UTC 16:00 የዓለም ዜና 220114
የዕለቱ ዜና
የዕለቱ ዜና
ከኣንድ ወር በላይ ለዘለቀውና ከ 10 ሺህ በላይ ሰዎች ለሞቱበት የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ውጊያ መፍትሄ ለመሻት ነገ ሐሙስ እዚያው ደቡብ ሱዳን ር/ከተማ ጁባ ውስጥ ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የምስራቅ ኣፍሪካ የልማት ቤይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ አባል ሓገራት መሪዎች ጉባዔ ቢሰረዝም የሰላም ጥረቱ ግን ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።
የጉባኤዉ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓትም ሰወስት ዓመት ያስቆጠረዉን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማቆም ከማለም ይልቅ የተፋላሚ ሐይላት መወነጃጀል፥ የየተፋላሚዎቹ ሐይላት ደጋፊዎች መወቃቀስ የጎላበት ነበር።
ሂዩማን ራይትስ ዎች የተሰኘው ዓለም ዓቀፋዊ የሰብዓዊ መብት ተንከባካቢ ተቐም በዛሬው ዕለት ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ በዓለም ላይ የ90 ኣገሮችን የሰብዓዊ መብት ይዞታ ገምግሟል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የሚካሄደውን ግጭት ለማስቆም የሚያግዙ ወታደሮችን ለመላክ ተስማምተዋል ። የአውሮፓ ህብረት የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ዘመቻና የጀርመን የአፍሪቃ ወታደራዊ ተልዕኮ የዛሬው አውሮፓ ና ጀርመን ዝግጅታች ትኩረት ነው ።
ፈረንሳዊው ፍራንስዋ ሎ ካድር በዋልደባ ገዳም እና መነኮሳት ላይ ጥናት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ ለቴሌቪዥን የሚቀርብ ፊልም አዘጋጃለሁ የሚል ሀሳብም አልነበረው።
የአዉሮጳ ህብረት መንግስት አልባ እየሆነች በመጣችዉ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ወታደሮችን ለመላክ ዛሪ ብራስልስ ላይ ተስማማ። የህብረቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ካለፈዉ አጋማሽ ጀምሮ ቀዉስ በተጠናወታት በዚችዉ ሀገር ወታደሮቻቸዉን የሚልኩት እየተጠናከረ የመጣዉን ዉጥረት ለመግታት ነዉ።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በእንግሊዝኛው ምህጻሩ UDJ ሊቀመንበርነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ።
ሊቀመንበርነታቸውን ብቻም ሳይሆን ከUDJ አባልነትም የተሰናበቱት ዶ/ር ነጋሶ ከዚህ በኃላ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ አልሳተፍም ብለዋል።
ግብፆች ሕይወት፥ ደም አካላቸዉን መስዋዕት ያደረጉበት አብዮት የምክር ቤት እንደራሴዎቻቸዉን፥ ለመጀመሪያ ጊዜ በነፃ እንዲመርጡ አስችሏቸዋል።ፕሬዝዳታቸዉንም እንደዚሑ።ሕገ-መንግሥትም አፅድደቀዋል።ዳር ግን አልዘለቀም።ከ1952 ጀምሮ የግብፅን የሚቆጣጠረዉ ጦር ሐይል የግብፅ ሠላማዊ ሕዝብ ፍላጎትና ምኞት እንዲሳካ ሥልጣኑን መልቀቅ አልፈቀደም።
የዓለም ዜና
የዓለም ዜና
የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የገጠሙትን አስከፊ ጦርነት ለማስቆም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የጀመረዉ የማደራደር ጥረት እስካሁን ተጨባጭ ዉጤት አላመጣም።
የደቡብ ሱዳን መንግሥት፤ ከአማጽያኑ ጋር በቅርቡ የተኩስ አቁም ሥምምነት ለመድረስ ተስፋ እንዳለዉ መግለጹን አሁን ማምሻዉን የደቡብ ሱዳን መንግሥትን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ። በሌላ በኩል በኢጋድ የቀረበዉ መደራደርያ ነጥብ በአማፅያኑ ተቀባይነት ማግኘቱን ተልጸዋል።
