#Ethiopia  #QilintoFire ወያኔ በህዝብ ላይ የሚሰራውን ድራማ ቀጥሎበታል። አድምጡት። ‹‹ሞቷል›› ተብሎ የተቀበረው የቅሊንጦ እስረኛ ሸዋ ሮቢት ተገኘ ። በህይወት የተረፉት እስረኞች ስም ዘርዝር ተለጥፏል ከተባለ ይህ ሞቷል ተብሎ በህይወት የተገኘውን ልጅ ስም መደበቁ ለምን አስፈለገ? የተቀበረውስ አስክሬን የማን ነው? ወያኔ …

‹‹ሞቷል›› ተብሎ የተቀበረው የቅሊንጦ እስረኛ ሸዋ ሮቢት ተገኘ ። Read more »

ባህር ዳር እሁድንና ዘመን መለወጫን በለቅሶ እያከበረች ነው። (#ማንደፍሮ_አስረስ ለ35 ቀናት የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ሊተርፍ አልቻለም) ባህር ዳር የአማራ ተጋድሎ በፍፁም ሰላም ተጀምሮ እስካሁንም ጭፍጨፋ የቀጠለባት ከተማ ናት። ለቁጥር አዳጋች ወጣቶችና ህፃናት ተሰውተዋል። ዛሬም በአጋዚ […]

ሰይድ ሃሰን (መሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ) መስከረም 1፣ 2009 በሲንሲናቲና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጳይዊያን የቀረብ አጭር የንግግር ንጥረ ሀሳብ (ተቀርፎ የወጣ) የንግግሬ ንጥረ ሀሳቦች በ4 ይከፈላሉ፡ በኢትዮጵያ የተከሰተው ሙስና ምን ይመስላል? እንደትስ ማስወገድ ይቻላል? ሙስናው በኤኮኖሚው ላይ […]

ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የተሠባሠቡ አባገዳዎች በክልሉ ባለው ተቃውሞና ግጭት ሳቢያ የበርካታ ሰዎች ህይወት እየጠፋ መሆኑን በመግለፅ ችግሩን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ በውይይት መንግስት እንዲያነጋግራቸው ጠይቀዋል፡፡ ከነሐሴ 23 ቀን ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሶደሬ ሆቴልና ሪዞርት ከ2 ሺ በላይ የሀገር ሽማግሌዎችና ሴቶች ባካሄዱት …

ሰላማችንን ራሳችን እንጠብቃለን:: “ያለ ህግ አግባብ የታሰሩ ሰዎች በአስቸኳይ ይፈቱ” = አባገዳዎች Read more »

።።።።የሰውየው ትዝብት በዘመነ 2008።።።።። ፩ኛ/ አሸባሪ ህግ እንጂ አሸባሪ ሰው የለም። ፪ኛ/ የስኳር በሽታ እንጂ የስኳር ምርት የለም። ፫ኛ/ ስጋት እንጂ ስጋ የለም። ፭ኛ/ ወጪ እነጂ ትርፍ የለም። ፮ኛ/ ማዕረግ እንጂ እውቀት የለም። ፯ኛ/ እስር […]

“ትግሬ አይሁድ ፣ አማራ እና ኦሮሞ ናዚ-ሒትለር” ስዩም መስፍን ያው እንደተለመደው ህወሓት እና ትግራይ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ገጽታ እንደሆኑ ነግሮናል። ስለዚህ ህወሓትን ተቃወምክ ማለት ትግሬን ተቃወምክ ማለት ነው፣ ህወሓት ይውደም ካልክ ትግሬ ላይ “ናዚ” ሆንክበት […]

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለደረሰው የህይወት መጥፋት መኢአድ መንግስትን ተጠያቂ አደረገ

የእርቅ መንግስት እንዲመሰረት ፓርቲው ጠይቋል

ባለፈው ሳምንት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ለደረሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት መንግስትን  ተጠያቂ ያደረገው የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፤ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል፡፡
ፓርቲው ሰሞኑን በፅ/ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤መንግስት በአደጋው 23 ታራሚዎች መሞታቸውን ቢናገርም ቁጥሩ ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለኝ ብሏል፡፡
መንግስት ለታራሚዎች ህገ መንግስታዊ ከለላ በመስጠት ደህንነታቸውን መጠበቅ ሲገባው፤ ይህ ሳይፈፀም መሞታቸውም ሆነ ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ለታሳሪ ቤተሰቦች ግልፅና የማያሻማ ፈጣን መልስ በመስጠት ፈንታ በቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጭንቀትና አሳዛኝ መጉላላት እንዲደርስ መደረጉን በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል መኢአድ፡፡ በጉዳቱ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት ማዘኑንም ፓርቲው አስታውቋል፡፡
ፓርቲው በመግለጫው፤ በማረሚያ ቤቱ የደረሰውን ጉዳት ጨምሮ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የደረሡ ጉዳቶች በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ፣ ለጠፋው ህይወት መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና የደም ካሣና የዜጎች ማቋቋሚያ ካሣ እንዲከፍል  ጠይቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ ነሀሴ 24 የሠጡት መግለጫ ‹‹ጦርነት ከማወጅ የማይተናነስ አሳዛኝም አስደንጋጭም ተግባር ነው›› ያለው ፓርቲው፤ በአስቸኳይ ትዕዛዙ እንዲሠረዝ አሳስቧል፡፡ ፓርቲው ከግጭቶችና ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ የታሠሩ እንዲፈቱና መንግስት ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር ውይይት በማካሄድ የዕርቅ መንግስት እንዲመሰረት ጠይቋል፡፡
አንጋፋ የኢህአዴግ አመራሮች ሠሞኑን በኢቢሲ እየሰጡ ያሉትን ማብራሪያ፣ አዲስ የመፍትሄ ሃሳብ ያፈለቀና ችግሩን አግባቡ የተረዳ አይደለም ሲል ፓርቲው አጣጥሎታል፡፡
የቂሊንጦ ማረምያ ቤት ቃጠሎን ተከትሎ በህይወት ያሉ ታራሚዎች ወደ ዝዋይ፣ ሸዋ ሮቢትና አዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች መዘዋወራቸውን ታውቋል፡፡   

