የተባባሰዉ የዩክሬን ቀዉስ
በሰዓቱ፣ በየደቂቃዉ እና አንዳንዴም በየሰከንዱ ከምሥራቅ ዩክሬን ተነስቶ ወደዚህ የሚደርሰዉ ዜና አስደንጋጭ እየሆነ ነዉ።
በሰዓቱ፣ በየደቂቃዉ እና አንዳንዴም በየሰከንዱ ከምሥራቅ ዩክሬን ተነስቶ ወደዚህ የሚደርሰዉ ዜና አስደንጋጭ እየሆነ ነዉ።
የዩክሬይን መንግሥት ወታደሮች ስሎቫንስክን ፣ መነጠል ይፈልጋሉ ከሚባሉት መፍቀሬ- ሩሲያ ኃይሎች እጅ አስለቅቆ ለመቆጣጠር ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻ መክፈታቸውን ጊዜያዊው የሀገር አስተዳደር ሚንስትር አርሰን አባኮቭ ገለጡ።
ብሉ ናይል በተባለው ተቋም አማካይነት በአባይ ላይ የተሰሩ ምርምሮችን በማሰባሰብ ተማራማሪዎችና ፖሊሲ አውጭዎችና መረጃውን የሚፈልጉ የተለያዩ አካላት እንዲያገኙት ለማስቀመጥ ተሞክሯል ።
ፈረንሳይ ከቀረቡላት ማመልከቻዎች የተቀበለችው ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ አስተችቷታል ። ከዚህ ሌላ ፈረንሳይ ተገን ጠያቂዎችን የምትይዝበት መንገድም ኢትዮጵያውያን ተገን ጠያቂዎችን አማሯል።
ኬሪ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቅርቡ የኢንተርኔት አምደኞችና ጋዜጠኞች መታሰራቸው እንዳሳሰባቸውም አስታወቀዋል ።
የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከነገ ጀምሮ አሜሪካን ይጎበኛሉ ። የሜርክል የአሁኑ ጉብኝት ከከዚህ ቀደሞቹ የአሜሪካን ጉብኝቶች በተለየ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚካሄደው ።
የጥበብ ሰው ስሜቱ ስስ ነው ይባላል። የጥበብ ሰው አብዛኛውን ጊዜ በአጠገቡ የሚከወኑ ነገሮችን እንደዋዛ ተመልክቶ አያልፋቸውም። በርን ስዊዘርላንድ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በእየሦስት ወሩ የሚያሰናዱትን የጥበብ እንቅስቃሴ እንመልከት።
ሰሞኑን በስፖርቱ አካባቢ ዘረኝነት እየተንጸባረቀ ነዉ። በስፓኙ ታዋቂ ባርሴሎና የእግር ኳስ ቡድኑ ተጫዋች የሆነ ብራዚላዊዉ ዳኒ አልቬን ኳስ ሜዳ ዉስጥ የተወረወረበትን ሙዝ አንስቶ በመቅመስ ዘነኞቹን ተሳልቆባቸዋል።
በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ፤ የኢንዱስትሪው አብዮት በእንግሊዝ ሀገር ከተጀመረ በኋላ ፣ በአፋጣኝ የዚህ እንቅሥቃሤ ተጋሪና አራማጅ ለመሆን ከበቁት ጥቂት ግንባር ቀደም ሃገራት መካከል አንዷ ጀርመን መሆኗ የሚታበል አይደለም። የፈላስፎችና የተመራማሪዎች
የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ለጉብኝት በዛሬዉ ዕለት አዲስ አበባ እንደሚገቡ እየተጠበቀ ነዉ። ኬሪ በጉብኝታቸዉ ወቅት በሁለቱ ሃገራት የጋራ ጉዳዮች ላይና በጎረቤት ሃገራት ሰላምና ፀጥታን በማስፈን ረገድ
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው ። የስድስት ቀናት የአፍሪቃ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ የሚጀምሩት የኬሪ ትኩረት የሰብአዊ መብቶች ቀውስ በተከሠተባቸው አካባቢዎች የሚሰጥ እርዳታ እንዲሁም የኤኮኖሚ ትብብር እንደሚሆን ተገልጿል ።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በእንግሊዝኛ ምህፃሩ «ዩኤንኤችሲአር» ሰሞኑን ባወጣዉ መግለጫ ከአዉሮጳ ሃገራት ስዊድን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ስደተኞችን መቀበሏን አመለከተ። እንደድርጅቱ ስዊድን በኮታ 1,900 ስደተኞችን ተቀብላለች።
