የአሜሪካ ድምፅና የወያኔ ውዝግብ
የአሜሪካ ድምፅ (VOA) የአፍሪቃ ቀንድ የቋንቋዎች ክፍል ሐላፊ ዴቪድ አርኖልድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተደረገ ዉይይትን አላአግባብ አሠራጭተዋል በሚል ከሥራቸዉ ታግደዋል የሚለዉን ዘገባ ጣቢያዉ አስተባበለ።
ዴቪድ አርኖልድ የዩናይትድ ስቴትስ የማሰራጪያ ጣቢያ የገዢዎች ቦርድ የመልክተኞች ጓድ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን ጋር ባደረገዉ ዉይይት ላይ ተካፍለዉ ነበር። በዉይይቱ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአሜሪካ ድምፅ ቃለ መጠይቅ እንዳይደረግላቸዉ ጠይቀዋል ያሏቸዉን ሰዎች ስም ዝርዝር አርኖልድ በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የአማርኛዉ አገልግሎት አሰራጭተዉ ነበር። ነጋሽ መሐመድ ሥለ ጉዳዩ የዋሽንግተኑን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን አጋግሮታል። ያዳምጡ
VOA – የአሜሪካ ድምጽ የስርጭቱን ይዞታ እስኪያሻሽል ወያኔ ትብብር አላደርግም አለ (reported on June 23, 2011)