የአፍሪቃ የጤና ባለሙያዎች ስብሰባ
ዛሬ በተጠናቀቀዉ ሥብሰባ ላይ ከተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት የተዉጣጡ የጤና ባለሙያዎች፤የሕክምና መሳሪያ አምራች እና የለጋሽ ድርጅቶች ተጠሪዎች ተካፍለዉ ነበር
ዛሬ በተጠናቀቀዉ ሥብሰባ ላይ ከተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት የተዉጣጡ የጤና ባለሙያዎች፤የሕክምና መሳሪያ አምራች እና የለጋሽ ድርጅቶች ተጠሪዎች ተካፍለዉ ነበር
ሱዳን በምሥራቅ ከምትዋሰናቸው ጎረቤቶቿ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጋር ግንኙነቷን ለማመጣጠን እየጣረች መሆኑ ተገለጠ። የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ዖመር ኧል በሽር የኤርትራ መዲና አስመራን በጎበኙ በጥቂት ወራት ውስጥ የኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ከሁለት ሣምንታት በፊት ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ተገኝተው ተነጋግረዋል።
«በአገራችን ኢትዮጵያ የደራስያን፤ የሙዚቀኞች ማኅበር ከተቋቋመ እጅግ ረጅም ግዜ ቢሆንም እስከ ዛሬ ሰዓልያን እና ቀራፅያን ማኅበር አቋቁመዉ ልምዶቻቸዉን ሲለዋወጡ ባለማየታችን፤ ይህን ማህበር አቋቋምን» ያለን ወጣት ሰዓሊ የዛሬዉ የወጣቶች ዓለም ዝግጅታችን እንግዳ ነዉ።
በደቡብ ሱዳን የኢጋድ አጣሪና ተቆጣጣሪ ቢሮ የበላይ ሐላፊ አምባሳደር ተፈራ ሻዉል እንዳሉት የኦስሎዉ ጉባኤ ከሠብአዊ ርዳታ በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሐይላት የተፈራረሙትን የሠላም ዉል ገቢር እንዲያደርጉ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግፊት ያደረገበትም ነበር
ባለፉት ሳምንታት ለ 59ኛ ግዜ የተካሄደዉ፤ የአዉሮጳ ሀገሮች የሙዚቃ ዉድድር መድረክ፤ ደማቅ በሆነ የሙዚቃ ዉድድር የኦስትርያዉ ከያኒ 290 ነጥብን በማግኘት፤ እስከ ዛሪ በዉድድሩ ከተመዘገቡ የአሸናፊነት ነጥብ በአብላጫነት፤ የአራተኛ ደረጃን መያዙ ተነግሮለታል።
በአሁኑ ዘመን ፤ በኢንዱስትሪ እጅግ ደርጅተው የሚገኙ ሃገራት እዚህ ደረጃ ለመድረስ የበቁት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምርምር አማካኝነት ሳይንስንና ቴክኖሎጂን የሙጥኝ በማለት እንደሆነ የሚያጠያይቅ አይደለም። ከምዕራባውያኑ ሃገራት መካከል የኢንዱስትሪው
አፍሪቃ፣ የዐረቡ ዓለም እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት እያጠናከሩት ያሉትን የንግድ ምክር ቤት ወደ አንድ የንግድ ቀጣና ለማሳደግ በሚያስችላቸው ዘዴ ላይ ከጥቂት ጊዜ በፊት ተስማምተዋል። የዛሬው የከኤኮኖሚው ዓለም ዝግጅት ትኩረት ምክር ቤቱ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት በማሳደጉ ላይ በያዘው ሚና ላይ አድርጓል።
በጥቁር ዐባይ ወንዟ ላይ ኢትዮጵያ ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት በመገንባት ያለችውን ግዙፍ ግድብ ጉዳይ በተመለከተ ለመነጋገር ፣የግብፅ ው ጭ ጉዳይ ሚንስትር ነቢል ፋኼሚ ወደ አዲስ አበባ ሳይጓዙ እንደማይቀሩ ታዋቂው የመንግሥት ጋዜጣ ኧል አህራም
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀዉ ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ከአራት ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ አስቸኳይ ሠብአዊ ርዳታ ያስፈልገዋል
የዓለም ዜና
ሰሜን ማሊ ኪዳል ከተማ ውስጥ የማሊ መንግሥት ወታደሮች ከቱዋሬግ አማፂያን ጋር ከባድ ውጊያ ማካሄዳቸው ተነገረ። በመንግሥትና በቱዋሬግ መካከል ድርድር ለማካሄድ የሚቻል አይመስልም ተብሏል።
