Category: Amharic News
«የመሰንቆው ሊቅ» ጌታመሳይ አበበ – ዶይቸ ቬለ
«የሽምብራው ጥርጥር የዛፎቹ ፍሬ የትም የትም ዞሬ ትዝ አለኝ ሀገሬ» የዛሬ ሳምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩን «የመሰንቆው ሊቅ» ጌታመሳይ አበበ ዘመን ተሻጋሪ ከሆኑ የባህል ሙዚቃ ጨዋታዎች በግንባር ቀደምትነቱ የሚታወቀዉ ነዉ። ሁለ ገቡ ከያኒ ጌታመሳይ አበበ «የጥበብ ገበሪም » በመባል ይታወቃሉ። …
የኢትዮጵያ ፌደራል አቃቢ ህግ በአቶ በቀለ ገርባ እና በ22 ሰዎች ላይ የሽብር ወንጀል ፍርድ መስርቶባቸዋል – VOA
ከፍተኛው ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮም ሰጥቷል
በዘውዲቱ ሆስፒታል የእንቅርት ታካሚዋ ለሃሞት ጠጠር ህክምና ሆዷ ተከፈተ

– የህክምና ስህተቱን የፈፀሙት ሃኪም ከሥራ ተባረዋል
– “የሃሞት ጠጠሩ በነፃ ስለወጣልሽ ዕድለኛ ነሽ” ሲሉ ዋሽተዋታል
በዘውዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በተፈፀመ የህክምና ስህተት ሣቢያ እንቅርት ለማስወጣት የሄደችው ታካሚ በስመ ሞክሼ በተፈጠረ ስህተት ለሃሞት ጠጠር ህክምና ሆዷ ተከፈተ። ታካሚዋ ከሁለት ዓመታት ወረፋ ጥበቃ በኋላ ተራዋ ደርሶ በአንገቷ ላይ የወጣውን እንቅርት ለማስወጣት ነበር ወደ ሆስፒታሉ የሄደችው፡፡
ሠላም ደሞዜ የተባለችው ታካሚ በአንገቷ ላይ የወጣውን እንቅርት ለማስወጣት አስፈላጊውን ምርመራ አድርጋ በሆስፒታሉ አልጋ ትይዛለች። በሌላ በኩል ሰላም ኪሮስ የተባለች ታካሚ ደግሞ ለሃሞት ከረጢት ጠጠር ህክምና ወረፋ ጠብቃ ቀጠሮዋ በመድረሱ ነበር ወደ ሆስፒታሉ ያመራችው፡፡ ወጣቷ በቀዶ ህክምና ከህመሟ ለመፈወስ አስፈላጊውን ምርመራ አከናውና በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ እንድተኛ ይደረጋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ሁለቱም ህሙማን የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው ቀጠሮ ተይዞላቸው ሲጠባበቁ ከቆዩ በኋላ ለእንቅርት ህክምና ወደ ሆስፒታሉ ያመራችው ሰላም ደሞዜ በቅድሚያ ወደ ቀዶ ህክምናው ክፍል ትገባለች። የእንቅርት ታካሚዋ በቀዶ ህክምናው ክፍል ከገባች በኋላ ለሃሞት ከረጢት ጠጠር ህክምና ሆዷ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ በታካሚዋ ሃሞት ውስጥ ለቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር አለመኖሩን ያስተዋሉት የቀዶ ህክምና ባለሙያው፤ ሆዷን መልሰው በመዝጋት የእንቅርት ማውጣት ህክምናውን ያደርጉላታል፡፡
ጉዳዩ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረባቸው ሃኪሙ፤ በወቅቱ ስለተፈፀመው ሁኔታ አንዳችም ነገር ሳይናገሩ የቀዶ ህክምና ክፍሉን ለቀው ይወጣሉ። ከስፍራው ያገኘናቸው ምንጮች እንደገለፁልን፤ የሀኪሙ ረዳቶችና በስፍራው የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ችግሩን ለመሸፈንና የተፈጠረውን ስህተት ለመደበቅ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ ታማሚዋ ለእንቅርት ቀዶ ህክምና ወደ ሆስፒታሉ ቢመጡም የሃሞት ከረጢት ጠጠር ችግር ስለተገኘባቸው ህክምናው በነፃ እንደተደረገላቸውና በዚህም ዕድለኛ እንደሆኑ በመንገር ቤተሰቦቻቸውን ለማሳመን ጥረት አድርገዋል ተብሏል፡፡ ሁኔታው ያልተዋጠላቸው የታማሚዋ ቤተሰቦች ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የህመም ምልክት ባልታየበት፣ ምርመራና ቅድመ ህክምና ባልተደረገበት ሁኔታ በድንገት ለሃሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና የሚያበቃ ችግር ሊፈጠር አይችልም በሚል ከሆስፒታሉ አስተዳደርና ከህክምና ባለሙያዎቹ ጋር ውዝግብ ይፈጥራሉ፡፡ ጉዳዩ የሆስፒታሉ አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ደርሶም እንዲጣራ ከተደረገ በኋላ ትልቅ የህክምና ስህተት መፈጠሩ ታምኖበት፣ የህክምና ባለሙያዎቹና አስተዳደሩ ቤተሰቦቿን ይቅርታ በመጠየቅ ለታካሚዋ የቅርብ የህክምና ክትትል እንዲደረግላት የተወሰነ ሲሆን የቀዶ ህክምና ባለሙያውና ረዳቶቹ ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የዘውዲቱ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ተረፈ አሰፋ፤ የህክምና ስህተቱ መፈፀሙን አምነው ስህተቱ የተፈፀመው በወቅቱ የቀዶ ህክምናውን ያደረጉት ሃኪምና ረዳቶቻቸው ታካሚዋ በትክክል የመጣችው ምን ዓይነት ህክምና ልትፈጽም መሆኑንና ሌሎች ሁኔታዎችን በአግባቡ ሳያረጋግጡ ህክምናውን በመጀመራቸው ነው ብለዋል፡፡
አንድ ሰው የቀዶ ህክምና ከማድረጉ በፊት በአግባቡ ሊደረግ የሚገባው “ሰርጂካል ሴፍቲ ቼክ ሊስት” መኖሩን የጠቆሙት ዶ/ር ተረፈ፤ በዚህች ወጣት ታካሚ ላይ ይህ ጥንቃቄ ሳይደረግ በመቅረቱ ስህተቱ መከሰቱን አስረድተዋል፡፡
የስህተቱ መፈፀም ሳያንስ በወቅቱ ስህተቱ አምኖና ስለ ሁኔታው ለቤተሰቦቿ ትክክለኛ መረጃ ሰጥቶ ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ የነበረ ቢሆንም ይህም አለመደረጉን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
“አሁን ታካሚዋ ለህይወቷ የሚያሰጋት ምንም አይነት ችግር የሌለባት መሆኑ በህክምና ባለሙያዎች በሚገባ ስለተረጋገጠ ስለጉዳዩ ለቤተሰቦቿ በቂ መረጃ በመስጠት ይቅርታ ጠይቀናቸዋል፡፡ ታማሚዋ ግን ከሆስፒታሉ እንድትወጣ በሃኪሞቿ ቢፈቀድላትም ሁለት ቀዶ ህክምና በማድረጓ በቅርብ ሆና የጤናዋን ሁኔታ እንድንከታተላት ስለፈለግን አሁንም በሆስፒታሉ ውስጥ ትገኛለች፡፡ የጤናዋ ሁኔታ ግን በጣም ጥሩ ነው” ብለዋል – ዶ/ር ተረፈ አሰፋ፡፡ ስህተቱን የፈፀሙት የቀዶ ጥገና ሃኪም በኮንትራት የተቀጠሩ መሆናቸውን ያመለከቱት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ፤ ከሥራና ከደመወዝ እንዲታገዱ በማድረግ የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል፡፡
ትልቁ ስህተት የቀዶ ሃኪሙ ቢሆንም ሥራው ላይ የተሳተፉት የሀኪሙ ረዳቶችም ከተጠያቂነት ሊያመልጡ እንደማይችሉ ጠቁመው እነሱም የዲሲፕሊን እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል – ዶ/ር ተረፈ፡፡
14 ኢትዮጵያውያን ትናንት በአሰቃቂ ሁኔታ በጋምቤላ ተገደሉ – VOA
