የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርትና የጀርመኑ የሙዚቃ ቡድን

ከ30በላይ የዓለም ቋንቋዎች ዝግጅቶችን የሚያሰራጨዉ ዶይቼ ቬለ ራድዮ እና የጀርመን የባህል ተቋም በመተባበር ባዘጋጁት መድረክ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሦስት ትምህርት ቤቶች ለተዉጣጡ ተማሪዎች በሙዚቃ የተደገፈ የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት ተሰጠ።