በየአምሥት ዓመቱ የሚደረገው የአውሮጳ ምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ የፊታችን ሐሙስ በኔዘርላንድስ እና በብሪታንያ የሚጀመር ሲሆን፣ እስከ ፊታችን እሁድ ባሉት ቀናት በ28 ቱ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ ይጠናቀቃል።
የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት መስሪያ ቤታቸዉ ኢትዮጵያን ለሐገር ጎብኚዎች ማራኪ ለማድረግ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ይሠራል።
በባልካን አካባቢ ሃገራት ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሟቾቹ ቁጥር እየጨመረ ነው። አንዳንድ ድርጅቶች ተጨማሪ የውሃ ሙላት አደጋ እንደሚያስከትል እያስጠነቀቁ ነው።
እስራኤል አይሁዳዉያንን ከኢትዮጵያ ዳግም መዉሰድ መጀመርዋ ተገለፀ። ባለፈዉ ሳምንት 64 ቤተ- እስራኤላዉያን፤ እስራኤል መግባታቸዉን ሃይፋ የሚገኘዉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ ገልጾልናል።
የሶሪያ ሕዝብ ጉልበት፤ሐብቱ ሞልቶ የተረፋቸዉ የሚችሉትን እስኪያደርጉ መጠበቅ አልቻለም።ያልቃል።ከመቶ ሐምሳ ሺሕ እስከ ሁለት መቶ ሺሕ የሚደርስ ህዝብ ተገድሏል።ሌላዉ ይሰደድ-ይፈናቀላል።ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተሰዷል ወይም ተፈናቅሏል።ቀሪዉ ይሸማቀቃል።
አንድ የሱዳን ፍርድ ቤት፣ በአንዲት የ 27 ዓመት ሴት፣ ከልጅነቷ አንስቶ የ ወላጅ እናቷን ሃይማኖት ስተከተል መኖሯን በይፋ ብትገልጸም ፣ ያላሳደጋትን ሙስሊም አባቷን ሃይማኖት እንደለወጠች በመቁጠር ሙት-በቃ በመፍረዱ፣ በዛ ያሉ ምዕራባውያን መንግሥታትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣
ሱዳን የኤሌትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ለመግዛት ዝግጅት ላይ መሆንዋ ይታወቃል። ባለፈዉ ሰምን አንዳንድ የብዙሃን መገናኛ ድረ-ገፆች እንደዘገቡት ደግሞ፤ ሱዳን ለኤርትራ የኤሌክትሪክ ኃይል ልትሸጥ በዝግጅት ላይ ናት።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል። አትሌቲኮ ማድሪድ ከ18 ዓመታት በኋላ የስፔን ላሊጋ አሸናፊ ሆኗል። የጀርመኑ ባየር ሙንሽን ተቀናቃኙ ቦሩስያ ዶርትሙንድን ድል ነስቶ ዋንጫውን በእጁ አስገብቷል። የጣሊያን ሴሪኣ ዋንጫን ጁቬንቱስ ጨብጧል። የእንግሊዝ «FA-Cup» ዋንጫን መድፈኞቹ ለንደን ይዘው ገብተዋል።
ከሰሜናዊ አፍሪቃ ሜዲትራንዬን ባህርን አቋርጠዉ ወደ ሀገርዋ የሚገቡባት ኢጣልያ ፤ ስደተኞችን ለማስተናገድ ከሌሎች አዉሮጳዉያን ሀገራት ርዳታ ይደረግልኝ ሥትል ጠየቀች። ወደ ኢጣልያ የሚገቡት የጀልባ ሥደተኞች ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተመልክቶአል።
በባልካን ሃገራት እና መካከለኛው አውሮጳ ውስጥ በደረሰዉ ከፍተኛ የዉሃ መጥለቅለቅ የሟቾች ቁጥር ከ 30 በላይ መድረሱ ተነገረ። በደቡብ ምሥራቅ አዉሮጳ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዉኃ መጥለቅለቁ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የዓለም ዜና
መወቃቀሱ ከልዩነትም አልፎ እንዳወዛገበ አነሆ ሃያ-ሦስተኛ ዓመቱን አለፈ። የሃያ ሦስት ዓመቱ ጥቅል ሒደት፤ የዉዝግቡ መሠረታዊ ምክንያትና የወደፊቱ ፖለቲካዊ ጉዞ እንዴትነት የዉይይታችን ትኩረት ነዉ።
መወቃቀሱ ከልዩነትም አልፎ እንዳወዛገበ አነሆ ሃያ-ሰወስተኛ ዓመቱን አለፈ።የሃያ ሰወስት ዓመቱ ጥቅል ሒደት፤የዉዝግቡ መሠረታዊ ምክንያትና የወደፊቱ ፖለቲካዊ ጉዞ እንዴትነት የዉይይታችን ትኩረት ነዉ።
ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ የተደረገዉ ፀረ- ሽብር ጉባኤ፤በተለይ በናይጀርያ በሚንቀሳቀሰዉ አሸባሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ቦኮ ሃራም ላይ ማነጣጠሩ ተመለከተ። የናይጀርያዉን አሸባሪ ቡድን ለመዉጋት፤ በተሻለና በተቀናጀ መንገድ የትብብር ሥራ ወሳኝ መሆኑም ዛሬ ፓሪስ ላይ በተካሄደዉ የደኅንነት ጉባኤ ላይ ተመልክቶአል።
በደቡብ ሱዳን ካለፈው ታህሳስ ወር ወዲህ በፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር መንግሥት ጦር እና በቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪየክ ማቸር በሚመሩ ዓማፅያን መካከል የቀጠለው ውጊያ እና ያስከተለው መዘዝ የአካባቢው ሃገራት መረጋጋትን እንዳያናጋ ማስጋቱ ተነገረ።
ወጣትነት ከመቼውም ጊዜ በላይ በርካቶች ሱስ የሚያሲይዙ ነገሮች ለመሞከር የሚፈተኑበት ጊዜ ነው። ከገቡበት ደግሞ ፤ የቻሉ በራሳቸው ኃይል ያልቻሉ ደግሞ እድሜ ልካቸውን ለሱስ አስያዦች ጥገኛ ሆነው ይቀራሉ። የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ራሱን ከሱሰኝነት አላቋል። ልደት አበበ አነጋግራዋለች።
እ ጎ አ ከ 1980 ዓ ም አንስቶ በሱዳን በኩልና በቀጥታም ከኢትዮጵያ ወጥተው በተለያዩ ጊዜያት እሥራኤል የገቡ፣ ቤተ እሥራኤል በመባል የታወቁ ኢትዮጵያውያን አይሁድ፣ በአንዳንድ መግለጫዎች መሠረት ወደ 80 ሺ ይጠጋሉ ፤ ከ 100 ሺ በላይ
የጀርመን ፍሪድሪኽ ኤበርት ድርጅት (እሽቲፊቱንግ) ፣ አዲስ አበባ ውስጥ ትናንት በሒልተን ሆቴል ባዘጋጀው ስብሰባ፤ የክርስትናና እሥልምና የዘመናት የመቻቻል ታሪክ ትኩረት እንደተደረገበት ተገለጠ። ድርጅቱ ፤ ከፓሪስ ዩንቨርስቲ ፣ በአፍሪቃ ቀንድና
ናይሮቢ ኬንያ ዉስጥ ዛሬ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ አስር ሰዉ ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለጸ። በርካቶችም ተጎድተዋል። የኬንያ ብሄራዊ የአደጋ መከላከል ዘመቻ ማዕከል ፍንዳታዉ የደረሰዉ በህዝብ ማመላለሻ መለስተኛ አዉቶቡስና ገበያ ዉስጥ መሆኑን ገልጿል። ለፍንዳታዉ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።
የዓለም የምግብ ድርጅት በዘንድሮዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2014 ለ6,5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን የምግብ ርዳታ ለመስጠት መዘጋጀቱን የጠቀሰ ዘገባ ሰሞኑን ይፋ ሆኗል። በኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሀገሪቱ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ሕዝብ ከ2,7 ሚሊዮን እንደማይበልጥ ያመለክታሉ።
የሰዎች ፍልሰት ለህብረተሰባዊ እና ለኤኮኖሚያዊ ዕድገት ፣ እንዲሁም ፣ በዓለም ድህነትን በመቀነሱ ረገድ የሚኖረው ሚና ትናንት በስዊድን መዲና ስቶክሆልም የተከፈተው በፍልሰት እና በልማት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ መድረክ