እስከአሁን ባደረግነው ክትትል በትናንትናው ዕለት 14 ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንና አስከሬኖቻቸው ተለይተው ዛሬ ለዘመድ አዝማድ መላካቸውን ለሆስፒታል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል። አስክሬን ፍለጋው መቀጠሉ ተነግሯል። ዝርዝሩን ያዳምጡ → listen
የአሜሪካ ሴናተሮች “ኢትዮጵያ ውስጥ አለ” ያሉትን አፈና አወገዙ – VOA
የኢትዮጵያ መንግሥት በሲቪል ማኅበረሰብ ላይ እያካሄደ ነው ያሉትን አፈና እንደሚያወግዙ አሥራ ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ለምክር ቤቱ የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አቅርበዋል። የውሣኔ ሃሣቡን የያዘው ሰነድ የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች ሲቪሎችን መግደላቸው በተገለፀበት በአሁኑ ሁኔታ የአሜሪካው …
ወጣቶቹ እና አደገኛው የጭነት መኪና – ዶይቸ ቬለ

ጥር 9/2008 ዓ.ም. ማለዳ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ አዲስ በተገነባው የፍጥነት መንገድ ላይ ይጓዝ የነበረ አሽከርካሪ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖታል። የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪው በከፍተኛ ፍጥነት እየተጓዘ ነው። ከተቃራኒ አቅጣጫ አንድ መለስተኛ አዉቶቡስ አስራ ስድስት ሰዎች ጭኖ ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘ ነው። የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪው የሚጓዝበትን መንገድ ስቶ
ታንዛኒያና ኬንያ በ74 ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ እየተወዛገቡ ነው
በታንዛኒያ በሕገወጥ ስደተኝነት ተፈርዶባቸው በእስር የቆዩ 74 ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ድንበር ከተማ ታቬታ ተጥለዋል። ድርጊቱ ያስቆጣት ኬንያ “በዓለምአቀፍ ሕግ የታንዛኒያን ሸክም የምቀበልበት እዳ የለብኝም” በማለት አውግዛ ባሳለፍነው ማክሰኞ ከእስር የተፈቱትን ኢትዮጵያዊያን ወደ ታንዛኒያ እንደምትመልስ ገልጻለች። ታንዛንያ እስረኞቹን ወደሀገራቸው ኢትዮጵያ ከመመለስ ይልቅ ወደ ኬንያ ወስዳ የመልቀቋ ምክንያት የታወቀ ነገር የለም (ምንጭ:- ኒውስ24) Filed under: NEWS![]()
ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲ የተመለሰው የብራና መጽሐፍ እያወዛገበ ነው

• ከዩኒቨርስቲው ጋር የተፈራረሙት የደብረ ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪ ከሥራቸው ታግደው ነበር
• ሐዋርድ ያዘጋጀው ውል የባለቤትነት መብትን ይነፍጋል
• ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትቀበለው ውል እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ ተሰጥቷል
“እውነት እና አገልግሎት” ተቋማዊ ብሂሉና መፈክሩ ነው፡፡ በተለይ፣ ለጥቁሮች በሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ዕድልና አስተምሮ በሚያወጣቸው ጥቁር ምሁራን ብዛት ይታወቃል – የአሜሪካው ሐዋርድ ዩኒቨርስቲ፡፡
የዘርና የቀለም ልዩነቶች፣ ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ በደሎች ያስከተሏቸውን መድልዎች፤ ለማኅበራዊ ፍትሕ በቆሙና ለሰብአዊ ነፃነት በሚሟገቱ ምሁራን ማስወገድ ዓላማው ያደረገው ዩኒቨርስቲው፤ በአፍሪካ፣ በአሜሪካና በሌላውም ዓለም የተበተኑ ጥቁሮችን የታሪክና የባህል ቅርሶች ያካበተበት የምርምር ማዕከሉም ከዓለም በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት መካከል ያደርገዋል፡፡
በየአጋጣሚው ያሰባሰባቸውን ቅርሶችና ውርሶች፣ ወደ ጥንት ቦታቸውና ትክክለኛ ባለቤቶቻቸው በሕጋዊ መንገድ መመለስ፣ “ታሪካዊና ባህላዊ ሀብቶቹን ማክበር ነው፤” ይላሉ፣ የዩኒቨርስቲው የሥነ መለኰት ት/ቤት የአካዳሚያዊ ጉዳዮች ተባባሪ ዲን ዶ/ር ጌይ ባይረን፡፡ በተለይም ኢትዮጵያዊ ቅርሶችን ለኢትዮጵያ የመመለስ ጉዳይ፣ የት/ቤቱ የቆየ ፍላጎት እንደነበርና ይህም በአሜሪካም ሆነ በሌላው ዓለም ቅርሶቹን በግልና በተቋም ለያዙ ግለሰቦች፣ ሙዝየሞችና ተቋማት አርኣያነት እንዳለውና ተነሣሽነትንም እንደሚፈጥር ዶ/ር ባይረን ያስረዳሉ፡፡
በት/ቤቱ ማኅደረ ቅርስ ከተከማቹት ኢትዮጵያዊ የብራና ሥነ ጽሑፍ ሀብቶች መካከል፣ ገድለ ቅዱስ ሰራባሞንና ገድለ ቅዱስ ጳውሎስ አንዱ ነው፡፡ የብራና መጽሐፉ፣ በ1993 ዓ.ም. ዶ/ር አንድሬ ቲውድ ከተባሉ የዩኒቨርስቲው የቀድሞው ተማሪ በስጦታ የተበረከተ ሲሆን የ4ኛው መ/ክ/ዘመኑን ሰማዕት ቅዱስ ሰራባሞንና የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ገድል በአንድ ጥራዝ የያዘ ነው፡፡ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከዐረብኛ ወደ ግእዝ የተተረጎመው በዘጠነኛው የደብረ ሊባኖስ ዕጨጌ አባ መርሐ ክርስቶስ አስተዳደር(ከ1456-1490 ዓ.ም.) ነበር፡፡
የጥንተ ክርስትና እና የሐዲስ ኪዳን ምሁር የሆኑት ዶ/ር ባይረን፣ የብራና መጽሐፉን ወደ ዲጅታል በመለወጥ፣ የትመጣውን ለማወቅ ጥናት ካደረጉት የሥነ መለኰት ት/ቤቱ ምሁራን አንዱ እንደነበሩ፣ የዩኒቨርስቲው ድረ ገጽ ዘግቧል፤ የገድሉ ጥንተ ባለቤት የደብረ ሊባኖስ ገዳም መሆኑ የታወቀውና ወደ ጥንት ቦታው ለመመለስ የተወሰነውም በጥናቱ ሒደት እንደነበር በዘገባው ተገልጧል፡፡ ከገድሉ ይዞታ ጋር በተያያዘ አስተዳደራዊና ሕጋዊ አካሔዶችን ጨምሮ የተለያዩ ዕንቅፋቶች ዩኒቨርስቲውን እንዳጋጠሙት፣ ድረ ገጹ በጥናቱ የተሳተፉ ምሁራንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ዩኒቨርስቲው ገድሉን ወደ ጥንት ቦታው በሕጋዊ መንገድ ለመመለስ በማሰብ፣ በሕግ አማካሪው አርቃቂነት “የስጦታ ውል” የተሰኘና በስምንት ነጥቦች የተዘረዘረ የስምምነት ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡ ውሉ በሐዋርድ ዩኒቨርስቲና በደብረ ሊባኖስ ገዳም መካከል የተፈፀመ መሆኑን የሚገልፀው ዘገባው፤ በሥነ መለኰት ት/ቤቱ ዋና ዲን ዶ/ር አልቶን ፖላርድና በገዳሙ ፀባቴ (አስተዳዳሪ) አባ ወልደ ማርያም አድማሱ እንደተፈረመበትም ጠቁሟል፡፡ ይሁንና የውሉ ይዘት ከባለቤትነት መብትና ከቅርሱ አመላለስ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ሆኖ ተገኝቷል ይላሉ ምንጮች፡፡