ከብዙ አዳጋች ሁኔታ በኋላ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመመስረት የተቃረበችው ቱኒዝያ ” ባለፈው ማክሰኞ ቤን አሊ የተወገዱበትን 3ኛ ዓመት አስባ ዋለች። የቱኒዝያ ሕዝብ ዓመፅ እና ቤን አሊ የሸሹበት ድርጊት ግብፅ፣ ሊብያ ፣የመን እና ሶርያን ለዓብዮት ማበረታታቱ አይዘነጋም።
የዕለቱ ዜና
የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦመር ሓሰን አልበሺር፣ ለሶሳት ቀናት ጉብኝት ትላንት አስመራ መግባታቸው ተዘግቧል።
በሶሪያ እየተካሄደ ያለውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማስቆም በሚቀጥለው ሳምንት በጄኔቫ ሲውዘርላንድ በተጠራው የሰላም ውይይት የሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎች መሳተፍ አለመሳተፋቸውን ዛሬ ቱርክ ኢስታምቡል ላይ የተሰበሰበው የተቃዋሚዎች ህብረት ይገልፃል ተብሎ ይጠበቃል።
በደቡብ አፍሪቃ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪቃ ዋንጫ ሻምፒዎና እንደቀጠለ ነው።
ሰሞኑን በሕንድ አንዲት ጀርመናዊት ወጣት እና ዴንማርካዊት እዛው ህንድ ውስጥ ተደፍረው ጉዳያቸው እያነጋገረ ይገኛል። በሕንድ ስለደረሱት የአስገድዶ መድፈር እና በኢትዮጵያ የሚደርሱ የወሲብ ጥቃቶች እንዲሁም ያለውን የፍትህ አሰራር በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንቃኛለን።
የዓለም ዜና
ለፍርድ ቤት ቃላቸውን የሰጡት 7 ኤርትራውያን ስደተኞች ናቸው ። ከመካከላቸው በተከሳሹ የተደፈረች የ18 ዓመት ልጃገረድ ትገኝበታለች ።
አስተያየት ሰጭዎቹ የሁለቱ ሃገራት የሰላም ውይይት ህዝባዊ ድጋፍ ሊያገኝ እንደሚገባ ከማሳሰብ አንስቶ መሠረታዊ የስርዓት ለውጥ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል ።
ጀርመን ውስጥ የውጭ ዜጎች ጉዳይ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚነሳ ሁሌም የሚያነጋግር ርዕስ ነው ። በአንድ ወገን የውጭ ዜጎች መበራከት ማህበራዊ ኑሮአችንን አዛብቶ ለችግር ይዳርገናል ሲሉ
በየቀኑ ኢትዮጵያውያን ከ 3 እስከ 4 በሚደርሱ ጀልባዎች የመን እየገቡ ነው ። እነዚሁ የመን የደረሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለእንግልት ና ለልዩ ልዩ ስቃይ መዳረጋቸውን ዘጋቢያችን አስታውቋል ።
የስጳኛውያኑ የሬአል ማድሪድ የእግር ኳስ ክበብ አጥቂ ፖርቱጋላዊ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2013 ምርጥ የወንዶች እግር ኳስ ተጫዋች ተብሎ የወርቅ ኳስ ተሸለመ።
በተለምዶ እሩቅ ምስራቅ ተብሎ በሚታወቀው የኢሲያ ክ/ዓለም ከጃፓን ባህር በስተምስራቅ በሰላማዊ ውቅኖስ፣ በደሴት መልክ የምትገኘው ጃፓን ስያሜዋም እራሱ በእነርሱ ቐቐ አተረጉዋጎም የጸኃይ መነሻ እንደማለት ነው።
ኤርትራ በበኩሏ ፣ አምባሳደሩ እንዳሉት ፤ ኢትዮጵያ በአሰብ ወደብ እንድትጠቀም ልትፈቅድ ይገባል።
ጀርመን ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የጸጥታ መረጃ ልውውጥን በተመለከተ አዲስ ስምምነት ለማድረግ የምትሻ ሲሆን ፤ በዚህ ረገድ የወደፊቱ ግንኙነት ምን መሆን እንደሚገባው ፤ የህዝብ እንደራሴዎቿን ም/ቤት ዛሬ አከራክሯል።
ውዝግብ ያዳቀቃት የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የሽግግር ምክር ቤት እንደራሴዎች ባለፈው ሳምንት የወረዱትን የቀድሞ ፕሬዚደንት ሚሼል ጆቶዲያን የሚተካ ለመመረጥ ጉባዔ ጀመሩ።
የዓለም ዜና
ከ7 ሳምንት በፊት ነበር ሶስት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የቤልጄምን ጦር ኃይል በፍርድ ቤት የከሰሱት። ይህም እኢአ በ2011 መጋቢት ወር ከሊቢያ ትሪፖሊ 72 ሰዎችን አሳፍራ ወደ ላምፔዱዛ ስትጓዝ የነበረች አንዲት ጀልባ የማዕበል አደጋ ከደረሰባት በኋላ በአካባቢዉ ከነበሩ ኃይሎች ርዳታ ባለማግኘታቸዉ ነው።
የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ከጦርነት በመሸሽ ላይ የነበሩ 200 ሰዎች መስጠማቸውን ገለጡ። የጦር ሠራዊቱ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ፊሊፕ አጉዔር፤ ነጭ ዐባይን ስታቋርጥ በሰጠመችው ጀልባ ተሣፍረው የነበሩት አብዛኞቹ ሴቶችና ሕጻናት ነበሩ።
በኩዌት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይ በሰው ቤት ተቀጥረው በሚሰሩት ላይ የተለያየ የመብት ረገጣ እንደሚፈፀም ተሰማ።
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በእንግሊዝኛ ምህጻሩ «ኦ ዲ ኤፍ» ወደ ኣገር ቤት ተመልሶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰኑን ኣስታወቀ።
የግንባሩ ፕሬዝደንት አቶ ሌንጮ ለታ እንደገለጹት ግንባሩ ከምስረታው ኣንስቶ ወደ ኣገር ቤት ለመመለስ ግልጽ አቐም ይዟል።
በዚህ በጀርመን ሀገር ፤ በስፋት የ 4ኛነቱን ደረጃ በያዘችው ከተማ
በኮሎኝ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው የእስፖርትና ባህል ማሕበር ፤
ከትናንት በስቲያ ፣ ረዘም ላለ ጊዜ የከተማይቱ ኑዋሪዎች የሆኑና
በቅርብ ጊዜም የመጡ በጠቅላላ 250
እ ጎ አ ከ 2001 – 2006 የእሥራኤል ጠ/ሚንስትር የነበሩትና ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ የአልጋ ቁራኛ ሆነው የቆዩት አሪዬል ሻሮን ፤ በዛሬው ዕለት በደቡብ እሥራኤል በነጌቭ በረሃ በራሳቸው የአርሻ ቦታ በወታደራዊ ሥነ ሥርዓት ግብዓተ መሬት ተፈጽሞላቸዋል።
አርየል ሻሮን።ሞቱ እንዳይባሉ ይተነፍሳሉ።አሉ እንዳይባሉ አይሰሙም፣ አይለሙም።ስምንት አመት።ሐኪሞች «ከስቃይ መገላገያ» በሚሉት ደንብ እንዳይረዷቸዉ «አይሁድ ነብስ አያጠፋም» የሚለዉ ሕግ አገዳቸዉ።እሳቸዉን ግን በነብስ አጥፊነት የሚወነጅሏቸዉ ብዙ ናቸዉ
ዛሬ፤ በመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ መውሊድን (የነቢዩ መሐመድን የልደት በዓል)አክብሮ መዋሉን ዘጋቢአችን ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።
የሳውዲ ዓረቢያ መንግስት ሕገ ወጥ ስራ ፈላጊዎች ያላቸው የውጪ ዜጎች እንዲወጡ ካዘዘ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ካለፈው ህዳር ወር እስካሁን በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ከ140,000 የሚበልጡ ዜጎችን ወደ ሀገር መልሶዋል።
በደቡብ ሱዳን ካለፈው ታህሣሥስድስት ወዲህ የቀጠለውን እና ከአንድ ሺ በላይ ህዝብ ያጠፋውን፤ ከ 200,000 በላይ ህዝብ ውጊያ ለማስቆም በተፋላሚ ዎቹ ወገኖች ተወካዮችመካከል በኢጋድ ሸምጋይነት በአዲስ አበባ
የእስራኤል መንግሥት አዲስ ያወጣውን የስደተኞች ሕግ እና በስደተኞች ላይ የሚያደርሰዉን በደል በመቃወም በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃዉያን ሰሞኑን በተከታታይ የአደባባይ ሠልፍ ሲያካሂዱ ሰነበቱ።
ቤቶች የተሰኘው ድራማ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ዝናን አትርፏል። ምዕራፍ፣ ትርፌ እና እከ የዛሬው እንግዳዎቻችን ናቸው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በከፋ ዞን፣ ኣርሶ ኣደሮች ያለፍላጎታችን ማዳበሪያ እንድንገዛ እየተገደድን ነው ኣሉ።
ማዳበሪያ ኣንቀበልም ያሉ በርካታ ኣርሶ ኣደሮች ደግሞ ከሚደርስባቸው እስራትና ወከባ በመሸሽ በየጥሻው እየተንከራተቱ ነው ተብሏል።
።ጄቶዲያ ንጃሚና ቻድ በተደረገዉ የማዕከላዊ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ECCAS) ጉባኤ ላይ ሥልጣን መልቀቃቸዉን ሲያዉጁ፥ የአዉሮጳ ሕብረት ደግሞ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ለማዝመት ማሰቡ ከብራስልስ ተሰምቷል
በከፍተኛ የህክምና ክትትል ሥር ያለው የፎርሙላ አንድ ፈጣን የመኪና እሽቅድድም ሰባት ጊዜ ሻምፕዮን ሹማኽር ዛሬ 45ተኛ ዓመቱን ደፍኗል ። አድናቂዎቹ ዛሬ በተኛበት ሆስፒታል አቅራቢያ ተሰባስበው ልደቱ አስበዋል ።