–>ዋኤል ጎኔም የግብጽ ደኅንነት ሰዎች ደብድበው የገደሉትን ካሊድ ሰኢድ ለማሰብ ‹‹እኔም ካሌድ ሰኢድ ነኝ›› የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ ከፍቶ ለግብጽ አብዮት ያበቃ ሰው ነው፡፡ የመጀመሪያውን የአደባባይ እንውጣ ጥሪ ያቀረበው ይኸው የፌስቡክ ገጽ ነው፡፡ ዋኤል አደባባይ የወጡበትን የመጀመሪያ ቀን (ጃንዋሪ 25) አንድ ዓመት ለማክበር (Revolution 2.0 የተባለ) መጽሐፍ አሳትሟል፡፡ የመጽሐፉ ገቢ በሙሉ በአብዮቱ ለተጎዱ ሰዎች መደጎሚያ እንደሚውልም ተነግሯል፡፡ አሁን እዚህ ልጽፍላችሁ ያሰብኩት ግን ዋኤል ገጹን እና የግል ማንነቱን አስመልክቶ ለሚቀርብለት ጥያቄ ይሰጥ የነበረውን መልስ ነው (መጽሐፉ ላይ እንዳሰፈረው)፤ ዋኤል ኢትዮጵያዊ ቢሆንና የከፈተው ገጽም ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ… በሚል ምናባዊ ምሳሌ፡፡ ስለዚህ ጽሑፉ በዋኤል የተጻፈው በኢትዮጵያኛ ተተርጉሞ ነው ልትሉት ትችላላችሁ፡፡

ስምህ ማነው?
[1]ስሜ ሽብሬ ደሳለኝ ነው፤
[2]ስሜ ዩሱፍ አብደላ ነው፤
[3]ስሜ እስክንድር ነጋ ነው፤
[4]ስሜ ርዕዮት አለሙ ነው፤
[5]ስሜ አሕመዲን ጀበል ነው፤
[6]ስሜ አንዱአለም አራጌ ነው፤
[7]ስሜ በቀለ ገርባ ነው፤
[8]ስሜ ኦልባና ሌሊሳ ነው፤
[9]ስሜ መስፍን ነጋሽ ነው፤
[10]ስሜ አርጋው አሽኔ ነው፤
ስሜ…. ብዙ ነው፡፡
እኔ በጎዳና ላይ የተገደልኩ፣ ያለወንጀሌ የታሰርኩ፣ ያለሀጢያቴ የተገረፍኩ፣ መብቴን በፍርሐት የተነጠቅኩ፣ ከገዛ አገሬ የተሰደድኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡
ዕድሜህ ስንት ነው?
ዕድሜዬ ይህን ያህል ነው አልልም፤ ነገር ግን ከተወለድኩ ጀምሮ ያለው ያው አምባገነን መሪ ነው፤… ሙስናውም ያው ነው፤…. ጭቆናው ያው ነው፤… እናም በአገሬ የገነነው የፖለቲካ ፓርቲ ‹‹ተስፋ የለም›› ይባላል፡፡
ከጠቀስካቸው ሰዎች ጋር ዝምድና አለህ?
እነዚህ ሰዎች የተኛውን ውስጤን ቀስቅሰውታል… ዕድሜ ለነርሱ አሁን ለውጥ ማምጣት እንደምችል ይሰማኛል፤… ታዲያ በራዕይ አልተዛመድንም ማለት ይቻላል?… አንድም ቀን አግኝቻቸው የማላውቃቸው እነዚህ ሰዎች ወንድሞቼ/እህቶቼ ናቸው፡፡
ይህንን የምታደርገው ለምንድን ነው?
ወገኖቼ ላይ የሚደርሰውን በደል ተመልክቼ ወደጥናት ክፍሌ ስገባ እምባዬን መግታት አልችልም፤… ፍርሐት የተጫናቸው ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ውርደትን እንደሚታገሱ አየሁ… ከራሴ በመጀመር በፍርሐት የምሠራውን ስህተት ሁሉ ማረም ጀመርኩ፤ እናም ለዛ ነው ይህንን ገጽ የፈጠርኩት፡፡ ለተበደሉ ወገኖቼ ያለቀስኩት ለሞቱ ዘመዶቼ ካለቀስኩት በላይ ነው… በየዕለቱ ፎቷቸውን ስመለከት ድብታ ውስጥ እገባለሁ፤ ኢ-ፍትሐዊነትን እስከመጨረሻው ለመዋጋትም ለራሴ ቃል እገባለሁ፡፡
ማነው በገንዘብ የሚረዳህ?
ፈጣሪ ይመስገን፣ የገንዘብ ምንጮቼ ብዙ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ንቃተ ሕሊናዬ ነው… ይህ ምንጬ በቀን አራት ሰዓተ ብቻ እንድተኛ እና ጠዋትም ፊቴን ከመታጠቤ በፊት የፌስቡክ ገጼን እንድከፍት ያስገድደኛል፡፡

