Tag: ethiopian news in amharic
የሰሞኑ የበዓል ገበያ ቅኝት – VOA
ያዳምጡ → listen
ዳን አድማሱ በ #EBC በቀጥታ በተላለፈው የአዲስ አመት ዋዜማ ዝግጂት ላይ በመገኘት የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ምልክት እያስየ ቀስቃሽ ዘፈኖቹን ብቻ በመዝፈን ተጫወተ
ዳን_አድማሱ በ #EBC በቀጥታ በተላለፈው የአዲስ አመት ዋዜማ ዝግጂት ላይ በመገኘት የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ምልክትን በማሳየት እና ወኔ ቀስቃሽ ዘፈኖቹን ብቻ በመዝፈን በራሱ በወያሌ ሚዲያ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብን ተቃውሞ አስተጋባ!!! ብዛት ያላቸው አርቲስቶች ሰው እየተገደለ […]
ባህር ዳር እሁድንና ዘመን መለወጫን በለቅሶ እያከበረች ነው
ባህር ዳር እሁድንና ዘመን መለወጫን በለቅሶ እያከበረች ነው። (#ማንደፍሮ_አስረስ ለ35 ቀናት የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ሊተርፍ አልቻለም) ባህር ዳር የአማራ ተጋድሎ በፍፁም ሰላም ተጀምሮ እስካሁንም ጭፍጨፋ የቀጠለባት ከተማ ናት። ለቁጥር አዳጋች ወጣቶችና ህፃናት ተሰውተዋል። ዛሬም በአጋዚ […]
ሙስናውና የሕዝብ አመፁ በኤኮኖሚው ላይ እያደረሰ ያለው ጣጣና መኮታኮት [ሰይድ ሃሰን]
ሰይድ ሃሰን (መሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ) መስከረም 1፣ 2009 በሲንሲናቲና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጳይዊያን የቀረብ አጭር የንግግር ንጥረ ሀሳብ (ተቀርፎ የወጣ) የንግግሬ ንጥረ ሀሳቦች በ4 ይከፈላሉ፡ በኢትዮጵያ የተከሰተው ሙስና ምን ይመስላል? እንደትስ ማስወገድ ይቻላል? ሙስናው በኤኮኖሚው ላይ […]
ሁላችንም ነፃ እስክንወጣ እንቁጣጣሽን ከአእምሯችን እናውጣ!! ሀዘን ላይ ነን!!!
።።።።የሰውየው ትዝብት በዘመነ 2008።።።።። ፩ኛ/ አሸባሪ ህግ እንጂ አሸባሪ ሰው የለም። ፪ኛ/ የስኳር በሽታ እንጂ የስኳር ምርት የለም። ፫ኛ/ ስጋት እንጂ ስጋ የለም። ፭ኛ/ ወጪ እነጂ ትርፍ የለም። ፮ኛ/ ማዕረግ እንጂ እውቀት የለም። ፯ኛ/ እስር […]
በደብረዘይት የሚገኘውና ለውጭ ሀገራት የስጋ ውጤቶችን በማቅረብ ላይ ያለው ግዙፍ የቄራ
በደብረዘይት የሚገኘውና ለውጭ ሀገራት የስጋ ውጤቶችን በማቅረብ ላይ ያለው ግዙፍ የቄራ
ይድረስ ለስዩም መስፍን:- የባድመው መሬት የት ደረሰ?
“ትግሬ አይሁድ ፣ አማራ እና ኦሮሞ ናዚ-ሒትለር” ስዩም መስፍን ያው እንደተለመደው ህወሓት እና ትግራይ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ገጽታ እንደሆኑ ነግሮናል። ስለዚህ ህወሓትን ተቃወምክ ማለት ትግሬን ተቃወምክ ማለት ነው፣ ህወሓት ይውደም ካልክ ትግሬ ላይ “ናዚ” ሆንክበት […]
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለደረሰው የህይወት መጥፋት መኢአድ መንግስትን ተጠያቂ አደረገ

የእርቅ መንግስት እንዲመሰረት ፓርቲው ጠይቋል
ባለፈው ሳምንት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ለደረሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት መንግስትን ተጠያቂ ያደረገው የመላው ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፤ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል፡፡
ፓርቲው ሰሞኑን በፅ/ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤መንግስት በአደጋው 23 ታራሚዎች መሞታቸውን ቢናገርም ቁጥሩ ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለኝ ብሏል፡፡
መንግስት ለታራሚዎች ህገ መንግስታዊ ከለላ በመስጠት ደህንነታቸውን መጠበቅ ሲገባው፤ ይህ ሳይፈፀም መሞታቸውም ሆነ ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ለታሳሪ ቤተሰቦች ግልፅና የማያሻማ ፈጣን መልስ በመስጠት ፈንታ በቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጭንቀትና አሳዛኝ መጉላላት እንዲደርስ መደረጉን በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል መኢአድ፡፡ በጉዳቱ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት ማዘኑንም ፓርቲው አስታውቋል፡፡
ፓርቲው በመግለጫው፤ በማረሚያ ቤቱ የደረሰውን ጉዳት ጨምሮ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የደረሡ ጉዳቶች በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ፣ ለጠፋው ህይወት መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅና የደም ካሣና የዜጎች ማቋቋሚያ ካሣ እንዲከፍል ጠይቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ ነሀሴ 24 የሠጡት መግለጫ ‹‹ጦርነት ከማወጅ የማይተናነስ አሳዛኝም አስደንጋጭም ተግባር ነው›› ያለው ፓርቲው፤ በአስቸኳይ ትዕዛዙ እንዲሠረዝ አሳስቧል፡፡ ፓርቲው ከግጭቶችና ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ የታሠሩ እንዲፈቱና መንግስት ከተለያዩ ፓርቲዎች ጋር ውይይት በማካሄድ የዕርቅ መንግስት እንዲመሰረት ጠይቋል፡፡
