በአዲስ አበባ የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ

ዛሬ አዲስ አበባ በበርካታ አከባቢዎች ታክሲዎች ስራ አቁመው ውለዋል። አዲሱ የስምሪት መመሪያ ጥቂቶችን ለመጥቀም የወጣ ነው ሲሉ ባለታክሲዎቹ አማረዋል።

የዛሬ ሳምንት ሰኞ የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የአዲስ አበባ ታክሲዎችን ስምሪትና የዋጋ ተመን የሚያሳይ አዲስ መመሪያ አዋጣ። መመሪያው አርብ ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ ሆነ። አርብ በተወሰነ ደረጃ ዛሬ ደግሞ ከፊል አዲስ አበባን የሸፈነ የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ተደረገ። ዘጋቢያችን ታደሰ እንግዳው ያነጋገራቸው አንዳንድ የታክሲ አሽከርካሪዎች፤ ገንዘብ ተቀባዮችና ተራ አስከባሪዎች እንደሚሉት መመሪያው ጥቂቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣ ነው። ዛሬ አዲስ አበባ በከፊል ጭር ብላ ነው የዋለችው። መንግስት የተፈጠረው ችግር ጊዜያዊ ነው። ዘላቂ መህትሄ እየፈለኩለት ነው ይላል። ያዳምጡ

ታደሰ እንግዳው
መሳይ መኮንን
ሂሩት መለሰ