ሁለተኛው ምንጬ መማሬ ነው፡፡ በመማሬ ደስተኛ ነኝ፤ ዕውቀቴን አገሬን ለማገልገል አውለዋለሁ፡፡
ሦስተኛው ምንጬ የልጆች አባት መሆኔ ነው፡፡ ሁሌም የሚጨንቀኝ ልጆቼ አንድ ቀን ‹‹አባዬ፤ ዜጎች ሲጨቆኑ እያየህ አቅምህ የሚፈቅደውን ለምን አላደረግክም?›› ብለው ይጠይቁኛል ብዬ ነው፡፡
የመጨረሻው ምንጬ የሕዝብ ፍቅር ነው፡፡ አይቶኝ የማያውቅ፤ አይቼው የማላውቀው እና በስም የማንተዋወቀው ሕዝብ ፍቅር… በየዕለቱ የአመሰግናለሁ ማስታወሻ ይደርሰኛል…. የተለያዩ ዲዛይኖች፣ ሎጎዎች፣ ቪዲዮዎች ይልኩልኛል… ገጹ ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ ያስተዋውቁልኛል፡፡
ስለዚህ ምንድን ነው የምትፈልገው?
ይህንን ገጽ የፈጠርኩት ራሴን ከአደጋ ለመጠበቅ ብቻ አይደለም.. ነገር ግን አገራችን መልሳ የኛው የሕዝቦቿ እንድትሆን ከመፈለግ በላይ ሌላ ዓላማ የለኝም… አንድ ቀን እንዲህ ይሆናል ብዬ አልማለሁ፡- እርስ በእርስ ዳግም እንዋደዳለን፤ ሁላችንም ኢ-ፍትሐዊነትን እንቃወማለን፤ ከመሐከላችን ማንኛውም ሰው ክፉ ነገር ቢያይ ራሱ ይፈታዋል… እናም የመንግሥት ቅጥረኛ አንድን ዜጋ በጥፊ ከመምታቱ በፊት አንድ ሺሕ ጊዜ ያስብበታል፡፡
አትፈራም?
በጣም እፈራለሁ እንጂ፤… ፍርሐት እኮ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ነው… ለተጨቆኑ ዜጎች የሚቆረቆር እንደእኔ እና እናንተ ያለ ሰው ግን ካለ ፍርሐቴ ይከስማል… ዕጣፈንታችንንም የምንወስነው እኛው ራሳችን እንሆናለን… እንዲህ እያልን፡- ‹‹ማንም ያለዕድሜው አይሞትም፣ ማንም ያለወንጀሉ አይታሰርም፣ ማንም አገሩን ለቅቆ አይሰደድም…›› አንድ ዘመዴ በ25 ዓመቱ ሞተ… ቁም ነገር ካልሠራሁበት የኔ ዕድሜ መርዘሙስ ምን ዋጋ አለው?