አንጋፋ የኢህአዴግ አመራሮች ሠሞኑን በኢቢሲ እየሰጡ ያሉትን ማብራሪያ፣ አዲስ የመፍትሄ ሃሳብ ያፈለቀና ችግሩን አግባቡ የተረዳ አይደለም ሲል ፓርቲው አጣጥሎታል፡፡
የቂሊንጦ ማረምያ ቤት ቃጠሎን ተከትሎ በህይወት ያሉ ታራሚዎች ወደ ዝዋይ፣ ሸዋ ሮቢትና አዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች መዘዋወራቸውን ታውቋል፡፡
“በኦሮሚያ የተጠራው የንግድ አድማ ተሳክቷል” – ኦፌኮ – “አድማው በህብረተሰቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከሽፏል” – መንግሥት
ከጳጉሜ 1 እስከ መስከረም 2 በኦሮሚያ በማህበራዊ የንግድ አድማ መጠራቱን ተከትሎ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ተግባራዊ መደረጉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያስታወቀ ሲሆን መንግስት በበኩሉ፤ የአድማ ጥሪው በህብረተሰቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ከሽፏል ብሏል፡፡
የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ለአዲስ አድማስ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፤ “በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች የንግድም ሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም፤ ሁሉም ነገር እንደታገደ ነው” ብለዋል፡፡ ሆቴል ቤቶች፣ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮችና የገበያ ስፍራዎች ዝግ ሆነው መሰንበታቸውን ኦፌኮ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በነቀምትና ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ ባለፈው ሰኞና ማክሰኞ 4 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው አቶ ሙላቱ ተናግረዋል፡፡
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሠኢድ ስለጉዳዩ ከአዲስ አድማስ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠሩት ችግሮች ከህገ መንግስቱ ጋር የማይጣጣሙ እንደሆኑ ጠቁመው ሁከቱ በዜጎች ህይወትና ንብረት ላይ ጥፋት ማስከተሉን አስታውቀዋል፡፡
“ህዝቡ በቅንነት የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከህዝቡ ከራሱ ጋር ተመካክሮ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነቱን መንግስት በመግለጫዎቹ አሳይቷል” ያሉት አቶ መሃመድ፤ ከዚህ በመነሳት የህብረተሰቡን አጀንዳ ቀምተው ለራሳቸው አላማ ለመጠቀም የሚሞክሩ አውዳሚ ኃይሎች እንዳሉ ህዝቡ የተረዳበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
“ህዝብ ከመንግስት ጋር እየተግባባ ችግሮችን ለመፍታት እየጣረ ነው” ያሉት አቶ መሃመድ፤ “በአማራም ሆነ ኦሮሚያ የተረጋጋ ሁኔታ ተፈጥሮ ህብረተሰቡ ቀድሞ ወደነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብለዋል፡፡
ሱቆች እንዲዘጉ፣ ከበአል ጋር ተያይዞ አርሶ አደሩ ምርቱን ባለማውጣት የንግድ አድማ እንዲደረግ መልዕክት የተላለፈ ቢሆንም ጥሪው በተጨባጭ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ሳያገኝ ከሽፏል ብለዋል፤ አቶ መሃመድ፡፡
በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የአድማ ሙከራ ቢኖርም ህብረተሰቡ ወደ ተጨባጭ ሰላማዊ ህይወቱ ተመልሶ በበአል ስሜት ውስጥ ሆኖ እየተገበያየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኦሮሚያን ከተሞች አቋርጠው ወደተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ጉዞ ያደረጉ የአይን እማኞች፤ በአብዛኞቹ ከተሞች የንግድ ቤቶች ተዘግተውና ሆቴል ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነው መመልከታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ብርቱዋ አትሌት አልማዝ አያና
ዘንድሮ በተለያዩ ውድድሮች ስኬታማ ውጤቶችን ያስመዘገበችው የ5000 እና 10,000 ሜትር ሩጫ ብርቱ ተፎካካሪዋ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ከሪዮ ኦሎምፒክ ድሏም በኋላ ተጨማሪ ድል አስመዝግባለች።