ከጳጉሜ 1 እስከ መስከረም 2 በኦሮሚያ በማህበራዊ የንግድ አድማ መጠራቱን ተከትሎ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ተግባራዊ መደረጉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያስታወቀ ሲሆን መንግስት በበኩሉ፤ የአድማ ጥሪው በህብረተሰቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከሽፏል ብሏል፡፡
የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለአዲስ አድማስ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ “በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች የንግድም ሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም፤ ሁሉም ነገር እንደታገደ ነው” ብለዋል፡፡ ሆቴል ቤቶች፣ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮችና የገበያ ስፍራዎች ዝግ ሆነው መሰንበታቸውን ኦፌኮ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በነቀምትና ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ባለፈው ሰኞና ማክሰኞ 4 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው አቶ ሙላቱ ተናግረዋል፡፡
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሠኢድ ስለጉዳዩ ከአዲስ አድማስ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠሩት ችግሮች ከህገ መንግስቱ ጋር የማይጣጣሙ እንደሆኑ ጠቁመው ሁከቱ በዜጎች ህይወትና ንብረት ላይ ጥፋት ማስከተሉን አስታውቀዋል፡፡
“ህዝቡ በቅንነት የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከህዝቡ ከራሱ ጋር ተመካክሮ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነቱን መንግስት በመግለጫዎቹ አሳይቷል” ያሉት አቶ መሃመድ፤ ከዚህ በመነሳት የህብረተሰቡን አጀንዳ ቀምተው ለራሳቸው አላማ ለመጠቀም የሚሞክሩ አውዳሚ ኃይሎች እንዳሉ ህዝቡ የተረዳበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
“ህዝብ ከመንግስት ጋር እየተግባባ ችግሮችን ለመፍታት እየጣረ ነው” ያሉት አቶ መሃመድ፤ “በአማራም ሆነ ኦሮሚያ የተረጋጋ ሁኔታ ተፈጥሮ ህብረተሰቡ ቀድሞ ወደነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብለዋል፡፡
ሱቆች እንዲዘጉ፣ ከበአል ጋር ተያይዞ አርሶ አደሩ ምርቱን ባለማውጣት የንግድ አድማ እንዲደረግ መልዕክት የተላለፈ ቢሆንም ጥሪው በተጨባጭ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ሳያገኝ ከሽፏል ብለዋል፤ አቶ መሃመድ፡፡
በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የአድማ ሙከራ ቢኖርም ህብረተሰቡ ወደ ተጨባጭ ሰላማዊ ህይወቱ ተመልሶ በበአል ስሜት ውስጥ ሆኖ እየተገበያየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያን ከተሞች አቋርጠው ወደተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጉዞ ያደረጉ የአይን እማኞች፤ በአብዛኞቹ ከተሞች የንግድ ቤቶች ተዘግተውና ሆቴል ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነው መመልከታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡  

ዘንድሮ በተለያዩ ውድድሮች ስኬታማ ውጤቶችን ያስመዘገበችው የ5000 እና 10,000 ሜትር ሩጫ ብርቱ ተፎካካሪዋ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ከሪዮ ኦሎምፒክ ድሏም በኋላ ተጨማሪ ድል አስመዝግባለች።

እንኳን ምህረት ለመባል ምህረት ለማድረግ ለሚከወን ጥናት ናሙና የማይበቁ ቀድሞውኑ ወንጀል ያልፈጸሙና ሊታሰሩ የማገይባቸውን ‹እስረኞች›ን በምህረት ስም በመፍታት ፕሮፖጋንዳ መስራት ፣ በ‹እሳት› ያለቁ ወገኖቻችንን ሃዘን በደስታ መለወጥ አይቻልም፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ‹ምህረት ተደረገ የምንለው› ሁሉም በነጻ […]

እንኳን ወደ ቤታችሁ ተመለሳችሁ ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን! እንኳን ለነጻነታችሁ በቃችሁ ውድ ኡስታዞቻችን፣ ዳዒዎቻችን፣ አራማጆቻችን፣ ጋዜጠኞቻችን!!! ለዲናችሁ ፍቅር የከፈላችሁትን መስዋእትነት ሁሉ አላህ ይቀበላችሁ! ቅዳሜ ጳጉሜ 5/2008 ውድ ጀግኖቻችን….! እንኳን ከቤተሰባችሁ፣ ዘመዶቻችሁና ከህዝባችሁ ለመገናኘት በቃችሁ! አስከፊ […]