ብዙ ሰዎች ይህንን ለማመን ይቸገራሉ፤ እውነቱን ለመናገር ቃሉ የወጣው ከልቤ ነው… አገሬን ከልቤ እወዳታለሁ እናም በተሻለ ሁኔታ የምንኖርባት አገር እንድትሆን እፈልጋለሁ፡፡ መፈንቅለ መንግሥት ወይም አብዮት የማቀጣጠል ዓላማ የለኝም… እራሴን እንደፖለቲካዊ መሪም አልቆጥርም… ዋሊያዎችን እና ሉሲዎችን የሚደግፍ፣ ካፌ ደጃፍ ላይ ቁጭ ብሎ ተቆራጭ እየበላ፣ ማኪያቶ እየጠጣ ጋዜጣ የሚያነብ ተራ ዜጋ ነኝ፡፡… የሚከፋኝ ብሔራዊ ቡድናችን በሰው አገር ሲሸነፍ ነው፡፡ … ቁምነገሩ በኢትዮጵያዊነቴ መኩራት እፈልጋለሁ፡፡… ማንም ሰው የዜግነት ክብሩን ተገፍፎ እንዲጨቆን አልፈልግም፡፡ ይኸው ነው ምኞቴ፡፡
—-
[1] – ሽብሬ ደሳለኝ፤ ምርጫ 97ን ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ የመንግሥት ጥይት ሰለባ የሆነች ወጣት ተማሪ፤ [1] – ዩሱፍ አብደላ፤ በተመሳሳይ ወቅት የተገደለ የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ተማሪ፤
[3] – እስክንድር ነጋ፤ በሽብርተኝነት ተከሶ የተፈረደበት ጋዜጠኛ፤
[4] – ርዕዮ ዓለሙ፤ መረጃ ለሽብርተኞች አቀብለሻል በሚል የተፈረደባት ጋዜጠኛ፤
[5] – አሕመዲን ጀበል፤ በሙስሊሞች የመጅሊስ ይቀየር ጉዳይ የታሰረ፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ፤
[6] – አንዱአለም አራጌ፤ ሽብር አሲረሃል በሚል የተፈረደበት የአንድነት ፓርቲ አባል፤
[7] – በቀለ ገርባ፤ ከኦነግ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል የተፈረደበት የኦፌዴን ም/ሊቀመንበር፤
[8] – ኦልባና ሌሊሳ፤ ከኦነግ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል 8 ዓመት የተፈረደበት የኦብኮ አባል፤
[9] – መስፍን ነጋሽ፤ በሽብርተኝነት አዋጅ/ክስ ምክንያት ከተሰደዱ የቀድሞዋ አዲስ ነገር ጋዜጠኞች አንዱ፤
[10] – አርጋው አሽኔ፤ የመረጃ ምንጩን እንዲሰጥ በመንግሥት ኃይሎች በግዴታ በመጠየቁ የተሰደደ ጋዜጠኛ፤

