ሰላሳ ሶስት መኮንኖች ከየታሰሩበት እዝ ተግዘው አለም በቃኝ ተወረወሩ:: (ስም ዝርዝር ተያይዟል::)
ሰላሳ ሶስት መኮንኖች ከየታሰሩበት እዝ ተግዘው አለም በቃኝ ተወረወሩ:: (ስም ዝርዝር ተያይዟል::) ………
#Ethiopia #EPRDF #EthiopianArmy #MinilikSalsawi #Unity #Change ….
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) …. የወያኔ ጉጅሌ አገዛዝ 7 መቶአለቆች 5 ሻምበሎች 8 ሻለቆች 13 ኮሎኔሎች በድምሩ 33 የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከሰሜን እዝ እና ከደቡብ ምስራቅ እዝ ታስረው የነበሩበት መኮንኖች ተግዘው አዲስ አበባ ቃሊቲ አለም በቃኝ ካለፍርድ መወርወራቸው በወታደራዊ ደህንነት መምሪያ ከፍተኛ መኮንን የሆኑ እና እስረኞቹ ተግዘው ወደ አለም በቃኝ ሲወርዱ የተመለከቱ የአይን እማኝ ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል:: የአይን እማኙ እንዳሉት በምድር ጦር የደህንነት ክፍል እና በወህኒ ቤቱ መካከል ከማንም እስረኛ ጋር እንዳይገኛኙ ተደርጎ እንዲታሰሩ በጥብቅ ምስጢር የተረካከቡት እስረኛ ወታደሮች በየእዙ ውስጥ በመንግስት ላይ ታሴራላቹ ወታደሩን ታነሳሳላቹ በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን እንዲነግስ አድርጋችኋል ሕገ መንግስታዊ መብቶች የሚሉ ጥያቄዎችን ደጋግማቹ ታነሳላቹ ከጠላቶቻችን ጋር አብራቹሃል በሚል ተሰብስበው የታሰሩ እና በእዞቹ አከባቢ ያለውን የአከባቢ ሰላም መደፍረስ እና የወታደሮች ጉርምርምታ በመፍራት ይዘዋቸው ወደ አዲስ አበባ ካለፍርድ አለም በቃኝ እንዳስገቧቸው ታውቋል::
1ኛ ኮሎኔል ተፈራው ደሳለኝ
2ኛ ኮሎኔል ጥግነህ አሳፍረው
3ኛ ኮሎኔል ዳርሰማ ፈርዶሴ
4ኛ ኮሎኔል ጊሚራው ወዳጆ
5ኛ ኮሎኔል መሃመድ እንድሪስ አሚር
6ኛ ሌ/ኮሎኔል ግደይ ሰመረ (ግማሽ ኤርትራዊ)
7ኛ ሌ/ኮሎኔል ዘይኑ አቦይውቅሮ
8ኛ ሌ/ኮሎኔል ጅባት ሞጋ
9ኛ ሌ/ኮሎኔል ካሳዬ ሃብታሙ
10ኛ ሌ/ኮሎኔል ሳላይህ ዋለ
11ኛ ሌ/ኮሎኔል ደርሶ ተስፋይ
12ኛ ሌ/ኮሎኔል ገሩ አዘዘኝ
13ኛ ሌ/ኮሎኔል ካህሳይ ንጉሰይ
ሻለቆች
1ኛ ሻለቃ ቃሉ ተሰማ
2ኛ ሻለቃ ዋቅጅራ ዱላ
3ኛ ሻለቃ ማንያዘዋል ደብሩ
4ኛ ሻለቃ ኡስማን ጡሃ ኽሊል(ፌስቡክ በሌላ ስም ሲጠቀም የተያዘ)
5ኛ ሻለቃ አለማው አበበ
6ኛ ሻለቃ ገብሬሉ ለጥአድርጋቸው
7ኛ ሻለቃ ካሳሁን በድሉ
8ኛ ሻለቃ የማነ ገረዝጊ
ሻምበሎች
1ኛ ሻምበል ሰማው ድንግሉ
2ኛ ሻምበል ተስፋዬ ቤተማርያም(ባቡሩ)
3ኛ ሻምበል ሁሴን አባድር