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ሰብሳቢ አቡብክር አህመድን ጨምሮ ዘጠኝ በሱ መዝገብ የተከሰሱ ጀግኖቻችን ሁለት ሴት ታሳሪዎች ተፈቱ ከቤተሰብ ጋር ተቀላቀሉ አህመዲን ጀበል፤አህመድ ሙስጠፋ፤ካሊድ ኢብራሂም፤ሙሃመድ አባተ ሌሎች በሌላ መዝገብ የተከሰሱ በርካታ አልተፈቱም መንግስት ለፕሮፖጋንዳ ለመስራት እንዲመቸው ተፈቺዎችን ለሁለት ቀናት ስልጠና ሲሰጥ …

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ሰብሳቢ አቡብክር አህመድን ጨምሮ ዘጠኝ በሱ መዝገብ የተከሰሱ ጀግኖቻችን ሁለት ሴት ታሳሪዎች ተፈቱ ከቤተሰብ ጋር ተቀላቀሉ Read more »

ቅዳሜ ነሐሴ 28, 2008፣ ማክሰኞ ጳግሜ 1, 2008 “የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ” ደጋፊ እና ጧሪ ወንድ ልጇ በግፍ የተገደለባት ኢትዮጵያዊ እናት! በእውነት ልባችን እጅግ ቆሰለ! እጅግ ተስፋ ሚያስቆርጥ ጭካኔን በዘመናችን አየን! […]

#OromoProtests – INTELLECTUALS DESTROY MIMI SEBHATU AND TPLF ON ZAMI RADIO [መደመጥ ያለበት ሕዝብ በድፍረት መናገር ጀመረ] ምሁራን በዘሚ ራድዮ ወያኔን አስገቡለት : ~ ወያኔ ተመርጦ አይደለም ስልጣን ላይ የተቀመጠው ፣ በጉልበት ነው :: ~ የመግስት በለስጣናት በስብሰናል ካሉ ያላቸው …

የመንግስት በለስጣናት በስብሰናል ካሉ ያላቸው አማራጭ ቦታውን መልቀቅ ነው::- ምሁራን በዘሚ ራድዮ VIDEO Read more »

ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተካሄደ ያለዉ ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እስርና እንግልት ይቁም፤ የመንግስት የፀጥታ ኃይላት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚወስዱትን የኃይል እርምጃ ያቁሙ፤ የታሰሩ ፖለቲከኞች የሐይማኖት መሪዎችና ጋዜጠኞች ይፈቱ፤ የዘር መድሎ ይቁም ሲሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን ላይ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ።

ጥሪ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለባለ ሶስት ደረጃ የሰላም መፍትሄ ህዝባዊ እንቅስቃሴ በጋራ እንነሳ!! ህዝባዊ ትብብር ለኢትዮጵያ ማስተባበርያ ማዕከል ዉድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ እኛ ኢትዮጰያዉያን በመከባበር፤ በፍቅር፤ በመቻቻልና በአንድነት ፍጹም የሚያኮራ ባህል መስርተን የምንኖር ህዝቦች ነን። እጅግ የሚያኮራ ታሪክ ያላት ሃገር …

ጥሪ ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ለባለ ሶስት ደረጃ የሰላም መፍትሄ ህዝባዊ እንቅስቃሴ በጋራ እንነሳ!! Read more »

ብሪታንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለንደን በሚገኘዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት ተሰልፈዉ የኢትዮጵያ መንግሥት እየፈፀመ ያለዉ ግፍ ይብቃ ሲሉ የተቃዉሞ ሰልፍ ማድረጋቸዉ ተመልክቶአል ።

ዛሬ ከ 800 በላይ የአማራ ተወላጅ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ተመድበው በሚማሩባቸው ትግራይ ውስጥ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች አንሄድም በማለት ጎንደር ላይ ተሰብስበው ነበር። የትግሬ ተማሪዎች በመላው የአማራ ክልል ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መልቀቂያ እየወሰዱ በትግራይ ክልል ትምህርት […]

ሐምሌ 2006 ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ ስዛወር፣ ዞን ሁለት ነበር የተመደብኩት። በወቅቱ በሽብር የተከሰሱ ብዙ ጎንደሬዎች ነበሩ። አልጋው ሥር “ደቦቃ” በማስተኛት ያስተናገደኝም ቢራራ የተባለ ጎንደሬ ነበር። ከዚያ በፊት ከሥሙ በስተቀር የማላውቀውን ፋሲል ደሞዝን አንድ ዘፈን ያስተዋወቀኝ እሱ ነው። ዘፈኑን እስከዛሬ ባልሰማውም ሁለቱን ስንኞች ግን በቃሌ ይዣቸዋለሁ። “አረሱትን አልሰማኸውም?” አለኝ ድጋሚ ‘አልሰማሁትም’ አልኩት ባለማወቄ ሲገረም አይቼ እያፈርኩ፤ ስንኞቹን ነገረኝ።