click here for pdfከጥቂት ቀናት በፊት ታዋቂው ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ› በሚል ርእስ አንድ አነጋጋሪ፣ አከራካሪና …

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለዉ “ከሁሉም ግን ፍቅር
ይበልጣል።”

(READ THIS ARTICLE IN PDF)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በውስጧ ብቻ ሳይሆን ከ

ርዕዮት ዓለሙ ከዚሕ ቀደም የበታች ፍርድ ቤት አስራ-አራት ዓመት እስራትና የገንዘብ መቀጮ በይኖባት ነበር።ይግማኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ግን ቅጣቱን ወደ አምስት-ዓመታት እስራት ዝቅ አድርጎታል።ርዕዮት ዓለሙ ለሰበር ሰሚዉ ችሎት አቤት ያለችዉ የአምስት ዓመቱ እስራትም የሕግ አተረጓገም ክፍተት አለበት በሚል ነበር የጋዜጣ …

የርዕዮት ዓለሙ ክስና የጠበቃዋ ተቃዉሞ Read more »

እንዲህ ያለ ዘመን ፣ዘመነ ጋንድያ፤ ሰው እንዴት ይሆናል፣ ከርሞ እንዳ ጥጃ፤ በሃገራችን ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ይገለፃል። ይህንንም ለማስቆም በትምህርቱ ዓመት መጀመሪያ ላይ የተመዘገቡትን ተማሪዎች ቁጥር መምህራን ተረክበው በዓመቱ መጨረሻ ማስረከብ እንዳለባቸው ለመፍትሔነት ቀርቧል። መምህራንም የደረጃ እድገት፣ የደመወዝ ጭማሪ ለማግኘት የተረከቧቸውን ተማሪዎች ቁጥር ሳይቀነሱ ማስረከብ እንደሆነ ተገልጿል። ይህን ዓይነት ቁጥጥር በሰሜን ኮሪያ ‘labor […]

click here for pdf ይህንን ደብዳቤ ላንቺ የምጽፈው የገናን በዓል ከልቤ የምወደው በዓል ስለሆነ ነው፡፡ የምወደው ደግሞ የገና ዛፍ ተተክሎ፣ በጥጥ ተውጦ፣ በከ…

በጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ላይ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ማፅናቱ ያሣዘናቸው መሆኑን ዓለምአቀፉ የሴቶ

በኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስለተመሰረቱት ሶስት የስራ ዘርፎች እንዲያራሩልን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፓብሊሲቲ ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ…

የሰው ልጅ ላይ ሊፍጸም የማይገባው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የመን ውስጥ ባሉ የተደራጁ አፋኞች ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ነው፡፡ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን በዓልን በገመድ ታንቀው ሲደበደቡ ከነበሩ እና ከሞት ተርፈው ሰነዓ ከገቡ ልጆች ጋር አሳለፍኩ፡፡ ሰውነታቸው ላይ በድብደባ ያረፈውን ቁስል እያየን አንገታቸው ላይ ገመዱ የከረከራቸው ምልክት ሰቅጥጦን ከሞት እንዴት እንደተረፉ እያወጉን በእንባ ታጅበን አሳለፍን፡፡ በዓልን ለማክበር ሁሌም […]

የሰው ልጅ ላይ ሊፍጸም የማይገባው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የመን ውስጥ ባሉ የተደራጁ አፋኞች ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ነው፡፡ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን በዓልን በገመድ ታንቀው ሲደበደቡ ከነበሩ እና ከሞት ተርፈው ሰነዓ ከገቡ ልጆች ጋር አሳለፍኩ፡፡ ሰውነታቸው ላይ በድብደባ ያረፈውን ቁስል እያየን አንገታቸው ላይ ገመዱ የከረከራቸው ምልክት ሰቅጥጦን ከሞት እንዴት እንደተረፉ እያወጉን በእንባ ታጅበን አሳለፍን፡፡ በዓልን ለማክበር ሁሌም […]

ከጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት በኋላ ባለፈዉ መስከረም ወር አጋማሽ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ስልጣን ሲይዙ ፤ የ

በዚህ ጦማር ላይ ከጻፍኩ ሰነበትኩ:: ነገር ግን ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት የጠፋሁት መጻፍ እርም ብዬ ሳይሆን ዞን ዘጠኝ ላይ መጻፍ በመጀመሬ ነው:: ታዲያ ምና

በማሕሌት ፋንታሁንመቼም ተቃዋሚ ስል የትኛው ዓይነቱን ተቃውሞ ለማለት እንደፈለኩ ሳይገባችሁ የቀረ አይመስለኝም፡፡ በሃገራችን በአሁኑ ሰዓት የኢሕአዴ…

ሓጂ ዓብደላ ሓሰን በመቀሌ ከተማ የህንጻ መሳሪያዎች ነጋዴ ናቸው፡፡
እኚህ ግለሰብ ምንም ጧሪ ቤተሰብ ለሌላቸው 12 የመቀሌ ነዋሪ እናቶች ለያንዳንዳቸው መኖ

