እርቀ ሰላሙ ሳይጀመር ተፈጸም፣ ሳይታሰር ተበተነ

(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 3/2010)፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአባቶች የሰላምና የዕርቅ ድርድር ሳይጀመር ተፈጸም፣ ልዑካኑም ሳይወያዩ ተበተኑ።

ከትናንት በስቲያ ሰኞ ይጀመራል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ይህ “የሰላምና የእርቅ ጉባዔ” በተሸማጋዬቹ መካከል ማድረግ የፈለገውን ውይይት ማድረግ ሳይችል፣ ሁለቱን ልዑካን ፊት ለፊት ማገናኘት ሳይችል፣ በቅድመ ሁኔታ ላይ ብቻ ሲደራደር ቆይቶ እንዲሁ ተበትኗል። ይኸው ውይይት ውጤት እንደማያመጣ በታወቀ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የአሜሪካው ወገን ቀድሞ ያዘጋጀው የሚመስለውን መግለጫ በ “ቋጠሮ” ድረ ገጽ ላይ አውጥቶታል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን