አባቶችን የማደራደሩ ውይይት ይጀመራል

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2010)፦ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ በተጀመረው እንቅስቃሴ ቅ/ሲኖዶስን ወክለው የሚወያዩት ልዑካን ከዚህ በፊት የዘገብናቸው ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣  ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስና ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሳይሆኑ ከሐምሌ ስድስቱ የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ማግስት ስማቸው በየጋዜጣው የተጠቀሰው ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣  ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ እና መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ ናቸው። የአሜሪካን አባቶችን ወክለው ደግሞ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እና ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ይደራደራሉ ተብሏል።