ጦርነት በቀጠለባት ደቡብ ሱዳን ለረሃብ አደጋ ለተጋለጠው ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ ለማቅረብ ለጋሽ ሃገራት ገንዘብ እንዲለግሱ ተጠየቁ ። ኦክስፋም የተባለው የብሪታኒያ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለችግሩ ከወዲሁ አፋጣኝ መልስ ካልተሰጠ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ህይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አስጠንቅቋል ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የዋለዉን የእናቶች ቀን በማስመልከት በርካታ ኢትዮጵያዉን በተለያዩ የማሕበራዊ ደረ-ገፆች እናትን የሚያወድስ እናትን የሚያመሰግን የተለያዩ ስነ-ፅሁፎና ግጥሞች ተለዋዉጠዋል። በተለይ በፊስቡክ ማህበራዊ ድረ መገናኛ ገፅ ላይ የእናቶቻቸዉን ፎቶ ግራፎች በማስቀመጥ እናቶቻቸዉን ያመሰገኑ ኢትዮጵያዉያን እጅግ ብዙ ናቸዉ።
በሩስያና በምዕራባውያን መካከል የተፈጠረው ቅራኔ ተካሯል ። በሩስያ ላይ የኤኮኖሚ ማዕቀብ የመጣሉ ዛቻ አሁንም እንደቀጠለ ነው ። የሩስያ የኤኮኖሚ እድገት እምርታ ቀደም ካለ ጊዜ አንስቶ ቀንሷል ። በአሁኑ ቀውስ ደግሞ እድገቱ ተገቷል ። ይህ ደግሞ በጀርመን የውጭ ንግድ ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ነው ።
ይሁንና በመኻሉ 450 ገደማ የሚሆኑትን ለማትረፍ ተችሏል። ማኒሳ በተባለው ክፍለ ሀገር ፤ ሶማ በተባለው ጣቢያ በሚገኘው የድንጋይ ከሰል ማውጫ ጉድጓድ አደጋ በደረሰበት ቅጽበት፤ ወደ 800 የሚጠጉ ሠራተኞ ች እንደነበሩ ተገልጿል።
በብዛት የታየው የአንበጣ መንጋ በአንዳንድ አካባቢዎች የመኪና መስኮቶችና እግረኞች ጋር እየተላተመ የትራፊክ ፍሰትን በመጠኑም ቢሆን ማስተጓጎሉ ተነግሯል ።
ኦልሜርት ጉቦ በመቀበል በቀረቡባቸው በሁለት የክስ ጭብጦች ከ6 ሳምንታት በፊት የጥፋተኝነት ብይን ተላልፎባቸው ነበር ። ኦልሜርት ላይ ትናንት ውሳኔ የተላለፈው ለሁለት ዓመታት ከተካሄደ የፍርድ ሂደት በኋላ ነው ። ኦልሜርት 160 ሺህ ዶላር የሚደርስ ጉቦ ተቀብለዋል ሲል ፍርድ ቤቱ አስታውቋል ።
የወደፊቱን የሰው ቀጣይ ህልውና ለማረጋገጥ ፤ ከወዲሁ ስለፕላኔታችን አያያዝ ጠንቀቅ ማለት እንደሚገባ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ምሁራን አጥብቀው ይመክራሉ። አንዳንዱ መግለጫቸው እንዲያውም አደናባሪም፤ ተስፋ አስቆራጭም የሚመስልበት ሁኔታ አለ።
«አፍሪቃ የምትፈልገዉ ተግባር ነዉ፤ አፍሪቃ ወደ ተግባር እንድትገባ ከተፈለገ፤ አፍሪቃ የራስዋን ወይም ደግሞ ሀገሮች፤ የራሳቸዉን ፍላጎት፤ ሌሎችን በመጠበቅ ሳይሆን፤ በራሳቸዉን መወሰን መቻል አለባቸዉ» የኤኮነሚ ጉዳይ ምሁሩ ደምስ ጫንያለዉ፤ የአፍሪቃን ዓመታዊ የኤኮነሚ ዘገባን በተመለከተ የተናገሩት ነዉ።
በየመን መንግሥት እና በዐረቡ ልሳነ ምድር በሚንቀሳቀው ፣ በምሕፃሩ «ኤ ኪው ኤ ፒ» በሚል መጠሪያ በሚታወቀው የአል ቃይዳ ክንፍ ዓማፅያን መካከል በምሥራቃዊው የሀገሪቱ አካባቢ በተለይ በማሪብ እና በአል ባይዳ ግዛቶች ውዝግቡ ከተባባሰ ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ የሀገሪቱ መንግሥት ቡድኑን ለመደምሰስ ዘመቻውን አጠናከረ።
ባለፈው እሁድ ምሥራቅ ዩክሬን በተካሄደው ህዝብ ወሳኔ አብላጫ ድምፅ አገኘን ያሉት የምሥራቅ ዩክሬን ተገንጣዮች ትናንት ነፃነታቸውን አውጀዋል ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም እውቅና እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው ።
በኢትዮጵያ የተቋቋመው መንግሥታዊ ያልሆነው ሀገር በቀል ድርጅት፣ « ቪዥን ኢትዮፕያ ኮንግረስ ፎር ዴሞክራሲ »
ለ 41 ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን ወጣቶች ሰሞኑን አስመረቀ።
የናይጀሪያው የሙስሊም ፅንፈኛ ቡድን ቦኮ ሃራም ከትምህርት ቤት ያገታቸውን ልጃገረዶች ለመልቀቅ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ የናይጀሪያ መንግሥት እንደማይቀበል አስታወቀ ። ቡድኑ ልጃገረዶቹን ለመልቀቅ የታሰሩበት ሚሊሽያዎች እንዲለቀቁ ያቀረበውን ጥያቄ የናይጀሪያ መንግሥት ውድቅ አድርጎታል ።