ሁለተኛዉ ዙር የሶርያ የሰላም ድርድር DW Amharic February 11, 2014 Tagged with Amharic, amharic news, Ethiopia, ethiopian news in amharic, Ethiopians, News in Amharic ሁለተኛዉ ዙር የሶርያ መንግሥትና የመንግሥቱ ተቃዋሚዎች ህብረት ድርድር ዛሬ በጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ተጀመረ። ሁለቱ ተፋላሚ ሃይላት ባለፈው ወር መጨረሻ ያደረጉት የመጀመርያዉ ዙር ድርድር ያለምንም ዉጤት ነበር የተጠናቀቀው። በሳምንቱ መጨረሻ የተመድ ለሶርያውያኑ የሆምስ ከተማ አስፈላጊውን የሰብዓዊ ርዳታ ማድረስ አልቻለም።