
በጎጃም የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች እየታዩ ነው። ከደጀን ተነስቶ ወደ ባህር ዳር የሚወስደዉን መንገድ እናበምርጦ ለማሪያም አድርጎ ከደሴ የሚመጣው መንገድ በምታገናኘዋ በግንደ ወይን ከፍተኛ ተቃዉሞ ተነስቷል። ከደጀን በደብረ ማርቆስ አድርጎ ወደ ባህር ዳር በሚወስደዉም መስመር፣ በጅጋ፣ ፍኖት ሰላም ፣ ማንኩሳ የሕዝቡ ቁጣ የተቀጣጠለ ሲሆን፣ ከወለጋ ወደ ወደ ባህር ዳር እና በደብረ ማርቆስ አድርጎ ከደጀን ወደ ባህር ዳር የሚወስዱትን መንገዶች የምታገናኘዋም የቡሬ ከተማ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ ተቃዉሞ ነው የተሰማው።
ከቻግኒ ከሚመጣውና በዳንግላ በኩል አድርጎ
ወደ ባህር ዳር ከሚወስደው መንገድ ዉጭ፣ በጎጃም ባሉ ዋና ዋና መንገዶች በሙሉ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች እየተደረጉ ናቸው። በቅርቡ በዳንግላ፣መራዊ በመሳሰሉት ቦታዎች ተቃዉሞ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በጎጃም ስለነበረዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ እንደሚከተለው አቅርቧል፡
ቡሬ ( በደብረ ማርቆስና በነቀምቴ መካከል ያለች ከተማ)
===
ቡሬ፤ በሬ ዛሬ የዐማራ ተጋድሎ ከተካሔደባቸው ከተሞች ዋነኛዋ ናት፡፡ ከጠዋቱ ሦስት ሰአት አካባቢ የጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እስከ ምሽት 12 ሰአት ድረስ ቆይቷል፡፡ የተጋድሎ ሰልፉ ማዶ በሚባለው የከተማው ክፍል የተጀመረ ሲሆን ከሰላሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጋድሏቸው ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ ወልቃይት ዐማራ ነው፤ ኮ/ል ደመቀ እና የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሜቴዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፤ መሬታችን ይመለስ፤ 25 ዓመት ታስረናል አሁን ግን በቃን፤ ዐማራነት ወንጅል አይደለም፣ ወያኔ ሌባ ነው፤ ብአዴን እኛን አይወክልም… የሚሉ መፈክሮች ገልተው ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ንብረት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ትንሳኤ ሆቴል (ባለቤቱ ዐማራ ሲያስገድል የኖረ ሕወሓት ነው)፣ ቀበሌ 01 ጽ/ቤት፣ አብቁተ፣ የዓባይና የንግድ ባንኮች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ሊያወድሙ የሚፈልጉ ተላላኪዎችን ወጣቱ ዐማራ አክሽፎታል፡፡ ኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ መቆም አለበት ሲሉም የዐማራ ሕዝብ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ መኖሩን በተመለከተ ላቀረብነው ጥያቄ የዐይን ምስክር ሲናገሩ ‹‹እኔ በዐይኔ አንድ ለእረፍት የመጣ የዩንቨርሲቲ ተማሪ አጋዚ ሲገድለው አይቻለሁ፤ ሦስት ዐማሮችም በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል፤ በሕይወት ስለመኖር አለመኖራቸው ያወቁት ነገር የለም›› ብለዋል አንድ እማኝ በስልክ እንዳረጋገጡልን፡፡ የአጋዚ ወታደሮች ያቆሰሏቸው ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በቡሬ ከተማ መግቢያና መውጫ በሮች ሙሉ በሙሉ በወጣቱ ተዘግተዋል፡፡
ጅጋ ( በደብረ ማርቆስና ቡሬ መካከል ያለች ከተማ)
===
ጅጋ፤ የጅጋ ዐማሮች ዛሬ ለሦስተኛ ቀን የዐማራ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ የጅጋ ከተማ ሕዝብ ከነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በየቀኑ ወደ አደባባይ እየወጣ ተጋድሎውን እያደረገ ነው፡፡ በጅጋ እስካሁን አንዲት እህታችን ተሰውታለች፡፡ ከተማዋንና አጠቃላይ ወረዳውን ዐማሮች ራሳቸው የተቆጣጠሩ ሲሆን ዛሬ ላይ የሃይማኖት አባቶች ወጣቱን ለመሰብሰብ ሞክረው ነበር፡፡ የዐማራው ወጣትም ከእንግዲህ በኋላ የዐማራ የመኖር መብት ሳይረጋገጥ ተጋድሎው እንደማይቆም እንቅጩን በአንድ ድምጽ ተናግረው ስብሰባው ያለስምምነት መበተኑን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በጅጋ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ምንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴም የለም፡፡ ሁሉም ዐማራ የተጋድሎ ጥያቄውን እያስተጋባ ነው፡፡ በስልክ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ‹‹ከእንግዲህ በኋላ ዐማራነት ወንጅል ሆኖ የምንኖርበት ምንም ምክንያት የለም፤ የአባቶቻችን የአርበኝነት ታሪክ በዚህ ትውልድ ይደገማል›› ሲሉ በጎበዝ አለቃዎች ጭምር መመራት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
ቋሪት
===
ቋሪት፤ በቋት ወረዳ ገነት አቦ ከተማ ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ አድማሱን አስፍቶ የወረዳዋ ከተማ ገበዘ ማርያምም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆናለች፡፡ ገነት አቦ ከተማ ትናንት ከቀኑ ከ9፡00 እስከ 12፡00 የነበረውን የዐማራ ተጋድሎ ለማደናቀፍ ከወረዳው የወያኔ ተላላኪዎች የተውጣጡ የፖሊስና የሚንሻ አባላት ወደ ገነት አቦ ተላኩ፡፡ የገነት አቦ ዐማሮችም በአንድ ድምጽ ‹‹በመጣችሁበት መኪና አሁኑ ተመለሱ፤ አይ ካላችሁ ሕይወታችሁን