ምክር ቤታዊ ምርጫ በደቡብ አፍሪቃ

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በዛሬው ዕለት ምክር ቤታዊ ምርጫ ተካሄደ። በዚሁ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደን ኔልሰን ማንዴላ ከሞቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ የአፍሪቃውያኑ ብሔረተኞች ኮንግረስ፣ «ኤ ኤን ሲ » እንደሚያሸንፍ እና መሪው ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማም ለቀጣዮቹ አምስት ዓመትትም በሥልጣናቸው እንደሚቆዩ ይጠበቃል።