አሜሪካኖች ከፍተኛውን እጣ ወስደዋል። ካናዳዎችና አውሮፓዎችም ከእጣው ተጋርተዋል፡ የእጣውን ቁጥሮች ይዘናል። ከጁላይ 29 እስከ ጁላይ 31 በአምስተርዳም በተካሄደው 8ኛው የኢትዮጵያዊያን አውሮፓውያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ እንዲወጣ ታስቦ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (በምህጻረ ቃሉ “ኢሳት”) መርጃ የተዘጋጀ ቶምቦላ ቅዳሜ ጁላይ 31 ቀን …

የ”ኢሳት” ቶምቦላ ወጣ Read more »

(በሔኖክ ያሬድ):- ሐምሌ 22 ቀን 2002 ዓ.ም. ሐሙስ በአዲስ አበባ በ”ባሕር” አቅጣጫ (በሰሜናዊ ምዕራብ አቅጣጫ) ጉለሌ አካባቢ ካንድ ዐውደ ጥናት ተገኝቼ በ10 ሰዓት አካባቢ ወደ ፒያሳ ሳመራ ቀልቤን የገዛ ክስተት ተመለከትኩ፡፡ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ራዲዮ ጣቢያ፣ የአሁኑን የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ፋኩልቲ እንዳለፍኩ፣ …

ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሲዘከሩ Read more »

አሪስ ታታሊስ ከሁለት ዓመት በፊት የነበረው የአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሁላችንም የቅርብ ትዝታ ነው። የፓርቲ ዕጩነቱን ከማሸነፍ አንስቶ እስከ መጨረሻው የኖቬምበር 4 ምርጫ ድረስ የብዙዎችን ቀልብ ስቦ የነበረ ምርጫ ነበር። ታዲያ በዚህ ምርጫ ወቅት ነበር አንዲት ኮረዳ ጎልታ የወጣችው። ስሟ አምበር …

ሠሎሞን ተካልኝ – ኢትዮጵያዊው ኦባማ ገርል Read more »

የመድረክ ጥምረት ወደ ግንባርነት እንዲሸጋገር ጠቅላላ ጉባኤው ወሰነ ከአስር ወራት በፊት መድረክ ሲመሰርት የተቀረፀው መለስተኛ ፕሮግራም ለግንባር አደረጃጀት እንዲሆን ተብሎ እንደነበርና ስድስቱም የመድረክ አባል ድርጅቶች በተናጠል በጉዳዩ ላይ የወሰዱት ውሳኔ ለትላንት በስቲያው ስምምነት ማብቃቱን የወቅቱ ሊቀመንበር አስታወቁ። ሽግግሩ ተግባራዊ እንዲሆንና …

መድረክ ወደ ግንባርነት እንዲሸጋገር ተወሰነ Read more »

‹‹ከእኛ ወገን አልያም ከዐመፀኛ ኀይሎች ጋራ ለመኾናችሁ ሚናችኹን ለዩ! በእንጀራችኹ ፍረዱ!! ፓትርያሪኩም ቢኾኑ አያድኗችኹም!!›› (አቡነ ፋኑኤል) ‹‹በእንጀራችሁ ፍረዱ!›› (ሥራ አስኪያጁ) (ደጀ ሰላም፣ ኦገስት 2/2010)፦ በሲዳማ፣ ጌዲኦ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ሦስት አጥቢያ …

በሐዋሳ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያት እና የሀገረ ስብከቱ ‹ልኡካን› ውዝግብ Read more »

ባለፈው ቅዳሜ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ኮልፌ በሚባለው አካባቢ በደረሰው የመኪና አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከተገለፀው ከፍ ሊል እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ።