ዩኒቨርስቲው÷ “ከማናቸውም ግዴታ ነፃ የሆነ የባለቤትነት መብት በብራና መጽሐፉ ላይ አለው” የሚለው የውሉ መግቢያ፣ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚመልሰውም “በስጦታ ለመስጠት በመፈለጉ” እንደኾነ ይገልፃል፡፡ የብራና መጽሐፉን ለገዳሙ በስጦታ የሚሰጥበት የባለቤትነት መብት እንዳለው ገዳሙ መስማማቱን የሚገልፀው ውሉ፤ ገዳሙም የብራና መጽሐፉን ሲቀበል፣ ዩኒቨርስቲው ሙሉ በሙሉ የሚያስተላልፈው፣ “አካላዊ የባለቤትነት መብት”ን እንደሆነ አስፍሯል፡፡ ገዳሙን በመወከል የፈረሙት ሓላፊም፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውል ስምምነቱን እንድታከብር የሚያደርግ ዋስትና የመስጠት ሥልጣን እንዳላቸው በውል ሰነዱ ላይ ተመልክቷል፡፡
ባለፈው ሰኞ፣ የዩኒቨርስቲው ሓላፊዎችና ምሁራን በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ተገኝተው ገድለ ቅዱስ ሰራባሞን ወጳውሎስን ለገዳሙ ባስረከቡበት ወቅት፣ በግልጽ የተነሡት ተቃውሞዎችና ስጋቶች፣ አስተዳዳሪው ከዩኒቨርስቲው ጋር የተፈራረሙት ሰነድ፣ የገድሉን ባለቤትነት ለገዳሙ ሳይሆን ለዩኒቨርስቲው መስጠቱን አረጋግጧል፡፡
ዩኒቨርስቲው ገድሉን ወደ ጥንት ቦታው መመለሱን ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፍተኛ አድናቆት እንደምትመለከተውና እንደሚያስደስታት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተናግረዋል፡፡ “ጥንታዊው ብራና ቅርሳችን በመሆኑ ብንቀበለውም ስምምነቱ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ የባለቤትነት መብት የሚጎዳ፣ በትውልዱም ዘንድ የሚያስነቅፍ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤” ሲሉ ተቃውመዋል፡፡
የውል ሰነዱም፣ በልዩ ጽ/ቤታቸው፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የውጭ ግንኙነት መምሪያ፣ በሕግ አገልግሎቱና በቅርሳቅርስ ጥበቃ መምሪያ በጋራ እንዲታይና እንዲመረመርም ፓትርያርኩ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
የደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኝበትን የሰሜን ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሊቀ ጳጳስነት የሚመሩት አቡነ ቀውስጦስ በበኩላቸው፣ የቅርሱ መመለስ የሁላችን ደስታ ቢሆንም የተመለሰበት ሒደት ግን የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓትና መዋቅር እንዲሁም የገዳሙን ክብር እንዳልጠበቀ ገልጸዋል፡፡ ሦስተኛ ወገን በማስገባት በአስተዳዳሪውና በዩኒቨርስቲው የተፈረመውን ስምምነት÷ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት፣ ሊቀ ጳጳሱ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ ቅዱስ ፓትርያርኩና ቅዱስ ሲኖዶሱ ሳያውቁትና ሳይመረምሩት ሕጋዊ የባለቤትነት መብትን በሚያሳጣ መልኩ መፈጸሙን ብፁዕነታቸው አስረድተዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናና መዋቅር በመጣስ “ለመታየት እና ለመግነን” ሲባል የተፈጸመው ድርጊት አግባብ ያለመሆኑን ሊቀ ጳጳሱ በርክክቡ ወቅት በመናገራቸውም፣ “እዚያች ገዳም ትኖራታለህ፤ እንተያያለን፤ የፈለከውን ሹምበት” በሚል በገዳሙ አስተዳዳሪ መዘለፋቸው ተጠቅሷል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የገዳሙ አስተዳዳሪ ባለፈው ረቡዕ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ÷ ከሥራ፣ ከደመወዝና ከአገልግሎት ታግደው እንደነበር ታውቋል፡፡ ከትላንት በስቲያ የገዳሙን መነኰሳት አስከትለው በመምጣት በፓትርያርኩ ፊት ሊቀ ጳጳሱን ይቅርታ በመጠየቃቸው በመካከላቸው ዕርቀ ሰላም ወርዷል፤ ተብሏል፡፡ ይኹንና አስተዳዳሪው “ተጠሪነቴ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ነው” በሚል ያለሥልጣናቸው ከዩኒቨርስቲው ጋር ፈጽመውታል የተባለው ስምምነት ያስነሣቸው ስጋቶችና ተቃውሞዎች ግን መቋጫ አላገኙም፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ የባለቤትነት መብቷን አሳልፋ ሰጥታ መልሳ በስጦታ መልክ የምትቀበልበት አንዳችም ምክንያት እንደሌለና የዩኒቨርስቲውም ፍላጐት እንዳልሆነ ሒደቱን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የስጦታ ውሉ ባስነሳው ውዝግብ ሳቢያ ዩኒቨርስቲው የሕግ አማካሪውን ሳያሰናብት እንዳልቀረም እኒሁ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቷ በበኩሏ፤ “የስጦታ ውል” ሰነዱን እንደምትቃወመው ለዩኒቨርስቲው በይፋ በማሳወቅ፣ ተቀባይነት ያለው ስምምነት እንዲዘጋጅ ጥያቄ ማቅረብ እንዳለበት ተወስኗል፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ቤ/ክርስቲያኗ የአሜሪካንና የአውሮፓን ዩኒቨርሲቲዎች፣ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ባደመቁት ሌሎች ቅርሶቿ አመላለስ ላይ የራሱ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡
የስኳር ሕመምና የዓይን ብርሃንን እስከ ማጣት ሊያደርሱ የሚችሉ የዓይን በሽታዎች – VOA
የበሽታዎቹን መከሰት ከወዲሁ የሚጠቁሙ አስቀድመው የሚታዩ ምልክቶች ይኖሩ ይሆን? የስኳር ሕሙማን በራሳቸው ሊወስዱ የሚችሏቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን? የስኳር በሽታን ተከትለው የሚከሰቱት አሳሳቢዎቹ የዓይን ሕመም ዓይነቶች የትኞቹ ናቸው? ተከታታይ ቅንብሮቹ የሕክምና አማራጮቹን ጨምረው ሕሙማንና የቤተሰብ አባላት ሊጠይቁና ሊመልሱ የሚሿቸውን ጭብጦች ይዳሳሳሉ።
ከመስመጥ የተርፉት ኢትዮጵያውያን 11 ብቻ ናቸው፤ ሦስቱን አነጋግረናቸዋል – VOA
ሚስትና ልጁን ያጣ፣ እናትና ወንድሞቹን ውሃ የበላበት፣ እህቱን እና 28 ጓደኞቹን ያጣ ናቸው። ስላሳለፉት ጉዞ አስቸጋሪነትና ለመሄድ ስለተዘጋጁ ስደተኖች የሚነግረን ወጣትም ከግብጽ አነጋግረናል። ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ 500 ስደተኞች ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ …
ከመስመጥ የተርፉት ኢትዮጵያውያን 11 ብቻ ናቸው፤ ሦስቱን አነጋግረናቸዋል – VOA Read more »
በደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ የሕወሓት ሰራዊት እንቅስቃሴ ምንም እንዳሌለ ምንጮች ጠቆሙ::
በደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ የሕወሓት ሰራዊት እንቅስቃሴ ምንም እንዳሌለ ምንጮች ጠቆሙ:: #Ethiopia #SouthSudan #Gambella #EUPF #MinilikSalsawi Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – የጋምቤላ ፖሊስ እና ልዩ ሃይል ወደ ካምፕ ሆን ተብሎ ሰብስቦ ማስገባትን መሳሪያ ማስፈታትን ወታደሩን ክፍል ከድንበር አከባቢ …
በደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር አከባቢ የሕወሓት ሰራዊት እንቅስቃሴ ምንም እንዳሌለ ምንጮች ጠቆሙ:: Read more »
አሰቃቂው የጋምቤላ ጭፍጨፋና የፀጥታ ኃይሎች አሠላለፍ
ራሱን ‹‹የደቡብ ሱዳን ቡድን›› በማለት የሚጠራው የሙርሌ ጎሳ ታጣቂ ቡድን የደቡብ ሱዳንን ወታደራዊ ዩኒፎርም በመልበስና ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች በመታጠቅ መቼ እንደተነሳ እስካሁን ማረጋገጫ ባይገኝም፣ ዓርብ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ለቅዳሜ አጥቢያ ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ጋምቤላ ደረሰ፡፡ ታጣቂው ኃይል ከደቡብ …
የደም ባንክ በመኪና አደጋ ብዛት የደም እጥረት ያጋጠመው መሆኑን አስታወቀ
የደም ባንክ በመኪና አደጋ ብዛት የደም እጥረት ያጋጠመው መሆኑን አስታወቀ በኢትዮጵያ በየዕለቱ የሚሰቀጥጡ የመኪና አደጋዎችን መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤፍ ኤም ሬዲዩ ጣብያዎችም በየማለዳው ከተለያዩ አካባቢዎች መረጃዎችን በማጠናቀር የሚጠብቋቸውን የትራፊክ ባለሞያዎች በማስተናገድ የደረሱትን የመኪና አደጋዎች ለህዝብ ያስተላልፋሉ፡፡ የህክምና ባለሞያዎችና …
የፀረ ኤች አይቪ መድኃኒቶች – ዶይቸ ቬለ
የዓለም የጤና ድርጅት ሰነድ እንደሚለዉ በአሁኑ ወቅት የዓለማችን 37 ሚሊየን ሕዝብ HIV ተሐዋሲ በደሙ ዉስጥ ይገኛል። ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ላይ 16 ሚሊየኑ ፀረ ኤች አይቪ መድኃኒት እንደሚወስዱ ተመዝግቧል። በሽታዉ እስካሁን ከ34 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። የመድኃኒቱ ስርጭት እና …
የሰማያዊ ፓርቲ የውስጥ ፍትጊያ ለበጎ ወይስ ለጥፋት ? ግርማ በቀለ
የሰማያዊ ፓርቲ የውስጥ ፍትጊያ ለበጎ ወይስ ለጥፋት ? መልካሙን ማሰብ ከመልካም ያደርሳልና— ጠንካራውን ሰማያዊ እንጠብቅ// (የሰማያዊ የውስጥ ፍትጊያ ለሚያስጨንቃችሁ፣ በተለይ ክፍተቱን ለማጥበብ የነበረኝን ድርሻ በሚመለከት አስተያየት እንድሰጥ ለጠየቃችሁኝ ) በቅድሚያ ይህን ጥረት ለማድረግ ያቀረብኩትን ጥያቄ በሙሉ ልብ ተቀብላችሁ በመተማመን ስሜት …
በጋምቤላ የደረሰዉ ጥቃት እና ትችቱ
በጋምቤላ ለተፈጠረዉ የሰዉ ሕይወት መጥፋት እና መታገት ምክንያቱ የመንግሥት ንዝህላልነት የፈጠረዉ ችግር ነዉ ሲሉ የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ወቀሱ።
በከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ የተለቀቁ ሁለት ሰዎች እስከዛሬ አልተፈቱም – VOA
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈዉ ሳምንት በሰጠዉ ዉሳኔ ነጻ ያሰናበታቸዉ ሁለት ሰዎች እንዳልተፈቱ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ፖሊስ ማእከላዊ የወንጀል ምርመራ እንደወሰዳቸዉም ተገልጿል። የፖሊስ እርምጃ ምክንያት ግን አልታወቀም። ዝርዝሩን ከመለስካቸዉ አመሃ ዘገባ ያድምጡ → listen
የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር – ዶይቸ ቬለ
በተለያዩ ምክንያቶች ከአፍንጫ ደም ሊፈስ ይችላል። ነስር የምንለዉ ማለት ነዉ። ብዙዎች መንስኤዉ ምንድነዉ ብለዉ ይጨነቃሉ። ነስር ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የመሆኑን ያህል አብዛኛዉን ጊዜ ቤት ዉስጥ ሊቆጣጠሩት የሚቻል እንደሆነ አንዳንድ የህክምና ጽሑፎች ይጠቁማሉ። ሆኖም አልፎ አልፎ ደግሞ ብዙ ደም የሚፈስበት ከባድ …
የ86 መንትዮች እናት በምጥ ትሰቃያለች– Girma Bekele
የ86 መንትዮች እናት በምጥ ትሰቃያለች– የአዋላጅ ሃኪሞች ‹‹ ቡድን ›› እየተጣራች ነው፤ በእናት የምትመሰለው አገራችን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በተለይም ካለፉት 25 ዓመታት ወዲህ በተለያዩ ከአንድ ምንጭ በሚቀዱ ህመሞች እየተሰቃየች በመፍትሄ ምጥ/መድሃኒት ፍለጋ/ ውስጥ ነች፡፡ እኛ ልጇቿ ከጊዜ ወደ ጊዜ የለቅሶ …
በዓለም ዝነኛው የቦስተን ማራቶን የኢትዮጵያ አትሌቶች በሴቶቹም በወንዶቹም ድል ተቀዳጁ – VOA
በ120ኛው የቦሰተን ማራቶን በሴቶቹ ተከታትለው በመግባት ያሸነፉት፥ አፀደ ባይሣና ትርፊ ነገሪ ናቸው። የወንዶቹን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ሥፍራ የወሰዱትና ታሪክ የሠሩት የኢትዮጵያ ሯጮች ደግሞ፥ ለሚ ብርሃኑ፥ ያለፉት ሁለት ዓመታት ሻምቲዮኑ ሌሊሣ ዴሢሣና ፀጋዬ ናቸው። listen
በኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ድንበር ያለው የጎሳ ግጭትና የወያኔ ሚና
በኢትዮ-ደቡብ ሱዳን ድንበር ያለው የጎሳ ግጭትና የወያኔ ሚና #Ethiopia #Gambella #SouthSudan #Sudan #MinilikSalsawi #CivilWar Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በጃኮው እና በኒያኒያንግ አቅራቢያ ሰፍረው የነበሩ ወታደሮች ለምን አከባቢውን እንዲለቁ እንደተደረገ የወያኔ አገዛዝ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል::ጭፍጨፋውን ተከትሎ ለምንስ አከባቢዎቹን መክበብ እና ወጪ …
አንድነትን ማጥበቅ በቁርጠኝነታችን ተማምነን እንጂ እንደው በሞቅ ሞቅና በሰሞነኛ መንገኝነት ተገፋፍተን እንዳይሆን እንጠንቀቅ፡፡
አንድነትን ማጥበቅ በቁርጠኝነታችን ተማምነን እንጂ እንደው በሞቅ ሞቅና በሰሞነኛ መንገኝነት ተገፋፍተን እንዳይሆን እንጠንቀቅ፡፡ #Ethiopia #Ethiopianoppositionparties #EPRDF #Miniliksalsawi Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – አላዋቂ እጅ መውደቅ እርግማን ነው፡፡ ደጋግመን መፈክር ስላሰገርንና፣ ደጋግመን በቃል ቃል ስለገባን ግባችንን በተግባር እንመታለን ማለት አይደለም፡፡ የምንጓዘው …
