13 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ትናንት መታሠራቸውን የፓርቲው ፕሬዚደንት ኢንጅንየር ይልቃል ጌትነት አስታወቁ። የፓርቲው መሪ ለዶቼ ቬለ እንዳስረዱት፣ ግለሰቦቹ የታሠሩት ፓርቲው ለፊታችን እሁድ ሊያካሂደው ላሰበው ሰልፍ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ እና ወረቀት ሲያድሉ በነበረበት ጊዜ ነው።

ኢጣልያ ባለፉት 48 ሰዓታት ከ1,000 የሚበልጡ ስደተኞችን ማዳኗን የሀገሪቱ የባህር ኃይል ትናንት አስታውቋል። ከሰሜን አፍሪቃ ወደ አውሮPA ለመግባታ ሲሞክሩ የመስመጥ አደጋ የሚያሰጋቸውን ስደተኞች ለማዳን ባለፉት ጊዚያት አንዳንድ ድርጅቶች ተቋቁ መው እየተንቀሳቀሱ ነው።

በ2003 ዓም ወደ ኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ በመግባታቸው እና የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ ከሚለው ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ታጣቂዎች ጋር አብራችኋል በሚል ተከሰው 438 ቀን ታስረው የነበሩትን ስዊድናውያኑ ጋዜጠኛ

ስምንተኛዉ የጀርመን አፍሪቃ የኃይል አቅርቦትና ፍላጎት መድረክ ባለፈዉ ሳምንት ከሚያዝያ 5 ቀን 2006ዓ,ም አንስቶ ለሶስት ቀናት ነበር በጀርመኗ ሰሜናዊ ግዛት ሃምበርግ ላይ የተካሄደዉ። የዚህ ዓመት የመድረኩ መሪ ቃል ለዘላቂ ጉድኝት አዲስ ኃይል የሚል ነበር።

በዩክሬን የተባባሰውን ቀውስ ያረግባል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የጄኔቫው ስምምነት እስካሁን ተግባራዊ መሆን አልቻለም ። ከስምምነቱ በኋላም የዩክሬን ውጥረት ተባብሶ ቀጠለ እንጂ አልቀነሰም ።

ቦኮ ሐራም የተሰኘው እስላማዊ አክራሪ ቡድን ናይጀሪያ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ከባድ ጥቃቶችን ሲሰነዝር ቆይቷል። የናይጀሪያ ምርጫ በተቃረበበት በአሁኑ ወቅት ሰሞኑን ከፍተኛ እልቂት ያስከተለ የቦንብ ጥቃትም ሰንዝሯል። ለመሆኑ ቦኮሐራም ማን ነው? ከሽብርተኛ ቡድኑ ጀርባ የሰሜንና የደቡብ ናይጀሪያ ባላሥልጣናት እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?

ለችግሩ መባባስ ምዕራቡ ዓለም ተጠያቂ የሚያደርጋት ሩስያ በኬቭ መንግሥት ላይ ወቀሳዋን አጠናክራለች ። ሩስያ የዩክሬን መንግሥት መገንጠል ከዩክሬን እንገንጠል በሚሉ ኃይሎች ላይ ፣ያለፈው ሳምንቱን ስምምነት በመጣስ ኃይል እየተጠቀመች ነው ስትል እየከሰሰች ነው ።

ከግጭቱ በኋላም በአዋሽና በሌሎች አካባቢች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ወደ ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ ከጅቡቲም ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ እንደነበርም ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።የኢትዮጵያ ፌደራል ጉዳዮች መስሪያ ቤት በበኩሉ ሰዎች መሞታቸውን የሚያመለክት መረጃ እንዳልደረሰው አስታውቋል ።

ህገ መንግሥቱን የሚያረቁት ተወካዮች በሃገሪቱ ስር እየሰደደ የሄደውን ፖለቲካዊና ጎሳዊ ግጭቶች በተለይ በምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል የሚቀርበውን የተጠናከረ የራስ ገዝ አስተዳደር ጥያቄ ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚኖርባቸው ተመልክቷል ። ረቂቁ እንደተጠናቀቀ ለህዝበ ውሳኔ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል ።

በምሥራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩሲያውያን ኃይላት በስሎቭያንስክ የሠዓት ዕላፊ ገደብ አወጁ። በአዋጁ መሰረት ማንኛውም ሰው የሠዓት ዕላፊው ገደብ ሳይጠናቀቅ ወደ ውጭ ወጥቶ መንቀሳቀስ አይፈቀድለትም።

