በአፍሪቃው ቀንድ የተከሰተው የድርቅ አደጋ አስከፊነት ቀስ በቀስ ሀቀኛውን ገጽታውን እያሳየ ነው። በተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ዘገባ መሰረት፡ ግማሽ ሚልዮን ህጻናት በአሳሳቢ የረሀብ አደጋ የሚሞቱበት ስጋት ተደቅኖባቸዋል።

ድርጅቱ ትናንት ባወጣዉ መግለጫዉ በሕዝብ ላይ ሽብር በመንዛት ሽብርተኝነትን ማስወገድ አይቻልም ብሏል።በሌላ በኩል በአሸባሪነት ተጠርጥረዉ የታሠሩት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የክስ ሒደት ለሌላ ጊዜ ተቀጥሯል

በምስራቅ አፍሪቃ በተከሰተው ድርቅ ሰበብ በብዙ ሚልዮን የሚገመት ህዝብ የሚቆጠር ህዝብ በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ የረሀብ አደጋ እንዳሰጋው የተመድ መስሪያ ቤቶች ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ የሚያወጡዋቸው መዘርዝሮች አስታወቁ።

ምስራቅ አፍሪቃን በመታው ድርቅ የተነሳ ኢትዮጵያ ፣ ኬኒያ ጅቡቲ ሱማሊያና ዮጋንዳ የሚኖር ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልፅዋል። ከድርቁ ጋር ተያይዘው የሚመጡ እንደ ኮሌራ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች እንዳይከሰቱም እየተፈራ ነው። ሮይተርስ የዜና ወኪል ባለፈው አርብ ይፋ እንዳደረገው አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን …

ኢትዮጵያውያን ያሰጋው የኮሌራ ወረርሽኝ Read more »

ሶሪያ ውስጥ በአምባገነኑ ገዢ በፕሬዚደንት ባሸር-አል-አሣድ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ በዋና ከተማይቱ በዳማስቆስ ጭምር እየጠነከረ ነው። የአገሪቱ የመብት ተቆርቋሪዎች እንዳስታወቁት ባለፈዉ አርብ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ ሲወጡ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋርም በየቦታው ግጭት ደርሶ ነበር።

በአፍሪቃ ቀንድ፡ በሶማልያ፡ በኢትዮጵያ፡ በኬንያ፡ በጅቡቲ እና በዩጋንዳ ከአስር ሚልዮን የሚበልጥ ህዝብ አስችኳዩ የምግብ ርዳታ ካልቀረበለት አስከፊ የረሀብ አደጋ እንዳሚያሰጋው ባለፉት ጥቂት ቀናት የወጡ የተመድ ዘገባዎች አስታወቁ።

የአሜሪካ ድምፅ (VOA) የአፍሪቃ ቀንድ የቋንቋዎች ክፍል ሐላፊ ዴቪድ አርኖልድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተደረገ ዉይይትን አላአግባብ አሠራጭተዋል በሚል ከሥራቸዉ ታግደዋል የሚለዉን ዘገባ ጣቢያዉ አስተባበለ። ዴቪድ አርኖልድ የዩናይትድ ስቴትስ የማሰራጪያ ጣቢያ የገዢዎች ቦርድ የመልክተኞች ጓድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ጋር ባደረገዉ …

የአሜሪካ ድምፅና የወያኔ ውዝግብ Read more »

  የምስራቅ አፍሪቃ አገራትን ዘንድሮ የመታዉ እጅግ አስከፊ ድርቅ በከፋ ደረጃ ላይ ደርሶአል፣ በእንስሳት ሃብት ላይም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ ሃላፊ አስታወቁ።

በኢትዮጵያ እና በጀርመን መንግስት መካከል የተካሄደዉ አዲስ የልማት ትብብር መረሃ-ግብር ድርድር ይበልጡን የትምህርቱን ዘርፋ ማስፋፋት ላይ ለማዋል በመስማማት መጠቃለሉን የጀርመን ኤኮኖሚ ተራድኦ ሚኒስቴር BMZ ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሌ ክልል የተለያየ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ ተደረሰባቸው ካላቸው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር ኦብነግ ተዋጊዎች ጋር የተያዙት የስዊድን ዜግነት ያላቸው ጋዜጠኞች ከታሰሩበት ከጅጅጋ ወደ አዲስ አበባ መንቀሳቀሳቸው ተሰምቷል ።