ሕገወጥ ገንዘብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ የሚከለክል ጥብቅ ሕግ ሊወጣ ነው
ለፖለቲካ ተፅዕኖ የተጋለጡ ግለሰቦች ሀብት ምንጭ እንዲመረመር ያስገድዳል
በዮሐንስ አንበርብር
በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን (መኒ ላውንድሪንግ) እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚል ስያሜ የተሰጠው ረቂቅ አዋጅ በዚህ ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