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 1/2010)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባቶች የሰላምና የዕርቅ ድርድር በነገው ዕለት ማለትም ሰኞ ኦገስት 2/2010 (ሐምሌ 26/2002 ዓ.ም) ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። ከሁለቱም በኩል ያሉ ተወካይ “የሰላም ልዑካን” ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ ተሰባስበዋል። እንደተለመደው ውይይቱ እንደሚደረግ በደፈናው ከመታወቁ ውጪ በምን …

ውይይቱና ሽምግልናው በምን ዙሪያ? Read more »

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከሐላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ፤ ችግሩን አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተወሰነ፤ ‹‹ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ኀበ ሐዋሳ ንሐውር፤. . . የሐዋሳን ሕዝብ  ከመውደዴ የተነሣ እኔ ራሴን የአጣሪ ኮሚቴው አባል ባደርግ ደስ ይለኝ ነበር፤›› (አቡነ ጳውሎስ)  ‹‹ምእመኑ ቤተ …

የሐዋሳ ከተማ ምእመናን ተወካዮች ከፓትርያርኩ ጋራ ተወያዩ Read more »

(በሚካኤል ተወልደ) ትናንት ረፋዱ ላይ ከኮልፌ 18 ማዞሪያ እስከ ፖሊስ ማሰልጠኛ አካባቢ ባለው ሥፍራ ሁለት ኮንቴይነሮችን የጫነ ከባድ የጭነት መኪና ባደረሰው አደጋ በሰው፣ በእንስሳትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ፡፡

(በታምሩ ጽጌ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት (መድረክ) በትናንትናው ዕለት ባደረገው 3ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ዝግ ስብሰባ የአባላቱን ሙሉ የድምፅ ድጋፍ በማግኘት ከጥምረት ወደ ግንባርነት መሸጋገሩን ምንጮች ገለጹ፡፡ በአመራሮች ላይም ለውጥ ያደረገ ሲሆን ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው የግንባሩ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ለአገሪቱ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ አዲስ ኮርፖሬሽን በ10 ቢሊዮን ብር ካፒታል አቋቋመ (በውድነህ ዘነበ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአገሪቱ የሚገኘውን የኢንጂነሪንግ ዘርፍ ወደላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ያለውን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በ10 ቢሊዮን ብር አቋቋመ፡፡

(በውድነህ ዘነበ) የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አካሂዶት የነበረውን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በሚል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ውድቅ ማድረጉን አዲስ የተመረጠው የአንበሳ ባንክ ቦርድ አጥብቆ ተቃወመ፡፡

አቡጊዳ – ሐምሌ 24 ቀን 2002 ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ እንደሚገልጸዉ ከእያንዳንዶቹ የመድረክ አባላት፣ ሰባት ሰባት ሰዎችን የያዘዉ የመድረክ ምክር ቤት፣ መድረክ ከቅንጅት ወደ ግንባር እንዲሸጋገር ወሰነ። የመድረክ አባል ድርጅቶች ከመቼዉም በበለጠ በመከባበርና በመግባባት የሚሰሩ መሆናቸዉን የገለጹት አንድ ያነጋገርናቸዉ የፖለቲካ …

መድረክ ከቅንጅትነት ወደ ግንባርነት እንዲሸጋገር ምክር ቤቱ ወሰነ ! Read more »

አጼ ኃይለ ሥላሴ መስከረም 2 ቀን 1967 ከስልጣን እስከተወገዱበት ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያን ከሃምሣ ዓመታት በላይ ያስተዳደሩ ንጉሥ ነበሩ። የዘውዳዊ አስተዳደሩን የተካው ወታደራዊ አስተዳደር የቀድሞውን የፊውዳል ስርአት ቅሪቶች በሙሉ ከፖለቲካው ዓለም ካስወጣ በኋላ፤ አንዳንዶቹን ሲገድል፣ ሌሎቹን ደግሞ ለእስር፣ ለእንግልትና ለስደት ዳርጓል። …

የአፄ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጆች ህገ-መንግስታዊ ዘውድ እንዲቋቋም እያቀነቀኑ ነው Read more »

