በዚህ የምርጫ ወቅት እየተቃረበ ባለበት ወቅት ስርዓቱ የመንግስትን ተቋማት ተገን አድርጎ የአንድነት አባላትን በመላ ኢትዮጵያ በማሰርና በማዋገብ ላይ ይገኛል። ለጥቅምት 25/2007 ዓ.ም. አጥቢያ ላይ በምዕራብ አምርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ የሚገኙ የአንድነት አባላት አቶ አንጋው ተገኝ የአካባቢው የአንድነት ሰብሳቢ፣ አቶ አባይ ዘውዱ እና አቶ እንግዳው ዋኘው የተባሉ የአካባቢው የአንድነት አመራር አባላት የፌደራል ፖሊሶች የቤታቸውን በር ገንጥለው […]

በመቀሌ የአንድነት አባል የሆነው ወጣት ሺሻይ አዘናው በዛሬው ዕለት ጥቅምት 26 2007 ዓም በመንግስት የድህንነት አካላት ከሚሰራበት መስሪያቤት የወሰዱት ሲሆን ከዚያ ወደ ቤቱ በመውሰድ ቤቱን ፈትሸው እዚያ ያገኙትን ወረቀት ሁሉ አፋፍሰው ከያዙ በኋላ በሽፍን ላንድኩረዘር መኪና ወደ አልታወቀ ቦታ ይዞውት ሄደዋል። ወጣት ሽሻይ አዘናው ቀደም ሲል አንድነትን ከመቀላቀሉ በፊት የአረና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበረ ሲሆን፤ […]

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር ዞን በፓርቲው አባላት ላይ በዘመቻ የሚደረገውን እስርና እንግልት በመቃወም መግለጫ አወጣ

በዛሬው ዕለት ጥቅምት 26 ቀን 2007 ዓ.ም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት የአንድነት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዳንኤል ሺበሺ ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ም/አፈ ጉባኤ የሺዋስ አሰፋ ፣ የአረና ፓርቲ የአመራር አባልና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር አብርሃ ደስታ እንዲሁም የአ/አ ዩኒቨርስቲ የማስትሬት ተማሪ ዘላለም እና በተመሳሳይ መዝገብ […]

Image

በኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ ታሪክ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በህገ መንግስት እውቅና ያገኘውና በይፋ ፓርቲ መመስረት የተቻለው በኢህአዴግ ዘመን ነው፡፡ ይህ መቸም እንደ ጅምር ሊያስመሰግን የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ምንም እንኳ ኢህአዲግ ለነፍሱ ብሎ ባያደርገውም፡፡ ሁኔታዎች አስገድደውት ያደረገው እንደሆነ ቢታወቅም በይፋ መደራጀት መቻልን እንደ ትልቅ ለውጥ ነው የምወስደው፡፡
ቁም ነገሩ ግን ኢህአዲግ የፈቀደልንን ህገ መንግስታዊ (ከጫካ ስለሆነ የመጣው ያለመፍቀድ እድልም ነበረው) የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ተጠቅመን ለውጥ ለማምጣት ተንቀሳቅሰናል ወይ? የሚለው ነው፡፡ ለእኔ መልሱ አይደለም የሚል ይሆናል፡፡ ከአዛውንቱ ዶክተር አስራት ወልደዬስ በቀር አንድም እንኳ ህዝብ አስተባብሮ መሬት ያረፈ ትግል ያደረገ እና ኢህአዲግን የተገዳደረ ፓርቲ ፈጽሞ የለም፡፡ ከጠብ-መንጃ ጋር ፊት ለፊት በባዶ እጅ የተጋፈጡት ቆፍጣናው ምሁር አስራት ውልደዬስ እድሜያቸውና ክብራቸውን በማይመጥን ሁኔታ ለእስር ተዳርገው ለሞት ቢበቁም ከእርሳቸው በኋላ ለምልክት እንኳ የተንቀሳቀሰ የፓርቲ መሪም ሆነ ፓርቲ አላየሁም፡፡
ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው አንድም እንኳ የፓርቲ መሪ ለእስርም ሆነ ለሞት ሲዳረግ ታይቶ አለመታቁ ነው፡፡ በአካልም ሆነ በመንፈስ አንዳች ጉዳት ደርሶባቸው አለማወቁ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የግድ ለምን አልታሰሩም ወይም አልሞቱም የሚል መንቻካ ሀሳብ ለማንሳት ሳይሆን ከኢህአዲግ አምባገነንነት አንጻር ምንም አይነት እርምጃ ያለመውሰዱ የመሪዎቹን ልክ ያሳያል ለማለት ነው፡፡ ሁሉንም የግፍ ገፈት የሚጨልጡት አባላትና ዜጋው ነው፡፡ ቆፍጣናዋን እንስት ብርቱካን ሚዴቅሳን ግን መርሳት ከቶ አይቻልም፡፡
በኢህአዲግ ክፍተት ወይም እንዝላልነት በአጋጣሚ የተገኘው የ1997 ዓ.ም ተሞክሮም ቢሆን በፖለቲከኞች ልፋት ያልመጣ መሆኑ ለክርክር የሚቀርብ አይደለም፡፡ የመለስ ዜናዊ ‹‹እንከን አልባ ምርጫ እንደርጋለን›› ፉከራን ተከትሎ ገርበብ ያውን በር ነጻነት የተጠማው ህዝብ በርግዶት ከመግባቱ በቀር ይህን አስተዋጽኦ አደርጌያለው የሚል ካለ ለክርክር ፈቃደኛ ነኝ፡፡
ምን ይሻል???
እስካሁን የነበረውን ‹‹የእናቴ ቀሚስ ጠለፈኝ›› ማስተባበያ ወደ ጎን ብለን ህዝቡ ድረስ በመውረድ ማደራጀት፤ የነጻነትን ጣዕም እንዲያውቅ ማንቃት፤ ዲሞክራሲን በተግባር ማለማመድ፤ ህዝቡ የሥነ ልቦና ለውጥ እንዲያመጣ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለውድቀታችን ሁሉ ኢህአዲግን መክሰስ ግን እንደ ቋንጣ የደረቀና አዋጭ ቢዝነስ አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ ለፖለቲካችን መበላሸት ኢህአዲግ ሰፊ መዳፍ የለውም የሚል የሞኝ አስተሳሰብ የለኝም፡፡ የእኔ መከራከሪያ የኢህአዲግ ባህሪ የታወቀ ስለሆነ እርሱን ወደ ጎን ትተን እና እረስተን ህዝቡ ጋር መድረስና ህዝባችን ማንቃት የሚል ነው፡፡ ምክንያቱም የነቃ ህዝብ ለጭቆና ስለማይች፡፡ በተቃራኒው ያልሰለጠነና ያልነቃ ህዝብ ‹‹ቢጭኑት አህያ ቢጋቡት ፈረስ›› ከመሆን አያልፍምና፡፡
‹‹መንግስት የቆመጠው ቆማጣ አይባልም›› ብሎ የሚተርትን ህዝብ መንግስት መቁመጥ መብቱ አለመሆኑን ማስረዳት ይኖርብናል፡፡ በተቃራኒው ህዝብ በመንግስት ላይ ያለውን የበላይነት አንጽሮ መንገርና ሀሳብ ማስታጠቅ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ የሀገራችን ፖለቲከኞች ኢህአዲግን ከመክሰስ እና ሰሞነኛ ነገር ከማራገብ ያለፈ ስር ነቀል ለውጥ የምንፈልግ አይመስለኝም፡፡
‹‹ኢህአዲግ ገዳይ ነው፤ ኢህአዲግ ያስራል ፤ ያፈናቅላል፤ ያሰድዳል፤ የመንግስትን በጀት ለድርጅት ይጠቀማል፤ ይዋሻል…..ብላ ብላ ከሚል ማላዘን ያለፈ ተጨባጭ አማራጭ የለንም፡፡ አለን የምንለው እንኳ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ አይደለም ሀገርን ያክል ትልቅ ነገር ይቅርና መንደር ለመምራት የሚያስችል አቅም ያለው ፓርቲ ማግኘት ጨረቃ ላይ እንደመውጣት ያለ ከባድ ነው፡፡
‹‹የኢህአዲግ የትምህርት ፖሊሲ የተሳሳተ ነው›› የሚል ተቃዋሚ አማራጭ የማቅረብ ግዴታ አይኖርበትም፡፡ እውነታ ግን ባ ተቃውሞ ብቻ ነው፡፡ የእያንዳንዱን ፓርቲ ገመና ቀርባችሁ ስታዩት ከበርሜል ጩኸት አይለይም፡፡ ባዶ ‹‹የእንዲህ ሆነብን›› ጩኸት!! ታዲያ በዚህ ሁኔታ እንዴት ለውጥ ማምጣት ይቻለል?? በነገራችን ላይ ‹‹ኢዴፓ›› መስተካከል ያለበት እንዳለ ሆኖ ማንም ፓርቲ ሊስተካከለው የማይችል ዝርዝር የትንታኔ ሰነድ ባለቤት ነው፡፡
መፍትሄው
መፍትሄው እራሳቸውን በሸንበቆ አጥር ከልለው በጸጉር ስንጠቃ አባዜ የተበታተኑ ፓርቲዎችን ወደ አንድ ጎራ እንዲፈሱ በማድረግ ግዙፍ የሆነ እና አማራጮችን ማቅረብ የሚችል የተቃውሞ ጎራ መፍጠር ብቻ ነው፡፡ ደግሞም ይህን ለማድረግ የሚያግድ አንዳች እንኳ ምክንያት የለም፡፡ ምን አልባት እንደ ዘመነ መሳፍንት ሁሉ በዬ መንደሩ አለቃ ሆነው የከረሙት የፓርቲ አመራሮች ይህ እንዳይሆን አይታገሉም ማለት አይደለም፡፡
ነገር ግን ኢህአዲግን ከመታገላችን በፊት እነዚህን ‹‹የመንደር አውራዎች›› ልክ ማስገባት ለነገ የማይባል ስራ መሆን ይኖርበታል፡፡ መነጋገሪያችን መሆን ያለበትም ፍትህ የተጠማውን ህዝባችን መታደግ የሚችል ፋና ወጊ ፓርቲ እንዴት መመስረት ይቻላል የሚል መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ ለዛሬ እንጅ ለነገ መባል አይገባውም፡፡