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ምርጫ ጥቂት ሳምንታት በቀረቡት በአሁኑ ጊዜ በየሃገሩ የምርጫ ዘመቻዎች እየተካሄዱ ነው ። በነዚህ የምርጫ ዘመቻዎችም የህብረቱ የልማት ፖለቲካ መርህ እምብዛም ትኩረት አለማግኘቱ እየተተቸ ነው ።
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ኪዳን ድርጅት በእንግሊዝኛ ምኅፃሩ «ኔቶ» የሩስያ ጦር ከዩክሬን ድንበር ማፈግፈጉን የሚመለከት ማረጋገጫ እንዳልደረሰው ገለጠ።
የዓለም የጤና ድርጅት የወባ በሽታ አፍሪቃ ዉስጥ በያንዳንዷ ደቂቃ አንድ ልጅ ትገድላለች ይላል። ጋዜጠኛ አንትየ ዲክሃንስ እንደምትለዉ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ዉስጥ ወባ ዛሬም የበርካታ ሕፃናትን ሕይወት ከሚቀጥፉ በሽታዎች ግንባር ቀደሙ ነዉ።
በርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች፤ በተለይ የባየርን ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች ዛሬ ማታ ከቴሌቪዥን ፊት ለፊት አይጠፉም።
ዩኤስ አሜሪካ እና የአውሮጳ ህብረት ማዕቀብ ሩስያ በዩክሬይን ቀውስ ላይ አካሂዳዋለች በሚሉት ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነት ሰበብ ቀደም ሲል ጥለውት የነበረውን ማዕቀብ በትናንቱ ዕለት አጠናክረዋል። አዲሱ የዩኤስ አሜሪካ ማዕቀብ የተጣለው ለፕሬዚደንት
«ሲፒጄ» ኢትዮጵያ ፕሬስን በድጋሚ በማዳከም ጋዜጠኞችን አስራለች ሲል መግለጫ አወጣ፣ የሩስያ ጦር ከዩክሬን ድንበር ማፈግፈጉን፤…
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ፤ በኢትዮጵያ ፣ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክና አንጎላ ጉብኝት ለማድረግ፣ ነገ አዲስ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዩኤስ አሜሪካ እና የአውሮጳ ህብረት ሩስያ በዩክሬይን ቀውስ ላይ እያካሄደችው ነው ባሉት ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነት ሰበብ ካሁን ቀደም የጣሉትን ማዕቀብ አጠናከሩ።
ዩኤስ አሜሪካ እና የአውሮጳ ህብረት ሩስያ በዩክሬይን ቀውስ ላይ እያካሄደችው ነው ባሉት ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነት ሰበብ ካሁን ቀደም የጣሉትን ማዕቀብ አጠናከሩ።
በትናንትናዉ ዕለት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሁለት ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳትን የቅድስና ሥርዓት አካሂዳለች። በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱሳን የተባሉት ዮሐንስ 23ኛ እና ዮሐንስ ጳዉሎስ ዳግማዊ የተባሉት በርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳትነት ያገለገሉ አባቶች ናቸዉ።
