በዓሉ ግርማ – ሕይወቱና ሥራዎቹ (መጽሃፍ ግምገማ በዳንኤል ክብረት)


በእንዳለ ጌታ ከበደ
የካቲት 2008 ዓም
ዋጋ፡- 120 ብር

እንዳለ ጌታ ከበደ በዓሉ ግርማን እንደ ጌታ ነፍስ ዘርቶ እንደደአልዓዛር ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ከትውልድ ቀየው ጀምሮ ‹እስከ መቃብሩ› ደረስ እየተከተለ፡፡ መዛግብቱን ያገላብጣል፣ እናውቃለን የሚሉትን ይጠይቃል፣ ያውቃሉ ብሎ የገመታቸውን ያናግራል፤ ሄዶበታል፣ ውሎበታል፣ ገብቶበታል፣ ወጥቶበታል የተባለው ቦታ ድረስ እየገባ ‹ማጀት በጎረሰው፣ ደጃፍ በመለሰው› ያገኘውን ያህል ይነግረናል፡፡

ሰው የሚያውቀውን ሲጽፍ፣ የሚጽፈውንም ሲያውቅ እንዴት የሚያጠግብ እንጀራ እንደሚጋግር በእንዳለ ጌታ መጽሐፍ ልኬቱን እናገኘዋለን፡፡ ከሱጴ እስከ ደርግ እሥር ቤት፣ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ፣ ከአሠሪ እስከ አሣሪ፣ ከወዳጅ እስከ አሳዳጅ ድረስ መረጃ ፍለጋ የኳተነው ‹ለሞተው› በዓሉ ነፍስ ሊዘራ እንጂ ለሌላ ነገር ነው ብሎ ለማመን እጅግ ጅል መሆንን ይጠይቃል፡፡

መጽሐፉ በቀብር ላይ እንደሚነበብ የሕይወት ታሪክ ሙቀት አልባ አይደለም፡፡ ድርቀት የተለየው፣ወዝ የተዋሐደው እንጂ፡፡ እንደ አንድ የሀገራችን ታሪክ ጠገብ ሽማግሌ ሆኖ ያወጋናል፡፡ ቃለ መጠይቅ ያደረገላቸውን ሰዎች እንደ አጃቢ ገጸ ባሕርይ ያስመስላቸዋል፡፡ በዓሉን ደግሞ እንደ ዋናው ገጸ ባሕርይ፡፡ ‹ተናደደ፣ ጠረጲዛ መታ፣ ፊቱን ጥቁር አደረገ፣ ሳቀ፣ ፈገግ አለ፣ ሮጠ፣ ተሹሎከሎከ› እያለ አብሮ የነበረ ያህል ነው የሚነግረን፡፡

በዓሉ በድርሰት ሥራዎቹ ሰዎችን ሲስል ፍጹማን አያደርጋቸውም፡፡ እንደ ሁላችንም እንከን ያላቸው፤ የበዓሉ ሰዎች አንድም እንከናቸውን አሸንፈው፣ አንድም እንከናቸውን ይዘው ኑሮን ድል ለማድረግና ታሪክ ለመሥራት የሚተጉ ናቸው፡፡ የበዓሉ ሰዎች የሠፈራችን ሰዎች የሚመስሉን ለዚህ ነው፡፡ የበዓሉ ሰዎች ጀንበርና ጥላ ያላቸው ናቸው፡፡

እንዳለ በዓሉን ሲጽፈው እርሱ ስለ ራሱ ቢጽፍ ኖሮ በሚጽፍበት መንገድ ነው፡፡ ጀንበርና ጥላ አድርጎ፡፡ በዓሉ ጎበዝ ደራሲ፣ ትኁት፣ ትጉ ሠራተኛ፣ ከሰው ጋር ተግባቢ፣ ዐዋቂ፣ ቆራጥና ጀግና ነው፡፡ ነገር ግን ደግሞ ሰው ነው፡፡ ጥላ ነበረው፡፡ እንከን ነበረው፡፡ ድካም ነበረው፡፡ ስሕተት ነበረው፡፡ ውሱንነት ነበረው፡፡ ከሻማው ሥር እንዳለው ጨለማ ያለ ነበረው፡፡ እንዳለ ይህንንም እንድናይ ያደርገናል፡፡