ምህረቱ -ምህረት የሚሆነው ሁሉም የኅሊና አስረኞች ሲፈቱ ብቻ ነው [ግርማ በቀለ]
እንኳን ምህረት ለመባል ምህረት ለማድረግ ለሚከወን ጥናት ናሙና የማይበቁ ቀድሞውኑ ወንጀል ያልፈጸሙና ሊታሰሩ የማገይባቸውን ‹እስረኞች›ን በምህረት ስም በመፍታት ፕሮፖጋንዳ መስራት ፣ በ‹እሳት› ያለቁ ወገኖቻችንን ሃዘን በደስታ መለወጥ አይቻልም፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ‹ምህረት ተደረገ የምንለው› ሁሉም በነጻ […]
እንኳን ደህና መጣችሁ ጀግኖቻችን! [ድምጻችን ይሰማ]
እንኳን ወደ ቤታችሁ ተመለሳችሁ ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን! እንኳን ለነጻነታችሁ በቃችሁ ውድ ኡስታዞቻችን፣ ዳዒዎቻችን፣ አራማጆቻችን፣ ጋዜጠኞቻችን!!! ለዲናችሁ ፍቅር የከፈላችሁትን መስዋእትነት ሁሉ አላህ ይቀበላችሁ! ቅዳሜ ጳጉሜ 5/2008 ውድ ጀግኖቻችን….! እንኳን ከቤተሰባችሁ፣ ዘመዶቻችሁና ከህዝባችሁ ለመገናኘት በቃችሁ! አስከፊ […]
አዝነናል ተከፍተናል – ቁጥራቸው ያልታወቁ በጥርጣሬ የተያዙ የፓለቲካ እስረኞች ሆነ ተብሎ በተቀነባበረ ግድያ በእሳት ተቃጥለው እና በጥይት ተደብድበው ተገደሉ
ቅዳሜ ነሐሴ 28, 2008፣ ማክሰኞ ጳግሜ 1, 2008 “የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ” ደጋፊ እና ጧሪ ወንድ ልጇ በግፍ የተገደለባት ኢትዮጵያዊ እናት! በእውነት ልባችን እጅግ ቆሰለ! እጅግ ተስፋ ሚያስቆርጥ ጭካኔን በዘመናችን አየን! […]
የኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ ሰልፍ በበርሊን – DW
ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተካሄደ ያለዉ ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እስርና እንግልት ይቁም፤ የመንግስት የፀጥታ ኃይላት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚወስዱትን የኃይል እርምጃ ያቁሙ፤ የታሰሩ ፖለቲከኞች የሐይማኖት መሪዎችና ጋዜጠኞች ይፈቱ፤ የዘር መድሎ ይቁም ሲሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን ላይ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ።
የኢትዮጵያዉያን የተቃዉሞ ሰልፍ በለንደን – DW
ብሪታንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለንደን በሚገኘዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት ተሰልፈዉ የኢትዮጵያ መንግሥት እየፈፀመ ያለዉ ግፍ ይብቃ ሲሉ የተቃዉሞ ሰልፍ ማድረጋቸዉ ተመልክቶአል ።
ትግራይ ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ የአማራ ተወላጆች እንኳን ትግራይ ሄደን እዚሁ ቤተሰቦቻችን ጋር ተቀምጠንም ለደህንነታችን በከፍተኛ ሁኔታ እየሰጋን ነው ብለዋል
ዛሬ ከ 800 በላይ የአማራ ተወላጅ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ተመድበው በሚማሩባቸው ትግራይ ውስጥ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች አንሄድም በማለት ጎንደር ላይ ተሰብስበው ነበር። የትግሬ ተማሪዎች በመላው የአማራ ክልል ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መልቀቂያ እየወሰዱ በትግራይ ክልል ትምህርት […]
የሆሳዕና እስረኞች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ገለጹ
በኢትዮጵያ ደቡብ ህዝቦች ክልል ሆሳዕና በሚገኝ እስር ቤት ካለፈው ዕሁድ ጀምሮ የመንግስት ሓይሎች በእስረኞች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ከእስረኞች አንዱ ገለጹ።
EthiopiaProtests: ‘የበሰለው ፍሬ’
ሐምሌ 2006 ከማዕከላዊ ወደ ቂሊንጦ ስዛወር፣ ዞን ሁለት ነበር የተመደብኩት። በወቅቱ በሽብር የተከሰሱ ብዙ ጎንደሬዎች ነበሩ። አልጋው ሥር “ደቦቃ” በማስተኛት ያስተናገደኝም ቢራራ የተባለ ጎንደሬ ነበር። ከዚያ በፊት ከሥሙ በስተቀር የማላውቀውን ፋሲል ደሞዝን አንድ ዘፈን ያስተዋወቀኝ እሱ ነው። ዘፈኑን እስከዛሬ ባልሰማውም ሁለቱን ስንኞች ግን በቃሌ ይዣቸዋለሁ። “አረሱትን አልሰማኸውም?” አለኝ ድጋሚ ‘አልሰማሁትም’ አልኩት ባለማወቄ ሲገረም አይቼ እያፈርኩ፤ ስንኞቹን ነገረኝ።
“አረሱት ይሉኛል የመተማን መሬት፣
ያውም የኛን ዕጣ
እነሱ ምን ያርጉ ከኛ ሰው ሲታጣ።”
ሰሞኑን 17 ያህል አርቲስቶች ለአዲስ ዓመት ዋዜማ አቅደውት የነበረውን የሙዚቃ ድግስ በሐዘናችን ምክንያት መሰረዛቸውን ሰማሁ። አርቲስቶቻችን ሰው እየወጣቸው ነው ማለት ነው የሚል ስሜት ተሰማኝ። እኛው ያከበርናቸው አርቲስቶች የሕዝባችንን ሐዘን ማክበር ከጀመሩ ትግላችንንም የሚቀላቀሉበት ግዜ ሩቅ አይሆንም፣ እኛም ‘አርቲስት’ የሚለውን ቃል ስድብ ከማድረግ እንቆጠባለን እያልኩ ሳስብ ሳልሰማቸው ያመለጡኝ ብዙ የትግል ዘፈኖች እንዳሉ ተረዳሁ።
