ወያኔ አባይን ለመገደብ ብቃት የለውም – ሰዬ አብረሃ

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ወያኔ/ኢሕአዴግ ለሕዝብ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄ ተገቢዉን መልስ እንዲሰጥ ተቃዋሚዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት ባጭሩ) ከፍተኛ ባለሥልጣን ጠየቁ። የፓርቲዉ ሥራ አሥፈፃሚ አባል አቶ ስዬ አብረሐ እንደሚሉት ኢሕአዴግ አሁን የሚከተለዉ መርሕ ከጭንቀት የመነጨ ነዉ።አንድነትን በአባልነት የሚያስተናብረዉ ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ እና የኢትዮጵያ መንግሥት በየሰበብ አስባቡ እየተወቃቀሱ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሠ እንግዳዉ አቶ ስዬን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል። ያዳምጡ