የ”ኢሳት” ቶምቦላ ወጣ

አሜሪካኖች ከፍተኛውን እጣ ወስደዋል። ካናዳዎችና አውሮፓዎችም ከእጣው ተጋርተዋል፡ የእጣውን ቁጥሮች ይዘናል።

ከጁላይ 29 እስከ ጁላይ 31 በአምስተርዳም በተካሄደው 8ኛው የኢትዮጵያዊያን አውሮፓውያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ እንዲወጣ ታስቦ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (በምህጻረ ቃሉ “ኢሳት”) መርጃ የተዘጋጀ ቶምቦላ ቅዳሜ ጁላይ 31 ቀን ከምሽቱ 8 ሰዓት አካባቢ አያሌ የኢሳት ደጋፊዎችና ጥቂት ተቃዋሚዎች በተገኙበት ወጣ። በዚህ እጣ ከተዘጋጁት 4000 ትኬቶች ውስጥ፡ በመረጃ ስህተት ምክንያት ሳይሸጥ ከቀረው 6 ትኬት ውጪ ከሶስት ሺህ በላይ ትኬት መሸጣቸውን የገለጹት የቶምቦላው አዘጋጆች፡ በወጣው እጣ መሰረት፡ የመጀመሪያ እጣ የሆነውን 42 ኢንች ዝርግ ቴሌቪዥን ቁጥር 1341 ከአሜሪካ ወስዶታል።

The winners of the Tombola are posted at ethsat.com

ሁለተኛው ላፕቶፕ ቁጥር 3662፡

ሶስተኛው እጣ አይፎን 3ጂ ደግሞ ቁጥር 1951 ሆኗል።

በዚህ ካናዳም አውሮፓም ከአሜሪካኖቹ ጋር በተጋሩት እጣ፡ የወጡት ቁጥሮች እንደሚከተለው ናቸው።

4ኛው እጣ፡ ዊ ኮንሶል፡ 3454፡

5ኛው ቪዲዮ ካሜራ እጣ፡ 2420፡

6ኛው 20 ኢንች ዝርግ ሞኒተር እጣ፡ 2234፡

7ኛው ዲጂታል ካሜራ፡ 188፡

8ኛው ጂፒኤስ፡ 2743፡

9ኛው አይፖድ ናኖ፡ 627፡

10ኛውና 11ኛው እጣዎች የኮምፒውተር ማዳመጫዎች ሲሆኑ ቁጥሮቹም 387፡ እና 3664 ናቸው።

ከ12ኛ እስከ 15ኛው እጣዎች ብሉ ቱዞች ሲሆኑ፡ ቁጥሮቹም፡ በተከታታይ 1621፡ 3458፡ 2189፡ እና 165 ናቸው።

በኢሳት ገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ በጸደቀውና በኢሳት ደጋፊዎች ራስ አነሳሽነት የተዘጋጀው ቶምቦላ ከፍተኛና አስደሳች የህዝብ ምላሽ እንደታየበት ገልጸው፡ እነዚህን ቁጥሮች የያዙ ሰዎች ቁጥራቸውንና ትኬታቸው ይዘው እየቀረቡ ሽልማቶቹን መቀበል እንደሚችሉ ገልጸዋል። በዚህ ዝግጅትና የኢሳት ድንኳን አካባቢ ሆኖ ሲታዘብ የቆየው የዚህ አጭር ዘገባ አቀናባሪ፡ አንዳንድ ሰዎች በኢሳት መመስረት ከመደሰታቸው የተነሳ አራት አምስት ትኬት እየገዙ “እጣው ከወጣ ለኢሳት ይሁን” እያሉ ትኬታቸው ለአዘጋጆቹ ትተው ሱሄዱ ተመልክቷል። እናቶች ልጆቻቸው ከኢሳት በረከት እንዲቋደሱ እጣውን እንዲያወጡ አሰልፈዋቸው ነበር።

የእጣው አወጣጥ ስነ ስርአት በቪዲዮ ካሜራ የተቀረጸ ሲሆን፡ አዘጋጆቹ አርትኦቱን እንደጨረሱ እንደሚለጥፉት ጠቁመዋል።

ልጅ ተክል፡ ከአምስተርዳም፡ ሀምሌ፡(ጁላይ 31) 2010