የኦሮምኛ ዘፋኞች ዘፈንን የትግል መሣሪያ ማድረግ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። ሁሉም ዕኩል መደመጥ አልቻሉም እንጂ ባለፈው አንድ ዓመት በአማካይ በቀን አንድ የትግል ዘፈን እየለቀቁ ነበር። ከሁሉም ግን በጣም ተወዳጅ የሆነውና ቋንቋውን የማታውቁትን ሳይቀር የሚወዘውዘው የሀጫሉ ‘ማለን ጅራ’ ነበር፤ ስለዚህ ዘፈንም መጀመሪያ የሰማሁት እዚያው ቂሊንጦ በመጣ ወሬ ነው።
ኪነ ጥበብ ትግሉን ሲቀላቀል የትግሉን መብሰል የሚያሳይ ምልክት አድርጌ ነው የማየው። በአዲስ አበባ መንግሥትን በገደምዳሜ የሚወርፉ ትያትሮች ከሌሎቹ የበለጠ ብዙ ተመልካች አላቸው፣ የመግቢያ ዋጋቸውም ውድ ነው። ምክንያቱም የሕዝቡን ዝምታ ይናገራሉና። አሁንም፣ አርቲስቶቻችን የትግል ዘፈኖችን ሲዘፍኑ በሕዝብ ልብ ውስጥ ያላቸው ዋጋ ይጨምራል።
ስለፋሲል ደሞዝ እነዚያ ስንኞች ሳወራ ወንድሜ “‹እንቆቅልሽ› የሚለውን አታውቀውም?” አለኝ። አላውቀውም ነበር። ይገርማል ፋሲልን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዘፈኑ ሰማሁት፣ አየሁት። ክሊፑ ላይ፣ ሴቲቱ እንቆቅልሽ ትጠይቀውና መልሱን ባለማወቁ “አገር ስጠኝ” ትለዋለች፣ እሱ ግን እንዲህ ይላታል።
“እንቆቅልሽ፣
በሰም ለበስ ቅኔ፣
አሁን ገና፣ መጣሽብኝ ባይኔ።”
ፋሲል “በይ ደስም አላልሽኝ ጨዋታ ቀይሪ” እያለ ሲያንጎራጉር የሆነ ልብን የሚኮረኩር ኃይል አለው። ወንድሜ “ይሄ ይገርምሃል እንዴ?” አለኝና የይሁኔ በላይ አዲሱን ዘፈን አስደመጠኝ። ለወትሮው፣ ይሁኔን ከፍቼ የማዳምጠው ዘፋኝ አልነበረም። ይሄንን ‘ሰከን’ የሚለውን ዘፈኑን ስሰማው ግን የማላውቀው ስሜት ልቤን አተራመሰው።
“…ሰከን በል፣
ሰከን ማለት፣
ነው ጨዋነት
ሰከን ማለት፣
ነው ጀግንነት
ወታደሩ፣ ሰከን በል
አፈሙዙን ሰከን አርገው፣
ቃታህንም እንዳትስበው፣
ባዶ እጁን ነው፣ የሚጮኸው፣
ሠላማዊ፣ ወንድምህ ነው፣
ሰከን በሉ፣ ሕዝቤን ተዉት
ድምፁን ስሙት፣ አትግደሉት…”
በማለት የመንግሥትን ሀጢያት “…ውጉዝ ከመአርዮስ” ብሎ በማውገዝ፣ ስለኅብረት ሲባል፣ “በወላጁ ጥፋት፣ አይወቀስ ልጁ” እያለ መስከንን ይመክራል።
ናቲ ማን ቀጠለ። ናቲ ደግሞ በኦሮምኛ ስልተ ምት “አሁን ተነካሁ” እያለ፣ እሽክም፣ እሽክም አስባለኝ።
“ኦሮሞን፣ ኦሮሞን ሲከፋው
አሁን ተነካሁ
አማራን፣ አማራን ሲከፋው
አሁን ተነካሁ…”
ከዚያ ደግሞ የመስፍን በቀለ ዜማ ቀጠለ። በቀረርቶ የሚጀምረው የመስፍን “ሠላም ለኢትዮጵያ” አዲስ ትውልድ መጥቷል ይላል። ወራደሩንም እንዲህ ይለዋል፦
“ወታደሩ ጓዴ፣ አንተ ያገሬ ሰው፣
ወንድምክን አትግደል፣ ብረትክን መልሰው።…”
ሌንሴ ለሜሳ ደግሞ ጆሮ በሚለሰልስ ድምፅዋ፣ “ተነቃንቋል” ትላለች፣
“ተነቃንቋል ጥርሱ ይነቀል፣
ይነቀል፣
ይነቀል ይውለቅ
የአሉላ የጆቴን ትከሉበት ወርቅ፣
ክፍተቱ እንዲሞላ ውበቱ እንዲደምቅ።…”
መክፈቻዬ ላይ የጠቀስኩትን ፋሲል ደሞዝን መዝጊያም ላድርገው። በቅርቡ በለቀቀው ዘፈኑ እንዲህ ይላል፣
“…ኧረግ ወዲያልኝ (ወዲያልኝ)
ኧረግ ወዲያልኝ (ወዲያልኝ)
በቃ ሒድልኝ (ሒድልኝ)
25 ዓመት አላገጥክብኝ።…”
ክብር ለእነዚህ አርቲስቶች ይሁን!
አሜን።
በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባሉ እርምጃዎች ሕይወት ጠፍቷል – VOA
በምዕራብ ሃረርጌ መሰላ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ሰሞኑን የፀጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባሉ እርምጃዎች ሁለት ሰው መገደሉን የወረዳው አስተዳዳሪ ገልፀዋል፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen
ሰበር ዜና! የህወሀት/አህአዴግ አገዛዝ በአማራ ክልል ሕዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት ፣ ይፋዊ የዘር ፍጅት አወጀ!
በአማራ ከልል የህወሀት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው የብአዴን ኮሚኒኬሽን ሐላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የስርጭት አድማሱ በአዲስ አበባና ዙሪያ ብቻ በተገደበው ሸገር ኤፍ.ኤፍ.ኤም ራዲዮ ቀርበው ‹‹ሕዝባዊ ንቅናቄ እያደረገ ባለው የአማራ ክልል ህዝብ ላይ የመከላካያ ሰራዊት እርምጃ እንዲወሰድ ታዟል›› ብለዋል!! ይህ የዘር ፍጅት የታወጀው በምእራብውያን አጋዥነት በቆመው የህወሀት ስርዓት መሆኑ አፅእኖት ሊሰጠው ይገባል!! በተያያዘ ዜናም ዛሬ ማምሻውን ሀይለማሪያም ደሳለኝ […]![]()
አስቸኳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን የጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በውጫሌ ዞረው ወደ ሰሜን ጎንደር እያመሩ ነው
አስቸኳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን የጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በውጫሌ ዞረው ወደ ሰሜን ጎንደር እያመሩ ነው
ከወሎ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች ግብረኃይል የተሰጠ መግለጫ !!
