የደቡብ ሱዳኑ ጅምላ ጭፍጨፋና የተ መ ድ አቋም

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፣ በዘርና በጎሣ ላይ ያተኮረው የደቡብ ሱዳን የጀምላ ግድያ እጅግ እንዳሳሰበው ገለጠ። የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ቃል አቀባይ እንዳሉት ድርጅቱ የጅምላ ጭፍጨፋውንና ለግድያው መባባስ አስተዋጽዖ ያደረጉትን አካላት አውግዟል።