ትምህርት ለአፍሪቃ እድገት ቁልፍ ሚና አለው። በማዳመጥ መማር የተሰኘዉ የዶቼ ቬለ መረሃ ግብር በመገናኛ ብዙሃን የርቀት ትምህርት በሁሉም የአህጉሪቱ ክፍሎች እውቀትን ለማዳረስ በጥረት ላይ ይገኛል።

. ‹‹ወጣቱን በተሐድሶአውያን ኅብረት አዲስ ጥምቀት በማድረግ በ‹ቅን ልቦና የመንፈሳዊ የፈውስ አገልግሎት› ሥር መሰብሰብ፤›› . ‹‹ሐሳባችንን የሚያደናቅፉ የአቡነ ሳሙኤል ደጋፊዎችን ተቋቁመን ልንጥላቸው ይገባል፤›› . ‹‹ወላጅ በሌላቸው ሕፃናት ስም የገንዘብ እና አልባሳት ርዳታን ከሙሉ ወንጌል አማኞች ማኅበር በመቀበል እና የቤት ለቤት …

የሊ/ካህናት ጌታቸው ዶኒ እና የአባ ሰረቀ ምስጢራዊ ደብዳቤ Read more »

 ፓትርያርኩ ቁልቢ አልሄዱም፣ (ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 29/2010)፦ የብፁዕ ወቅዱስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን 18ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ‹‹በልዩ ሁኔታ ለማክበር›› በሚል በተቋቋመው የበዓል አከባበር ኮሚቴ፣ ከ300‚000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ዐጸድ ውስጥ …

የቅዱስነታቸውን ሐውልት በማቆም የቅድስት ማርያም ስብከተ ወንጌል ማኅበር ከፍ ያለ አስተዋፅኦ አድርጓል›› (ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል) Read more »

የአውሮፓ ህብረት ልዑካኑ የፊታችን ረቡዕ ለሚካሄደውና ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ ለቆየው ውሳኔ ህዝብ ስለተደረገው ዝግጅት ለመረዳት ባለፈው ሰኞ ከኬንያ ጊዛዊ ነጻ የምርጫ ኮሚሽን ኣባላት ጋር ስብሰባ አድርገዋል። ሎጂስቲካዊ ዝግጅቱን እና በህገመንግስቱ ላይ ስለሚደረገው ምርጫ ህዝቡን የማስተማሪያ ፕሮግራሞች ላይ ያተኮረ ውይይት ነበር። …

የአውሮፓ ህብረት ኬንያ ለህገ መንግሥቱ ውሳኔ ህዝብ በያዘቸው ዝግጅት ደስተኛነቱን ገለጠ Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 29/2010):- የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለማስፈጸም እነበጋሻውንና ቡድኑን እንዳያስተምሩ የከለከሉት የአዋሳ ቅ/ገብርኤል የቀድሞ አስተዳዳሪ በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ከቦታቸው ከተነሱ ጀምሮ ምእመኑ ይህንኑ በመቃወም የተለያዩ እርምጃዎች ወስዷል። የገዳሙ አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ ዋሕድ ወልደ ሳሙኤል ወደ ቦታቸው …

በአዋሳ የምእመኑ ተቃውሞ፣ የፓትርያርኩ ምላሽ እና የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ማስፈራሪያ Read more »

የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍሮንሷ ፊሎን ሀገራችው ከአል-ቃይዳ ጋር ጦርነት ላይ መሆንዋን በፈረንሳይ ራድዮ ተናግረዋል። የፈረንሳዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤርናር ኩችነር ይኽው ቡድን  የውጭ ሰዎች ጠለፋና አልፎ አልፎም ግድያ የሚፈጽምበት  ወደሆነው ወደምዕራብ አፍሪካ ጉብኝት ሲያካሂዱ ቆይተዋል።  ቡድኑ ፈረንሳዊውን የረደኤት ሰራተኛ ሚሼል …