ከዚህ በታች ስማቸሁ ለተጠቀሱ የአማራ ከተሞች፣ የገጠር ቀበሌዎችና ገበሬ ማህበራት ነዋሪዎች በሙሉ፡- እንደሚታወቀው በጎንደር እና በጎጃም ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች ትግሉን አሁን በደረሰበት ራስን ነጻ የማውጣት ደረጃ አድርሰውት ይገኛሉ። ይሁንና አፋኙና […]
ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ ስለህዝባዊ ተቃውሞዎችና መንስኤያቸው ያብራራሉ
ስለ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና መንስኤያቸው ያብራራሉ ጭቆናን ለማጥፋት የሚደረግ ትግል ኖሮ አያውቅም ህዝብ ቋቱ ሲሞላ ነው አልችልም፤ በቃኝ ያለው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የተናገረው የሚያስደንቅ ነው በሦስት መንግስት ውስጥ አልፈዋል – ታዋቂው ምሁርና አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕ/ር መስፍን […]
መንግሥት ፈርሷል?! [የዐማራ ተጋድሎ]
በብዙ የዐማራ አካባቢዎች የመንግሥትን መዋቅር ሕዝቡ ተረክቧል፤ የጎበዝ አለቃዎች ጸጥታ የማስከበሩንና የመሪነት ሚናውን በሚገባ እየተወጡ ነው፡፡ የአርባያ በለሳና የቋሪት አንበሶች ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ በድፍን ጎጃምና በድፍን ጎንደር ሕዝብ አገዛዙን አሽቀንጥሮ ለመጣል እየታገለ ነው፡፡ በወሎና በሸዋ […]
ወረታ ከተማ በአሁኑ ሰአት ምድር ቀውጢ ሆናለች
ነሐሴ 22/2008 ዓም ከባህርዳር አካባቢ ተነስቶ በሀሙሲት አድርጎ በደብረታቦር አድርጎ ወደ መቀሌ በመጓዝ ላይ የነበረ ወታደሮችን የጫነ ኦራል ጉመራ ወንዝ ላይ በጀግኖቹ የጎንደር ወጣቶች ጉመራ ወንዝ ላይ ድልድዩን በመዘርጋታቸው መሻገር ባለመቻሉ መሄጃ ያጣው ሠራዊት ወደ ጎንደር ለመመለስ ተገዷል ከጉማራ ሸሽቶ ወደ ጎንደር ሲሮጥ ሌሎቹ ጀግኖች ርብ ወንዝን በመዘርጋት መውጫ ቀዳዳ አሳጥተው እየተንከራተተ እንደሚገኝ ታውቋል. ወረታ […]![]()
#Ethiopia: “What is the Solution?”
በአሁኑ ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ በአጋዚ ወታደር መወረሯ ታወቀ
በአሁኑ ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ በአጋዚ ወታደር መወረሯን መረጃ ደርሶናል፡፡ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ትገኛለች፡፡ ማርቆስን ጥቁር ደመና ተጭኗታል፡፡ ህዝቡ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ለአጋዚ ወታደር የምግብና የመጠጥ አቅርቦት የሚሰጥ ሆቴል ካለ ህዝቡ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው በተደረገው ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ የትልቅ ሆቴል ህዝባዊ ወገንተኝነቱን ወደ ጎን በማለት የሰረታው ስህተት ዋጋ እያስከፈለው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋናው […]![]()
የጎጃም ተቃዉሞ ገንፍሏል
በጎጃም የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች እየታዩ ነው። ከደጀን ተነስቶ ወደ ባህር ዳር የሚወስደዉን መንገድ እናበምርጦ ለማሪያም አድርጎ ከደሴ የሚመጣው መንገድ በምታገናኘዋ በግንደ ወይን ከፍተኛ ተቃዉሞ ተነስቷል። ከደጀን በደብረ ማርቆስ አድርጎ ወደ ባህር ዳር […]
ኮ/ል ደመቀ ዘውዴን ለመውሰድ ህወሀት ያደረገው ዘመቻ ከሸፈ
የሰሜን ጎንደር ዞን አድማ በታኝ ም/አዛዥ ኢንስፐክተር መልካሙ የሺዋስ ረዕቡ ዕለት ከስራ ተሰናበቱ። በአንገረብ ወህኒ ቤት ኮ/ል ደመቀን ለመውሰድ የተከፈተውን ዘመቻ ያከሸፈው የሰሜን ጎንደር ልዩ ሃይል አካል የሆነው የአድማ በታኝ ጦር ም/አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ ”ህዝባችን ላይ አንተኩስም” በማለት የሚመሩትን ጦር አቋም እንዲይዝ አድርገዋል። በዚህም ከስራ ተባረዋል። ጦሩ ግን ከጎናቸው ነው። Filed under: NEWS![]()
Understanding Ethiopia’s Crisis through Rio Olympic
ስለነገው የአዲስአበባ ሰልፍ ሳስብ የቻይና ባምቡ ወይም ቀርከሃ ዛፍ ታወሰኝ (ያሬድ ጥበቡ)
ያሬድ ጥበቡ የቀርከሃ ዛፍ ፍሬ ከተተከለ በኋላ ለአራት አመታት ከትንሽ እምቡጥ ቅጠል በቀር ምንም እድገት አያሳይም ። ተካዩ እነዚያን ሁሉ አመታት በተስፋ መጠባበቅ አለበት ። አንድ ቀን ሳይታሰብ ያቺ እምቡጥ ወደሰማይ መመዘዝ ትጀምራለች ። እነዚያን ከአፈር በላይ ያላደገችባቸውን አራት አመታት …
ስለነገው የአዲስአበባ ሰልፍ ሳስብ የቻይና ባምቡ ወይም ቀርከሃ ዛፍ ታወሰኝ (ያሬድ ጥበቡ) Read more »
