የግልገል ጊቤ ሁለት ጥገና ሥራ 70 በመቶ መጠናቀቁ ተነገረ

(በቃለየሱስ በቀለ)

በተመረቀ በአጭር ጊዜ በደረሰበት የመሬት ርደት ሳቢያ አገልግሎት መስጠት ያቋረጠው የግልገል ጊቤ ሁለት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጥገና ሥራ ከ70 በመቶ በላይ እንደተጠናቀቀ ተገለጸ፡፡