የደቡብ ሱዳን ግጭት እስካሁን በሺህዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ነዋሪዎችንለሞት ዳርጓል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችም ቀዬያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አስገድዷል። ከወራት በፊት በሁለቱ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት መካከል አዲስ አበባ ውስጥ የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተፋላሚዎችን ደም ከመፋሰስ አልታደገም።
ዩናይትድ ስቴትስ በሲና በረሃ አካባቢ ለገጠማት የሽብር ስጋት እንዲዉሉ በሚል አስር አፓቼ ሄሊኮፕተሮችን ለግብፅ ልትሰጥ መሆኗን ሰሞኑን አስታዉቃለች። ይህንኑ ድጋፍ ተከትሎ የግብፅ መንግስት ወታደራዊ አቅሙን እያጠናከረ የሚገኘዉ
መፍቀሬ-ሩስያ ታጣቂዎች ይዘው ያቆዩዋቸውን የተወሰኑ የ«ኦኢሲዲ» ታዛቢ ቡድን አባላት ለመገናኛ ብዙኃን እይታ አቀረቡ። ከተያዙት ታዛቢዎች መካከል አንድ ስዊድናዊ የስኳር ህመም ስላለበት መለቀቁን ታጣቂዎቹ አስታውቀዋል።
ዜና 27.04.2014
የሠማያዊ ፓርቲ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው ሠላማዊ ሠልፍ መንግሥት እየተከተለው ነው ያለውን ብልሹ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ሙስናና ደካማ የመሠረተ-ልማት አቅርቦት ያሻሽል ሲል ጠየቀ።
በአካባቢያቸዉ የሚገኝና ለእነሱ የዕለት ተዕለት ህይወት ትርጉም ያለዉ የደን ሃብት የምንጠራ አደጋ ባንዣበበበት ወቅት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የመዠንገር ማኅበረሰብ አባላት «መዠንገሮች ዉሃ ብቻ ሳይሆን ደግም ህይወት ነዉ» የሚል መመሪያ እንዳላቸዉ ገልጸዉልን ነበር።
ዜና 26.04.2014
በደቡብ አፍሪቃ አፓርታይድ ከተገረሰሰበ በነገው ዕለት 20 ዓመት ይሆናል። የፀረ ዘር አድልዎው ትግል ታሪክ እና ስለ ሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ምን ይመስላል?
ስድስት ጦማሪያን እንዲሁም አንድ ጋዜጠኛ ትናንት ከቀትር በኃላ አዲስ አበባ ውስጥ መታሰራቸው ተሰማ። ዞን «9» በመባል የሚታወቀዉ የጦማርያን ስብስብ አባላት ላይ ላለፉት ሰባት ወራት ከፍተኛ ክትትል ሲደረግ መቆየቱም ተመልክቶአል።
የአውሮጳ የደኅንነትና የትብብር ድርጅት በእንግሊዝኛ ምኅፃሩ «ኦሴ» ታዛቢ ቡድን አባላት እንዲፈቱ የጀርመን ፌዴራል መንግሥት ጥሪ አቀረበ።
መፍቀሬ-ሩስያ ታጣቂዎች ይዘው ያቆዩዋቸውን የተወሰኑ የ«ኦሴ» ታዛቢ ቡድን አባላት ለመገናኛ ብዙኃን እይታ አቀረቡ። ከተያዙት ታዛቢዎች መካከል አንድ ስዊድናዊ የስኳር ህመም ስላለበት መለቀቁን ታጣቂዎቹ አስታውቀዋል።
«የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ» የሚል ስያሜ እንዳለው የጠቀሰው ማኅበር ሕጋዊ ምሥረታ ባካሂድም የፌዴራል በጎ-አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጀንሲ ሕጋዊ ዕውቅና ነፈገኝ ሲል አማሯል።
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ-መንግሥት በኢትዮጵያናኤርትራ ላይ ከፍተኛ ትኩረት አድርጎ እንደሠራ ይጠቀሳል። አማርኛና ትግርኛን ጨምሮ የተለያዩ ቋንቋዎችም ሊቅ ነበር፤ ስዊድናዊዉ ዶ/ር ዮሐንስ ኮልሞዲን።
በዩክሬን የምዕራቡ ዓለም ፍጥጫ እያየለ መምጣቱ ተዘግቧል። የዩክሬይን ባለሥልጣናት ሩስያ «ሦስተኛው የዓለም ጦርነትን» ለማጫራል ትሻለች ብለዋል።