ፈረንሳይ፥ የአፍሪካ አገሮች አልቃይዳን እንፋለማለን አሉ Read more »

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2010)፦ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ በተጀመረው እንቅስቃሴ ቅ/ሲኖዶስን ወክለው የሚወያዩት ልዑካን ከዚህ በፊት የዘገብናቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ ብፁዕ …

አባቶችን የማደራደሩ ውይይት ይጀመራል Read more »

“እናንተ መሪዎች የሆናችሁት በእነዚያ ሴቶችና በሕፃናቱ ምክንያት ነው፡፡ እናንተን ሥልጣን ላይ ያስቀመጧችሁ ሰዎች ናቸው – እነርሱ፡፡ እንደ አንዲት አፍሪካዊት ሴት እና የአራት ልጆች እናት ማለት የምፈልገው ይህቺ አፍሪካ፣ የሚኖሩባት ሰዎች ሁሉ መሆኗን ነው፡፡ አፍሪካ ከባርነት ማነቆዎቿ ተላቅቃለች፤ ነፃነታችንንም ጨብጠናል፡፡ እና …

15ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ በካምፓላ Read more »

የዓለም የምግብና ግብርና ድርጅት በአዉሮጳዉያኑ 2007ዓ,ም ይፋ ባደረገዉ ዘገባ ኢትዮጵያ የደን ይዞታቸዉ እየተመናመነ ከሚገኙ አገራት ከመጨረሻ በአምስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል።

– አዳዲስ ምርቶቹን አስተዋወቀ (በታምሩ ጽጌ) በዓለም ላይ በሴሚ ኮንዳክተር ቴሌኮሙዩኒኬሽን፣ ዲጂታል ሚዲያና ዲጂታል ሚዲያ ኮንቨርጀንስ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሽያጭ የሚታወቀው የደቡብ ኮሪያው ሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ሊትድ፣ በሚቀጥሉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የመገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ እንደሚከፍት አስታወቀ፡፡

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 27/2010)፦ በጀርመን ሀገር ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ሕክምናቸውን ፈጽመው ወደ ሀገር ቤት ተመለሱ።  ብፁዕነታቸው ለሚያሰቃያቸው የጀርባ ሕመም መፍትሔ ለማግኘት ቀደም ብሎ በግሪክ ከዚያም ደግሞ በጀርመን ሲታከሙ ቆይተው ባለፈው ሐሙስ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ በቅተዋል። ብፁዕነታቸው አሁን …

ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ወደ ሀገር ቤት ተመለሱ Read more »

ባሪ በሚባለው በምዕራቡ የሶማሊያ ክፍለ ግዛት ቦሳሶ ከተማ አቅራቢያ በፑንትላንድ ኃይሎችና በስላማዊ ተዋጊዎቹ መካከል ከባድ ውጊያ ተካሂዷል። የፑንትላንድ ፕሬዚደንት አብዲራህማን  ፋሮሌ ዛሬ ማለዳው ላይ ባካባቢው በነበሩ የመንግሥቱ የጸጥታ ጥበቃ ኃይሎች ላይ ተኩስ በመክፈት ውጊያውን የቀሰቀሱት ሽምቅ ተዋጊዎቹ እንደሆኑ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። …

የፑንትላንድ ኃይሎች ቦሳሶ አቅራቢያ ከእስልማዊ ሸማቂዎች ጋር እየተፋለሙ ናቸው Read more »

ሣምንቱ በአትሌቲክሱ የስፖርት መድረክ ሞናኮ ላይ የዲያመንድ ሊግ ውድድር የተካሄደበት ነበር። ካናዳ-ሞንክተን ላይ ሲካሄድ የሰነበተው የዓለም አትሌቲክስ ፌደሬሺኖች ማሕበር የወጣቶች ሻምፒዮናም ባለፈው ምሽት ተጠናቋል።