢንተርኔት ይፋ የሚያደርጉ ጠበብት ቁጥር እየጨመረ ሄዷል። ስለሆነም፤ ዕውቀትን ባፋጣኝና በቀላሉ ለመቃኘትም ሆነ ለመቅሰም የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ የሚያጠራጥር አልሆነም።
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የአዲስ አበባ ከተማን ለማስፋት በሚል የተነደፈዉን አዲስ የከተማ ልማት እቅድ በመቃወም ሰልፍ የወጡ ተማሪዎች ላይ የደረሰዉን የህይወት ህልፈት፣ ድብደባና እስራት በመቃወም፤
የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ የቻይና እና የአፍሪቃ የንግድ ግንኙነት ይበልጥ በእኩልነት ላይ የተመረኮዘ እንደሚሆን ተናግረዋል። የቻይናእና የአፍሪቃ ፤ በተለይም የቻይናና የኢትዮጵያ የንግድ ግንኙነት እንዴት ይገመገማል?
ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በዛሬው ዕለት ምክር ቤታዊ ምርጫ ተካሄደ። በዚሁ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደን ኔልሰን ማንዴላ ከሞቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ የአፍሪቃውያኑ ብሔረተኞች ኮንግረስ፣ «ኤ ኤን ሲ » እንደሚያሸንፍ እና መሪው ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማም ለቀጣዮቹ አምስት ዓመትትም በሥልጣናቸው እንደሚቆዩ ይጠበቃል።
ባለፈዉ ሳምንት በጤናና አካባቢ ዝግጅት በተለታዩ የአፍሪቃ ሃገራት ወባ የምታደርሰዉን ጉዳትና የወባ በሽታን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን ካስቃኘዉ ዝግጅታች ማቅረባችን ይታወሳል።
ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ አንድ አዲስ የፍጥነት መንገድ ትናንት ተመርቆ ተከፈተ። ከሁለት ሳምንታት በኋላ በይፋ ለተሽከርካሪዎች የሚከፈተውን መንገድ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋ ባንድነት መርቀው የከፈቱት ኢትዮጵያን የጎበኙት የቻይና ጠቅላይ ሚንስትር ሊ ኬኪያንግ ናቸው።
በዕድሜ ብዛት በኢትዮጵያ በማርጀት እና በመፈራረስ ላይ ያሉ ባህላዊ ቅርሶችን ለመጠበቅ ስዊድን ውስጥ አንድ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች እንክብካቤ ማህበር ተቋቁሞ ሥራ ጀምሮዋል። በቅርስ አጠባበቅ ሥራ ላይ ያተኮረው ይኸው ማህበር የተመሠረተው ከአንድ ዓመት በፊት ነበር።
የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ትናንት በዋሽንግተን ጉብኝት ያደረጉትን የጅቡቲ ፕሬዚደንት ኢዝማኤል ኦማር ጉሌህን በኋይት ሀውስ ቤተመንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል።
የዩክሬን ግጭት ከምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍል ወደ ደቡብም ተስፋፍቷል።በተለያዩ ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከፍ እያለ ነው ።
በሚቀጥሉት ቀናት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እና የቀድሞው ምክትላቸዉ ሪይክ ማቻር የሰላም ውይይት ለማካሄድ እና ለወራት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም ይገናኙ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ይደረጋል።
በዛሬው ዝግጅት ፤ አትሌቲክስ፤ የሜዳ ቴኒስ ፣ በይበልጥ ደግሞ እግር ኳስና ይሆናል ላቅ ያለ ትኩረት የሚሰጠው።
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ከኢራቅ ጠቅልሎ ከወጣ በኋላ የመጀመሪያውን ምክር ቤታዊ ምርጫ ኢራቃውያን ረቡዕ፤ ሚያዝያ 22 ቀን፣ 2006 ዓም አከናውነዋል። በከፍተኛ ጥበቃ ነው የኢራቅ ምርጫ የተከናወነው። በኢራቁ ምርጫ ለመምረጥ ከተመዘገበው ነዋሪ ሲሦው ድምፁን መስጠቱም ተገልጿል።
የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬኪያንግ ምጣኔ ሀብታዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ወደ አራት የአፍሪቃ ሀገራት ጉዞ ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አርበኞችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በተካሄደው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ ለሃገራቸው የተዋደቁ አርበኞች የሚያገኙት የጡረታ ገንዘብ እንዲሻሻል ተጠይቋል ።
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ እሁድ፤ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓም «የእሪታ ቀን» በሚል አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሠላማዊ ሰልፍ አካሄደ። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተለያዩ ብሶቶችን የሚያንፀባርቁ መፈክሮች፥ የተሰሙበትና አልባሳትም የታዩበት እንደነበር የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።
ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ እ ጎ አ ከ 1903 ዓ ም አንስቶ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት መሥርተው የሚገኙናበተለይ ከ 2ኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ የጋራ ትብብርን አጠናክረው የሚገኙ አገሮች ናቸው። በመንግሥታት ደረጃ ግንኙነቱ ያልሠመረው በደርግ
ትልቁ የዚምባብዌ የተቃውሞ ፓርቲ የዴሞክራሲ ለውጥ እንቅስቃሴ፣ በምህፃሩ፣ «ኤም ዲ ሲ » አመራር አባላት መካከል የተፈጠረው ልዩነት በፓርቲው ህልውና ላይ ስጋት ደቀነ።
በመፍቀሬ-ሩሲያ አማፅያን ታግተው የቆዩ የአውሮጳ የፀጥታ እና የትብብር ድርጅት በእንግሊዘኛ ምኅፃሩ «ኦኤስሲኢ» ታዛቢዎች ትናንት ምሽት ጀርመን መዲና በርሊን ገቡ። እንደ አማፅያኑ፤ ታጋቾቹ ነጻ የተለቀቁት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነዉ።
መፍቀሬ-ሩሲያ አማፅያን የታገቱ የአውሮጳ የፀጥታ እና የትብብር ድርጅት ታዛቢዎች ዛሬ ተለቀቁ። እንደ አማፅያኑ፤ ታጋቾቹ ነጻ የተለቀቁት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነዉ።
ኦሮሚያ መስተዳደር በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ፤ የኦሮሞ ብሔር አባላት የሆኑ ተማሪዎች ፣ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ፣ ከኦሮሚያ ክልል ቦታ በመጨመር የምትሰፋበትን አካሄድ በሰላማዊ ተቃውሞ ሲገልፁ፤ ከፖሊስ ጋ በተፈጠረዉ ግጭት ቢያንስ 11 መገደላቸውን መንግስትን ጠቅሶ አሶሲየትድ ፕረስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።
የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ ይባላል። ወጣቱ የሚስላቸው ስዕሎች ብቻ ሳይሆኑ የሚስልበት ሁኔታም ከበርካታ ሰዓሊዎች ለየት ያደርገዋል።
የአፍሪቃ ግብርና ሚኒስትሮች ጉባኤ በአፍሪቃ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በተመድ ለአፍሪቃ ልማት በተለያዩ ዘርፎች እንቅስቃሴዎች መደረጋቸዉን ተከትሎ የዘንድሮዉ የጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ደግሞ የግብርናዉ ዘርፍ ትኩረት እንዲያገኝ ተወስኗል።