ባህር ዳር እሁድንና ዘመን መለወጫን በለቅሶ እያከበረች ነው

ባህር ዳር እሁድንና ዘመን መለወጫን በለቅሶ እያከበረች ነው። (#ማንደፍሮ_አስረስ ለ35 ቀናት የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ሊተርፍ አልቻለም)
ባህር ዳር የአማራ ተጋድሎ በፍፁም ሰላም ተጀምሮ እስካሁንም ጭፍጨፋ የቀጠለባት ከተማ ናት።
ለቁጥር አዳጋች ወጣቶችና ህፃናት ተሰውተዋል።
ዛሬም በአጋዚ ቆስለው በሞትና ህይወት መካከል ካሉት ውስጥ አንዱ የቀበሌ አራት እንቁጣጣሽ ሆቴል ፊት ለፊት ወጣቱ #ማንዴ_ህይወቱ አልፏል። ቀብሩም በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ደምቆ አሁን።ከደቂቃዎች በፊት መድሃኒያለም ቤተ ክርስትያን ተፈፅሟል።
ማንዴ በአጋዚ ጥይት ሆዱን የተመታው አባይ ማዶ (August 1) ነው።
ይህ ዕለት ማንዴና መሰሎቹን ያስነጠቀን ክፉ ቀን ነው።ሰዎች ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲገልፁ መስዋት ሆነዋል።
ማንዴና መሰል የአማራ አብራኮች የዘላለም የትግል ምሰሶ ተክለው አልፈዋል።እኛ የምንሞተው የተሰው ጓደኞቻችን አላማ ዳር ሳናደርስ ስንቀር ነው።
አያለው መንበር ክ ባህር ዳር