በቀብር ላይ እንደምናነበው ታሪክ ‹ትጉ፣ቅን፣ሰው ወዳጅ፣ ታታሪ፣ ታማኝ፣ እግዜርን የሚፈሩ ነበሩ› ብeሎ አይደመድምም፡፡ በዓሉ ሰው ነበረ፡፡ ሰው ሆኖ ሠርቶ ሰው ሆኖ ነው የሞተው ይለናል፡፡ እንድናደንቀው ብቻ ሳይሆን እንድንበሳጭበት፣ እንድንወደው ብቻ ሳይሆን ‹ለምን ይህን ያደርጋል› እንድንለው፣ እንድናከብረው ብቻ ሳይሆን እንድንተቸው፣ ‹እንኳን አደረገ› እንድንል ብቻ ሳይሆን ‹ምን ነካው› እንድንል አድርጎ ነው የሳለው፡፡

በዓሉና እንዳለ ልብ ለልብ ተናበዋል፡፡ ይል ነበር በሚባለው የጎጃም ልቅሶ ላይ ስለ ወዳጃቸው አሣምረው እየገጠሙ የዋሉ አንድ ሰው ነበሩ አሉ፡፡ በዚህ በጎንጅ ጽላሎ፡፡ ሁኔታውን የታዘበች አልቃሽ
እርሳቸው እርሳቸው እርስዎም እርስዎ
እንዴው የወዳጅ ልብ ምን አሰረቀዎ
ብላቸዋለች አሉ፡፡ የወዳጅዎን ልብ ሰርቀው ቢወስዱት እንጂ እንዲህ አድርገው የልቡን እንዴት ዐወቁት ማለቷ ነው፡፡ የቅጅ መብትን ባልፈራ ለእንዳለ እለው ነበር፡፡
በዓሉን የሚወድ፣ የሚያደንቅና ስለ በዓሉ ማወቅ የሚፈልግ ሰው አሁን የእንዳለን መጽሐፍ ከማንበብ የተሻለ አማራጭ የለውም፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ በዓሉ ብቻ ሳይሆን እንዳለም ተጽፏል፡፡ ሲወጣና ሲወርድ፣ ተሥፋ ሲያደርግና ሲቆርጥ፣ ሲያገኝና ሲያጣ፣ ሲያዝንና ሲደሰት፣ እናየዋለን፡፡

ተራራ ቁልቁለት ወጥቼ ወርጄ
ስሙ የማይታወቅ ሩቅ ሀገር ሄጄ
እንዳለቺው የከበደ ሚካኤል የአይጥ ግልገል የተደበቀውን ለመግለጥ ‹ስሙ የማይታወቅ ሩቅ ሀገር› ድረስ ሲተጋ እናየዋለን፡፡ እኛም አብረነው እየተጓዝን ‹እንዘ ሥውር እምኔነ፣ ይእዜሰ ክሡተ ኮነ› እንላለን፡፡

የእንዳለ አጻጻፍ የታላላቆቻችን ታሪኮች እንዲህ በፍቅርና በትጋት ተሠርተው፣ ሰው ሰው ሸተው፣ በደረቅ እንጀራ ሳይሆን በአዋዜ ቢቀርቡ እንደ ወግ ተደምጠው፣ እንደ ፊልምም እንደሚታዩ ማንጸሪያ ነው፡፡ የእንዳለ መጽሐፍ በዓሉን አግኝቶ ከማነጋገር ቀጥሎ ስለ በዓሉ ሊነግረን የሚችል ሁለተኛው መዝገብ ይመስለኛል፡፡ ምናልባትም ደግሞ ከራሱም ከበዓሉም በላይ፡፡
እናም
በድግሱ የተደሰተ የቆሎ ተማሪ የወረበውን ማኅሌተ ገንቦ እንወርብለታለን፡፡
ዝ ጠላ ከመ ወይን ጣዕሙ
እስኩ ድግሙ ድግሙ፣ እስኩ ድግሙ፤