“አረሱት ይሉኛል የመተማን መሬት፣
ያውም የኛን ዕጣ
እነሱ ምን ያርጉ ከኛ ሰው ሲታጣ።”

ሰሞኑን 17 ያህል አርቲስቶች ለአዲስ ዓመት ዋዜማ አቅደውት የነበረውን የሙዚቃ ድግስ በሐዘናችን ምክንያት መሰረዛቸውን ሰማሁ። አርቲስቶቻችን ሰው እየወጣቸው ነው ማለት ነው የሚል ስሜት ተሰማኝ። እኛው ያከበርናቸው አርቲስቶች የሕዝባችንን ሐዘን ማክበር ከጀመሩ ትግላችንንም የሚቀላቀሉበት ግዜ ሩቅ አይሆንም፣ እኛም ‘አርቲስት’ የሚለውን ቃል ስድብ ከማድረግ እንቆጠባለን እያልኩ ሳስብ ሳልሰማቸው ያመለጡኝ ብዙ የትግል ዘፈኖች እንዳሉ ተረዳሁ።

የኦሮምኛ ዘፋኞች ዘፈንን የትግል መሣሪያ ማድረግ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። ሁሉም ዕኩል መደመጥ አልቻሉም እንጂ ባለፈው አንድ ዓመት በአማካይ በቀን አንድ የትግል ዘፈን እየለቀቁ ነበር። ከሁሉም ግን በጣም ተወዳጅ የሆነውና ቋንቋውን የማታውቁትን ሳይቀር የሚወዘውዘው የሀጫሉ ‘ማለን ጅራ’ ነበር፤ ስለዚህ ዘፈንም መጀመሪያ የሰማሁት እዚያው ቂሊንጦ በመጣ ወሬ ነው።

ኪነ ጥበብ ትግሉን ሲቀላቀል የትግሉን መብሰል የሚያሳይ ምልክት አድርጌ ነው የማየው። በአዲስ አበባ መንግሥትን በገደምዳሜ የሚወርፉ ትያትሮች ከሌሎቹ የበለጠ ብዙ ተመልካች አላቸው፣ የመግቢያ ዋጋቸውም ውድ ነው። ምክንያቱም የሕዝቡን ዝምታ ይናገራሉና። አሁንም፣ አርቲስቶቻችን የትግል ዘፈኖችን ሲዘፍኑ በሕዝብ ልብ ውስጥ ያላቸው ዋጋ ይጨምራል።

ስለፋሲል ደሞዝ እነዚያ ስንኞች ሳወራ ወንድሜ “‹እንቆቅልሽ› የሚለውን አታውቀውም?” አለኝ። አላውቀውም ነበር። ይገርማል ፋሲልን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዘፈኑ ሰማሁት፣ አየሁት። ክሊፑ ላይ፣ ሴቲቱ እንቆቅልሽ ትጠይቀውና መልሱን ባለማወቁ “አገር ስጠኝ” ትለዋለች፣ እሱ ግን እንዲህ ይላታል።

“እንቆቅልሽ፣
በሰም ለበስ ቅኔ፣
አሁን ገና፣ መጣሽብኝ ባይኔ።”

ፋሲል “በይ ደስም አላልሽኝ ጨዋታ ቀይሪ” እያለ ሲያንጎራጉር የሆነ ልብን የሚኮረኩር ኃይል አለው። ወንድሜ “ይሄ ይገርምሃል እንዴ?” አለኝና የይሁኔ በላይ አዲሱን ዘፈን አስደመጠኝ። ለወትሮው፣ ይሁኔን ከፍቼ የማዳምጠው ዘፋኝ አልነበረም። ይሄንን ‘ሰከን’ የሚለውን ዘፈኑን ስሰማው ግን የማላውቀው ስሜት ልቤን አተራመሰው።

“…ሰከን በል፣
ሰከን ማለት፣
ነው ጨዋነት
ሰከን ማለት፣
ነው ጀግንነት
ወታደሩ፣ ሰከን በል
አፈሙዙን ሰከን አርገው፣
ቃታህንም እንዳትስበው፣
ባዶ እጁን ነው፣ የሚጮኸው፣
ሠላማዊ፣ ወንድምህ ነው፣
ሰከን በሉ፣ ሕዝቤን ተዉት
ድምፁን ስሙት፣ አትግደሉት…”

በማለት የመንግሥትን ሀጢያት “…ውጉዝ ከመአርዮስ” ብሎ በማውገዝ፣ ስለኅብረት ሲባል፣ “በወላጁ ጥፋት፣ አይወቀስ ልጁ” እያለ መስከንን ይመክራል።

ናቲ ማን ቀጠለ። ናቲ ደግሞ በኦሮምኛ ስልተ ምት “አሁን ተነካሁ” እያለ፣ እሽክም፣ እሽክም አስባለኝ።

“ኦሮሞን፣ ኦሮሞን ሲከፋው
አሁን ተነካሁ
አማራን፣ አማራን ሲከፋው
አሁን ተነካሁ…”

ከዚያ ደግሞ የመስፍን በቀለ ዜማ ቀጠለ። በቀረርቶ የሚጀምረው የመስፍን “ሠላም ለኢትዮጵያ” አዲስ ትውልድ መጥቷል ይላል። ወራደሩንም እንዲህ ይለዋል፦