የደቡብ አፍሪቃ ህዝብ ነፃነቱን ካገኘ ከ20 ዓመት በኋላ የሀገሪቱ ወጣቶች ለመሆኑ ምን ያህል ተዋህደው እየኖሩ ነው? ብዙዎችእንደሚሉትግን ከሆነ አሁንም በሀብታም እና ደሀ ፣ በጥቁር እና ነጭ መካከል ልዩነቱ በሰፊው ይስተዋላል።
በዩክሬን የሰፈነው ውጥረት ተባብሶ ዛሬ ወደ ግጭት ተሸጋግሯል ። በዛሬው እለት የዩክሬን ወታደሮች ምሥራቅ ዩክሬን ከሚገኙት መፍቅሬ ሩስያ ኃይሎች ጋር ተጋጭተው ቢያንስ ሁለት ሚሊሽያዎችን መግደላቸውን መንግሥት አስታውቀዋል ።
ሀሳብን በስፋትና በጥልቀት የመግለፅ አቅሙ እጅግ የዳበረ እንደሆነ ይነገርለታል፤ ጥንታዊው የግእዝ ቋንቋ። አንዳንዶች ግእዝ ሞቷል መቀበር ብቻ ነው የቀረው ሲሉ ይደመጣል። ሌሎች ደግሞ የለም፤ ቋንቋው በቤተክህነትና በሌሎችም ቦታዎች አገልግሎት ላይ እየዋለ ነው አልሞተም፤ እንደውም አሁን እያንሰራራ ነው በማለት ለማስረዳት ይሞክራሉ።
ኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ችግር እየተባባሰ መሄዱን እዚያ የሚገኙ ስደተኞች አስታወቁ ። የኬንያ መንግሥት ስደተኞች በሙሉ በሃገሪቱ ወደሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች እንዲገቡ ካዘዘ ወዲህ በተለይ በከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የፍርሃትና የስጋት ህይወት እንደሚገፉ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።
ከ 14 ዓመት በፊት የተባበሩት መንግሥታት አጠቃላይ ጉባዔ በተለመው መሠረት አዳጊ አገሮች በ ስምንት ዐበይት ነጥቦች ላይ በማትኮር ፤ በተለይ ድህነትን ግማሽ በግማሽ ለመቀነስ፤ መሠረታዊ ትምህርት ለሁሉም ዜጋ ለማዳረስና
ጠ/ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፤ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት፤ ዛሬ ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በመገኘት መንግሥታቸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከናወነውን የአቅድ አፈጻጸም ማቅረባቸውን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ ያስረዳል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፣ በዘርና በጎሣ ላይ ያተኮረው የደቡብ ሱዳን የጀምላ ግድያ እጅግ እንዳሳሰበው ገለጠ። የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ቃል አቀባይ እንዳሉት ድርጅቱ የጅምላ ጭፍጨፋውንና ለግድያው መባባስ አስተዋጽዖ ያደረጉትን አካላት አውግዟል።
በዓለም ዙሪያ በአጽዋማት ጊዜ ብቻ ፤ ከሥጋና ከእንስሳት ተዋጽዖዎች የሚታቀቡ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መኖራቸው የታወቀ ነው። ዘወትር የሚጾሙት በተለይ «ቤጋንስ» የሚባሉት የሚከተሉት የአመጋገብ ስልት መንስዔ ምን ይሆን? ከጤንነት አኳያስ አመጋገቸው ምን ያህል የተሟላ ነው?
ከ 60 በላይ ብሔር ብሔረ ሰቦች በሚኖሩባት በደቡብ ሱዳን ውጊያው ካለፉት አራት ወራት ወዲህ እንደቀጠለ ነው። የዲንካ ጎሣ ተወላጅ በሆኑት በፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር እና ከኑዌር ጎሣ በሚወለዱት በቀድሞው ምክትላቸው