ከድርቁ ይልቅ መግለጫው ያደርቃል!

(የትነበርክ ታደለ) ትናንት ምሽት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞች ጋር ያደረጉትን የጥያቄና መልስ ቆይታ የተከታተለ ሰው እንደ ተለመደው የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ብዥ እንደሚልበት የታወቀ ነው። ጋዜጠኞቹ ራሳቸውን እየጨመቁና እየተሽቆጠቆጡ ለሚያቀብሏቸው ጥያቄዎች ሚንስትሩ ለራሳቸው ብቻ በሚመች መልክ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ብቻ በሚያሳምን መልኩ ምላሽ ሰጥተው ዞር ብለዋል። ይደንቃል! አሁን አለም በሀገራችን ውስጥ የተከሰተውን ድርቅና ረሀብ በደምብ አብላልቶ እያወራው […]