“ወታደሩ ጓዴ፣ አንተ ያገሬ ሰው፣
ወንድምክን አትግደል፣ ብረትክን መልሰው።…”

ሌንሴ ለሜሳ ደግሞ ጆሮ በሚለሰልስ ድምፅዋ፣ “ተነቃንቋል” ትላለች፣

“ተነቃንቋል ጥርሱ ይነቀል፣
ይነቀል፣
ይነቀል ይውለቅ
የአሉላ የጆቴን ትከሉበት ወርቅ፣
ክፍተቱ እንዲሞላ ውበቱ እንዲደምቅ።…”

መክፈቻዬ ላይ የጠቀስኩትን ፋሲል ደሞዝን መዝጊያም ላድርገው። በቅርቡ በለቀቀው ዘፈኑ እንዲህ ይላል፣

“…ኧረግ ወዲያልኝ (ወዲያልኝ)
ኧረግ ወዲያልኝ (ወዲያልኝ)
በቃ ሒድልኝ (ሒድልኝ)
25 ዓመት አላገጥክብኝ።…”

ክብር ለእነዚህ አርቲስቶች ይሁን!
አሜን።

ለህዝባዊ እንቢተኝነት ትክክለኛው ምላሽ የሥርዓት ለውጥ ብቻ ነው !!! ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ (ብ/ም/ቤት 4ኛ ዓመት 2ኛ ልዪ አስቸኳይ ስብሰባ ጳጉሜ 1 ቀን 2008 ዓ.ም) ሰማያዊ ፓርቲ ከግንቦት 16/2007 ምርጫ ማግሥት ጀምሮ በተደጋጋሚ እንደገለጸው፣ ያለ ነፃና ፍትሐዊ …

ለህዝባዊ እንቢተኝነት ትክክለኛው ምላሽ የሥርዓት ለውጥ ብቻ ነው !!! ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ Read more »

በኮንሶ 60 ቤቶች ተቃጥለው ነዋሪዎች ለስደት ተደርገው በከፍተኛ መከራ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ከአካባቢው ህዝብ ተነጥለው ለመንግስት ያደሩ የኮንሶ ካድሬዎች በታጣቂ ኃይል ታግዘው አባሮባ ቀበሌ አማራማ መንደር 60 ቤቶችን አቃጥለው ነዋሪዎቹ ለስደት መዳረጋቸውንና በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ዜጎች …

በኮንሶ 60 ቤቶች ተቃጥለው ነዋሪዎች ለስደት ተደርገው በከፍተኛ መከራ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ #KonsoProtests Read more »

የተጨቆኑ ሕዝቦች እሪታና ጩኸት በዛሬው እለት የቂሊንጦ ታሳሪ ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ቂሊንጦ ዙሪያ ሰልፍ አደረጉ ። አዛውንቶች እና ሴቶች የሚበዙበት ይህ ሰልፍ በወያኔ ፖሊሶች ወከባ እየተደረገበት ሲሆን እናት አዛውንቶች ልጆቻችንን በማለታቸው ተደብድበው ታስረዋል ። Via – Minilik Salsawi

ስለቂሊንጦ ጥቂት መረጃዎች ———–  Elias Gebru Godana የቂሊንጦ እስር ቤት አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊን አግኝቶ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ ለማጠናከር እጅግ ከብዷል። ግን የሰማሁትን ጥቂት ነገር እንዲህ እናገራለሁ። – ሁለት እስረኞች የአተት በሽታ እንደተገኘባቸውና ይህንንም ተከትሎ ከቤተሰብ (ከውጪ) የሚመጣ ምግብ ለእስረኞች …

ስለቂሊንጦ ጥቂት መረጃዎች – Read more »

የኦሮሚያ ክልል ውሎ እና የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ ስኬት #Ethiopia #Oromoprotests #CivilDisobedience #AmharaProtests #MinilikSalsawi Minilik Salsawi – mereja.com – በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ::ለኣንድ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ በሻሸመኔ ኣዲስ ኣበባ ቡራዩ በኣምቦ በነቀምት …

የኦሮሚያ ክልል ውሎ እና የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ ስኬት Read more »

በበርካታ የደቡብና የኦሮሚያ ክልሎች ገንዘብ የለም የተባሉ ደምበኞች “ያስቀመጥነውን ገንዘባችንን እንፈልገዋለን፣ ለልጆቻችን ትምህርት ቤት ወጪና ለአዲሱ ዓመት ያስፈልገናል፣ ገንዘባችን ካልተሰጠን አንሄድም” ስላሉ በፖሊስ ድብደባ ደርሶባቸዋል። የባንኮች ቀውስ ወደ አዲስ አበባ እየተቃረበ ሲሆን፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ዋና ባንኮች ነጋዴዎችና …

ገንዘባቸውን ከባንክ ለማውጣት የሞከሩ ደምበኞች በፖሊስ ተደበደቡ Read more »

በወሎ ክፍለሃገር በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል :: #Ethiopia #AmharaResistance #Amharaprotests #Wello #Dessie Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በወሎ ክፍለሃገር የደሴ ከተማ በዛሬው እለት በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማን በሁሉም ንግድ ድርጅቶች ላይ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል ሆኖም ግን …

