ከ ደብረብርሃን ሸዋ አማራ ወጣት የተላከ መልክት: #ቤተ_አማራ
“ዛሬ የደብረብርሃን ባጃጅ ሾፌሮችን የከተማው ከንቲባ እና ካድሬዎች ሰብስበው የእሁዱን ሰልፉ እንዳትወጡ ከወጣችሁ ታሪፍ እንጨምራለን እያሉ ሲያስፈራሩን ዋሉ።በሌላ በኩል ደግሞ የቀበሌ ካድሬዎች ቤት ለቤት እዬዞሩ እሁድ ሰልፍ እንዳትወጡ እያሉ አንዳንድ ወጣቶችን ፊርማ ሲያስፈርሙ ውለዋል ። በጣም የገረመኝ ግን ካድሬዎች ለእግራቸዉ የረባ ጫማ እንኳ የላቸውም ። ”
የ #ቤተ_አማራ መልክት ለደብረብርሃን ካድሬዎች: –
#የአማራ_ተጋድሎ እናንተም የተወለዳችሁበትን አማራነት ለመጠበቅ የሚደረግ ተጋድሎ ነው እና አብራችሁ ተጋደሉ!! አማራነታችሁን እያጠፋ በድህነት ለሚያማቅቃችሁ የህወሓት ስርአት ማደግደግ ምን ትርፍ አለው? ዛሬ ህወሓት የምትወረውርላችሁን ፍርፋሪ ጥቅም ነገ አማራ ነፃነቱን ሲጎናፀፍ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይመልስላችኋል። አማራነታችሁም ይተርፋል ። ከሕዝባችሁ ጋር ቁሙ!
ሸዋ የአባቶቻችን የነገስታት አማሮች ዙፋን! የአማራነት ምሰሶን ከወደቀበት መልሶ የተከለው የታላቁ አባታችን የዩኩኑ አምላክ ምድር ፣ የጦረኛው የዘረ ያቆብ ቀዬ ፣ የክንደ ብርቱው የአምደ ፅዬን መፍለቂያ ፣ የደቦል አንበሳው የናኦድ ሙሽራ ፣ የሲሲኒዬስ ሃረግ ፣ የፋሲል ናፍቆት ፣ የስሃለ ሥላሴ ደሴት ፣ የምኒሊክ ማማ…የአማሮች ኩራት ሸዋ ለአማራነት ዝም አትልም!!
#የአማራ_ተጋድሎ በሁሉም የአማራ ምድር …
#ቤተ_አማራ