ጠልታችኋል ማለት ነው›› አላቸው፡፡ ከመኪና ሳይወርዱ ተመለሱ፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ለዛሬ ጠዋት ቀጠሩ፡፡ በቃላቸው መሠረት ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ የተጋድሎ ሰልፉ ተካሄደ፡፡ የገበዘ ማርያም ከተማ ዐማሮችም ተጨመሩ፡፡ የከተማ ፖሊሶች ዝም አሉ፡፡ ከዞን የመጣ ሁለት መኪና የፌደራል ፖሊስም የቋሪትን ዐማራ መጋፈጥ አልቻለም፡፡ የፌደራል ፖሊሶች ልብሳቸውን ቀይረው ተደብቀው ዋሉ፡፡ ነፍጠኛው ዐማራ ጥይቱን ሲቆላው ዋለ፡፡ ለዚህማ ቋሪትን ማን ብሎት፡፡ በቋሪት ነገም የዐማራ ተጋድሎ ይቀጥላል፡፡
ማንኩሳ
=====
ማንኩሳ፤ በማንኩሳ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን ሰምተናል፡፡ በማንኩሳ ትናንት የተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ መጠነኛ ቢሆንም ዛሬ ግን ወደ አደባባይ ያልወጣ የከተመዋ ነዋሪ አልነበረም ነው የተባለው፡፡ በማንኩሳ ዝርዝር ጉዳዮችን በስልክ መቆራረጥ ምክንያት ማግኘት አልቻልንም፡፡
ፍኖተ ሰላም
=======
በፍኖተ ሰላም ከተማ የዐማራ ተጋድሎ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ ትናንት የአንድ ዐማራ ወጣት ነፍስ ያጠፈው ቅጥረኛ ምንሻ ቤት መቃጠሉንም ሰምተናል፡፡ የፌደራልና የአጋዚ ጦር በፍኖተ ሰላም ከተማ ከመጠን በላይ መግባቱን ሰምተናል፡፡ ዛሬ ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ሰዐት ድረስ መንገዶች ሁሉ ዝግ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡
ጉንደወይን
======
(ጉንደወይን ከደጀኝ አድርጎ በሞጣ፣ ደብረ ወርቅ በኩል አድርጎ ወደ ባህር ዳር በሚወስደው መንገድ ላይ ያለች ከተማ ናት)
በእነሴዎች አገር ጉንደወይን ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ታላቅ የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ተካሒዷል፡፡ የጎንቻ ሲሦ እነሴ ወረዳ ዐማሮች ትናንት ባካሔዱት ተጋድሎ የትግራይ የበላይነት ይብቃ፣ የማንነት ጥያቄያችን መልስ ይሰጥ፣ ዐማራነት ወንጀል አይደለም፣ የወንድሞቻችን ደም መፍሰስ መቆም አለበት… የሚሉ መፈክሮች መሰማታቸውን ዛሬ ከጉንደ ወይን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በተያያዘም ነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በብቸና አንድ የአገዛዙ መሣሪያ የሆነ ሰው ተገድሎ መገኘቱንም ሰምተናል፡፡
ንጉሡ ሞቱማ says:
August 26, 2016 at 7:54 pm