በተባበረ ክንድ ወደ ነጻነት የምንጓዝበት ቀን ሩቅ አይሆንም!!
…………….እናቸንፋለን……!!!

አቶ ሀብታሙ አያሌው ግራ እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት ችሎቱን ተቀምጦ ለመከታተል መገደዱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ተከሳሾች ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው ::
7 ሙስሊም ወንድሞች እስላማዊ መንግስት በኢትዮጵያ ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ በሽብር ወንጀልም ተሳትፈዋል›› የተባሉ ተከሰዋል ::

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በሽብር የተከሰሱት አራቱ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ አስሩ ተከሳሾች ዛሬ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የዋስትና ጉዳያቸውን ለማየት ለህዳር 2/2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ሀብታሙ አያሌው፣ የሽዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሺን ጨምሮ አስሩ ተከሳሾች ላይ የፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ከቀናት በፊት መመስረቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የዋስትና ጉዳያቸውን አይቶ ብይን ይሰጣል ቢባልም የተከሳሽ ጠበቆች አጭር የጊዜ ቀጠሮ በጠየቁት መሰረት ለህዳር 2/2007 በአምስት ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ከ1-5ኛ እና የ9ኛ ተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ የተከሳሾች የዋስትና ጉዳይ ከመታየቱ በፊት በተከሳሾች ላይ የቀረበው ማስረጃ የገጽ ብዛት ተጠቅሶ ለጠበቃዎቹ እንዲደርሳቸውና የአቃቢ ህጎቹ ስም እንዲጠቀስ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
ጠበቃው የዋስትና ጉዳዩን በተመለከተ በቃል ጥያቄውን ማድረስ እንደሚችሉ ገልጸው፣ ነገር ግን ጊዜ ተሰጥቷቸው በጽሑፍ ለዳኞቹም ለአቃቤ ህጎቹም ማቅረብ እንደሚችሉ ለችሎቱ በጠየቁት መሰረት ለቀጣይ ቀጠሮ በጽሑፍ አዘጋጅተው እንዲቀርቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ አቃቤ ህግ በበኩሉ ያለውን የሰነድ ማስረጃ ከክሱ ጋር አያይዞ ማቅረቡን በመግለጽ የሰው ማስረጃዎችም እንዳሉት አስረድቷል፡፡
አቶ ሀብታሙ አያሌው ግራ እግሩ ላይ ጉዳት ስለደረሰበት ችሎቱን ተቀምጦ ለመከታተል መገደዱንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ ሀብታሙ አያሌው 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን ሌሎች ተከሳሾች ደግሞ 1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ 3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ፣ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ፣ 5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ፣ 6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ፣ 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን፣ 8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ፣ 9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ፣ እና 10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ 7 ሙስሊም ወንድሞች እስላማዊ መንግስት በኢትዮጵያ ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል፣ በሽብር ወንጀልም በዋና ወንጀል አድራጊነት ተሳትፈዋል በሚል አቃቤ ህግ ዛሬ ክስ እንደመሰረተባቸው ታውቋል፡፡
ተከሳሾቹም፡-
1ኛ. ተከሳሽ ጃፋር መሀመድ
2ኛ. መሀመድ ኑሩ
3ኛ. መሐመድ ሰሊም
4ኛ. ኑረዲን ጀማል
5ኛ. መሀመድ አባብያ
6ኛ. አኑዋር ጃኒ
7ኛ. ጀማል አብዱ ናቸው፡፡
= በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርት =

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

የምርጫዉን ውጤት የገመገሙልን በባልቲሞር ሞርጋን ስቴት ዮኒቨርሲቲ የፓለቲካ ሳይንስ መምህር ዶክተር ጌታቸዉ መታፈሪያ የፕሬዚደንት ኦባማ የአገርና የዉጪ ፓሊሲዎች ላይ ከፍተኛ እንድምታ ይኖረዋል ብለዋል። ከፊታችን ጥር ወር ጀምሮ በሁለቱም ምክር ቤቶች ማለትም በመምሪያዉና በመወሰኛዉና ክፍሎች የአብላጫ ድምጽ የሚኖራቸዉ ሬፑብሊካዉያን ሲቃወሙዋቸዉ የነበሩ ለምሳሌ እንደ ፕሬዚደንት ኦባማ የጤና ጥበቃ ሕግ ያሉትን ሊሽሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል። የሆነ ሆኖ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣን እንዳላቸዉ ይታወቃል።

 

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እውነታው ከልብወለድ በላይ እንግዳ ነገር ነው!   እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 7/2014 “ድፍረት፡ የፊልም ጠለፋ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባወጣሁት ትችት ድፍረት በሚለው ፊልም ላይ የኢትዮጵያ መሪ ተዋንያን ሆና በሰራችው የውርጃ ድርጊት ላይ የነበረኝን ቁጣ ገልጨ ነበር፡፡ በአበራሽ በቀለ እውነተኛ ታሪክ ላይ …

የጠለፋ ጋብቻ በኢትዮጵያ ፡ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ወንጀል Read more »

በሕዋ ለመመራመርም ሆነ ለመንሸራሸር፣ የሚደረግ ጉዞ፣ በምድር ላይ እንደምናውቀው የተለያየ የማጓጓዣ ዘዴ ፍጹም ቀላል አይደለም። በሕዋ ጎዞ የማይታሰብ የተለያየ ችግር ሊያጥም እንደሚችል በማሰብ ማሰላሰል ፤ አማራጭ መላዎችን ሁሉ መሻቱ ተገቢ ነው።

በቻይና የመጠጥ ዉኃ ምንጭ በደንብ በተመጣጠነ ሁኔታ ለኅብረተሰቡ አልተከፋፈለም። በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ከሚገኘዉ የመጠጥ ዉኃ አገልግሎት ይልቅ በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በብዛት ተዳርሷል።

በዩኤስ አሜሪካ ትናንት በተካሄደው አጋማሽ የምክር ቤት ምርጫ ሬፓብሊካውያን በሁለቱም የምክር ቤት ክፍሎች አሸነፉ። በሕግ መምሪያው ምክር ቤት አብላጫውን ድምፅ የያዙት ሬፓብሊካውያን 100 መንበሮች ባሉት በሕግ መወሰኛው ምክር ቤትም ውስጥ 52 መንበሮችን በማግኘት አብላጫውን ድምፅ መያዝ ችለዋል።

በብዙ የኢትዮጵያ ከተሞች እየታየ ያለው የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በዕለት ተዕለት ኑሮው እና ስራ ላይ ከፍተኛ ችግር እንዳስከተለባቸው ዜጎች በምሬት ገልጸዋል። በሕዝቡ ኑሮ ላይ አሉታዊ ጫና የፈጠረውን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ መንግሥት ባለፉት ዓመታት ብዙ ስራ መሰራቱንና ይህንኑ ጥረቱን መቀጠሉን የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ገልጾዋል።

የአፍሪቃን ኤኮኖሚ ዕድገት ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንዲቻል በተለይ ትኩረቱ በከፍተኛው ትምህርት ዘርፍ ላይ ማረፍ እንደሚገባው በአዲስ አበባ የተመ የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥ ለአራት ቀናት የተካሄደው ጉባዔ አሳሰበ።

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ  የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ( ሰመጉ) ባወጣው 132ኛ ልዩ መግለጫ በክልሉ በመንገሽና ጎደሬ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተገደሉ የ60 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ እንደቀረበው 27 የአማራ፣ 27 የመዠንገር፣ 2 የከፋና 4 የኦሮሞ ተወላጆች ተገድለዋል። እንዲሁም 16 የአማራና 6 የመዠንገር ተወላጆች …

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የተቃዋሚ አመራሮችን በመያዝ እያሰረ ነው::  በትግራይ ክልል በምዕራባዊያን ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ የአረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ዘነበ ሲሳይ ጥቅምት 25፣ 2007 ዓም ከቤታቸው ተነጥለው በመወሰድ ሲታሰሩ፣  በተመሳሳይ ቀን በሁመራ የአረና የቁጥጥር ኮሚቴ አባል የሆኑት …

ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ በመሰረተባቸው አቶ ዘላለም ወርቅነህ፣  ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሽዋስ አሰፋና በሌሎች 5 ተካሳሾች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረውን ውሳኔ አራዘመ። ፍርድ ቤቱ የሁሉም ጠበቆች ተዘጋጅተው ባለመቅረባቸው ውሳኔውን ለህዳር 2 ፣ 2007 ማራዘሙን አስታውቋል። እስረኞቹ በሽብር …

ኢሕአዴግ በጭራሽ እራሱን ነፃ ለሆነ የምርጫ ውድድር እያዘጋጀ አይደለም !የፖለቲካ ሊቃውንት እንደሚያስገነዝቡት እና ዓለም አቀፍ ነባሪዊ ሁኔታ የሚያመላክተው ለምርጫ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ ፤በእኩል ደረጃ ባይወንም እንኳን በአንፃራዊነት የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ነፃነት እና እኩል ተሣትፎ ሊኖር ይገባል፣ፓርቲዎችን ሊያወዳደሩ የሚችል ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ምርጫ ቦርድ እና ጉዳዩን ሙያዊ ስነምግባር መሠረት በማድረግ ለህዝብ መረጃ የሚያደርስ ነፃ ሚዲያ ያስፈልጋል፡፡እነዚህ መሰል ዋንኛ መስፈርቶች ባልተሟሉበት በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ግንቦት ወር ነፃ ምርጫ ማካሄድ የሚታሰብ አይደለም፡፡

