የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን ጎንደር የዞን ሰብሰቢ አቶ አግባው ሰጠኝ በገዢው ፓርቲ ሀይሎች ታፈነ

ትናንትና ምሽት አካባቢ ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍኖ የተወሰደው የዞኑ አስተባባሪ እስከአሁን ሰዓት ድረስ ያለበትን ቦታ ማወቅ አልተቻለም፡፡ ትናንት ማምሻውን በሲቪል እና መሳሪያ በታጠቁ የገዢው ፓርቲ ሀይሎች ቤቱ ተበርብሮ ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍኖ መወሰዱን በዞኑ ያሉ የፓርቲው አካላት አረጋግጠዋል፡፡
ከሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ዞን አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ በተጨማሪም ወደ ስድስት(6) የሚደርሱ የአንድነት እና መኢአድ ፓርቲ አባላትም ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍነው መወሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡
በሌላ በኩል በጎንደር ባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ክትትልና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነ የዞኑ ተጠሪዎች አመልክተዋል፡፡