በወሎ ክፍለሃገር በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል :: Read more »

• የህዝቡን ጥያቄ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሳንሶ ማየት እብደት ነው • አሁን መፍትሄው ህዝብን በተለያዩ ስልቶች ማነጋገር ነው • ሁኔታው ሳይባባስ በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀለት አስጊ ነው አሁንም ከመቀዝቀዝ ይልቅ በየጊዜው እየሰፋና እየጋለ ለመጣው ህዝባዊ ተቃውሞና ግጭት ምሁራንና የአገር ዕውቅ ሽማግሌዎች …

የህዝቡን ጥያቄ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሳንሶ ማየት እብደት ነው Read more »

“መንግሥት የሀገሪቱን መሰረታዊ ችግር አልተገነዘበም” የሰሞኑ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ መግለጫ፤ የወቅቱን የሀገሪቱን ችግሮች በአግባቡ የፈተሸና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል አለመሆኑን የገለፁት ተቃዋሚዎች፤ በሀገሪቱ በተከሰቱት ችግሮች ዙሪያ ያስቀመጧቸውን የመፍትሄ ሃሳቦች ከግምት ውስጥ ያስገባ የሰጠ አይደለም ብለዋል፡፡ መንግስት የአገሪቱን መሰረታዊ ችግር ባለመገንዘቡ፣ አሁንም …

ኢህአዴግ “እታደሳለሁ” ማለቱን ተቃዋሚዎች አጣጣሉት Read more »

አሳዛኝ ሰበር ዜና! ርሸናው ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተሸጋግሯል ትላንት ቅዳሜ ነሐሴ 28/2008 ለሊት 8 ሰዓት አካባቢ መንግስት ኮሚቴዎቻችን በሚገኙበት በቃሊቲ እስርቤት በዞን 1 ውስጥ ታስረው ከሚገኙ ታሳሪዎች መካከል 2 ሰዎችን የረሸነ ሲሆን ሁለቱን ደግሞ በጥይት መቶ ማቁሰሉን ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ …

አሳዛኝ ሰበር ዜና! ርሸናው ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተሸጋግሯል Read more »

አርብና ቅዳሜ በተለያዩ ከተሞች ህዝቡ ገንዘቡን ለማውጣት ተሰልፎ ታይቷል። ነገር ግን ከብዙዎቹ ባንኮች ወያኔ ገንዘቡን ዘርፎ ወደትግራይ በማሸሹ ካዝናችው ባዶ ሆኗል። በዚህም ምክንያት ገንዘባቸውን ማውጣት ያልቻሉት ደምበኞች ምሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። ገንዘብዎትን እንዳያጡ ከፈለጉ በአስቸኳይ ከሚከተሉት ባንኮች ያውጡ። ብሔራዊ ባንክ፣ ወጋገን …

ደምበኞች ገንዘባቸውን ከባንኮች ለማውጣት ተሰልፈዋል Read more »

ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ /ም አቶ ታምራት ላይኔ መጀመሪያ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል!! አቶ ታምራት ሰሞኑን ስለ ወቅቱ ጉዳይ ተናግረዋል። የአቶ ታምራት ላይኔ አዲሱ ቃለመጠይቅ ለማዳመጥ የሚቀጥለውን ይጫኑ። https://www.youtube.com/watch?v=FtugwEqb0d0  አቶ ታምራት ላይኔ መጀመሪያ በሕዝብ ላይ ለፈፀሙት የህዝብ ጭፍጨፋ …

አቶ ታምራት ላይኔ መጀመሪያ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል!!! Read more »

ያሬድ አማረ ከመጀመሪያ ጀምሮ የጦር ሀይል አማራጭን በመጠቀም ሽንፈትን ያስተናገደዉ ሕወሃት በዲፕሎማሲም ዳግም ተመልሶ ሊያገግም በማይችል ሁኔታ ዛሬ 27/12/2008 ጎንደር ከተማ ላይ ልኩ ተነግሮት በኪሳራ ተሸኝቷል። ሁሌም ቢሆን “የእኔ መንገድ ብቻ ትክክል ነው” በሚል ትእቢቱ የምናዉቀዉ ህወሃት አማራ ምድር ላይ …

የወያኔ ልዑካን የጎንደር ውሎ በውርደት ተጠናቀቀ Read more »

የጫት ሱሰኛ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ በደም የሚጨብስ ፌዴራል ፖሊስ ሃገሪቷን ባጥለቀለቀበት ሁኔታ የሕወሓት ስልጣን ይርዘም ብሎ የሚያስብ ካለ ሞራሉ የላሸቀ ነው።

#AmharaResistance; ዐማሬ ዛሬ (ነሃሴ 27 ቀን 2008 ዓ.ም.) Muluken Tesfaw የጠ/ሚውን አዋጅ ተከትሎ በመተማ፣ አምባ ጊዎርጊስና ደብረ ታቦር ከ50 በላይ ዐማሮች በሁለት ብቻ ቀናት ተገድለዋል • በሽንፋ ከተማ የቀን ሠራተኞች በጥይት ተደብድበዋል • በደብረ ታቦር ዳግመኛ የቤት ውስጥ አድማ ተጠራ …