እንደ መግቢያ፡- በመዝገበ ቃላት አተረጓጎም መሠረት “ዲሞክራሲ ማላት በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት ማለት ሲሆን የመጨረሻውም ሥልጣን በሕዝብ ቁጥጥር ስር ያለ፣በቀጥታ በራሳቸው ወይም እነርሱ በወከሉት ወገን ብቻ በሥራ የሚተረጐምና በነፃ ምርጫ ስርዓት የተመረኮዘ ነው” ይላል፡፡ በአብርሃም ሊንከን አባባል “ዲሞክራሲ ከሕዝብ የወጣ ፣በሕዝብ የተመረጠና ለሕዝብ የሚያገልግል መንግስት ነው፡፡”በማለት የሰጠው ትርጓሜ በአብዛኛው ተቀባይነት ያገኝ ሃሳብ ነው፡ሦስቱ መሠረታዊ የመንግስት ምሶሶዎች ተብለው የሚታወቁት ማለትም ሕግ አውጪ፣ሕግ አስፈጻሚ እና ሕግ ተርጓሚ በሁለት መንገድ ሥራቸውን ያከናውናሉ፡፡እነኚኽም አካሄዶች ቀጥተኛ እና የተወካይ ዲሞክራሲ ተብለው ተለይተው ይታወቃሉ ፡፡
ቀጥተኛ ዲሞክራሲ ዜጎች የሚመርጧቸው ምንም ዓይነት ተወካይ አይኖራቸውም፡፡ይህ ማላት ግን አስተዳዳሪ ወይም መሪ የላቸውም ማለት አይደለም፡፡በማናቸውም ጉዳዮች ውሳኔ የሚወስነው በቀጥተኛ የህዝብ ተሳትፎ ነው፡፡ለየትኛውም የህዝበ ውሳኔ ጉዳዮች ፣ዜጎች በጋራ ተሰባስበው በመመክር በአንድ ዓይነት ስምምነት፣ ውይም በድምፅ ብልጫ ውሳኔ የሚያስተላልፉበት ስርዓት ነው፡፡የዲሞክራሲ እናት በመባል የምትታውቀው አቴንስ ከ4 ሺህ እስከ 7ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ስብሰባ በማካሄድ ነበር ቀጥተኛ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ተግባራዊ ታደርግ የነበረችው፡፡ይሁን እንጂ ከሕብረተሰብ ብዛት እና ከውስብስብነቱ አኳያ ለቀጥተኛ ዲሞክራሲ ተግባራዊነት የሚሰጠው ጥቅም ውስን በመሆኑ ብዙም ሳይጓዝ እንዲቀር ተደርጓል፡፡በአሁን ወቅት በዓለማችን በአብዛኛው ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የዲሞክራሲ ዓይነት የተወካዮች ዲሞክራሲ ነው፡፡እንዲህ ዓይነቱ ዲሞክራሲ ዜጎች የፖለቲካ ውሳኔዎችን የሚወስንላቸው ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ነው፡፡ተመራጮችሁም በበኩላቸው የመረጣቸውን ሕዝብ ወክለው ውስብስብ መንግስታዊ ሥራዎችን እውቀታቸውን፣ጊዜያቸውን እና ጎልበታቸውን ሰውተው ግልጋሎት ይሰጣሉ፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ፡- ከቀጥተኛ ዲሞክራሲ ይልቅ የተወካዮች ዲሞክራሲ ውጤቱ አጥጋቢ ባይሆንም፣ ተግባራዊ ለማድረግ ሙከራዎች ከዚህ ቀደም ተደርጓአል፡፡በተለይ በቀዳማዊ ንጉሳችን ኃይለ ስላሴ የተወካዮች ዲሞክራሲ ወደ አገራችን በማስገባት የዲሞክራሲ በዓላችን እንዲዳብር የተደረገው ጥረት እና ውጤት በታሪክ በአውንታዊ ጎን ተፅፎ የሚኖር ነው፡፡ይሁን እንጂ የተወካዮቹ አመራረጥ እና የሥራ ሂደታቸው ሲለካ ውጤቱ ምን እንደነበር ለታሪክ አዋቂዎች ቢተዉ የተሻለ ይሆናል፡፡ከዚህ ባለፈ በደርግ የተካሄደው የብሔራዊ ሸንጎ እና የኢሕአዴግ የ4 ዙር አገር አቀፍ ምርጫ ለዜጎች ከሰጠው ፋይዳ ይልቅ የአምባገነን ሥርዓት ለማስቀጠል የሰጠው ጥቅም የበዛ ነው፡፡
ከምርጫ 1997 ዓ.ም ወዲህ፣ ገዥው መንግሰት የምርጫን መቃረብ ተከትሎ መንገዶችን ይሰራል፣ የጋራ መኖራይ ቤት ገንብቶ በዱቢ እና በረጅም ወራት ክፍያ ለተጠቃሚዎች ያስተላልፋል፣ለመንግሰት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ያደርጋል፣በአንድ ለአምስት አደረጃጀት በመጠቀም የምረጡኝ ዘመቻ ይጀምራል፣አብዮታዊ ዲሞክራሲ ስልጠናና ጥምቀትን ያካሂዳል፣ዘላቂነት የሌላቸው ጊዚያዊ የሥራ እድሎችን በመፍጠር የሥራ አጦችን ካርድ ይነጥቃል፤ይህ ሣይሆን ሲቀር ኢ-ፍህታዊ ጥቅማ-ጥቅምን በመስጠት ደጋፊን ያበዛል፡፡ በተጨማሪም መቼም የማይፈፀሙ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በየቦታው የመሠረት ድንጋይ በመጣል ዳንኪራ ያስጨፍራል፣ከዚህም በላይ የሆነበትን ደግሞ ቃል ይገባል ፡፡እነዚህና መሰል የሆኑ ሁሉ ነገሮችን ማከናወኑ ለምርጫ ካርድ እንጂ ለዘለቂታዊ ልማት አይደልም፡፡የምርጫ ወቅት ሲቃረብ መንግስት ደፋ ቀና ደፈ ቀና የሚለበት ሥራ ሁሉ ለይስሙላ እንጂ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ እንደሌለው ላለፉት አራት ዙር በተደረጉ ምርጫዎች ለማረጋገጥ ይቻላል ፡፡ በይበልጥ ደግሞ የፊታችን ግንቦት ወር ይካሄዳል የሚባለው ምርጭ በገዥው መንግሰት ቀጥተኛ ተፅኖ ስር በወደቀው ምርጫ ቦርድ እና ፣በመንግስት በኩል መንገስት ስል ኢሕአዴግ ወይም ወያኔ ለማለት እንደተፈለገ ግንዛቤ ይወሰድልኝ፡፡ምክንያቱ ደግሞ ገዥው ፓርቲ እና መንግስት ባልተለያዩበት ሥርዓት ውስጥ በመሆናችን ነው፡፡ስለሀኖም በእነዚህ ሁለት ሃይሎች ተፎካካሪ ወይንም አማራጭ በሆኑ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ይህ-ቀረሽ የማይባል ጫና እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ችግሩ ደግሞ ቀጥተኛ በሆነ መንግድ የሚፈፀም ስለመሆኑ ከዚህ በታች በመጠኑ ለማመላከት ይሞከራል፡፡
የገዥው መንገስት ቀጥተኛ ጫና በፓርቲዎች፡-
በዓለም አቀፍ የተባበሩት መግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባሄ ባፀደቀው መግለጫ ኢትዮጵያም በፈረመችው ስለ መሰብሰብ እና መደራጀት መብቶች በሚከተሉው መልኩ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ “ የዜጎች የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶች ተግባራዊ ሂደት ገደብ በማይጣልበት ሁኔታ መከበር ሲኖርበት ነገር ግን ገደብ ቢደረግ እንኳን ገደቡ የዓለም ዓቀፍ ህግና ሰብዓዊ መብቶችን መሰረት ያደረገ እና የእነዚህን መብቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ እዉን የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡በተለይም ዜጎች የፖለቲካ እና የአይማኖት ለማስከበር የሚያደርጓቸው ተቃውሞዎች መደገፍ አለባቸው፡፡”የሚል ነው ፡፡
ይህ እጅግ በጣም ጠንካራ የሆነ ዜጎች በፖለቲካ የመደራጀት መብታቸውን የሚያስከበር ዓለም አቀፍ ሕግ ነው፡፡አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገመንገስት ይህን ህግ በመቀበል አካቶ ይገኛል፡፡እርግጥ ነው ህገመንግስቱ በራሱ ማሻሻይን የሚፈልጉ በርካታ አንቀፆች አሉት፡፡በዚህ አጋጣሚ ሰማያዊ ፓርቲ ዜጎችን በጋራ አግባብቶ በዘላቂነት ሊያገለግል የሚችል እና ለሕገመንግሰት መሠረት ወይም ምሶሶ የሚሆን “የዜጎች ቃል-ኪዳን ሰነድ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ”የተሰኘ ሠነድ በማዘጋጀት ለህዝብ ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ለዚህም መልካም ጅማሮ ለሰማያዊ ፓርቲ አድናቆት ሊቸረው ይገባል፡፡ወደጉዳያችን ስንመለስ በዓለም አቀፍ እዲሁም በኢትዮጵያ ሕግ የፖለቲካን ዓላማ ለማስፈፀም ሕግን መሠረት ያደረገ አደረጃጀት የተፈቀደ ነው፡፡ይሁን እንጂ ይህን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት ኖራቸው በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቃወሚ ፓርቲዎች፤ ሰብዓዊና ዲሞክራሳዊ መብቶች ይከበሩ፣የሕግ የበላይነት ይረጋገጥ፣ህዛባዊ መንግሰት ይመስረት በማለታቸው እና ለተግባራዊነቱ በመንቀሳቀሳቸው ብቻ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ለሞት፣ለእስራት፣ለስደት እና ለእንግልት እየተዳረጉ ይገኛሉ፡፡