የመጨረሻው ሰዓት የዳግም አድዎ ዘመቻ ጥሪ ፣ ቁጥር 23 አሰቸኳይ አዋጅ ( Very Urgent last Call for all oposition party’s to come up under one umberrela of great Adowa freedom movement to save Ethiopia first!!!) የሽግግር ደንብ ሁሉ በ24 ሰአት የመረጃ አገልግሎት በኢሳት ሬድዮ ይተላለፈል። ኢሳትን፣ ግንቦት 7 ፣ የአቶ ኦባንግን ድርጅት ተሳፈዎቻችን ናቸው እርዱ እባካቹ!!! ጥሪው ለሁሉም ድርጅቶች እና ኢትዮጵያዊ የማዳን ጥሪ ነው። ከአሁን በጛላ ደም እያፈሰሱ፣ እስርቤት እያሰቃዩ አስመስሎ ሥልጣን ላይ መቆየት በኢትዮጵያ ምድር ከቶም አይሞከርም። ሁሉም በቋንቋው እና በኢትዮጵያነቱ በ አማራ፣ አሮሞ፣ በትግራይ፣ ደቡብ፣ሱማሌ፣አፋር፣ ጋምቤላ ሁሉም አንድ ነን ብለህ በመጀመሪያ ከአጠገብህ ያሉትን ሆዳሞችን እናጥራ ጉዞ ወደ ድል ጎዳና። ወያኔዎች ጋኔኖች መሆናቹ አለም አወቃቹ ለትግራይ ህዝብ ላይ ነጥለን እነዚህ የግዚያዊ ጋኔኖችን ነጥለን አናውጣ። መስነጣጠቅ አበቃ ኦሆዴድ፣አነግ የዘር መርዝ የድሮ መንግስት እንደዚህ አረገ አበቃ ሁሉም ነቃበቹ በ21ኛ ክፍለ ዘመን 25 አመት ሽወዳቹን በቃቹ 2ኛ ግዜ መሸወድ ከሰባቹ የመጨረሻ ደውል ሊደወልባቹ ነው። እናንተ ጋላ የምትሉት ስድብ መስሎአቹ ይሆናል? ግን የላቲን ትርጉሙ ጋላ ማለት ጀግና እውነተኛ ወደ ጛላ የማይመለስ ማለት ነው። አማራ ነፍጠኛ አላቹ አባሎቹን የንፁሐን ደም ጠ ጣ ቹ አንቺ ጋኔን ወያኔ በቃች አሁን! ኢትዮጵያዊ ነኝ ስትል በትርጉሙ ከእግዚአብሔር የወርቅ ስጦታ መጠሪያ ተብለህ የምትጠራ፣ አረንጓዴ፣ ብጫ፣ቀይ ቀስተ ደመና መለያህ፣ የጋኔኖች ኮከብ የሌለው በአንድነት የምትጠራ፣ ከአለም በፈት ክርስትናን ተቀብለህ የወንድሞችህን የምትኮራበትን መስሊም እምነት አሰጠልለህ ዛሬ ለአለም የበረከትክ በአንድነት ተነስ። አየር ሀይል፣ በቴኮንዶ የሠለጠንክ፣ በጦር፣ በፓሊስ የጎበዝ አለቃ ምረጥ ፈጣረህን ለምነህ ተሰለፈ ከሁን በኋላ ዝም ብሎ መሞት የለም። የደሀውን ንብረት አታውድሙ ኮከብ የሴይጣን ምልክት የሰቀለ እርምጃ ይወስድበታል። ከአሁን በኋላ ደረጃችን ከፍ አጠገብ ባላህ መሳሪያ አንደ አረብ አብዬት ሁሉም በአንድ ቀን እና ስአት ውጥቶ ይጨርሳል። ትግስተኛው ህዝባችን ጨዎነት በተሞላ መልክ እነዚህን ጋኔን ወያኔዎችን ነጥሎ ብቻ ከንፀሑ ትግራይ ህዝብ በወጣ መልኩ ደረጃውን ከፍ ያለ ትእዛዝ ተቀብላቹ ከሽግግሩ ሰላማዊ አስተዎፃኦ እንደታደርጉ እናሳስባለን።
1ኛ አሁን የወሬ ግዜ የለንም የታወራቺ ፓለቲከኞች ካላቹ ሜዳውን ለቃቹ ውጡ። ምንም አይነት ክፍተት በአገራችን ሳይፈጠር የሽግግር መንግስት ለ5 አመት ፔሬዝዳንት በደ/ር ብርሐኑ ነጋ እና ጦሩ በሙሉ በጄ/ር ከማል ገልቹ እና የትግራይ ነፃ አውጭ ይመራል። ከ 5 አመት የፈለገ እኔ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ አይን አስተዳደራለሁ የሚል ብቻ ተመርጦ ይረከባል። የሥልጣን ግዜ ከበዛ በጥምረት ለ 8 አመት ብቻ የተገደበ የሆናል። ከዚህ ውጭ ካላቹ ደ/ር ብትሆነም የሕዝባችን መከራ በአንድ ላይ ቆመን ማብቃት አለብን።
