ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሾሙ

በዮናስ አብይ

በደቡብ ክልል የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ረጅም ጊዜ ያሳለፉትና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) መሥራቾች አንዱ የሆኑት አቶ ደበበ አበራ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