11 Comments on “በዓሉ ግርማ – ሕይወቱና ሥራዎቹ (መጽሃፍ ግምገማ በዳንኤል ክብረት)”

  1. Dnial kibret

    yante tumera bafinchachin yewta!!
    Ata Tewodrosin yemesdeb min moral aleh ?ante mehayim Debtere !!!

    YE WEYANE ASHKER MEHONKIN ENAWKALEN EKO ANTE SEBAQI 1

  2. losing the substance by grasping the air ይሉሀል ይኼ ነው!የተማርከው አማርኛም ጠፋብህ!?የሆኑትን ጥለው ያልሆኑትን ለመሆን መዳከር ከሁለት ያሳጣል።”ግምገማ“ ያልከውን መወድስ በሚል ቀይረው

  3. Daniel kiberet we have known you very well as you are working as a secret service of woyane please twice what you have defamed the great king tewodros of ethiopia

  4. Daniel kibret once you are pinpionted who you are and the road of zigzag doesnt work now so what ever shadowed article you wrote it is nonesence

  5. Daniel weyane wede Hager selemeyasgebaw

    50 000 yewech Haimanot min asteyayet aleh ?

    WECHEW YE WEYANE SELAY DEBTERA NEH KKKKKK

    YE MENDER WEREGNA 1

  6. አልገባኝም ለመሆኑ ይህ ዳንኤል ክብረት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለመሆኑ ምን መረጃ አለ። ማንም ተነስቶ እኮ ስሙን ለሚፈልገው አላማ መጠቀምበት ይችላል። ስለዚህ ከትችት በፊት እስቲ ጽሑፉን በአድራሻው ላኩለትና የዲያቆን ክብረትን መልስ እንስማ።

  7. Betam yaznkubt qen binor ye Mulugeta
    metasbia qen shir gud silu yenbrut
    bemulu le Bealu Girma mot yemn ije
    indalebt indemayawuqu siwun melak
    ardgw bashkabachochu bene Addisu Abebe
    siwdes lehulum yeijun yestew neaw
    yemiyasblw .

  8. Hello guys back to normal. He is a history
    student. He knows and he is doing as a hoby for all writing. Please appreciate his skills. Welll,
    he had woyana id and he is writing good, but
    sometimes he is badly to critisize if someone is beyond his level of skills. My advice for
    him try to follow the truth as much as
    possible. We all a cursed generation
    With sins and no one stand infront of jesus
    With out his mercey.

  9. ገና መቼ ቀጣይ የዕናት ምጥ በጎጥና በጠባቦች የተለከፈችው ሃገራችን መከራዋ እንድህ በዋዛ የሚለቃት አይመስልም ምክንያቱም ቀይ ሽር ተሸንፎ በተረኛው ነጭ ሽብር (ኢሕአፓ) ስልጣን ይዞ በተራው ኢትዮጵያን ለከፋ ችግር አጋልጠዋታል የኢትዮጵያን ልጆች ማጥፋትና የሃገሪቱን አንድነት፣ግዛት ማጥበብ ስራው ነው፡፡
    የአማራ ማንነት አደጋ ላይ መሆኑን እየታየ ነው? ኦሮሞስ ማን ነው? እያሉን ነው !
    እሱ ነው

  10. Ayyy Wedase….Derasiw gwadgnah mehonu yastawkal…ene segmgmew dersetu libweld ymeslal mknyatum abro yale yahel enkskaswn ygelsal.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*