ውርደት ሞት ለ ሆዳም 1000 ለአደዎ፣ ወቅሮ ሐዲጊዎች ወያኔዎች ኢትዮጵያን ሳያቋት በግምት 25 ገዙ።
2ኛ የትግራይ ነፃ አውጭ ልዩ ሐይል በመቀሌ ፣ በአዲስ አበባ ከዋና ባለሠልጣን ጠበቂዎች ጋር ተደራድሮ አየጨረሰ ይገኛል። የጎበዝ አለቃዎች ፓሊሶች እና ህዝቡ ሚድያው ላይ ወዲያውኑ የማረጋጋት ዘመቻ ታደርጋላቹ።
3ኛ ከአሁን በኋላ ስው ገላቹ የትም አለም ኢትዮጵያዊ ባለበት መኖር አይችሉም። በወንድም ኤርትራውያን ስም የፓለታካ ጥገኝነት የጠየቃች ከኢሐዲግ እና ኢምግሬሽን ፀ/ቤት በእጃችን ገብቷል።
4ኛ ከአሁን በኋላ በማንኛውም ቦታ አልሸባብ ወይም ተቀዎሚ ብሎ በፈነዳ 100% የኢሐዲግ የሽብር ገብረሐይል ሁሉም ተጠያቂ ነው አሁን በእጃችን በገባው መረጃ መሠረት።
5ኛ መረጃቹ ሁሉ ከእናንተ ጋር አየዋልን ተቆጣጥረናችሃል። አሁን የሚያዎጣች ለአደረጋቹ በደል ከአንደበታቹ የቅርታ ይህንን ጨዎ ሕዝባችንነው ጠይቃቹ ስልጣን አስከ መስከረም 15 ቀን 2009 ድረስ ማሰረከብ አለበለዚያ ህዝቡ ከጦሩ ጋር በአንድ ቀን ስአት ይበላችሃል። በየለበት ለጦሩ ፣ ለፓሊስ ድንበር አከባቢ ጠመንጃውን እንዲያዞር በራሪ ወረቀት በትኑ፣ ለእናት አባታቸው አስተላለፈ።
ንጉሡ ሞቱማ የኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ማህበር የለውጥ አራማጅ የአምቦ ኮር አዛዥ።
ግልባጭ:• በአገር ውስጥ እና ውጭ ባላቹበት የኮር አዛዦች
[Reply]
Reply
What happened to g7 45000 army at this critical moments?
ለህዝብ ይሰራሉ ያገለግላሉ የተባሉ ከከፍተኛ እስከታችኛው እርከን ድረስ ያሉ ትግሬ/ኢህአዴግ ሹሞች በዘረጉት የጥቅም ትስስር መረብ የህዝቡን የአገሪቱን የመንግሥትን ሀብት ያለአንዳች ይሉኝታና ርህራሄ ያውም ህዝብ እያወቀ ግጠው ልጠው በልተውታል፡፡ጊዜና አጋጣሚ የሰጣቸውን መንግሥታዊ ወንበር ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ ለዘረፋና ለቀማኛነት አውለውታል፡፡
ትግሬ/ኢህአዴግ ውስጡ ባለመጥራቱ ጥገኛውና ኪራይ ሰብሳቢው ኃይል አይሎ በመገኘቱ ከመጋለጤና ከመጠየቄ በፊት ትርምስ መፍጠሩ ያዋጣኛል በሚል ለተፈጠሩት ቀውሶች ሁሉ ምክንያት በመሆኑ ህዝቡን ተቃውሞ
እንዲህ የከረረ ደረጃ አድርሰውታል ::
ማንበብ ለወያኔ ጠንቅ ነው! የሚያነብ ሰው ከኢትዮጵያ ይጥፋ የወያኔ መፈክር!
የሕዝብ መተባበር ለወያኔ ውድቀት ነው!
ሕዝብ አብሮ አይኖርም!እንዳይተባበር በመካከላቸው ጎጠኞችን ያሰማራል! ሆድ አደር ሃገሩን ወገኑን ያጠፋል!
ወያኔ ኢትዮጵያዊያን ከድህት አትወጡም እኛ ወያኔዎች እንገድላለን!እናስገድላለን!
የሃይማት ተቆሞችን ያፈርሳል!
በሃማኖታችሁ አታምኑም!
ጸሎት አታደርጉም!
በሃገራችን አትኖሩም! ስደት ሂዳችሁ ነሩ!
ከቤትንብረታችሁ እናፈናቅላለን!
