ዲያቆን ሙት!
አሊ ጓንጉል

ይህ ጽሁፍ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቅርቡ ‘“ሀገር ማለት ሰው ነው”! እስቲ ሙት በለኝ!’ ሲል ለለቀቀው ጽሁፍ መልስ ነው። … እስካሁን ድረስ “ሀገር ማለት ሰው ነው” የሚባል ዘፈን መኖሩን ሰምቼም አይቼም አላውቅም። በዚህ ስም የሚጠራ ዘፈን ኖሮ እኔ ያላወቅሁ እንኳን ቢሆንም፣ “ሀገር ማለት ሰው መሆኑን” ሊያስክድ የሚችል አንዳችም ነገር ያለ አይመስለኝም። በዚህ ስም የሚጠራ ዘፈን ጨርሶ ሳይኖር፣ የበድሉ ዋቅጅራን “ሀገር ማለት የኔ ልጅ … ሰው ነው …” በሚል ርዕስ የሚታወቀውን ታላቅ ግጥም እንዲሁ “ዘፈን” በማለት ለመተቸት ወይም ለማውረድ ከሆነ ደግሞ፣ ዲያቆኑን የባሰ የታሪክ፣ የኃይማኖት እና ከሁሉም በላይ የስነ-ጽሁፍ ድህነቱን ይናገርበት ይመስለኛል። ምክንያቱም ሀገር ማለት ሰው ነው! ላስረዳ።