4ኛ ሻምበል ጉኡሽ ኪዳኔ
5ኛ ሻምበል ሓዲስ አረጋይ
መቶ አለቆች
1ኛ መቶ አለቃ ከፍያለው ገናነው
2ኛ መቶ አለቃ ጃኮብ ኦጁሉ ቶም
3ኛ መቶ አለቃ ሲሳይ አማረ
4ኛ መቶ አለቃ ድልሰፋ ይርጋ
5ኛ መቶ አለቃ ስሜነህ ታምሩ
6ኛ መቶ አለቃ ጌታነህ ደበላ
7ኛ መቶ አለቃ ገመቹ ዳባ
የተባሉ ወታደራዊ መኮንኖች በወያኔ መንግስት ላይ አሲርዋል በሰራዊቱ መካከል አለመተማመን ፈጥረዋል ወዘተረፈ በሚል ሰበብ በየእዙ ምድር ቤት በሚገኙ እስር ቤቶች ሲሰቃዩ ከርመው ካለምንም ፍርድ እና ሕግ ፊት ሳይቀርቡ በሰሜን እዝ እና በደቡብ ምስራቅ እዝ አከባቢ ያለው የሰላም መደፍረስ እንዲሁም በወታደሩ አከባቢ የሚታየውን ማጉረምረም ተከትሎ እስረኞቹ ወደ አለም በቃኝ መምጣታቸው ታውቋል::
እንደሚታወቀው በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ ሽኩቻ እና አለመተማመን ሲኖር የወያኔ ጉጀሌ አገዛዝም ወታደሮቹ ጦርነት ቢከፈትብኝ ከጠላት ጋር ያብሩብኛል በሚል ከፍተኛ ፍራቻ ስላደረበት በጦሩ ውስጥ አስጊ የተባሉ መኮንኖችን እየለቀመ ማሰር ከጀመረ መቆየቱ ይታወሳል:;ይህም የጅምላ እስር/ግዞት የዚሁ የወያኔ ስጋት አንዱ አካል መሆኑን እማኙ ተናግረዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ
አሁን 33 ያዝኩ ቢል ወያኔ ሥነልቦናው በመነካቱ ሊያደርግ ወሥኗል ከዚህ ባሻገር ጠባሣው ግን 33ሺህ ወታደርን ይወክላል ውጤቱን አብረን እናየወለን።
አሁንም ብርቅዬው ወታደር ባንዳነት መንፈሥ የሌለህ አፈሙዙን ጠምዝ ንቃ ወያኔ ህዝቡን አይወክልም
ወያኔ ወይም ሞት ቢልህ አትቀበለው ወንድሞችህ ነን ጠላት አልሸባብ ነው እኛን አይወክልም ወያኔ ለቅድመ ጥንቃቄ ላሣያችሁን እገዛ አድናቆታችን ይድረሥህ ወያኔ በከንቱ የወንድምህን ደም እንድትጠጣ ሬት ቢያዘጋጅም ራሡን አጠጣው።
ድል ለግ7 ጅግኖች
ኢትዮጵያን ያረከሷት:-ዝሙት,ስካር,ዘረኝነት ወዘተ ናቸው::በአዲሱ አመት አዲስ ማንነት እንያዝ:ያለፈው አልፏል
እነኚሁ ጀነራሎች የሚፈፅሙት ትምክህተኝነት በአሁን ሠአት ህብረተሠቡ መሀል በመሸሸግ ህዝቡን ለሥጋት ዳርገውታል ለዚህም ማሥረጃ በን/ላፍቶ ወረዳ3 ኢራን ኤምባሢ ጎን የሚገኝ ሢሆን ቦታው ለጎርፍ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ዜጎች ሢሆን በጉልበት ነጥቀዋል የኤንባሢውና ህብረተሠቡ ቦታው በኦራል እየተከበበ ጭንቅ ውሥጥ ይገኛሉ ይህን መሠል የተንኮል ሤራ ህዝቡ እንዲታዘብና ለሚደርሠው አደጋም ተጠያቂው ወያኔ መሆኑን ይሠመርበት።
ዜና ቢስ