ተውኝ
በባህርዳር ከተማ የሕዝብ አልገዛም ባይነቱ እንደቀጠለ ነው:: በዛሬው እለት መንግስት በአማራው ህዝብ ላይ መከላከያ ሰራዊቱ የዘር ማጥፋት እርምጃ እንዲወስድ ካዘዘ በኋላ ሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ሲቃወም ውሏል:: በዚህም መሰረት የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች ከሰሞኑ ተቃውሞዎች አፍሰው ወስደው ያሰሯቸውን እስረኞች ሕዝቡ እስር ቤት ሰብሮ በመግባት ማስፈታቱ ታውቋል::
የባህርዳር ዙሪያ አርሶአደሮች ባደረጉት ከፍተኛ ተጋድሎ በሰባታሚት እስር ቤት የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞችን ሲያስፈቱ በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ከሕዝቡም ከመከላከያ ሰራዊቱም ለጊዜው ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው መቁሰሉ ተሰምቷል::
በባህርዳር ሕዝብ ጎማዎችን በየአካባቢው ሲያነድ እና በድንጋይ መንገዶችን በመዘጋጋት ከትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ጋር ሲፋለም ነው የዋለው::
ዛሬ ባህርዳር የጦር አውድማ መስላ የዋለች ሲሆን ጋዜጠኛ ሙሉ ቀን ተስፋው ምን ሲፈጠር እንደዋለ እንደሚከተለው አስቀምጦታል::
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወታደሮችን በማመላለስ ተጠምዷል
* ዛሬ ከባሕር ዳር አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከጠዋት ጀምሮ የትግሬ መከላከያ ሠራዊት ሲያመላልስ ውሏል። እስካሁን ድረስ 5 ትልልቅ አውሮፕላኖች ከ1000 በላይ አጋዚ አራግፈዋል። የባሕር ዳር ወጣቶች በአየር መንገድ በኩል ያለውን መንገድ እንዲዘጉም መረጃውን የሰጡን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ወያኔ በማንኩሳ ዐማሮች ላይ ሙለ ጦርነት አውጇል
ከማንኩሳ አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የወያኔ ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች ሕጻናትን ጨምሮ በደካሞችና አዛውንቶች ላይ ሁሉ እያነጣጠሩ እየተኮሱ ነው።
* ከባሕር ዳር 45 ኪሎ ሜትሮችን በምትርቀው የጉማራ መንደር እስከ ዛሬ ሌለት ድረስ በቆየ የተኩስ ልውውጥ 8 የወያኔ ፌደራሎች ተገድለዋል። 2 ዐማሮች በተጋድሎው ተሰውተዋል። የ8 ፌደራል ሙሉ ትጥቅ ገበሬው ተከፋፍሏል። መንገዶች ዝግ ሲሆኑ ሕዝቡም ራሱን እያስተደዳረ ነው።
* በባህር ዳር እና አዋሳኝ በሆኑ ከተሞች በህዝብና በወያኔ ቅልብ ወታደሮች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው፡፡ ከባህር ዳር ወደ ጭስ አባይና አዴት ሞጣ ቢቸና በሚወስደው መንገድ ላይ በምትገኘው ሰባታሚት ላይ የአማራ ህዝብ ወያኔን በአኩሪ ጀግንነት እየተፋለመ ነው፡፡
በባህር ዳርም ቀበሌ 7 እና 17 ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው።የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አማራውን በተለይም ጎጃም እና ጎንደርን እንደ ሶሪያና ሕዝቧ ሊያወድማት እየተዘጋጀ ነው:: ዛሬ የሕወሃት ተላላኪው ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመከላከያ ሰራዊቱ አማራውን እንዲያጠፋ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ በደሴ መስመር ብረት ለበስ መኪናዎችና የጦር መሳሪያዎች ወደ ጎጃም እና ጎንደር እየተጓዙ መሆናቸው ጨጨሆ ላይ እነዚህን በደሴ መንገድ እየተጋዙ ያሉትን የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮችን ህዝብ እንዲያስቆማቸው ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ምን ላይ እንደደረሰ ግን ለማወቅ አልተሳካም::
በሌላ በኩልም ከነቀምት ወደ ቡሬ ጎጃም የጦር ታንኮች እየተጋዙ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሆነ በጎጃም እና ጎንደር ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ እልቂት ለማድረስ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ቆርጦ በመነሳቱ ታንኮችን ጭምር እያጋጋዘ ነው::