የዘንድሮ የትንሳኤ በአል ገበያ …
በተለያዩ የአዲስ አበባ የገበያ ስፍራዎች ተዟዙረን የበዓል ገበያ ዋጋን ለመቃኘት እንደሞከርነው፤ በአብዛኛው ከዓምና ተመሳሳይ የበዓል ገበያ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡ በአቃቂ ቄራ ገበያ የበሬ ዋጋ ከ5 ሺህ እስከ 22 ሺህ ብር ድረስ ሲሆን ዓምና በተመሳሳይ በዓል የበሬ ዋጋ ከ8 ሺህ ብር እስከ 25 ሺህ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
በአቃቂ ቄራ፡- የበግ ዋጋ ከ700 ብር እስከ 3500 ብር ሲሆን በዓምና የፋሲካ ገበያም በግ ከ900ብር እስከ 3500 ብር ተሸምቷል፡፡ በአቃቂ የቁም እንስሳት ቄራ ገበያ፣ ከፍተኛው የፍየል ዋጋ 7ሺህ ብር መሆኑን ከነጋዴዎች የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡
በገበያው ቋሚ የበግና የፍየል ነጋዴ የሆነው ወጣት መስፍን ይልማ፤ በግና ፍየሎችን ከአዳማና አርሲ አካባቢ አምጥቶ እንደሚሸጥ ገልፆ፤ ዘንድሮ ገበሬው በግና ፍየል ለነጋዴው እየሸጠበት ያለው ዋጋ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በአማካይ እስከ 200 ብር ቅናሽ ማሳየቱን ተናግሯል፡፡
ገበሬው ለመጪው ክረምት የሰብል ምርት የሚያስፈልገውን ማዳበሪያ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት የትንሳኤ በዓል የከብት ገበያን እንደመልካም አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ይኸው ነጋዴ ገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ዋናው ቄራ ገበያ የሃረር ሰንጋ በሬዎች፡- ከ18 ሺህ ብር እስከ 25 ሺህ ብር እየተሸጡ ሲሆን በሰውነት አቋማቸው አጫጭር የሆኑት የጅማ ሰንጋዎች ደግሞ ከ6 ሺህ ብር እስከ 10ሺህ ብር እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በግ በቄራ አካባቢ ባሉ ገበያዎች መካከለኛው፡- ከ1300 ብር እስከ 2ሺህ ብር፣ ሙክት በግ እስከ 5 ሺህ ብር ይገኛል፡፡
የዶሮ ዋጋ ዝቅተኛው 130 ብር፣ ከፍተኛው 400 ብር ሲሆን እንቁላል በነጠላ 3 ከ50፣ ቅቤ በኪሎ፣ ከ180 ብር እስከ 240 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በአስኮ ገበያ ዶሮ ከ250 ብር እስከ 350 ብር፣ እንቁላል በነጠላ 3 ብር 50፣ ቅቤ በኪሎ ከ180 ብር እስከ 250 ብር፣ አይብ ከ65-75 ብር በኪሎ ይሸጣል፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በበኩሉ፤ 5ሺህ የሚሆኑ የእርድ እንስሳትን የሚያቀርብ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 2500 በሬዎች፣ 2300 ደግሞ በግና ፍየሎች እንደሆኑ ገልጿል፡፡ ከድርጅቱ ባገኘነው መረጃ መሰረት፤ ለበዓሉ ድርጅቱ በራሱ የመሸጫ ሱቅ የበግ ስጋ በኪሎ 130 ብር ይሸጣል፡፡
Addis Admass

Engdih Abzagnaw sew tsomun sayfeta lela tsom liyez new
Tsomun bepolis masyaz new !
Tsomu sefata hulum ya sega zer yewadadale,emsn chamero
Amareña be englizeña fidel
siTaf ende amareñanetu
ynebeb lemiyaqut slehone.
he hu hi — hie h ho
le lu li la lie l lo
red color = qey qelem
goodness = chernet
only = bcha
salt = Cew = chew
fatty meat = coma sga
shoe =camoch
smoke = cis
student = temari
breast = Tut
monday = seño = seNo
one = and
oozo = uzo
ethiopia = itiyopiya
= etiopia
tortoise = ieli = eli
mother = enat = ènat
buyer =gex
brave = jegna
start = mejemer
page = geT
poet = gTm geTami
drink = meTeT
study = Tnat
correct = right = tkkl
patience = tgst
but = gn
orange = brtukan
ethiopian bir=yeitiyopiya br
pen = b-er = eskrbito
picture = s-el
duke = luul= lu-ul
your pencil = ersas-h
= ersassh
your mattress = frashish
= frashih
miyadenagerun aswegdu:
consonant plus e = le geez
yemejemeriya fideloch
consonant plus i= li sals
3 ña biet fideloch
malet brhan new, gn
birhan weym berhan aybal
mkniyat ox = berie, gn bere aybal mkniyat consonant/tenebabi plus vowel/asnebabi e = g-ez 1ña biet fidel new.
ye Ethiopia Hizb eko tsom keyaze 25 ametu new!!!
dero yene bite be kilo 10,birr tsom yefeta neber !!
MOT LE WEYANE NIZI