አንድነትን ማጥበቅ በቁርጠኝነታችን ተማምነን እንጂ እንደው በሞቅ ሞቅና በሰሞነኛ መንገኝነት ተገፋፍተን እንዳይሆን እንጠንቀቅ፡፡ Read more »
ማኅደረ ማርያም – ማኅደረ ታሪክ
ማኅደረ ማርያም ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በፋርጣ ወረዳ፣ ከደብረ ታቦር 28 ኪሎ ሜት ርቀት ላይ፣ በ2450 ሜትር ከፍታ ከባሕር ወለል በላይ፣ በቧኢት ተራራ ላይ ወደተተከለቺው ማኅደረ ማርያም ደብር ተጉዤ ነበር፡፡ የጉዞዬ ዋና ዓላማ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ለምሠራው ጥናት …
በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ በዳዳ ገልቹ የሚባል ወጣት በመንግስት ታጣቂዎች መገደሉ ተነገረ – VOA
በኦሮሚያ ክልል አልፎ አልፎ በተማሪዎችና በነዋሪዎች የሚካሄደዉ ተቃዉሞና የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ ምላሽም ቀጥሏል። በጉጂ ዞን ኦዶሻኪሶ ወረዳ መጋደር በተባለ መንደር ባለፈዉ ማክሰኞ በዳዳ ጋልቹ የሚባል ወጣት በመንግስት ሃይሎች መገደሉን የአካባቢ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ገልጸዋል። በወረዳዉ የሻኪሶ ከተማ አስተዳዳሪዎች …
በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ በዳዳ ገልቹ የሚባል ወጣት በመንግስት ታጣቂዎች መገደሉ ተነገረ – VOA Read more »
“የሰርቆ አደሮች” ስብሰባ ” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ሰሞኑን በአዲስ አበባ አንድ ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የአዲስ አበባ ደረጃ አንድ ሌቦች ስብሰባ አድርገው ነበር፡፡ የስብሰባው መሪ ቃል ‹የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ሌቦች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?› የሚል ነው፡፡ ስብሰባው እንደተጀመረ አንደኛው የታወቀ ሌባ እጁን አወጣና ‹መፈክሩ ላይ የተጠቀስንበት ስም ትክክል …
በጋምቤላ ጥቃት 108 ህጻናት ታፍነው ተወስደዋል – ዶይቸ ቬለ
በምዕራብ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ድንበር የተሻገሩ ታጣቂዎች በዕለተ አርብ ማለዳ በፈጸሙት ጥቃት ህጻናት መታገታቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ተናገሩ። ቃል-አቀባዩ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ በጥቃቱ ምን ያኽል ሰዎች ታግተው እንደተወሰዱ አለመናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ከ 800 በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ – VOA
በኦሮሚያ በየደረጃው የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ ሃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ ከ 800 በላይ አመራሮች ከደረጃ ዝቅ ብለው እንዲሰሩ የማድረግና ከሀላፊነት የማንሳት እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። በክልሉ የተጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን የኦሮሚያ ክልልና የፌደራሉ መንግስት ማስታወቃቸው ይታወሳል። ዘጋብያችን እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ የላከው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል።
በዓሉ ግርማ – ሕይወቱና ሥራዎቹ (መጽሃፍ ግምገማ በዳንኤል ክብረት)
በእንዳለ ጌታ ከበደ የካቲት 2008 ዓም ዋጋ፡- 120 ብር እንዳለ ጌታ ከበደ በዓሉ ግርማን እንደ ጌታ ነፍስ ዘርቶ እንደደአልዓዛር ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ከትውልድ ቀየው ጀምሮ ‹እስከ መቃብሩ› ደረስ እየተከተለ፡፡ መዛግብቱን ያገላብጣል፣ እናውቃለን የሚሉትን ይጠይቃል፣ ያውቃሉ ብሎ የገመታቸውን ያናግራል፤ ሄዶበታል፣ ውሎበታል፣ ገብቶበታል፣ …
የኢኮኖሚ እድገቱ ወደ 4.5 በመቶ ያሽቆለቁላል – IMF // መንግስት በ7 በመቶ ያድጋል ብሏል
እንደወትሮው መንግስት እና የዓለም ገንዘብ ድርጅት፣ የኢኮኖሚ እድገትንበተመለከት ያወጡት መረጃ ዘንድሮም የተራራቀ ሆኗል፡፡ ባለፉት አስር ዓመታት ኢኮኖሚው በአስር በመቶ ሲያድግ መቆየቱን መንግስት የሚገልፅ ሲሆን፣ የዓለም ገንዘብ ድርጅት በበኩሉ፤ የእድገቱ መጠን 8 በመቶ ገደማ እንደነበረ ይናገራል፡ ፡ ዘንድሮ በድርቁ ሳቢያ ኢኮኖሚው …
የኢኮኖሚ እድገቱ ወደ 4.5 በመቶ ያሽቆለቁላል – IMF // መንግስት በ7 በመቶ ያድጋል ብሏል Read more »
በጆሐንስበርግ መድኃኔዓለም የተፈጠረ ውዝግብ ምዕመናንን ለዐምባጓሮ አደረሰ
– አምስት ምእመናን ለእስር ተዳርገዋል – የውጭ ጉዳይ ሓላፊው ተጠያቂ ተደርገዋል – ሰበካ ጉባኤው በፕሪቶርያ ፍ/ቤት ክሥ መሥርቷል አለማየሁ አንበሴ በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደር ሳቢያ የተፈጠረ አለመግባት ወደ ዐምባጓሮ አምርቶ 8 ምእመናን የተጎዱ ሲሆን ጉዳዩም …
ኢትዮጵያዊቷ በኩዌት አሰሪዎቿን “በሰው በላነት” ከሰሰች
በኩዌት በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ የምትሰራ ስሟ ያልተጠቀሰ ኢትዮጵያዊት፣ የአሰሪዎቿን ቤተሰቦች የሰው ስጋ ይበላሉ ስትል መክሰሷን ገልፍ ዲጂታል ኒውስ የተባለው ድረገጽ ዘገበ፡፡ሳላዋ በተባለው የአገሪቱ አውራጃ በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ የምትሰራው ኢትዮጵያዊቷ፣ በአሰሪዎቿ መኖሪያ ቤት ውስጥ የሰው ራስ ቅል ተደብቆ ማየቷን በመጥቀስ ለፖሊስ …
ሰማያዊ ፓርቲ አደጋ ላይ ነው :: ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጋር ቃለምልልስ
• ፓርቲው የውስጥ ችግሩን መፍታት ለምን ተሳነው? • ለፓርቲው ቀውስ ተጠያቂው ማን ነው? • የመበታተን አደጋ ያሰጋው ይሆን ? ሰማያዊ ፓርቲ በተለይ ሊቀመንበሩና ሌሎች አመራሮች መዝብረዋል የተባለውን ገንዘብ መነሻ በማድረግ በአጋጅ ታጋጅ ድራማ ታጅቦ በቀውስ እየተናጠ ይገኛል፡፡ በፓርቲው ችግሮች፣ በመፍትሄዎቹ፣ …
መንቃት ያለብን ወሳኝ ወቅት – የምንፈልገውን ነጻነት ለማረጋገጥ ጊዜው በፍጹም አረፈደም !!!