በምሥራቅ ዩክሬይን መፍቀሬ ሩሲያውያን ኃይላት በስሎቭያንስክ የሠዓት ዕላፊ ገደብ አወጁ። በአዋጁ መሰረት ማንኛውም ሰው የሠዓት ዕላፊው ገደብ ሳይጠናቀቅ ወደ ውጭ ወጥቶ መንቀሳቀስ አይፈቀድለትም።

በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በቦር፣ ጆንግሌይ የሚገኘውን የተመድ ሰፈር አጥቅተው ቢያንስ 50 ሰዎች ገደሉ። በዚሁ ቢያንስ 5000 ሰዎች ከለላ ባገኙበት ሰፈር በተጣለው ጥቃት ከቆሰሉት መካከልም ሁለት የተመድ ሰላም አስከባሪዎች ይገኙባቸዋል።

የእየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታስበበት የስቅለት በዓል ዛሬ በመላው አለም በሚገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ ተከብሮ ዋለ ። በዓሉ በተለይም በሺህዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በተገኙበት በእየሩሳሌም ክርስቶስ መስቀል ተሸክሞ እንደተጓዘበትና ስቃይና መከራ እንደተቀበለበት በሚታመንበት መንገድ መስቀል ተሸክሞ በመጓዝ ተከብሯል ።

የሩሲያን ጨምሮ የዩክሬን የዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ኅብረት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ጄኔቭ ላይ ትናንት ባካሄዱት ዉይይት አማካኝነት የደረሱበት መግባባት በቀዉስ በተወጠረችዉ ሀገር የተባባሰዉን ሁኔታ ለማርገብ ያስችላል እየተባለ ነዉ።

ዘንድሮ የትንሣኤ በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ዘንድ በተመሳሳይ ቀን ይከበራል። የአይሁዳውያን ፋሲካም በትንሣኤ ቀን ይውላል። የትንሣኤ በዓል ከሐይማኖታዊ ዳራው ባሻገር እንደየሀገሩና የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችም አሉት። በተለይ የዶሮ እንቁላል ሀገር ቤትም ሆነ እዚህ ጀርመን በትንሣኤ በዓል ልዩ ስፍራ ይሰጠዋል።

ይህ የአራትዮሹ ንግግር ለዩክሬን ቀውስ ምን ዓይነት መፍትሄ እንደሚያስገኝ ከወዲሁ መገመት ቢያዳግትም ቢያንስ ዩክሬንና ሩስያን የዩክሬን ቀውስ ከተባባሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ላይ እንዲወያዩ በማድረጉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ።

የጀርመን መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ተጠሪ ክርስቶፍ ሽትሬሰር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ በተለይ ግጭቶች እየተባባሱ በሚሄዱባቸው አካባቢዎች ህዝቡን በሰብዓዊ እርዳታ መደገፍ ከዚያም አልፎ ተፋላሚ ወገኖችን ቢቻል በሰላማዊ መንገድ አለያም በኋይል ማስቆም እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በአፍሪቃ እስካሁን 3000 ቤቶች ሌት ብርኃን እንዲያገኙ አስችሏል። ኤሌክትሪክ ፈፅሞ ባልነበረበት ቦታ የኤሌክትሪክ ኃይል ይዘን እንመጣለን ይላል። ሞቢሶል የተሰኘው ከፀሀይ ብርሃን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መሣሪያ የሚፈበርከው ድርጅት።

በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ሳምንት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነዉ። የዘርፉ ባለሙያዎች ከተማዋ የትራፊክ አደጋ እንደሚበዛባት፤ አደጋዉም በሶስት ዓበይት ምክንያቶች እንደሚከሰት ያስረዳሉ።

ምሥራቅ ዩክሬን ውስጥ መፍቅሬ ሩስያ ሚሊሽያዎች ዛሬ ስድስት ብረት ለበስ ወታደራዊ መኪናዎችን መያዛቸውን ዩክሬን አስታወቀች ። የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር መኪናዎቹ እንዳይንቀሳቀሱ መጀመሪያ በአካባቢው ነዋሪዎች ከታገዱ በኋላ አክራሪ ኃይሎች እንደወሰዱዋቸው ዛሬ ተናግሯል።

የዓለም ባንክ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራት ለመርዳት የሚያስችለው አዲስ የልማት መርሀግብር አወጣ። ባንኩ በዓለም ድህነት አንፃር የጀመረውን ዘመቻ ለማሳካት ከሚመለከታቸው ሀገራት ጋ ፣ ከኢትዮጵያ ጋ ጭምር ተባብሮ ይሰራል።

የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ግጭት ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ። የርስ በርስ ግጭቱን ለማስቆም እዚያ የሚገኘውን የፈረንሳይና የአፍሪቃ ህብረት ኃይል ለማገዝ የአውሮፓ ህብረት ወታደሮችን ለመላክ በዝግጅት ላይ ነው ። በዚሁ ዘመቻ ጀርመን ተካፋይ ብትሆንም ተሳትፎዋ መገደቡ ግን አስተችቷታል።

የአዉሮጳ ኅብረት ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ። በሉክዘምበርግ ትናንት የተሰባሰቡት የኅብረቱ የ28 ሃገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ንብረት የማንቀሳቀስና የቪዛ እገዳ ለማሳረፍ በሙሉ ድምፅ መስማማታቸዉ ተገልጿል።

የአየር ንብረትን አስመልክቶ በተመድ የተካሄደ አንድ ጥናት ታዳሽ የኃይል ምንጭን መጠቀም አማራጭ እንደሌለዉ አመለከተ። በርሊን ላይ ይፋ የሆነዉ ይህ ጥናት በርካታ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ከተከማቸበት ከቅሪተ አፅም ከሚገኘዉ የኃይል ምንጭ ዓለም ባስቸኳይ ተላቆ ከባቢ አየርን ከጉዳት እንዲያድን ይማጸናል።

በዓለም ደረጃ በአጠቃላይ ለጦር መሣሪያ ግዢ የሚወጣው ገንዘብ ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር በትንሹ ዝቅ ብሏል። ይህም የሆነበት ምክንያት ትናንት ስቶኮልም ላይ ይፋ የወጣው አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ዮናይትድ ስቴትስ ለኢራቅ ጦርነት የምታወጣው ገንዘብ በመቀነሱ ነው።

አልጀሪያን እጎአ ከ1998 አንስቶ ለ16 ዓመታት በሦስት የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው አንቀጥቅጠው ገዝተዋል፤ ፕሬዚዳንት አብደልአዚዝ ቡተፍሊካ። ካለፈው ዓመት አስንስቶ በነርቭ ዕክል በሽታ የሚሰቃዩት የ77 ዓመቱ አዛውንት ስልጣን ዛሬም አልበቃኝም፥ ለአራተኛ ጊዜ መጥቻለሁ ብለዋል። የፊታችን ሐሙስ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።

ስዊድን በጉዲፈቻ ያደጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማህበር ባለፈው እሁድ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ ባዘጋጀው ስብሰባ የማህበሩ አባላትና ሃገር ቤት የሚገኙ ወላጆቻቸው እርዳታና ምክር በሚያገኙበት መንገድ እንዲሁም በጉዲፈቻ ማዕከል ምሥረታ ላይ ተነጋግረዋል ።

የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን በአገሪቱ መሰል ጥቃቶችን የሚያደርሰው ቦኮሃራም በጥቃቱ ተጠርጣሪ መሆኑን ተናግረዋል ። አደጋው የደረሰበትን አካባቢ የጎበኙት ፕሬዝዳንቱ ሃገሪቱን ወደ ኋላ ለመጎተት የሚፈልጉ ባሏቸው ኃይሎች ተቀነባበረ ያሉትን ጥቃት አውግዘዋል ።

የመኢአድ አባላት ከእስር ሌላ በአንዳንድ አካባቢዎች ስብሰባ ማድረግ እንደሚከለከሉና በአጠቃላይ የመደራጀት መብታቸው እንደተነፈገ አመራሮቹ አስታውቋል ። የክልሉ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ ሰሞኑን የቀረበ ቅሬታ መኖሩን እንደማያውቅ ከዚያ ቀደም ሲል ግን በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው እንደሌለ አስታውቋል ።

የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ሥልጣን ከያዙ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለሀገራቸው ሕዝብ ለማሟላት የገቡትን ቃል መጠበቅ ተስኗቸዋል። በሀገሪቱም የፀጥታው ስጋት እየጨመረ ሄዷል።

ጊኒ ቢሳው ውስጥ አጠቃላዩ ምርጫ እሁድ ሚያዝያ 5 ቀን፥ 2006 ዓም ሲካሄድ ዋለ። የሀገሪቱ ሕዝብ እአአ በ2012 ዓም መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ወዲህ አንድ ሕጋዊ መንግሥት እንዲመሠረት ሲጠብቅ ነው የቆየው። ለብዙ ጊዜ ሲተላለፍ በቆየው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