በዩክሬይን የሩስያና የምዕራቡ ዓለም ፍጥጫ
ዩክሬይን፤ ዛሬም የዓለም ልዕለኃያላኑን እንዳፋጠጠች ነው። በክሬሚያ የነገሰው ውጥረት ልሣነ-ምድሪቱን በሕዝበ-ውሳኔ ለሩስያ ግብር ዳርጎ ወደ ምሥራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ተዛምቷል። መፍቀሬ-ሩስያውያን በምሥራቅ ዩክሬይን በርካታ የመንግሥት ተቋማትን እንደተቆጣጠሩ ነው።
ዩክሬይን፤ ዛሬም የዓለም ልዕለኃያላኑን እንዳፋጠጠች ነው። በክሬሚያ የነገሰው ውጥረት ልሣነ-ምድሪቱን በሕዝበ-ውሳኔ ለሩስያ ግብር ዳርጎ ወደ ምሥራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ተዛምቷል። መፍቀሬ-ሩስያውያን በምሥራቅ ዩክሬይን በርካታ የመንግሥት ተቋማትን እንደተቆጣጠሩ ነው።
የዕለቱ ዜና
ድርጅቱ በመንግሥት ይፈፀማል ካለው ስለላ ሰለባዎች መካከልም ተቃዋሚዎች ጋዜጠኞች እንዲሁም ፀረ መንግሥት እንቅስቃሴ አካሂዳችኋል ተብለው የታሰሩ ሰዎች ይገኙበታል ። መንግሥት ግን ለአንዳንድ የዜና ወኪሎች በሰጠው ምላሽ ዘገባውን አስተባብሏል ።
ጊኒ ቢሳው ውስጥ ለብዙ ጊዜ ሲተላለፍ የቆየው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እሁድ ሚያዝያ 5 ቀን፥ 2006 ዓም ይካሄዳል። የሀገሪቱ ሕዝብ እአአ በ2012 ዓመ መፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ ወዲህ አንድ ሕጋዊ መንግሥት እንዲመሠረት ሲጠብቅ ነው የቆየው።
የዓለም ዜና
የጀርመን የኤኮኖሚና የልማት ትብብር ሚኒስቴር ሀገሪቱ ለልማት የምታዉለዉን የርዳታ በጀት ማሳደጉን አስታወቀ። ምክር ቤት ከትናንት በስተያ በልማት በጀቱ ላይ ክርክር አካሂዷል። የተቃዉሞ ፖለቲከኞች ሀገሪቱ ከዓመታት በፊት ለአዳጊ ሃገራት የልማት ርዳታ የበለጸጉት በየዓመቱ እንዲያዋጡ ከተስማሙበት መጠን ለመድረስ ጀርመን ይቀራታል ሲሉ ተችተዋል።
በሸንጎዉ መግለጫ መሠረት ነፃ ምርጫ ለማድረግ እስመራጭ ኮሚሽን፤መገናኛ ዘዴዎች፤ፍርድ ቤቶች፤ ሕግና ፀጥታ አስከባሪዎች ገለልተኛ መሆን አለባቸዉ
ማንኛውንም መንገድ ተደቅመው ዳግም ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚሰደዱ ወጣት ኢትዮጵያንኖች ባለፈው ህዳር ወር የሳውዲ ዓረቢያ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ ህገ ወጥ የሚለውን ስደተኞች እያሰረ ከሀገር ሲያባርር፤
የአንደኛዉ የዓለም ጦርነት ከመጀመሩ በፊት አባታቸዉ የቀድሞዉ የጀርመን የቅኝ ግዛት አፍሪቃ ሃገር ከካሜሩን ወደ ጀርመን ሲገቡ፤ በደስታ ነበር አቀባበል የተደረገላቸዉ። ቆየት ብሎ ግን አፍሪቃዊዉ በቆዳ ቀለም ላይ የተመሰረተ ጥላቻን አዩ፤ እየቆዩም የቅኝ ግዛት ፊልሞችን በተመለከተ በሚሰሩ ፊልሞች ላይ አጫጭር ተዉኔቶችን እንዲተዉኑ ተደርገዋል።
የአዲስ አበባ፤ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች፤የመጠጥ ዉሃ ቧንቧ፤ ከመፀዳጃ ቤት ቧንቧ ጋር በመገናኘቱ ለህመም ተዳርገናል ሲሉ አማረሩ።
ከሊቢያ የባህር ዳርቻ በሜዲተራንያን ባህር በኩል በጀልባ ወደ ደቡባዊ ኢጣልያ ግዛቶች የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ።
ዩጋንዳ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በእስር የሚፈለጉትን የዓማፂው ቡድን «ሎርድ ሬዚስተንስ አሚ፣ » በምሕፃሩ « ኤል አር ኤ» መሪ ጆሴፍ ኮኒን ለመያዝ በጀመረችው እንቅስቃሴ ላይ ዩኤስ አሜሪካ ተባብራ ትሰራለች። በዚሁ ትብብሯ ቀደም ሲል 100 ወታደሮች የላከችው የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ባለፈው