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን እንደተምኔት ሳይሆን እንደተጨባጭ ነገር ማስተዋል ይገባናል፡፡ ፅንፍና ፅንፍ እየቆሙ፣ ማዶና ማዶ የጎሪጥ እየተያዩ፣ በደፈረሰ ልብ እያሰሉ፣ የምንመኘውን ዓይነት ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው፡፡ ከቶውንም፤ በትንሹ የምንመኛቸውን ነገሮች እንኳ በእጃችን ማስገባት አዳጋች ይሆናል፡፡ እንደሶስተኛው ዓለም …
መንቃት ያለብን ወሳኝ ወቅት – የምንፈልገውን ነጻነት ለማረጋገጥ ጊዜው በፍጹም አረፈደም !!! Read more »
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተገደሉ።
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች ዐርብ ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተገደሉ። የኑዌር ጎሳ አባላት የመኖሪያ መንደሮች ላይ ባነጣጠረው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ221 በላይ መሆኑን ሱዳን ትሪቡዩን ዘግቧል። ሱዳን ትሪቢዩን የደቡብ ሱዳን ጦር መለዮ የለበሱ …
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተገደሉ። Read more »
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ 140 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ – ዶይቸ ቬለ
ጋምቤላ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ140 በላይ ሰዎች ዐርብ ሚያዝያ 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ተገደሉ። የኑዌር ጎሳ አባላት የመኖሪያ መንደሮች ላይ ባነጣጠረው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ221 በላይ መሆኑን ሱዳን ትሪቡዩን ዘግቧል።
የጫት ጉዳትና ጥቅሞች በኢትዮጵያ – ዶይቸ ቬለ
ጫት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ጥቅምና በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በቅጡ እንዲጤን ስለ ጫት ጥናታዊ ጽሁፎች ያቀረቡ ምሁራን አሳሰቡ ። «ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ» የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ባዘጋጀው አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት ቀናት በተካሄደው ዐውደ ጥናት ላይ የጫት ኤኮኖሚያዊ እና ባህላዊ …
በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከ30 በላይ ሰዎች መታሠራቸውን ተማሪዎች ተናገሩ – VOA
በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ውስጥ ሰኞ እና ማክሰኞ በተማሪዎችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎች ገለጹ። ከግጭቱም በኋላ ከሰላሳ ሰው በላይ መታሰሩን ተናግረዋል። የከተማው ፖሊስ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም ይላል። የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረባ ቱጁቤ ኩሳ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ …
በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከ30 በላይ ሰዎች መታሠራቸውን ተማሪዎች ተናገሩ – VOA Read more »
የኪነ ጥበብ ማህበራት ለደራስያን ማህበር የሰጡት ምላሽ (በ“ቃና” ቲቪ ጉዳይ)
ይድረስ ለኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር
ሰሞኑን ሥርጭቱን በጀመረው “ቃና ቲቪ” ይዘት እና አሰራር ላይ ለመወያየት በደብዳቤ
ባሳወቅናችሁ መሰረት ተወካያችሁን መላካችሁ ይታወቃል፡፡ የኪነ ጥበብ ሞያ ማኅበር ተወካዮቹ (የእናንተም ባሉበት) በተጠቀሰው ጉዳይ ለሁለት የተለያዩ ቀናት የጋራ ውይይት አካሂደው የጋራ የአቋም መግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ይህ የጋራ አቋም በፅሁፍና በንባብ ለሚዲያ ከመቅረቡ በፊት የእናንተ ሁለት ተወካዮችን ጨምሮ የሁሉም የሞያ ማኅበር ተወካዮች መስመር በመስመር በጥንቃቄ ተመልክተው ማሻሻያና ማረሚያ ካደረጉ በኋላ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫው የተሰጠ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ መግለጫ ከመሰጠቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ (በ20/07/2008) የደራስያን ማኅበር ልሳን በሆነውና ዘወትር ማክሰኞ ምሽት በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በሚቀርበው ፕሮግራም ላይ የመግለጫውን ፍሬ ሃሳብ ለህዝብ በመግለፅ ሚዲያዎች እንዲገኙ መረጃ ስታደርሱ እንደነበርም ይታወቃል፡፡ይህ ጥሬ ሀቅ ባለበት ሁኔታ ባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 1 ቀን 2003 ዓ.ም በወጣው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የደራስያን ማኅበር ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙሴ ያዕቆብ የሰጡት ከእውነት የራቀና የተዛባ መግለጫ እጅግ የሚያሳፍርና የሚያሳዝን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ የመላው የደራስያን ማኅበር አመራርና አባላት እምነት እንዳልሆነም እናምናለን፡፡ የእሳቸው ማኅበር ተወካይና ሌሎች የጥበብ ማኅበራት በጋራ ተወያይተው ያወጡትን መግለጫ በምን ምክንያትና መነሳሳት ለመካድ እንዳነሳሳቸው ለጊዜው ያወቅነው ነገር የለም፡፡ በሂደቱ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ሲሳተፍ የነበረውን የማኅበራቸውን ተወካይ፤ “መግለጫውን ለመከታተል የተገኘ ነው” በማለት ከደራሲያን ማኅበር ተወካይነት ወደ ሚዲያ ተወካይነት ለውጠው፣ ለጋዜጣው ለመግለፅ ለምን እንደተገደዱም አልተረዳንም፡፡ ከዚህም በላይ ማህበራቱ የቴሌቪዥን ጣቢያውን በሚመለከት እያቀረቡት ካለው አመክንዮና ለህዝብ ከገለፁት አቋም ፈፅሞ የራቀና የማናውቀውን ጉዳይ በመናገር አንባቢን ግራ ከማጋባታቸውም በላይ የማኅበራቱን ጥያቄ ያልተገባ ለማስመሰል መሞከራቸው ከምን በመነጨ አስተሳሰብና ዓላማ እንደሆነ ለጊዜው አልደረስንበትም፡፡ በእሳቸውና በመላው የጋዜጣዊ መግለጫው ተሳታፊ በነበሩ የሚዲያ አካላት እጅ በሚገኘው ባለ አምስት ገፁ የሞያ ማኅበራቱ የአቋም መግለጫ በየትኛው አንቀፅ ላይ ይሆን የሳንሱር ጉዳይ የተነሳው!? የኢትዮጵያ ደራስያንን እወክላለሁ የሚል
የማኅበር ፕሬዚደንት የተፃፈን ፅሑፍ አንብቦ መረዳት ተሳነው ቢባልስ ማን ያምን ይሆን!? የሆነስ
ሆነና “እነ በዓሉ ግርማን የመሳሰሉ ፀሐፍት በሳንሱር ምክንያት የሕይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል”
ማለታቸውስ የደራስያን ጉዳይ ጉዳዬ ነው ብሎ የፕሬዚደንትነት ሥልጣን ከተቆናጠጠ ግለሰብ ይጠበቃል ወይ!? ሌላው ቢቀር የደራስያን ማኅበር የአመራር አባል በነበረው ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ጥልቅ ጥናትና ምርምር የታተሙትን “ማዕቀብ” እና “የበዓሉ ግርማ ሕይወትና ሥራዎች” የተሰኙ በብዙዎች የተነበቡ መፃሕፍትን ቢያነቡ ኖሮ በዓሉ ግርማን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በሳንሱር ምክንያት የሕይወት መስዋዕትነት የከፈለ (የተገደለ) አንድም ደራሲ እንደሌለ በተረዱ ነበር፡፡ እንደሚታወቀው የኪነ ጥበብ ሞያ ማኅበራቱ በመግለጫቸው ያሉት ዋና ፍሬ ሀሳብ ዶ/ር ሙሴ በስህተት አልያም በችኮላ ተረድተው እንዳሉት ሳይሆን “ቃና” ቴሌቪዥን ለውጭ ሀገር ፕሮግራሞች የሰጠው (70%) ተገቢ አይደለም የሚል ነው፡፡ ይህ ሀሳብ የሳንሱር ሳይሆን በሀገር ውስጥ፣ በሀገር አቅም በሚሰሩ ፊልሞች ላይ ጫና ፈጥሮ ፍትሀዊ ተወዳዳሪነት እንዳይኖር በማድረግ፣ ዳዴ በማለት ላይ ያለውንና የብዙ ዓይነት ጥበቦችና ባለሙያዎች ውህደት ውጤት የሆነውን የኢትዮጵያ ሲኒማ አቀጭጮ ያጠፋል፣ አዲስ ለሚከፈቱ ጣቢያዎች በቀላሉና በውስን ሰዎች ሳይለፉ ገንዘብ እንደሚሰራ በማሳየት በመስኩ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ዜጎች በሀገራቸው ስለ ሀገራቸው ጉዳይ የሚተርክ ፊልም በመስራት እንዳይጠቀሙና ሞያውን እንዳያሳድጉ እንቅፋት ይሆናል፣ ህዝብን የሚያረካ ሥራን የሰሩና ይሁንታን በማግኘት የተደነቁ ባለሙያዎችም ዝናቸውን በመጠቀም የደሀ