ጋዜጠኛ ጳዉሎስ ኞኞ በህይወት ዘመኑ ለአንባብያን ያበረከታቸዉ ሥራዎች ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ተበረከተ።

በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በኢትዮጵያ ያሉትን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለይ በትምህርትና ምርምር ለማገዝ የሚያስችል …

click here for pdf ቀሲስ ስንታየሁ አባተ በግብፅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወኪል  ይኽን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሣኝ ነገር በቅርቡ ቤተ ክር…

ነዋሪዎቹ ለዶቼቬለ እንዳሉት ህግን ባልተከለ ሁኔታ ቤታቸው በአፍራሽ ግብረ ኃይል መፍረሱን ለተለያዩ አካላት አቤቱታ አቅርበዋል ። አቤቱታ ካቀረበላቸው መ…

ከትናንት ከሰአት በኋላ አንስቶ እስከ ዛሬ ጠዋት በቀጠለው ግጭት ተማሪዎች እንደቆሰሉና በተማሪዎች መኝታ ክፍሎች ላይም ጉዳት መድረሱን የአይን ምስክሮች

click here for pdf ቤተ ክርስቲያን ይህንን ሰሞን ከዕርቅና ከፓትርያርክ ምርጫ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ወገኖችን የሐሳብ ፍጭት እያስተናገድች ትገኛለች፡፡ አ…

በመሐመድ ካሊድበአንድ የግል ጋዜጣ የዘንድውን አወዛጋቢ የመጅሊስ ምርጫ አስመልክቶ የተመረጡትን ሰዎች ፕሮፋይል እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ከጎኔ የነበረ…

click here for pdf ሰሞኑን በኒውዮርክ በበጎ ፈቃድ በተሠማሩ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ላይ እሩምታ የከፈተው ተኳሽ ይህንን ያደረገበትን ምክንያት ‹መግደል ደ

በበፍቃዱ ኃይሉሃይማኖት ከጊዜ ወደጊዜ ፖለቲካዊ አቅሙን እያጣ የሚሄድ እና በገለልተኛ አስተሳሰብ የሚተካ እንደሆነ ፖለቲከኞች ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም …

አቡነ ጳውሎስ በህይወት ሳሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተጀመረው የእርቀ ሰላም ውይይት ቢቀጥልም ምን ደረጃ ላይ እን

በዋሽንግተን ዲሲና አባባቢዋ ያሉ የተወሰኑ ትውልደ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ዕሁድ ታኅሣስ 21 / 2005 ምሽት ላይ ሻማ የማብራት ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል፡፡

በበፍቃዱ ኃይሉያጣናቸው ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ግን ቀስ በቀስ ስላጣናቸው አጠፋፋቸው እየቆየ ብቻ ነው የሚገባን፡፡ ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ኢሕአዴግ የመሪነቱን

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የኢኮኖሚውና የንግዱ እንቅስቃሴ ቀዝቀዝ እያለ ነው፡፡ ልዩ ጥናትና ምርምርም አያስፈልገውም፤ በግልጽ የሚታይ ነውና፡፡

•    አዲሱ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ነገ ርክክብ ይፈጽማሉ
በዳዊት ታዬ
በአገሪቱ ከሚገኙ የግል ባንኮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ንብ ኢንተርናሽናል ባ

ተሰናባቹ የንብ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አመርጋ ካሳ
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከአርባ ዓመታት በላይ በመቆየት ከሚታወቁ የባንክ ባለሙያዎች መካ

በውድነህ ዘነበ
የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ትላልቅ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ለመመርመር የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት፣ ከብሔራዊ ደኅንነት ኤጀንሲ ጋር…

ለፖለቲካ ተፅዕኖ የተጋለጡ ግለሰቦች ሀብት ምንጭ እንዲመረመር ያስገድዳል
በዮሐንስ አንበርብር
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ሕጋዊ

በዮናስ አብይ
በደቡብ ክልል የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ረጅም ጊዜ ያሳለፉትና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) መሥራቾች አንዱ የ…