Beyeqenu taseru tedebedebu new, meshenef new bezihu menged meqetelu. Andem teketay atagegnu, sew simerew ynesal aymselachuh, aylemdegnm blo endene brtukan, endene qnjitoch ketglu yweta. Enien yaye yqeta ylal, end ehapa debzaw ytefal.Kewetaderu, ketemariw, kenegadiew, keteqawamiw, kesra atu, geberie sayqer keyaqtachaw woyanie eyeleqem asrual, mereja agentual, ahunm endelbu eyagegne new, bachru teqawamiwechn sergo gebtual, enqsqasiyachuhn teqotatrotal, fresuna adis aquaqumu. Bekentu sew atastequ, beqa techemari masteqiya hunachuhual. Internet wanaw meteqiya hunual, sntun lewoyanie agalto settoal. Liela zedie meteqem ybejal.
ይህ ነው ጀግንነት እንዴ ድንቄም ዲሞክራሢ ሞቶም የሞት መንፈሥ የሚመራቸው ሙታን አጋንንት ወያኔዎች የልማት ጭምብል ለብሠው የሚርመሠመሡ ራሣቸው ፈንጂ ቀብረው ተቃዋሚ ፈፀመ የሚሉ ባንዳዎች ብርቅዬ ህዝቡን አይወክሉም ቢያለሙም ልማቱ የህዝቡ ነው ይህን አልሚ ህዝብ ደግሞ በሙሥና እየጠለፈ ሆን ብሎ የሢምንቶና ብረት ላይ ጫና ፈጥሮ የህዝቡን ልማት አግቶታል የመሬት ግዥ ሊዝ ከፍ አርጎል ለመቶ አመት ለውጭ ባለሀብቶች ሀገሩን ሽጧል በገዛ መሬቱ ገበሬውን ነፍጠኛ ሆነ መብራት ይኸው ድፍን 10 አመት መሥተካከል አልቻለም በጭለማ ቶርች እያረገ ነው ……ሥንቱ ይዘክዘክለት።
ብቻ መልካም ቀንን እ/ር ያምጣ የፍትህ እንባ አባይን ትሙላ!!!
ሞት ለወያኔ ድል ለኢትዬጵያ ልጆች!!!
ክቡር ጀግና ወታደር ሆይ ያሥተላለፍንልህ መልእክት በሆድህ ይዘህ ባንዳውን ወያኔ አብረን እንገንድሠው የደርግ ሠራዊትን የጣልከውም አንተ ነህ ሳትሣቀቅ መረጃውን አሥተላልፍ ደምህን ለወያኔ ሤጣን አትገብር በአንተ ወኔና ደም ወያኔ ዛሬ ከፍተኛ ዶላር እያግበሠበሠ ነው ሞተህም ለቤተሠህ እንኳ አንድ ጣት ያጣ የማሽን ሠራተኛ የማያገኘውን ክፍያ ካሣ ደብቀውህ ሢከፍሉ አይተናል ይህ ነው የሠላም አሥከባሪ ተልኮ ድራማ ንቃ ይችህ አገር ጠላቷ አንድ ነው ረሀብና ወያኔ ሌላው የጥጋብ ምልክቶች ናቸው በቀለም ይመለሣሉ ክቡር ሆይ የምንፈልገውን መንግሥት ለመምረጥ ተቸገርን ተሠደድን ተገደልን ይህ ሉጎሙን አኝኮ የጨረሠው የወያኔ ጥቁር ፈረሥ ግልቢያ የገደል አፉፍ ደርሥሷል ሥንዴውን ማዶ ሆነን እናሣየው ኦሮማይ