ይህም በመሆኑ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላቶቺ ታስረዋል፣የመንግሰት ታጣቂ ሃይሎች በግልፅ እና በስውር በፓርቲ አባላት ወከባና እንግልት እየፈፀሙ ይገኛሉ፣ጠንካራ የሚባሉ የተቃዋሚ ሃይሎች የቀን-ተቀን ሥራቸውን የሚያከናውኑበት ቢሮ መከራየት እንዳይችሉ አከራዩች በቀበሌ ካድሬዎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ከብዙ ልፋት እና እንግልት በኋላ በሚያገኙት ቢሮ የፓርቲ አባላቶች ወደ ቢሮ ሲገብ እና ሲወጡ እየጠበቁ የመንግሰት ደንነቶች ወከባ ከፍ ሲልም ትንኮስ እየፈፀሙ ይገኛሉ፣ ፓርቲዎች ዋንኛ የተቋቋሙለትን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ማናቸውም እንቅስቃሴዎች ከደጋፊዎቻቸው ጋር በመሆን በነፃነት አደባባይ ወጥተው ቅስቀሳ እንዲሁም ተቃውሞ ማድረግ የሞት ሽረት ትግል ነው፡፡በተለይ ደግሞ አዲስ ተመዝጋቢ አባላት የአባልነታው የእጩ ቀናት መቁጠር ከመጀመራቸው በፊት በመንግሰት ታጣቂ እና በካድሬዎች የሚደርስባቸው ማስፈራሪያ እና ዛቻ ልጉድ ነው፡፡ከምንም በላይ ደግሞ የአባላትን ወራዊ መዋጮ እና ድጋፍ የፓርቲዎች የፋይናስ አቅም አይነተኛ መንግድ ነው፡፡ሆኖም ግን ይህ ገንዘብ በራሱ በቂ አይደለም፡፡ይህም በመሆኑ የፓርቲ አባላት ሣይሆኑ ደግፍ መስጠት ለሚፈልግ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ በልብ ሙሉነት ገንዘባቸውን እንዳይለግሱ ጫና ይደረግባቸዋል፡፡የጉዳዩ አሳሳቢነት ምን ያኸል እነደሆነ ለማሳያ አነድ ምሣሌ መጥቀስ ይቻልል፤አቶ የሺዋስ አሰፋ፣አቶ አብታሙ አያሌው፣አቶ ደንኤል ሽበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ በማእከላዊ እስር ቤት በዋንኛነት የሚደረግባቸው ምርመራ “የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድነው ? ማነው በቋሚነት ድጋፍ የሚያደርግላችሁ ?ገንዘቡ የት ነው የሚቀመጠው” የሚሉት ዘወትር የተለያየ የምርመራ ዘዴዎች በመጠቀም የሚጠየቁት ጥያቄ ነው፡፡ነገሩን ይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው ከላይ የተገለፁት የፓርቲ አባለት የተያዙት “በሽብር ወንጀል በመጠርጠር ነው”በማለት ገዥው መንግስት ገልፆአል ሆኖም በምርመራ ወቅት ግን የሚጠየቁት የፓርቲ ገንዘብ ወጪና ገቢ ነው፡፡ በአጠቃላይ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል በመሆን ብቻ ነጋዴው ከንግዱ፣ተማሪው ከት/ት፣ሰራተኛው ከስራው፣ገበሬው ከእርሻው፣አርብቶ አደሩ ከከብቶችሁ እየተፈናቀለ ይገኛል፡፡
ስለዚህም ተፈካካሪን የተቃወሚ ፓርቲን በእንዲህ መልኩ እያዳከመ እና አንዳንዶችን በጭራሽ ከወደቁበት እንዳይነሱ እያደረገ ይገኛል፡፡በእንዲህ መልኩ ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ጋር ኢሕአዴግ ተፎካካሪ በመሆን ለመርጫ እራሱን እያዘጋጀ ነው እንዴት ሊባል ይቻላል ?
የገዥው መንገስት ቀጥተኛ ጫና በምርጫ ቦርድ ፡-
በየደረጃው ትክክለኛ ምርጫ እንዲካሄድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 102 ላይ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሹመታቸው ከመንግስት መልካም ፍቃድ የመነጨ ሲሆን አሰራራቸውም ለገዥው መንግስ በእጅጉ በጣም ያደላ ነው፡፡ስለዚህም ምርጫ ቦርድ ህገመንግስቱን መሠረት አድርጎ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ለማለት ከበድ ድፍረትን የሚጠይቅ ነው፡፡የስከዛሬውም የምርጫ ቦርድ የሥራ አንቅስቃሴ ለገዥው መንግስት ያለው ታማኝነት እና አገልጋይነት በድብቅ ሣይሆን በአደባባይ “እዩልኝ፣ስሙልኝ” እያለ በራሱ ላይ መስክሮ የእኛን መስክርነት ከሰጠን አመታት ተቆጠሩ፡፡ከወረዳ የምርጫ አስፈፃሚ ጀምሮ እስከላይ ያለው የምርጫ ቦርድ ሃላፊ፣ በገዥው መንግሰት ቀጥተኛ ተፅእኖ ስር መሆናቸው ግልፅ እና አሻሚ ያልሆነ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ላይ ከዘህ በላይ ማሣያዎችን ለማመላከት መሄድ ዉሃ ቅዳ ዉሃ መልስ ይሆናል ነገሩ፡፡
በመሆኑም ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በአገራችን የለም፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ ሣለ ከተፈካካሪ የተቃወሚ ፓርቲዎች ጋር ኢሕአዴግ ለመርጫ እራሱን እያዘጋጀ ነው ማለት እንዴት ይቻላል ?
የገዥው መንገስት ቀጥተኛ ጫና በነፃ በጋዜጠኛ ላይ ፡-
ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ አሳብን ለመግለፅ ይቅርና ከገዥው መንግስት ፍላጎት እና አሳብ ውጪ ማሰብ በራሱ ለእስራት እና ለእንግልት ይዳርጋል፡፡ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለማችን መጥፎ ሪከረድ አስመዝግባለች፡፡በአሁን ወቅት ከ17 የማያንሱ ጋዜጠኞች በእስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡21 የሚሆኑ ጋዜጠኖች በስደት መከራን እየተቀበሉ ነው፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ተጠራርጎ ቃሊቲ የሚገባበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡በውጪ አገር የሚገኙ የተለያዩ ሚዲያዎችም ቢሆኑ፣በአገር ውስጥ ተደማጭ እና ተነባቢ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ አፈና እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡
ስለዚህም ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ተፈካካሪ ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻ ቅስቀሳ የሚያደርጉት በይትኛው ነፃ ጋዜጣ እና መፅሔት ነው ? ህሊናውን እና ሙያውን ብቻ መሠረት አድርጎ የሚሰራ ጋዜጠኛ ምን ያህል አለ ? እርግጥ ይህ ፁሑፍ የቀረበበት ሚዲያ ጋዜጣ በቀጣይ የሌሎች ጋዜጣ እና ጋዜጠኞች እጣ ፈንታ እንደማይደረሰው በምንም እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡በምንም!!
እናም ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ጋዜጠኛ እና የእትመት ውጤት ሣይኖር መርጫ እንዴት ይታሰባል፡፡አገራችን በጋዜጠኛ ድርቅ እንድትመታ ገዥው መንግሰት ሆነ ብሎ ያደረገው መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ይህ በሆነበት ሁኔታ ኢሕአዴግ ለመርጫ እራሱን እያዘጋጀ ነው ማለት በራስ ላይ እንደመተኮስ ይቆጠራል ፡፡