የዲሞክራሲ ቀለሞች – ከሽግግር እስከ ችግግር! [ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ – አሜሪካ)]
በሽግግሩ መንግስት ወቅት የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ፤ ከፓርላማው ወረድ ብሎ፤ ከቤተ መንግስቱ በአጓዳኝ፤ ወይም ወደ ግቢ ገብርኤል መሄጃ ላይ ይገኝ ነበር። ያን ሰሞን ከበአላት ወይም ቅዳሜና…
እለታዊ መረጃ.. ከአዲስ አበባ ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
በአዲስ አበባ ከፍተኛ ውጥረት አለ። በአንዋር መስጊድ አካባቢ ከፍተኛ ፍተሻ በመካሄድ ላይ ነው። ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ እንዲሁም በየመስሪያ ቤቱ በእሁዱ ሰልፍ ላይ እንዳትገኙ እያሉ…
መቀሌ ውስጥ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ የሆኑ 650 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በትግራይ ገዥ እየሰለጠኑ ነው
መቀሌ ውስጥ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ የሆኑ 650 የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በትግራይ ገዥ እየሰለጠኑ መሆኑ ስናውቅ የሌላው ዞን ተመራቂ ሣይጠራ ወልቃይቴ ብቻ መሆኑ አላማው ምን እንደሆነ ብናውቅም…
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሰራተኞች ጎንደርን እንዲያወግዙ ለማስገደድ የተጠራው ስብሰባ ተካሄደ [ቱባ]
በውጪ ሀገር የሚገኙ የቀድሞ የመስሪያ ቤቱን ባልደረቦች የግንቦት ሰባት አባላት ሲሉም ፈርጀዋል፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሰራተኞች የህወኃት የበላይነት ይቁም በሚል የተነሳውን የጎንደርን አልፎም…
በመጭው እሁድ ነሐሴ 15 በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ
በመጭው እሁድ ነሐሴ 15 በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ለሚደረገው ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ “ነሐሴ 15 መስቀል አደባባይ እንገናኝ።” የሚሉ የሰልፍ ጥሪ ቀይ ካርዶች በየቦታው እየተሰራጩ…
የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በመጪው ቅዳሜ ነጭ ልብስ በመልበስ በህወሃት/ኢህአዴግ የተገደሉትን ሰዎች እንደሚያስቡ አስታወቁ
ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008) በተለያዩ የተቃውሞ ስልቶች ውስጥ የቆዩ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ከፊታችን ቅዳሜ ነሃሴ 14, 2008 ዓም ጀምሮ “ነጭ በመልበስ” እና በመንግስት የጸጥታ…
“ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ! የሽግግር መንግስት ይቋቋም” ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ
8 ነሓሴ 2008 በአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት…
ለመሆኑ አማራ ማነው? ከታሪክ መዝገብ በኀይሌ ላሬቦ
ኀይሌ ላሬቦ ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግሥት ዐማራ በተባለው ኅብረተ-ሰብ ላይ ብዙ ግፍና ዐመፅ እንደፈጸመና እንዳስፈጸመ በገፍ ይነገራል። በኅብረተሰቡ ላይ ተፈጸሙ ከተባሉት ድርጊቶች አብዛኞቹ…
ከ ደብረብርሃን ሸዋ አማራ ወጣት የተላከ መልክት: #ቤተ_አማራ
“ዛሬ የደብረብርሃን ባጃጅ ሾፌሮችን የከተማው ከንቲባ እና ካድሬዎች ሰብስበው የእሁዱን ሰልፉ እንዳትወጡ ከወጣችሁ ታሪፍ እንጨምራለን እያሉ ሲያስፈራሩን ዋሉ።በሌላ በኩል ደግሞ የቀበሌ ካድሬዎች ቤት ለቤት እዬዞሩ…
በአገር ስላለው ሁኔታ አጭር ዘገባ – #ግርማ_ካሳ
ሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓ.ም – በዛሬ እለት በጎንደር ኮሎኔል ደመቀ ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረበት። ሆኖም በፍርድ ቤቱ ብዙ ሺህ ስለነበረ ዳኞቹ ፈርተው፣ ዛሬ ሳያቀርቡት…
በመጪው ቅዳሜ በመላ ኦሮሚያ አካባቢዎች ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
ባለፈው ሰንበት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአስርታት ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ተቃውሞ በሰላም ወደ ቤቱ ተመለሰ። በጣም ጥሩና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በእለቱ…