ህዝባቸውን ችግር ለመቅረፍ በሚደረጉ የማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ የሚያደርጉትን በጎ እንቅስቃሴና ቅስቀሳ ተፅዕኖ አልባ በማድረግ ያዳፍነዋል የሚል ነው፡፡ በእግረ መንገድም ፊልሞቹ በአብዛኛው ከምዕራባውያን የሚመጡ እንደመሆናቸውና የሚተላለፈው ለቤተሰብ ቅርብ በሆነው የቴሌቪዥን ሚዲያ በኩል ከመሆኑ አንፃር አጉል ባህል በቀላሉ ታዳጊ ህፃናትና ልጆች ላይ እንዳይሰርፅ ሥጋታችንን የገለፅንበት ነው፡፡ የኪነ ጥበብ ሞያ ማኅበራቱ በጋራ ባካሄዱት ውይይት ዶ/ር ሙሴ የእሳቸውን ማኅበር በመወከል በተገኘው ግለሰብ እምነት ከሌላቸው፣ ከቢሮአቸው በአራት እርምጃ ከሚርቀው የጋራ ማኅበራቱ
መሰብሰቢያ ቢሮ በመምጣት ጉዳዩን ማጣራት ይችሉ ነበር፡፡ አልያም በአሁን ሰዓት የደራስያን አመራር አባል የሆኑት የሥራ ባልደረባቸው በዚሁ ጋዜጣ ሚያዝያ 26 ቀን 2008 ዓ.ም የፃፉትን ጥልቅና ለብዙዎች ስለ ጉዳዩ የበለጠ ግንዛቤ ያስጨበጠ ፅሑፍ ቢቻል አንብበው ካልሆነም ካነበበ ሰምተው አስተያየታቸውን ቢሰጡ ኖሮ ትዝብት ላይ የሚጥል ስህተት ባልሰሩ፣ መልካም ሥም የነበረውን ማኅበራቸውንም ባላቀለሉ ነበር እንላለን፡፡
(ተፃፈ፡- ከ “የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ማኅበራት
ጊዜያዊ አስተባባሪ”)
በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በጠፍ ሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱት እነ ዓለማዬሁ ለሳምንት ተቀጠሩ
ከደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በጠፍ ሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱትና ከ20/07/08 ጀምሮ በአዋሳ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ታስረው የሚገኙት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የኦህዲኅ አባል አቶ አብርሃም ብዙነህና የቀድሞ …
በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በጠፍ ሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱት እነ ዓለማዬሁ ለሳምንት ተቀጠሩ Read more »
በጂንካ ከተማ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ባዛር ሊካሄድ ነው ::በልማት ስም ገንዘብ የባለሥልጣናት ኪስ ማደለቢያ ሊውል አንፈቅድም
የዞኑ መስተዳድር በዞኑ ነዋሪዎች የተቋቋመ ‹ነጻ› በሚባል የልማት ማህበርጋር የገንዘብ ማሰባሰቢያ ባዛር ለማዘጋጀት ህዝቡን በመቀስቀስ ላይ መሆኑን፣ ለዚሁ ባዛር መምህራንን ለማሳመን በየትምህርት ቤቱ ….. በመሰብሰብ ያወያየ ሲሆን ከመምህራን የተለያዩ ጥያቄዎች መነሳታቸውንና ለዚህም በቂ መልስ መስጠት ባለመቻሉ ለሌላ ጊዜ ሰፊ ውይይት …
በጂንካ ከተማ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ባዛር ሊካሄድ ነው ::በልማት ስም ገንዘብ የባለሥልጣናት ኪስ ማደለቢያ ሊውል አንፈቅድም Read more »
“አቶ መለስ በታሪክ ሊጠየቁበት የሚችለው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው ነው” ዶክተር ፍሰሃ አሰፋው
በርካታ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ችግሮች ሲፈጠሩ የአገሪቱን ፖሊሲ አውጭዎችና ህግ አስፈጻሚዎችን በድፍረት ከመተቸትም ሆነ መልካም ጎኖችን ከማበረታታት ታቅበው ይታያሉ። ቁጥራቸው በዛ ያሉ አይሁን እንጂ በገዥው ፓርቲ ጉያም ሆነ በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ምሁራንም ምሁራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሲንቀሳቀሱ እናያለን። ከተቃውሞውም …
“አቶ መለስ በታሪክ ሊጠየቁበት የሚችለው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጋቸው ነው” ዶክተር ፍሰሃ አሰፋው Read more »
የድምፃዊት አለም ከበደ አስራ አንድ አመት የፈጀ የሙዚቃ አልበም – VOA
አለም ከበደ ለየት ባለው የአዘፋፈን ስልቷ ትታወቃለች። ከሙዚቃ ህይወት ባትርቅም አዳዲስ ስራዎች ለአድማጭ ለማቅረብ ግን ረጅም ጊዜ ወስዶባታል።
በአምቦ ዩኒቨርስቲ የውሃና መብራት መቋረጥ ተቃውሞ አስነሳ፤ የግቢው ተማሪዎች ተደበደቡ – VOA
በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዋሮ ግቢ ካለፈው አርብ ጀምሮ ውሃ መቋረጡን፣ መብራት ከዕረቡ ጀምሮ መጥፋቱን እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ መነሲቡ ወረዳ ከሠላሳ በላይ ሰዎች መታሠራቸው በዚህ ዘገባ ተካቷል።
ኮሌስትሮልን ተከትለው የሚመጡ የጤና ሁከቶችን መከላከያ ቅድመ ጥንቃቄ – VOA
በሕክምናው አጠራር “ኮሌስትሮል” በመባል በሚታወቀው፤ በአንድ በኩል ለጤና በእጅጉ አስፈላጊ፤ መጠንና ዓይነቱ ሲለወጥ ደግሞ ጎጂ በሚሆነው በደማችን ውስጥ የሚዘዋወረው ስብ መሠል ንጥረ ነገር ምንነትና የሕክምናው ዓለም ምልከታዎች ዙሪያ የሚያተኩር ተከታታይ ቅንብር ነው። ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን የልብና የውስጥ ደዌ ከፍተኛ አማካሪ …
ኮሌስትሮልን ተከትለው የሚመጡ የጤና ሁከቶችን መከላከያ ቅድመ ጥንቃቄ – VOA Read more »
አዲሱ “ቃና” ቴሌቭዥን የአርቲስቶችን መንደር አናወጠ

የኢትዮጵያ ፊልም ሰሪዎች፣ የቲያትር ባለሙያዎች ፣ የሙዚቀኞችና የሰአሊያን ማህበራት እንዲሁም አላቲኖስ የፊልም ሰሪዎች ማህበር ሰሞኑን በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ አዲሱ የ“ቃና” ቴሌቪዥን የፕሮግራም ይዘት የአገሪቱን የሲኒማ ጥበብ አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ይዘቱን ሊያስተካክል ይገባል አሉ፡፡
“ቃና” ቴሌቪዥን በበኩሉ፤ የአገሪቱን የፊልም ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እተጋለሁ ብሏል፡፡
“ቃና” 70 በመቶ የውጭ ሀገር ፊልሞችን፣ 30 በመቶ የአገር ውስጥ ፕሮግራሞችን ሊያቀርብ መዘጋጀቱን የጠቆሙት ማህበራቱ፤ የይዘት ምጣኔው የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያላገነዘበና የባህል ወረራን የሚያስፋፋ ነው ሲሉ ነቅፈዋል፡፡ የአደጋው ምንጭ በዋናነት የውጭ ሀገር ፊልሞችን ተርጉሞ በዳቢንግ (ድምጽ በመቅዳትና አስመስሎ በመለጠፍ) ማቅረቡ ነው ብለዋል፡፡
በቴሌቪዥን ጣቢያው የሚቀርቡት የውጭ ሀገር ፊልሞች ንግድ ተኮር በመሆናቸው ምንም አይነት ትምህርታዊና ሞራላዊ ይዘት የላቸውም ያሉት ማህበራቱ፤ የባህል ወረራን በማስፋፋት ትውልድን ከማጥፋታቸው በፊት መንግስት ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡
ጣቢያው አጭር እድሜ ያለውን የተከታታይ ድራማ ታሪካችንን በማቀጨጭ የፊልም ኢንዱስትሪውን ዕድገት የሚያሰናክል በመሆኑ ፕሮግራሙን በድጋሚ ሊከልስ ይገባዋል ብለዋል፤ ማህበራቱ፡፡