ከላይ በመጠኑ የዚህ ፁሑፍ አቅራቢ ለመዳሰስ የሞከራቸው እና ሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ኢሕአዴግ በጭራሽ እራሱን ነፃ ለሆነ የምርጫ ውድድር እያዘጋጀ አይደለም !የፖለቲካ ሊቃውንት እንደሚያስገነዝቡት እና ዓለም አቀፍ ነባሪዊ ሁኔታ የሚያመላክተው ለምርጫ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ ፤በእኩል ደረጃ ባይወንም እንኳን በአንፃራዊነት የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ነፃነት እና እኩል ተሣትፎ ሊኖር ይገባል፣ፓርቲዎችን ሊያወዳደሩ የሚችል ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ምርጫ ቦርድ እና ጉዳዩን ሙያዊ ስነምግባር መሠረት በማድረግ ለህዝብ መረጃ የሚያደርስ ነፃ ሚዲያ ያስፈልጋል፡፡እነዚህ መሰል ዋንኛ መስፈርቶች ባልተሟሉበት በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በመጪው ግንቦት ወር ነፃ ምርጫ ማካሄድ የሚታሰብ አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

ጎንደር ፦ የህዝቦችን መብቶች የማይወክሉ የወያኔ ሰንደቅ አላማዎች ከሚውለበለቡበት ወረዱ ::
#Ethiopia #Gonder #Kimant #ESAT #MinilikSalsawi #Freedom

– በሰሜን ጎንደር ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ:: ESAT
– በሰሜን ጎንደር ዞን 130 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው አልተገኙም።
– በአድማው የመንግስት መስሪያ ቤቶች ይካተታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቅማንት ተወላጆች ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ በተጠራ የስራ ማቆም አድማ በዞኑ የሚገኙ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ የተዘጉ ሲሆን፣ መንግስት እስከ መስከረም 30 መልስ የማይሰጥ ከሆነ፣ ተቃውሞው ግብር ባለመክፈል እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በርካታ አስተባባሪዎች ተይዘው የታሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው እስከ መስከረም መጨረሻ መልስ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

እስካሁን ከ130 ሺ ያላናሱ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው የቀሩ ሲሆን፣ ሌሎች ትምህርት ቤቶችና የመንግስት መስሪያ ቤቶችም በአድማው ይቀጥላሉተብሎ ይጠበቃል። በተዘጉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚውለበለቡ ሰንደቃላማዎች እንዲወርዱ ተደርጓል። ሰንደቃላማዎች እንዲወርዱ የተደረገበት ምክንያት የህዝቦችን መብቶች የሚወክሉ አይደሉም በሚል ነው።