የጀርመን ሩዋንዳ ትብብር በመግባባትና በጋራ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ እንደሆነ የሩዋንዳ ባለስልጣን አመለከቱ። የሩዋንዳ የትምህርት ሚኒስትር ዴታ ማቲያስ ሃርባሙንጉ ሀገራቸዉ በአሁኑ ወቅትም በትምህርት ዘርፍ ከጀርመን የዳበረ ልምድ እየተጠቀመች ነዉ ይላሉ።
ሎንዶን ብሪታን ዉስጥ በዝቅተኝነት ከሚመደቡት ትምህርት ቤቶች በአንዱ ይማር የነበረ አዳጊ ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቢድ ካምሮንን ጨምሮ የሀገሪቱ 19 ሚኒስትሮች ወደተማሩበት ኮሌጅ የመግባት እድል አገኘ።
የሰርቢያ ተወላጅና የቀድሞዉ የጋና ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የነበሩት ጎራን ስቲባኖቪች ዋሊያዎቹን ለማሰልጠን ተመረጡ።
‘አረና ትግራይ’ በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን አፅቢ ወምበርታ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማካሄድ በተንቀሳቀሰበት ባለፈዉ ቅዳሜና እሁድ ከፍተኛ የአመራር አባላቱን ጨምሮ አባላቱና ደጋፊዎቹ መታሰራቸዉንና በድንጋይ መደብደባቸውን አመለከተ።
በአሁኑ ወቅት የአፍሪቃና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ግንኙነት አዲስ አቅጣጫ እንዲከተል ያስፈለገበት ምክንያትና ጥቅሙ ምንድነው ? የኤኮኖሚ ግንኙነቱ በሁለቱ ክፍለ ዓለማት የፖለቲካና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይስ ምን ዓይነት ተፅእኖ ያሳድራል ?ከኤኮኖሚው ዓለም የሚያነሳቸው ጉዳዮች ናቸው ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይዘሮ አስቴር ማሞን የሲቭል ሰርቪስ ሚንስትር እና በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር እና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪ እንዲሆኑ በዛሬው ዕለት ሾመ። ምክር ቤቱ ይህን ሹመት ያፀደቀው በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት ነው።
የዩክሬንና የሩስያ ውዝግብ ተባብሷል ። በሩስያ ስር መሆን እንፈልጋለን የሚሉ ኃይሎች ካለፈው እሁድ አንስቶ በአንዳንድ የምሥራቅ ዩክሬን ከተሞች ነፃነታችንን አውጀናል እያሉ ነው ። በነዚህ ኃይሎች ላይ ዩክሬን እርምጃ እንዳትወስድ ሩስያ እያስጠነቀቀች ነው ።
ኃይለኛ ትኩሳት፤ ራስ ምታትና የጡንቻ ህመም ከሚያስከትላቸዉ የህመም ስሜቶች ይጠቀሳሉ። በትንፋሽ ሳይሆን ከአካል በሚወጣ ፈሳሽና በመነካካት ይተላለፋል። እስካሁንም መድሃኒት አልተገኘለትም ኢቦላ ቫይረስ። ከሳምንታት በፊት ጊኒ ዉስጥ በሽታዉ ተከስቷል
በስዊድን በካሮሊንስካ ኢንስቲቱት እና በ«ሳይንስ ፎር ላይፍ» በተባለ ድርጅት መሪነት አምስት የስዊድን ዩኒቨርሲቲዎችን ያጠቃለለው የካንሰር ተመራማሪ የጥናት ቡድን በዓይነቱ ልዩ የካንሰር መከላከያ ዘዴ እንዳገኘ
የጥቁር ዓባይ ምንጭ የሆነው የጣና ሐይቅ እና አካባቢው በሚገባ ካልተጠበቀ እና እንክብካቤ ካልተደረገለት በመጪው ጊዜ አሳሳቢ መዘዝ ሊከተል እንደሚችል የጀርመን የተፈጥሮ ጥበቃ ድርጅቶች ጠበብት ጠቁመዋል።