የጠ/ሚውን አዋጅ ተከትሎ በመተማ፣ አምባ ጊዎርጊስና ደብረ ታቦር ከ50 በላይ ዐማሮች በሁለት ብቻ ቀናት ተገድለዋል Read more »

በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባሉ እርምጃዎች ሁለት ሰው መገደሉን የወረዳው አስተዳዳሪ ገልፀዋል፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen

በአማራ ከልል የህወሀት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው የብአዴን ኮሚኒኬሽን ሐላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የስርጭት አድማሱ በአዲስ አበባና ዙሪያ ብቻ በተገደበው ሸገር ኤፍ.ኤፍ.ኤም ራዲዮ ቀርበው ‹‹ሕዝባዊ ንቅናቄ እያደረገ ባለው የአማራ ክልል ህዝብ ላይ የመከላካያ ሰራዊት እርምጃ እንዲወሰድ ታዟል›› ብለዋል!! ይህ የዘር ፍጅት የታወጀው በምእራብውያን አጋዥነት በቆመው የህወሀት ስርዓት መሆኑ አፅእኖት ሊሰጠው ይገባል!! በተያያዘ ዜናም ዛሬ ማምሻውን ሀይለማሪያም ደሳለኝ […]

አስቸኳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን የጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በውጫሌ ዞረው ወደ ሰሜን ጎንደር እያመሩ ነው

ከዚህ በታች ስማቸሁ ለተጠቀሱ የአማራ ከተሞች፣ የገጠር ቀበሌዎችና ገበሬ ማህበራት ነዋሪዎች በሙሉ፡- እንደሚታወቀው በጎንደር እና በጎጃም ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች ትግሉን አሁን በደረሰበት ራስን ነጻ የማውጣት ደረጃ አድርሰውት ይገኛሉ። ይሁንና አፋኙና […]

 ስለ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና መንስኤያቸው ያብራራሉ ጭቆናን ለማጥፋት የሚደረግ ትግል ኖሮ አያውቅም ህዝብ ቋቱ ሲሞላ ነው አልችልም፤ በቃኝ ያለው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የተናገረው የሚያስደንቅ ነው በሦስት መንግስት ውስጥ አልፈዋል – ታዋቂው ምሁርና አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕ/ር መስፍን […]

በአማራ ክልል የሕዝቡ ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው። #Ethiopia #Amharaprotests #BahrDar #AmharaResistance #MinilikSalsawi Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በባህር ዳር ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ መቀጠሉ ታውቋል።ከባሕር ዳር 45 ኪሎ ሜትሮችን በምትርቀው የጉማራ መንደር እስከ ዛሬ ሌለት ድረስ በቆየ የተኩስ …

በአማራ ክልል የሕዝቡ ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው። Read more »

ከትላንትናው እለት ጀምሮ በጎጃም ክፍለሃገር፣ አገው አዊ ዞን፣ አንከሻ ጓጉሳ ወረዳ የሚገኘው ፖሊስ ጣቢያና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በህዝብ ተከበዋል። በመንግስት መስሪያቤቶች የሚውለበለቡ የወያኔ ሰንደቅ ዓላማዎች ተነስተው ትክክለኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተተክተዋል። በባህር ዳር የወያኔ ንብረቶች ተቃጥለዋል።

በብዙ የዐማራ አካባቢዎች የመንግሥትን መዋቅር ሕዝቡ ተረክቧል፤ የጎበዝ አለቃዎች ጸጥታ የማስከበሩንና የመሪነት ሚናውን በሚገባ እየተወጡ ነው፡፡ የአርባያ በለሳና የቋሪት አንበሶች ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ በድፍን ጎጃምና በድፍን ጎንደር ሕዝብ አገዛዙን አሽቀንጥሮ ለመጣል እየታገለ ነው፡፡ በወሎና በሸዋ […]

ነሐሴ 22/2008 ዓም ከባህርዳር አካባቢ ተነስቶ በሀሙሲት አድርጎ በደብረታቦር አድርጎ ወደ መቀሌ በመጓዝ ላይ የነበረ ወታደሮችን የጫነ ኦራል ጉመራ ወንዝ ላይ በጀግኖቹ የጎንደር ወጣቶች ጉመራ ወንዝ ላይ ድልድዩን በመዘርጋታቸው መሻገር ባለመቻሉ መሄጃ ያጣው ሠራዊት ወደ ጎንደር ለመመለስ ተገዷል ከጉማራ ሸሽቶ ወደ ጎንደር ሲሮጥ ሌሎቹ ጀግኖች ርብ ወንዝን በመዘርጋት መውጫ ቀዳዳ አሳጥተው እየተንከራተተ እንደሚገኝ ታውቋል. ወረታ […]