አስቸኳይ መልዕክት! ይድረስ ለብአዴን አመራር (ያሬድ ጥበቡ)
የትግራይ ማህበረሰብ ውስጥ ለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ምላሽ ተደርጎ የሚታየው ብአዴን በነፍጠኞች ተይዟል፣ መሪዎች መመንጠር አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን የድርጅቱ ልሳኖች ከሰሞኑ ዘግበዋል። በመሆኑም እነ አቶ ገዱ…
የአማራ ሕዝብ ትግል፤ ብዙ እርምጃዎች ወደፊት!! (ሙሉቀን ተስፋው)
የአማራ ሕዝብ አኩሪ ታሪክ ጽፏል፡፡ የአማራ ወጣቶች የአያቶቻቸውን አርበኝነት አስመስክረዋል፡፡ ወሮበላው የወያኔ ቡድንና ተላላኪዎቹ እነደመቀ መኮንን፣ ይህ ሁሉ ሕዝብ በየአካባቢው ገንፍሎ ወጥቶ የጠየቀውን ጥያቄ፣ ከእነሱ…
በቅርብ የኢትዮጵያ ታሪክ ትግራይ እሚባል ክፍለ-ሃገር አልነበረም
ትግራይ ሳይሆን፡ ትግሬ ጠቅላይ- ግዛት የሚባለው ግን በአጼ ምንሊክ የተካለለ ነው። “ትግራይ” እሚለው ታድያ እንዴት መጣ? የየትኛው አካባቢ መጠርያነበር? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ፡ ብዙ ሰው (ወጣት የትግሬ ክፍለሃገር ተወላጅ ጭምር)የማያቀውን ሃቅ እንደሚከተለው እጠቅሳለሁኝ። ኤርትራ እሚባል እንዳልነበረ ሁሉ፡ ትግሬ ጠቅላይ ግዛት እሚባልም አልነበረም። ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው፡ በአጼ ምንሊክ ግዜ ነው በጠቅላይ ግዛትነትየተዋቀረው። ልብ በሉ፡ ትግሬ እንጂ ትግራይ አላልኩም። ትግሬ ጠቅላይ ግዛት የሚለው አጠራር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ(በአጼ ኅይለሥላሴም በደርግም ጊዜ)የነበረ አጠራር ነው። ትግራይ የሚለው አጠራር ታድያ መⶬ ነው የታወቀው? መልሱ በ1928 ወረራ አካባቢ፡በጣልያንና በእንግሊዝ የሚል ይሆናል፡ ከዛ በፊትና በሃላ ትግራይየሚለው ቃል የየትኛው አካባቢ መጠርያ ነበር? ትግራይ ማለት ብዙ ባላባቶⶭ ያልነበሩበት አካባቢ፡ ከተለያዩ አካባቢዎች(ከኤርትራ፡ ከተቀረው የትግሬ አውራጃዎⶭ) ለከብቶቻቸው ሳር ፍለጋ፡ ወይምበሽፍትነት ሄደው እዛው የቀሩ ሰዎች የሰፈሩበት፡አሁን በትግሬ ክፍለ-ሃገር ሽሬ እና አካባቢው የሚገኘው፤ በሰሜን እስከ ኤርትራ ድንበር፡ በምአራብ እስከ ተከዜወንዝ ያለው ቦታ ነው። አንዳንዴ ሰዎⶭ ዓድዋንም ይጨምራል ይላሉ። በአሁኑ አጠራር፡ ሰሜናዊ ምአራብ እየተባለ እሚጠራው አካባቢ ብⶫ ነበር ትግራይተብሎ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲጠራ የነበረው። ለምሳሌ ያክል ለመጥቀስ፡ አንድ የተንቤን ተወላጅ፡ያኔ፡ ከተንቤን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ለመሄድ ሲነሳ፡ የት ነውእምትሄድው ተብሎ ቢጠየቅ፡ መልሱ (ናብ ትግራይ ኢየ) ወደ ትግራይ ነው እምሄደው የሚል ይሆናል። ተንቤኖⶭ ትግራይ ሲሉ፡ ቀደም ብዬ የጠከስኩትንአከባቢን ነበር እሚያቁት። በዓጋሜ በኩል ቢሆንም ተመሳሳይ ነው። የዓጋሜ ነዋሪዎⶭ ትግራይ ሲሉ፡ ከዓጋሜ በስተ መእራብ ሲሄዱ የሚገኙትን፡ ቀደም ብዬየጠከስኩውⶨውን ቦታዎⶭ ማለታⶨው ነበር። ይሄ እንግዲህ ጸህፊው በሚያቀው፡ በኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ 70ⶩ ድረስ የነበረ ነው። ምሳሌ ልጥቀስ፡ የደርግእድገት በህብረት ዘመⶫ በተጀመረበት ወቅት ነው። በትግሬ ጠቅላይ ግዛት ተመድበው ሲሰሩ የነበሩ የዘማⶮⶭ ሃላፊዎⶭ፡ ከዓዲ ግራት ተነስተው፡ በላንድሮቨራቸው ፡ወደ ሽሬ በሚያመሩበት ጊዜ ብዘት እምትባል ትንሽ ከተማ ይደርሳሉ። ብዘት እንደደረሱ፡ አንድ መንገደኛ ወደ እነሱ ጠጋ ይልና፡ አፈናጥጡኝሲል ይጠይቃቸዋል። እነሱም፡ ወድየት ነው እምትሄደው ብለው ቢጠይኩት ወደ ትግራይ ሲል መለሰላቸው። ትግራይ ያለው ሽሬ አካባቢ ማለቱ ነበር። እንግዲህ የህዝቡ ስሜትና ኩራት በአውራጃ የተመሰረተ ሲሆን፡ ከፍ ሲል ደግሞ በኢትዮጽያዊነቱ የሚኮራ ነበር። አሁንም ቢሆን፡ አውራጃዊ ስሜት ትግራይከሚለው ስሜት ያይላል። በኤርትራም እንደዚያው ነው። የትግራይ እና የኤርትራ ዘመናዮⶭ ከፈረንጆⶭ የሰነቁትን የጥላⶭ ፍሬ፡ ከበረሃ ምሽጋⶨው ሆነው እየዘሩኤርትራንና ትግራይ አሚለውን ማንነት ለመፍጠር ብዙ ተጉዘዋል። በዚ አንጻር ሲታይ፡ የመሃል አገር ሰው አውራጃነትን ከተወ ዘመናት አልፈዋል። አነሰ ቢባልበጎንደር፡ጎጃም፡ወሎ እና ሽዋ ነው እሚያስበው፡ ያም ቢሆን በጣም የደበዘዘ ነው። አብዛኛው የነዚህ ጠቅላይ ግዛቶⶭ ህዝብ በኢትዮጽያዊነቱ ይቆረቆራል። ይሄከፍተኛ የእድገት ልዩነት ነው። ለዚህም ነበር፡ ወራሪዎⶭ፡ ይህንን የኢትዮጽያ ክፍልንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለይተው ሲዘምቱባⶨው የነበረውና፡ አሁንምበተወካዮⶫⶨው በኩል ያንን የሚያደርጉት። ትምክህተኛ እያሉ የሚጠሩት፡ ከነሱ ልቆ ስለሄደ ነው። እነሱ በአውራጃ በሚያስቡበት ጊዜ፡ የጠቀስኩዋⶨው የመሃልአገር ሰዎⶭ ኢትዮጽያዊነትን ያራምዱ ነበር። ትምክህቱ እንግዲህ ላቅ ብለው ማሰባⶨው ነው።