አሜሪካ የሚገኘዉ የዓለም ዓቀፍ ወንዞች ተቋም፣ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጥናት ያካሄደዉ ቡድን ያወጣዉ ዘገባ፤ ግድቡ በተቀናጀ እና መጠነ ሰፊ ጥናት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን የሚጠቁም እንደሆነ ገለጸ።
ለበርካታ ዓመታት በራድዮ ጋዜጠኝነትና በአሰልጣኝነት ያገለገለችው ጋዜጠኛ ወይዘሮ ዓለምሠገድ ፈቃደ ሥላሴ ህሩይ አረፈች።
ፓሪስ ውስጥ በተካሄደው የማራቶን ሩጫ ውድድር አሸናፊ የሆነው ቀነኒሣ በቀለ ጡንቻው ላይ ህመም ባይሰማው ኖሮ የበለጠ ፈጣን ሠዓት ሊያስመዘግብ ይችል እንደነበር ለዶቸቬለ ገለፀ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል የዋንጫ ግስጋሴውን እያሳመረ ነው። ቸልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ ዋነኞቹ የሊቨርፑል ተፎካካሪዎች ሆነዋል።
የምርጫዉ ሒደት፤ነፃነቱ፤ አፎካካሪ፤ አሳታፊነቱም፤ ያዩ እንደመሰከሩት ፤ለእልቂት ፍጅት ማዕከሊቱ ታሪካዊት ሐገር አዲስ ታሪክ ነዉ።አፊቃኒስታን።ዘንድሮ አስራ-ሰወስት ዘመን የተዋጋባትን-የዉጪ ጦር ሸኝታ የአስራ-ዘመን ታሪኳን ለሚቀይር ሌላ ታሪክም ተሞሽራለች።
በትናንቱ የአፍጋኒስታን ምርጫ ምንም እንኳን እስልምና አክራሪው የታሊባን ታጣቂ ቡድን ጥቃት እንደሚዘነዝር ዝቶ የነበረ ቢሆንም፤ ለምርጫው በርካታ ሕዝብ መውጣቱን እንደሚያደንቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ገለፀ። ግድያ የታከለበት በርካታ ግጭት ቢከሰትም፤ የትናንቱን ምርጫ የተመድ ስኬታማ ሲል አድንቋል።
የዓለም ዜና
የዕለቱ ርዕሶች፤
ካሜሮን፤ ሶስት ታጋጆች የደረሱበት አልታወቀም
ናይጄሪያ፤ 30 የሚሆኑ ሞቱ በርካቶች ቆሰሉ
ማሌዢያ፤ የተሰወረው አይሮፕላን ፍለጋ እና ፍንጭ
አፍጋህኒስታን፤ ኦባማ ምርጫውን አወደሱ
ጀርመን፤ ወደ ሀገሪቱ ሕገ ወጥ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር ክፉኛ ጨመረ
ኢትዮጵያ፤ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የፓሪሱን ማራቶን አሸነፈ
ለትራፊክ አደጋዎች መከሰት የመንገድ አጠቃቀም ደህንነትን ከግምት አለማስገባት ዋናዉ መንስኤ እንደሆነ ይታመናል።
ወጣት የርዋንዳ ዜጎች በሀገራቸው እአአ 1994 ዓም በተካሄደው የጎሣ ጭፍጨፋ የሞቱትን ለማሰብ 2014 ዓም ከገባ ወዲህ አንድ ማስታወሻ ችቦ በመላይቱ ሀገር ይዘው በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ። እአአ የፊታችን ሰኞ፣ ሚያዝያ ሰባት፣ 2014 ዓም ችቦው መዲናይቱ ኪጋሊ ይገባል። በዚሁ ዕለት የጎሣው ጭፍጨፋ የተጀመረበት 20ኛ ዓመት ይታሰባል።
አፍጋኒስታን ውስጥ ዛሬ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በመካሄድ ላይ ነዉ። ፕሬዚዳንት ሃሚድ ካርዛይን የሚተካ ለመምረጥ ወደ 12 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ለምርጫ መጠራቱ ተመልክቷል።
አንድ ሰው ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ እንዲማር ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለበት ግልፅ ነው።የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ከነዚህ ተማሪዎች አንዱ ነው።
ብራሰልስ ቤልጂግ ውስጥ ለ2 ቀናት የተካሄደው 4ተኛው የሁለቱ ክፍለ ዓለማት መሪዎች ጉባኤ ሲጠናቀቅ መሪዎቹ የጋራ ችግሮቻቸውን በጋራ ለመፍታትም ፅኑ አቋም እንደያዙ አስታውቀዋል ።
