ዛሬ አቅስታ ከተማ የድንጋይ መከላከያ በለበሱና አስለቃሽ ጭስ በያዙ ፌደራል ፖሊሶች ተከባ በርካታ ወጣቶችን ሲያፍሱ ዉለዋል።

መንግስት በደ/ወሎ ለጋንቦ ወረዳ ያስነሳዉ እረብሻ እሱ እንደለለበትናዩኒቨርስቲዉ በጭራሽ እንዳልተነሳ ለማስተባበል እየሞከረና ጉዳዉን ከሙስሊሞች ጋራ ለማያያዝ ከዚህ ቀደም ጊባ ከተማ ላይ በተደረገዉ የሰደቃ ፕሮግራምና መንግስት ከፍተኛ ጭፍጨፋ ያደረገበትን ድርጊት በማንሳትበየመድረኩ እየለፈፈናደፋቀና እያለና የክልሉ ርእሰመስተዳደር አቶ ገዱ ለምክር ቤት አባሉናአቶ ደመቀ በስልክ እሁድለት ከ10፡00 በሆላ ጊባላይ በተደረገዉ ስብሰባ ተናግረዋል።

ይሁንና በሁኔታዉ ጎረቤት ወረዳዎች ሳይቀሩ ሁኔታዉን ለማስቀየር ትልቅ የቤት ስራ የተሰጣቸዉ ሲሆን ከፌስቡክ ጀምረዉ ወጣቱን እንድከታተሉ አቶ ገዱ ለምክር ቤቱ አባላት አስተላልፈዋል።አንዳንድ ጎረቤት ወረዳዎችም እዉነታዉን ወደፌት እንደሚደርሱበት የተናገሩ ሲሆንናያኔ ኢሃድግ እንደለለ የሚናገሩበትናከህዝብ ጋራ የሚሰለፉበት ጊዜ እንደሚሆን ተናግረዋል።ትናት ጀምሮ በለጋንቦ ፖሊሶች ጠቆሚነት ብዙ ወጣቶች፣ደላላዎች፣ወያላዎችናወደፊት ሁኔታዉን ያቀጣጥላሉ ተብለዉ የሚጠረጠሩ እየታሰሩ መሆኑ ይታወቃል።

ምንም እንኮን የለጋንቦ ህዝብ የሚያስተዳድረዉ አስተዳደር የሳይንት ተወላጅ ቢሆንም የወረዳዋን ህዝብ ለሳማ ቀቃይ ዩኒቨርስቲ ምኑነዉ፣ደህና መኖሪያ ቤት የሌላችሁ ብሎ በመሳደቡ የተቆጣዉ ህዝብ አሁንም ቢሆን በነሱ ላይ ታልፎ ግንባታ እንደማይ ፈፀም እየተነጋገረ ነዉ።ዛሬ አቅስታ ከተማ የድንጋይ መከላከያ በለበሱናአስለቃሽ ጭስ በያዙ ፌደራል ፖሊሶች ተከባናቤት ለቤት እየዞሩ በርካታ ወጣቶችን ሲያፍሱ ዉለዋል።

አብዛሀኛዉ ወጣት ከተማዋን እየለቀቁ ለግዜዉ ወደገጠር መግባታቸዉ ታዉቆል።ይሁንና ቤትለቤት ፌደራል እየመሩ የሚጠቁሙት የከተማዋ ፖሊሶች በመጀመሪዉ ቀን ህዝብን የተሳደበ አስተዳደር ሲያጅቡ የተደበደቡናመሳሪያቸዉን የተቀሙ ቢሆኑም ለድጋሜ ጥቃት የተጋለጡ መሆናቸዉይታወቃል።

ድምፃችን ይሰማ ከማሻ-መቅደላ