በህብረተሰብ እድገት ደረጃ -ቤተሰብ፡ዘመድ፡ መንደር፡ወረዳ…ወዘተ…- እያልን በምንመዝንበት ጊዜ፡ ላቅ ብሎ እምናገኘው ኢትዮጽያዊ የመሃል አገሩ ነው። ለዛም ነው፡ በኢትዮጽያዊነቱ እማያመነታው። ጣልያን፡ ኤርትራን ሲለቅ፡ ኤርትራዊነት የሚለውን ስሜት ለመፍጠር ቢሞክርም፡ ቢዙም ሳይሳካለት ነው አገሩን ለቆ የሄደው። የኤርትራን የማንነት ስሜትመፍጠር ያልቻለው ጣልያን፡ ትግራይ የሚለውንም መፍጠር አልቻለም፡ አንዳንድ የሰሜን ባላባቶⶭን ከማማለሉ በስተቀር። ጣልያንን ተከትሎ የመጣውእንግሊዝ ግን የዋዛ አልነበረምና፡ በደንብ ነው የሰራበት። ከዓድዋ በፕሮተስታንት እምነታⶨው ምክንያት በድንጋይ ተወግረው የተባረሩት አቶ ወልደማርያም፡ ወደኤርትራ ሄዱና ከአንድ የሰራየ ሴት ወልደአብ የሚባል ልጅ ወለዱ፡ ብሁዋላ አቶ ወለደአብ ወልደማርያም የተባሉት፡ፕሮቶስታንቱ፡ የኤርትራው ብሄረተኛመሆናⶨው ነው። ያኔ ነው፡ በእንግሊዝ መንግስት የትግራይ ትግርኚ የሚለውን ሃገር የመከፋፈል ደባ፡ ከኦጋዴን ፕሮጀክቱ ጋር አዳብሎ የገፋበት። ይሄ እንግዲህበ1930ዎⶩ (በአውሮጻውያኑ 1940ዎⶩ)መሆኑ ነው። በዛን ጊዜ በኤርትራ የተወለዱ ሰዎⶭ አሁን የ80 ዓመት እድሜ ባለጸጎⶭ ናⶨው። እነዚህ ናⶨውእንግዲህ፡ ያ በልጅነታⶭው የተለከፉበት መርዝ አለቅ ብሎአⶨው ለሺዎⶭ አመታት አንድ ሆኖ የኖረውን ህዝብ በዘረኝነት ሲያተራምሱት እሚታዩት። ለነገሩ፡ክአድዋ የሚወለዱት የስብሃት ነጋ ዘመዶⶭ ትውልዳⶨው ከእንግሊዝ ይመዘዛል። 5 ትውልድም አይደርስም፡ ዋአሮ የወለደⶫⶨው ፡የአገር ጎብኚው ማንስፊልድልጆⶭ ናⶨው። ለገሰ ዜናዊ የአበባው የልጅ ልጅ ነው፡ ጎጃሜ። አበባው-ነጋድራስ ተሰማ – አስረስ- ዜናዊ:፤ ይገርማል! መለስ ዘሩ ጠፋበትና፡ ወንድም ከወንድምሲያጋድል ሴኦል ገባ። ወይ ጉድ። ዘርኡ መሃሪ
በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ሰሮቃን ለቀው በመውጣት በየጫካው መሽገዋል
ሴቶችና ህጻናት ሰሮቃ ከተማ ለቀው ወጥተዋል። ትናንት በሚሊሺያዎችና በወታደሮች መካከል የነበረው ፍጥጫ በሽማግሌዎች እንዲበርድ ቢደረገም፣ ገዢው ፓርቲ ራሱ ያስታጠቃቸው አርሶአደር ታጣቂዎች ከእንግዲህ በህወሃት አንገዛም በማለት…
ዐማራው፣ ዐማራዊ ማንነቱን አረጋግጦ፤ ጀግንነቱንና ኢትዮጵያዊነቱን በደሙ እያስከበረ ነው! (ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት)
ቅዳሜ ሐምሌ ፴ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፲፱ ዐማራው የኢትዮጵያዊነት ዋልታና ማገር፣ ወራጅና ጭምጭም፣ ስሚንቶና አሸዋ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ማንነቱን ጠንቅቀው…
ትናንት በጎንደር በተከሰተ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ
በጎንደር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉትን የወልቃይት ኮሚቴ አባላት የፍርድ ጉዳይ ለመከታተል ትናንት ፍ/ቤት አካባቢ ተሰብስበው በነበሩ ነዋሪዎችና የፀጥታ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን የፍርድ ቤት ውሎ ለመከታተል ጎንደር ፒያሣ አካባቢ በሚገኘው ፍ/ቤት በጠዋቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሰብስበው የነበረ ሲሆን ፍ/ቤቱ የተጠርጣሪዎቹን ጉዳይ ለነሐሴ 4 ቀን 2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ እንደተሰማ ግርግር መፈጠሩን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ ተቃውሞ የሚያሰሙትን ነዋሪዎች ለመበተን ሙከራ ማድረጉን የጠቆሙት ምንጮች፤ ከቆይታ በኋላ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመሳሪያ ተኩስ መሰማቱንና ተኩሱ በየአቅጣጫው እስከ አመሻሹ ድረስ መዝለቁን ተናግረዋል፡፡
የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በድንጋይ መዘጋጋታቸውንና ወጣቶች በቡድን እየሆኑ ተቃውሞ ሲያሰሙ መዋላቸውንና ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የከተማዋን ከንቲባ ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት የሞባይል ስልካቸው ዝግ በመሆኑ ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ በግጭቱ የሰዎች ህይወት ማለፉን ምንጮች ቢጠቁሙም ከፖሊስ ለማረጋገጥ አልቻልንም፡፡
ባለፈው እሁድ በከተማዋ መንግስትን የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