በአፍጋኒስታን የምርጫ ዋዜማ ለመዘገብ ወደዚያ አምርተው ከነበሩ ጋዜጠኞች መካከል አንዲት ጀርመናዊት የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ በዛሬው ዕለት መገደሏ ተነገረ። ካናዳዊቷ ባልደረባዋ ቆስላለች። አፍጋኒስታን ዛሬም ፀጥታዋ መረጋጋትን አይጠቁምም።ታሊባኖች ፣ 6 ዓመታ
የጀርመን ፌደራል ጦር እጎአ ከ2010 አንስቶ የሶማሊያ ወታደሮችን በማሠልጠን ይሳተፋል። እስካሁን ሥልጠናው የሚሰጠው ዩጋንዳ ነበር። የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ከአሁን በኋላ የጀርመን ወታደሮች ስልጠናውን ሶማሊያ ውስጥ መስጠት ይጀምራሉ።
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ሪፖርት አቅራቢ ፤ በኤርትራ ሳይቋረጥ የቀጠለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በተለይም በብሔራዊ የውትድርና አገልግሎት ረገድ የሚታየው እጅግ የሚያሳስብ ነው ሲሉ ድርጅቱ ሁኔታውን እንዲከታተሉ ያሠማራቸው ወ/ት ሼይላ
«ዩክሬን ለወደፊቱ የትልቅ ገበያ ትስፋ አላት።»ተስፋዉ በርግጥ አማላይ ነዉ። የዩክሬን እዉነታ ከሚባለዉ መቃረኑ እንጂ ቀቢፀ-ተስፋዉ። የዩክሬን ሕዝብ የነብስ ወከፍ ገቢ የሞንጎሊያን እንኳን አያክልም። 3800 ዶላር። ኢንዱስትሪዎችዋ-አሮጌ ናቸዉ። ብልጣብልጥ፤ አታላይ፤አጭርበርባሪ ነጋዴ ፤ደላላ፤ ባለሥልጣናት ከብረዉባታል።
ኬንያ በተጠርጣሪ አሸባሪዎች ላይ ዘመቻ ከፍታለች ። ፖሊስ ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ በአሸባሪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቤት ለቤት አሰሳ እያደነ በማሰር ላይ ነው። እስከ ትናንት ድረስ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች መታሰራቸው ተገልጿል።
በደቡብ ኢትዮጵያ በምትገኘው የቡታጂራ ከተማ የሚገኘው ሀኪም ቤት ከአውሮጳ ህብረት በተገኘ 40 ሚልዮን ዩሮ ርዳታ የእናቶችን እና የሕፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚያስችል ፕሮዤ ጀምሮ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። የተመ የሕፃናት መርጃ
4ኛው የአፍሪቃ መንግሥታት እና የአውሮጳ ህብረት ጉባዔ ትናንት ብራስልስ፣ ቤልጅየም በተከፈተበት ወቅት፣ ስለ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ እና ስለ ፕሬስ ነፃነት የተመለከተ ሴሚናር በዚችው ከተማ ተካሂዶዋል። ሴሚናሩን የጠሩት እና ያዘጋጁት
የዓረብኛ ሥነ-ፅሁፍ በኢትዮጵያ በተሰኝባቀረብነዉ ዝግጅት ላይ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ቋሚ ባልደረባ አቶ አህመድ ዘካርያ በኢትዮጵያ የተገኙት የዓረብኛ ሥነ-ፅሁፎች በዓረብኛ ፊደላት ይቀመጡ እንጂ ቋንቋዉ አገርኛ እንደሆነ በዝርዝር ገልፀዉልናል።
ጉባኤዉ ገና ሳይጀመር በፊት የአዉሮጳ ሕብረት የአፍሪቃ ሕብረት አባል ያልሆኑትን የአፍሪቃ መሪዎች ጋብዞ አባል ከሆኑት አንዳንዶቹን አለመጋበዙን የተቃወሙ የአፍሪቃ መሪዎች በጉባኤዉ አልተሳተፉም
ኢንተርኔት ፤ በአሁኑ ዘመን ችላ የማይባል የዕለታዊ ህይወት አንድ አካል ነው ከተባለ፣ አባባሉ ሢሦውን የዓለም ሕዝብ ብቻ ነው የሚመለከተው። አብዛኛው የዓለም ሕዝብ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባቀረበው መረጃ መሠረት የኢንተርኔት ተጠቃሚ