Image

ትናንትና ምሽት አካባቢ ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍኖ የተወሰደው የዞኑ አስተባባሪ እስከአሁን ሰዓት ድረስ ያለበትን ቦታ ማወቅ አልተቻለም፡፡ ትናንት ማምሻውን በሲቪል እና መሳሪያ በታጠቁ የገዢው ፓርቲ ሀይሎች ቤቱ ተበርብሮ ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍኖ መወሰዱን በዞኑ ያሉ የፓርቲው አካላት አረጋግጠዋል፡፡

ከሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ዞን አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ በተጨማሪም ወደ ስድስት(6) የሚደርሱ የአንድነት እና መኢአድ ፓርቲ አባላትም ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍነው መወሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡

በሌላ በኩል በጎንደር ባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ክትትልና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነ የዞኑ ተጠሪዎች አመልክተዋል፡፡

ጋዜጠኛ አንተነህ መርዕድ

በዙህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ በሁለት ምክንያቶች ከራሴ ጋር ብዙ ታግያለሁ። መጀመርያ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አይደለም ለራሳቸው፤ ለሌላም የሚተርፍ አንደበት አላቸውና ራሳቸው መልስ  ይስጡ በማለት ሲሆን ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ ትልልቅ አገራዊ ጉዳይ እያለ በዚህ ጠባብ ነገር መጠመድ ለማን ይበጃል በሚል ነበር።በሁለቱም ትክክል አልነበርሁም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመሰረቱት ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ዛሬ ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አደረገ፡፡ ‹‹ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የፕሮግራም መርሃ ግብር ለመክፈት ወስኖ የመጀመሪያው ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ […]

የአንድነት ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች መዋቅሩን የዘረጋ ድርጅት ነው። ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ፣ ፓርቲው እስከታች በመዝለቅ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድርጅታዊ መዋቅሩን ዘርግቶ የሚንቀሳቀስ ነው። – የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተቋቋመው በአዲስ አበባ ከሚገኙ 23 የምርጫ ወረዳዎች በተወከሉ ስድስት ስድስት አባላት ነው። በአጠቃላይ 138 አባላት አሉት። – በ23ቱም የምርጫ ወረዳዎች ፣ […]

“በሽብር” ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የፓርቲ አመራሮች ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት፣ ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ም/አፈ ጉባኤ፣ መምህርና የአረና ፓርቲ የአመራር አባል አብርሃ ደስታ እንዲሁም የአ/አ ዩኒቨርስቲ የማስትሬት ተማሪ ዘላለም እና ተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች 5 ግለሰቦች ነገ ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ልደታ በሚገኘው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ […]

የምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው አቶ ደረጀ ክበበው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ አቶ ደረጀ በጠና ታሞ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ጠዋት በአዳማ ከተማ ቀበሌ 07 በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ያረፈ ሲሆን የቀብር ስነስርዓቱ በትላንትናው ዕለት ከቀኑ በ 7፡00 ሰዓት አዳማ በሚገኘው መድኃኒአለም ቤ/ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ ፓርቲው በአቶ ደረጀ ክበበው ሞት […]

– የመከላከያ እና ፖሊስ ሰራዊቱ ላይ አለመተማመኑ እየጨመረ መጥቷል። – የደህንነት አባላቱ መረጃን በግል ጥቅም በመለወጥ እየሰሩ ነው የሚል ግምገማ ቀርቦባቸው ተንጠዋል። – የሃገሪቱን ጉዳይ በተመለከተ ለበታች “ተከታይ ” ባለስልጣናት መረጃ መስጠት ቆሟል። – የሕወሓት ታጣቂዎች ከምቾት ኑሮ ተነስተው ለመሸሽ እንጂ ታጥቀው ደም ለመፋሰስ ዝግጁ አይደሉም ። በኢትዮጵያ ውስጥ መጭው ጊዜ በህዝቡ ዝምታ ተከትሎ በስርአቱ […]

በደቡብ ጎንደር የፎገራ ወረዳ የአንድነት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አለበል ዘለቀ በዛሬው ዕለት ከሚሰሩበት የእርሻ ቦታቸው ላይ በፌዴራል በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን እንዲሁም በአማራ ክልል ምዕ/ጎጃም ደጋ ዳሞት ወረዳ የወረዳው አንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን አበበ በተጨማሪም በወረዳው ያሉ 3 የአንድነት አባላት ከቤታቸው በፌዴራል ፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸው ከስፍራው ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የደረሰው ዜና […]

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ቅርብ ወራት ያሰራቸውን የኢንተርኔት አምደኞችና ጋዜጠኞች፤ ጉዳይ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት የወሰዳቸው እርምጃዎች ተከትሎ የተለያዩ ትችቶች ለመገናኛ ብዙኃን መብት የቆሙ ወገኖችን ጨምሮ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየተሰሙ ነው።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በቅርቡ ለአገሪቱ ፓርላማ ባሰሙት ንግግራቸው የግል ጋዜጦችንና ሞያውን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ፤ ”የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችንና ጋዜጠኝነትን አስመልክቶ እያራመደ ያለው ፖሊሲ ለአገሪቱ የንግግርና የፕሬስ ነጻነት አይበጅም፤” ሲል ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ ተችቷል።

በሰሞንኛው የመንግስቱ እርምጃዎችና በንግግር ነጻነት መብት ላይ አንድምታ ባላቸው የተለያዩ የአገሪቱ ሕጎች ዙሪያ ከኅግ ባለሞያ ጋር የተካሄዱ ተከታታይ ቃለ ምልልሶች ከዚህ…

ውጥረት በተመላበት ኹኔታ ተጀምሮ ተጋግሎ የሰነበተውና በመጨረሻም ወደ መግባባትና አንድነት የመጣው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ÷ ለኹለት ሱባዔ ያኽል ሲያካሒድ የቆየውን የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ነገ፣ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከቀትር በፊት ያጠናቅቃል፡፡ በስብሰባው ማጠናቀቂያ÷ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰንበቻውን ስለተነጋገረባቸው ጉዳዮች፣ ስላሳለፋቸው ውሳኔዎችና ስለወሰዳቸው አቋሞች የምልአተ ጉባኤው ርእሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በንባብ የሚያሰሙት ጋዜጣዊ መግለጫ …

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ የተላኩ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ደህንነቶች፣ ወደ ፓርቲው መሪዎች ቤት ከንጋቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ በመሄድ፣ መኖሪያ ቤቶቻቸውን ሰብረው በመግባትና አንዳንዶችንም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደዋቸዋል። የመተማ ወረዳ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በላይነህ ሲሳይ፣ የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ አንጋው ተገኝ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ …

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ትብብር የመሰረቱ 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አድርገዋል። ‹‹ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የዝግጅት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል። ‹‹ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ …

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅማንት ተወላጆች ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ በተጠራ የስራ ማቆም አድማ በዞኑ የሚገኙ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ የተዘጉ ሲሆን፣ መንግስት እስከ መስከረም 30 መልስ የማይሰጥ ከሆነ፣ ተቃውሞው ግብር ባለመክፈል እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በርካታ አስተባባሪዎች ተይዘው የታሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው እስከ መስከረም …

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተይዘው በነበሩት ተማሪዎች ላይ ከ1 እስከ 5 በሚደርስ እስር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል። በሌላ ዜና ደግሞ በአዳማ ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ባስነሱት ተቃውሞ ፖሊሶች ተጎዱ። የአከባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት  ከከተማ አስተዳደሩ ቤት አፍራሽ ግብረ ሀይል  ህገወጥ የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ ወደ ስፍራው …

#FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #Ethiopia 
ዛሬ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ ይሰየማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የጦማርያኑ እና የጋዜጠኞቹ ችሎት ከወትሮው በተለየ ጥብቅ ጥበቃ ለአጭር ደቂቃዎች ተከናውኗል፡፡ 

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከተከሰሱት 10 ተከሳሾች ( አንድ በሌለችበት) ዘጠኙ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ሲሆን በእለቱ ፍርድ ቤቱ የክሱ ላይ የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ሀግን መልስ አይቶ ብይን ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ 

ችሎቱ ከተለመደው አዳራሽ ይከናወናል በሚል እሳቤ ወዳጅና ቤተሰቦች ቢገኙም መጀመሪያ በደፈናው ወደ ችሎት አዳራሽ መግባትን በመከልከል በማስከተል ደግሞ የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ችሎት ውስጥ አንዲገቡ ተደርጎ ነበር፡፡ ከአፍታ ቆይታ በኋላ ግን ችሎቱ ውስጥ ያለው የድምጽ ማጎያ ስለማይሰራ ይበልጥ አነስተኛ ወደሆነ ክፍል ችሎቱ አንዲዘዋወር ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የተከሳሽ ወዳጅና ቤተሰቡ ባልታደሙት አጭር ችሎት ሁለት የግራ እና የቀኝ ዳኞች አዲስ የተለመወጡ በመሆናቸውና ኬዙን ስላልመረመሩት ለህዳር ሶስት ( ኖቬምበር 12) ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት የዛሬው ቀጠሮ በአጭሩ ተዘግቷል፡፡ 

እስር ላይ የሚገኙት ሴት ተከሳሾች ጉብኝት መብትን አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቢሰየምም ለውጥ አለመኖሩን በመጥቀስ አቤቱታቸው ያሰሙ ሲሆን የማረሚያ ቤት ሃላፌው በሚቀጥለው ቀጠሮ መጥተው አንዲያስረዱ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ 

ዛሬ ከፍተኛ ግርግር እና የቦታ እጥረት አንዲሁም ወላጆች መንገላታት የታየ ሲሆን ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ እነደቀድሞው ችሎት ነጭ ልብስ በመልበስ በመልካም ሁኔታ ላይ አንደሚገኙ ታይቷል፡፡ 

በተያዘ ዜና የጦማርያኑን የዋስትና ጥያቄ አስመልክቶ ጠበቃቸው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ የተባለ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ነገ ጠዋት በሚሰየመው ችሎት ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ( አጋርነታችሁን የምታሳዩ የዞን 9 ነዋሪያን ነገ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎት በመገኘት አጋርነታችሁን እነድታሳዩ ጥሪ እናቀርባለን)

የፕሮግራም መግለጫ

ወደ 98 ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ አማርኛ ብሔራዊ የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በቅርብ የተካሄዱ የቅኝት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዋቂ በሚባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ካለው ሕዝቧ አንድ አምስተኛ የሚሆነው የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያን (የቪኦኤን) ሥርጭቶች ያዳምጣል፡፡ ይህ ቁጥር ቪኦኤ በዓለም ዙሪያ ከሚያሠራጭባቸው ቋንቋዎች ሁሉ ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ከሚባሉት የአድማጭ ብዛት አንዱ ነው፡፡

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ ከሚያሠራጨው የ60 ደቂቃ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች በተጨማሪ ከሰኞ እስከ ዐርብ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ 1 ሰዓት ተኩል በአማርኛ የሚተላለፍ የግማሽ ሰዓት ሥርጭት በ1431 መካከለኛ ሞገድ ላይ አለው፡፡

የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራሞች በተጨማሪም በናይል ሳት ይተላለፋሉ፡፡

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ለሁሉም የዕድሜ ክልሎች የታሰቡት የሣምንቱ የመጨረሻ ቀናት ዝግጅቶቻችን የሃሣብ ማንሸራሸሪያ መድረኮችንና የመዝናኛ ቅንብሮችን ያካተቱ ናቸው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በአሜሪካ መንግሥት በጀት የሚንቀሣቀሱ ትክክለኛና ተዓማኒነት ያላቸውን ዜናዎች እንዲሁም ሰፋፊ ፕሮግራሞችን እያደራጀ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በሞባይል መሣሪያዎችና በኢንተርኔት በ45 የዓለማችን ቋንቋዎች የሚያሠራጭ ዋና መቀመጫው ዋሺንግተን ዲሲ የሆነ የዜና ተቋም ነው፡፡

ቪኦኤ በአማርኛ በሣምንት የዘጠኝ ሰዓት ተኩል ሥርጭት ያስተላልፋል፡፡

በሶማልያ ፕሬዝደንት ሃሰን ሼኪ ሞሃመድ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ አብዱዊሊ ሺካህ አህመድ መካከል የተፈጠረዉ የስልጣን ሽኩቻ ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ በጦርነት ስትታመስ የቆየችዉን ሀገር ዳግም እንዳያንኮታኩታት ማስጋቱን የአዉሮጳ ሕብረት እና የተመድ አሳሰቡ።

በጣሊያኒኛዉ«ማሬ ኖስትሩም» ወይም ባህራችን በሚል መጠሪያው ለአንድ ዓመት ያህል ሜዲትራኒያን ባህል ላይ ችግር የሚገጥማቸውን በተለይም ስደተኞችን ባህር ሰምጠው እንዳይቀሩ የማዳን ተግባር ሲያከናዉን የነበረው የኢጣልያ ባህር ኃይል ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በትሪቶን ተተክቷል።