ባለፈው ዓመት “ዳና” የቴሌቪዥን ድራማ 8 ሚሊዬን ብር ገቢ ለመንግስት ማስገኘቱን የጠቀሱት ማህበራቱ፤ “ቃና” በዚህ ይዘቱ የሚቀጥል ከሆነ ግን ትውልድ ከማጥፋቱ በተጨማሪ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ያሳጣዋል ብለዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ በብሄራዊ ቲያትር በሰጡት በመግለጫ ላይ የቴሌቪዥን ጣቢያውን የሥራ ሐላፊዎች ለምን እንዳልጋበዙ የተጠየቁት ማህበራቱ፤ የተቻላቸውን ያህል ጥረት ቢያደርጉም ሊያገኙአቸው እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡ የ“ቃና” ቴሌቪዥን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ኃይሉ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው፤ ጣቢያው በመግለጫው ላይ አለመጋበዙን ገልፀው፤ በይዘቱ ዙሪያም ቀርቦ ሊያናግራቸው የሞከረ ማህበርም ሆነ ግለሰብ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ በፕሮግራሙ ይዘት ላይ ችግር አለ ብሎ የሚያምን አካል በማንኛውም ጊዜ ሊያነጋግራቸው እንደሚችልም ገልፀዋል – ሃላፊው፡፡
ባለፉት 50 ዓመታት የቴሌቭዥን ታሪክ በተለያዩ አገራት በራሳቸው ቋንቋ ተተርጉመው ባህልና እሴቶችን ሳይጋፉ የቀረቡና እየቀረቡ ያሉ የመዝናኛ ስራዎች፣ በየአገሩ ያሉትን የፊልምና የቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ አሁን ላለበት ደረጃ አድርሰውታልም ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ጣቢያው ከመቋቋሙ በፊት በአገሪቱ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፤ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን ከሚመለከቱ ኢትዮጵያውያን ግማሽ ያህሉ የሚያዩት የውጭ አገር ይዘት ያላቸውንና በሌላ ቋንቋ የተሰሩትን ሲሆን የሚያዩትም እንዲሁ እንደወረዱ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ኃይሉ፤ አሁን ጣቢያው ለእይታ የሚያበቃቸው ፊልሞች ግን የተመረጡና ለማህበረሰቡ ትርጉም ሊሰጡ የሚችሉት ብቻ ናቸው፡፡
ፊልሞቹ በቀጥታ የተተረጐሙ ሳይሆኑ በእኛ ሀገር ባህል፣ አባባልና አስተሳሰብ የተቃኙ እንደሆኑም ጠቁመው፤ ያልተገቡ የተባሉ የፊልሙ ክፍሎችም ተቆርጠው እንደሚወጡ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
ጣቢያው በቲያትር ጥበባት የተመረቁ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንን በፀሐፊነት፣ በዳይሬክቲንግ፣ በድምጽና በቪዲዮ ኤዲቲንግ ቀጥሮ እያሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ኃይሉ፤ በቀጣይም የእራሱን አገራዊ ስራዎች ለመስራት በእንቅስቃሴ ላይ ነው ብለዋል። ለ“ቃና” ፕሮግራሞቹን የሚያቀርበው “ቢ. ሚዲያ” የተባለው ኢትዮጵያዊ ድርጅትም ፕሮግራሙን በዶላር በመሸጥ፣ የውጪ ምንዛሪ ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገባም የጣቢያው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አክለው ገልፀዋል፡፡
ደራሲያንና የፊልም ምሁራን በጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት ለማወቅ አዲስ አድማስ ሁለት አንጋፋ ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡ የጣቢያው ይዘት ለኢትዮጵያዊው ተመልካች ያን ያህል ይጠቅማል ብዬ አላምንም፤ ጉዳቱ ግን ከፍተኛ ነው ያለው ደራሲ ኃይሉ ፀጋዬ፤ የፕሮግራሙ ይዘት የአገር ውስጥ 30፣ የውጪው 70 እጅ መሆኑ ለአገር ውስጥ እጅግ ዝቅተኛ ትኩረት መሰጠቱን ያሳያል፤ ይሄ ደግሞ እየተንገዳገደ ያለውን የፊልም ኢንዱስትሪ ያቀጭጨዋል ብሏል፡፡
የጣቢያው የፕሮግራም ይዘት ከፍተኛ የባህል ወረራን ከማስፋፋቱም በላይ ለጥቂት ሰዎች የስራ እድል በመፍጠር በመስኩ የተሰማሩ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን ስራ እንደሚያሳጣም ደራሲው ገልጿል፡፡
ተቋሙ ገንዘብን መሰረት ያደረገ መሆኑን የገለፀው ኃይሉ ፀጋዬ፤ ይህ ደግሞ ኃላፊነት የጎደለው ስራ ነው ብሏል፡፡
የትያትር ባለሙያው ረዳት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ጀዋሬ በበኩሉ፤ “የጣቢያው መፈጠር ገንቢ ነገር አለው፤ ለምሳሌ የህብረተሰቡን የፊልም ማጣጣም አቅም ይጨምራል፡፡ ሆኖም ጣቢያው ለውጪ ፊልሞች የሚሰጠው ድርሻ ዝቅ ማለት አለበት” ሲል አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡
“ባህልን ባላገናዘበና ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችል ህግ ባልተረቀቀበት ሁኔታ በስፋት መልቀቁ ግን አደጋ አለው ያለው ፕሮፌሰሩ፤ መጀመሪያ ህግ መውጣት አለበት፤ ፊልሞቹ ባህልን፣ ስነ ልቦናንና፣ እምነትን ጠብቀው ተጣርተው የሚቀርቡና በህግ የሚመሩ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡ “በርግጥ ውድድር መኖር አለበት፤ ውድድር መኖር ያለበት ግን በእኩል የመወዳደሪያ ሜዳ ላይ ነው፡፡ ካልሆነ ግን የውድድር አምዱን ኢ-ፍትሃዊ ያደርገዋል፡፡ ይህ ለኔ ወንጀል ነው” ሲልም አስረድቷል ሙሉጌታ ጀዋሬ፡፡
በሳተላይት የሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፤ “በሳተላይት ለሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፍቃድ አልሰጥም፤ እነዚህ ጣቢያዎች ከውጪ አገራት ፍቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ከባለስልጣኑ እውቅና ውጪ ናቸው” ብሏል፡፡ ሆኖም ጣቢያዎቹ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጁአቸው ፕሮግራሞች ሲኖሩ ባለስልጣን መ/ቤቱ የብቃት ማረጋገጫን እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን የፕሮግራሞች ይዘት የሚቆጣጠርበት አሰራር ግን እንደሌለው ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡
ከትንሽ ጋር እንደመታገል ምን የሚያደክም ነገር አለ?!! ወረታው ዋሴ
ከትንሽ ጋር እንደመታገል ምን የሚያደክም ነገር አለ?!! ለኢትዮጵያውያን አብሮ መስራትና ሥርዓት መስርቶ መሄድ ከጊዜ ወደጊዜ ምን ያህል ከባድ እየሆነ እንደመጣ ለመረዳት ያለፉት አርባና ሃምሳ አመታትን ታሪካችንን ምስክር ነው፡፡ አለመተማመንና አምባጓሮ ሳይፈጥርበት ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ተቋም ለመፍጠር ምን ያህል እየተቸገርን እንደሆነ …
የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት IFM አስታወቀ – VOA
በዓለም በፍጥነት በማደግ ላይ ከነበሩ አስራ ሀገሮች ሰባቱ የአፍሪካ ሀገሮች ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ሆና ቆይታለች። የያዝንው የአውሮፓዊያን ዓመት ግን ይሄ ሁኔታ እንደሚቀየር ነው የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ (IMF)በየዓመቱ የሚያወጣው የዓለም ምጣኔ ሀብት ግምገማ ዘገባው አስታውቋል። ባለፈው ዓመት …
የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እድገት ለሚቀጥለው አንድ ዓመት እንደሚያሽቆለቁል የዓለም የገንዘብ ድርጅት IFM አስታወቀ – VOA Read more »
ትክክለኛውን ቴዲ አፍሮን ምን ያህሎቻችን እናውቀዋለን? (ኤርሚያስ ቶኩማ)
ብዙዎቻችን ቴዲ አፍሮን ከሙዚቃ ሥራውና ከሐገር ወዳድነቱ ባሻገር እምብዛም የግል ሕይወቱን እና ምን አይነት ሰው እንደሆነ አናውቀውም እርሱም ቢሆን ስለራሱ ማውራት ስለማይወድ እና ይህንን ፈፀምኩኝ ብሎ ስለማያወራ የቴዲን ማንነት በግልጽ ልናውቀው አልቻልንም ሆኖም ቴዲ አፍሮ እንደዚህም አይነት ሌላ ገፅታ አለው። ★ ሐምሌ 30,1998 ዓመተ ምሕረት በድሬዳዋ ደርሶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ30 ሺህ ብር […]
በካድሬዎች ስር የወደቀችው ቤተ ክርስትያን (አምዶም ገብረስላሴ)
ከአምዶም ገብረስላሴ ኣቶ መኮነን ኣስፋው በምርጫ 2007 ዓ/ም በተካሄደው ምርጫ ዓረና-መድረክን ወክለው በኣላማጣ ምርጫ ክልል ለክልል ምክር ቤት ተወዳድረው ህወሓትን ኣምበርክከዋል ዳሩ ድምፃቸው ተዘረፉ እንጂ። ኣቶ መኮንን በ1974 ዓም ወደ በረሃ ወጥቶ ያታገሉ ሲሆኑ ከነ ሓየሎም ኣርኣያና ገብሩ ኣስራት ጎን …