Some Facebook friends are recently tagging me with their posts of ‘solutions’ to the contemporary crisis in Ethiopia. (i.e. the anti-government protests in Oromia and Amhara, two biggest regions in Ethiopia). Most of these Facebook friends recommend maintenance or what’s otherwise called ‘cosmetic change’ to the regime. Others seem to be conspirators against the ‘unprecedented’ cooperation of biggest players in Ethiopian politics, the Oromo and Amhara people, against the ruling Tigrian elites group, TPLF.  (The group claims to represent 6% of Ethiopian people (Tigrians) as compared to 62% – Amhara + Oromo people). The latter (of facebook friends suggesting solutions) claimed that it is only Oromo Protests that’s genuine and some went far to portraying Amhara protests as an act of power mongering.
There is no Half Liberty!
In my opinion, it is hardly possible to give one sect of a society its freedom and denying the rest. Freedom will either be assured for all or is denied for all. One of the nations in Ethiopia cannot be given regional autonomy and proportional representation in the federation while others are denied these. It will be oppressed with the rest, or get freedom with them. Even TPLF (which is the supreme Front in the coalition of four parties in the name of EPRDF) including its makers and supporters will only get liberated or be free when it lets others free. The common understanding that a jailer is not free until it frees its prisoners is true. One has to free their prisoners to regain their freedom of movement; otherwise, they will have to be sitting there watching their victims. 
So What to Do?
The solution should be all inclusive. But this happens only if all of us have the genuine intention to compromise on our interests for the sake of justice, fairness and peace. Now, all the power and opportunity is controlled by the ruling party, EPRDF. So, EPRDF must be the sole body willing for this to be true. The issue is freeing the party itself as well as its dissent. Otherwise, however its oppression increases, the public grievance and riot will also increase and the challenge that can be solved through compromise today may not tomorrow. 
In this, maybe naïve, understanding of mine that EPRDF may become willing to hear alternative solutions, I suggest a filtered compilation of alternative solutions from what I heard of people’s recommendations.

1) Apology
Ethiopian people deserve an apology. TPLF/EPRDF should ask the Ethiopian people an apology for all the mistakes and wrong doings that it has done from its conception up until today and even for leading the country to a dangerous end. This has to be done in a written format.
2) Amnesty and Warranty 
We have to cross the bridge of past failures at some point. EPRDF should give amnesty and release all people who were convicted and are on hearings of court proceedings in relation to their political stance. The amnesty should not be with any pre- & post-conditions. In addition, the ruling group should cancel the proclamation that labelled dissent organizations as ‘terrorists’;  it should give warranty for the return of exiled politicians, journalists and activists so that they would be able to contribute for the political fate of their country. Rebel groups should also be given the guarantee to peacefully and legally act according to their political program. A proclamation of amnesty and warranty should be passed by the parliament as to this end. 
3) Discourse
Anti-terrorism proclamation, the charity law and the press laws inacted in the country are used to restrict democratic discourse. Therefore, they should be cancelled for the time being until a legitemate house ratifies other ones (or until it amends them in a way) that don’t stifle constitutional rights. In the mean time, successive and multiple country-wide dialogue that are broadcasted live in the state-owened television with the participation of all stake holders and with moderation of international rights groups should be conducted.  
4) Election
Finally, by freezing the current parliament including the electoral board and by establishing a temporary electoral board of technocrats from other independent countries, there should a new election to be launched at ‘national’ and regional level.
Having suggested that, I have also considered possible criticisms for these alternative solutions:
A) These don’t consider TPLF’s position not to ever compromise;
B) A naïve comment that has assumed the recent protests have shakendown EPRDF’s hold;
C) A solution that encourages dependency on foreign support;
D)  A comment that disregarded the immediate necessity of resolving the controversial issues regarding federal structure, electoral system, Parliament system, land ownership and others in the constitution.
Regarding the first two possible comments (put in ‘A’ & ‘B’), it is because I have the fear that the crisis we are in go worse than better that I wanted to take the risk of being ignored speaking rather than keeping quite. On the other hand, I suggested the participation of independent foriegn technocrats and rights groups because they are the only possible bodies who wouldn’t have much interest to rig the election for transition. My answer for the possible criticism put in ‘D’ is my enthusiasm that if we once established a legitimate house of representatives, the rest would be taken care of by them. Controversial issues will always be there. But, in the way down the road from there, everything to reform including constitutional ammendments is possible for it is easy to do so once a platform is lay for democracy. The most urgent and important issue, for me, now is forming a legitimate government for the majority.

በአሁኑ ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ በአጋዚ ወታደር መወረሯን መረጃ ደርሶናል፡፡ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ትገኛለች፡፡ ማርቆስን ጥቁር ደመና ተጭኗታል፡፡ ህዝቡ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ለአጋዚ ወታደር የምግብና የመጠጥ አቅርቦት የሚሰጥ ሆቴል ካለ ህዝቡ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው በተደረገው ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ የትልቅ ሆቴል ህዝባዊ ወገንተኝነቱን ወደ ጎን በማለት የሰረታው ስህተት ዋጋ እያስከፈለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው […]

በጎጃም የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች እየታዩ ነው። ከደጀን ተነስቶ ወደ ባህር ዳር የሚወስደዉን መንገድ እናበምርጦ ለማሪያም አድርጎ ከደሴ የሚመጣው መንገድ በምታገናኘዋ በግንደ ወይን ከፍተኛ ተቃዉሞ ተነስቷል። ከደጀን በደብረ ማርቆስ አድርጎ ወደ ባህር ዳር […]