በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር • ‹‹አባላቶቻችን በትግስቱ ደጋፊዎች የእጅ ጽሁፍ በሚቀርብ አቤቱታ በቀጥታ እየተሰረዙ ነው›› ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያስመዘገባቸው ዕጩዎች በትግስቱ አወሉ ደጋፊዎች የእጅ ጽሁፍ በሚያቀርቡት አቤቱታ ምርጫ ቦርድ…

The post ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን መሰረዙን ቀጥሏል appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የማነ ናግሽ የአገር መከላከያ ሠራዊት ብሔራዊ ተዋጽኦ የጠበቀና የተመጣጠነ መሆን ያለበት ቢሆንም እንደ የተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ የሚከፋፈል እንዳልሆነ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላላ ኤታ ማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ተናገሩ፡፡ በአማራ…

The post ‹‹የአገር መከላከያ ሠራዊት ተዋጽኦ እንደ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ የሚከፋፈል አይደለም›› ጄኔራል ሳሞራ የኑስ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለመዋሀድ የሚያስችለውን ቅድመ ስምምነት ማድረጉንና በአንድ የምርጫ ምልክት ለመወዳደር መወሰኑን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁን የገለጸው የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት (ኦሕዴኅ)፣ ከቦርዱ ጋር መግባባት ባለመቻሉ ውዝግብ ተፈጥሯል፡፡ ኦሕዴኅ…

The post በሰማያዊ ፓርቲ ምልክት መወዳደር አለብኝ የሚለው ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ጋር ተወዛገበ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

The story about Ethiopian Hero Ato Andargachew Behonegn, who lost his life while saving 58 people.
Admas:- የ58 ሰዎችን ነፍስ ያተረፈው ብዙም ያልተነገረለት ሰው! Dying while saving 58 souls – A story of an Ethiopian Mechanic and driver.
ከሰሞኑ በተደጋጋሚ የመኪና አደጋ ከአገር ቤት መስማት እየተለመደ መጥቷል። መኪና ተጋጨ ሁሉም ሞቱ የሚል ዜና በበዛበት በዚህ ወቅት፣ ከሶስት ሳምንት በፊት ራሱ ህይወቱን አጥቶ፣ ግን 58 ሰው ስላተረፈው ሰው ታሪክ ልናካፍላችሁ ወደድን።
_______
ጃንዋሪ 28 /2015 ዓ.ም ስድሳ ሰው የጫነ አውቶቡስ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ይጓዝ ነበር፣ ከቀኑ 12 ሰአት አካባቢም ልክ…

ፍቃዴ ለቅቄያለሁ ያሉት ዳኛ ደግመው ተሰይመዋል! 

ለሶስት መቶ ቀናት በእስር ላይ የቆዬት ጦማርያን ለ20ኛ ጊዜ “ፍርድ ቤት” ቀርበዋል፡፡ 

ትላንትና የካቲት 11 ቀን ገዥው ህወሃት 40ኛ ልደቱን ባከበረበት በተመሳሳይ ቀን በነሶልያን ሽመልስ የክስ መዝግብ “ፍርድ ቤት” የቀረቡት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡

“የፍርድ ሂደቱ” ጠዋት ሊጀመር ተቀጥሮ የነበረ ቢሆንም ያለቅጥ ዘግይተው የተሰየሙት ዳኞች ተከሳሾቹ ለከሰአት ስምንት ሰአት ለሚጀምረው ችሎት አንዲገኙ ለከሰአት ተቀጥረው ነበር፡፡ ከሰአት ስምንት ሰአት ላይ ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት ባሉት ሰአታት ልደታ ፍርድ ቤት ጊዜያቸውን ያሳለፉት ጦማርያን ከሰአት በኋላ “ፍርድ ቤት” ቀርበዋል፡፡ ችሎቱ ላይ ባለፈው ቀጠሮ አቤቱታ ቀርቦባቸው አቤቱታውን “ፍርድ ቤቱ” ባይቀበለውም በገዛ ፍቃዴ ከችሎቱ ለቅቄያለሁ ያሉት ዳኛ ሸለመ በቀለ መልሰው ችሎቱን ሰብስበዋል ፡፡ ከችሎቱ ለመነሳታቸውም ሆነ ላለመነሳታቸው የተሰጠ ማብራሪያ ሳይኖር ከሁለተኛ ተከሳሽ ከጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ጀምሮ እያንዳንዳቸው ተከሳሾች በስም እየተጠሩ የተጠረጠሩበትን ወንጀልመፈጸም እና አለመፈጸማቸውን ቃል አንዲሰጡ የተጠየቁት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ሲመልሱ

በፍቃዱ ሃይሉ – እኔ ክሱን ከአምስት ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ አንብቤዋለሁ ምንም የሚገባ ነገር አላገኘሁበትም ሲል ዳኛው አቋርጠውት አሁን ምንም አይነት ዝርዝር ውስጥ አልገባም በማለታቸው “የሽብር ወንጀል ለመፈጸም አላሰብኩም አልፈጸምኩት አልፈጽምም ሽብር ተፈጽሞብኛል” ሲል መልሷል፡፡ ከበፍቃዱ በማስከተል ቃሉን የሰጠው ጦማሪ ናትናኤል “ህግ የሚከበርበት አገር ቢሆን ኖሮ ዛሬ እዚህ ቦታ መቆም የነበረባቸው አሳሪዎቼ ናቸው ፣ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም “ያለ ሲሆን ጦማሪ አጥናፍ “ወንጀል አልፈጸምኩም” ፣ ጦማሪት ማህሌት “ምንም አይነት ወንጀል አልፈጸምኩም” ብላ ቃሏን ስትሰጥ ጦማሪ አቤል በበኩሉ “ክሱ ግልጽ አይደለም” ሲል ዳኛው ምንም አይነት ተጨማሪ ነገር ሳያስፈልግ ቀጥታ ቃል እንዲሰጥ ማሰጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም አቤል “የህብረተሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ምንም አይነት የሽብር ተግባር አልፈጸምኩም አላሴርኩም” ሲል በቀጥታ ክሱ ላይ የተጠቀሰውን አንቀጽ ጠቅሶ ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ጦማሪ ዘላለም በበኩሉ የተከሰሰበት ወንጀል አንዲብራራለት የጠየቀ ሲሆነ “ፍርድ ቤቱ” ወደኋላ አንመለስም የሚል ማስፈራሩያ በማሰማት በቀጥታ ቃሉን እንዲሰጥ ሲነገረው “የተከሰስኩበት ክስ ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ የእምነት ክህደት ቃሌን መስጠት አልችልም” በማለት በመናገሩ ቃሉን ሳይሰጥ ቀርቷል ፡፡ በህጉ መሰረትም ጥፋተኛ አይደለሁም አንዳለ ተቆጥሮ ተመዝግቧል፡፡
ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ -” ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም እኔ ነጻ ሰው ነኝ ” ስትል ጋዜጠኛ አስማመው “ወንጀል አልፈጸምኩም” ጋዜጠኛ ተስፋለም ደግሞ “እኔ ጋዜጠኛ ነኝ ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም እኔ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም” ብሏል፡።

የእምነት ክህደት ቃል መስጠቱነ ተከትሎ አቃቤ ህግ ምስክሮቸን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠኝ ብሎ በጠየቀው መሰረት ከአርባ ቀን በኋላ ለመጋቢት 21-23 ለሶስት ቀናት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ለማቅረብ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ የተከሳሾች ጠበቆች በበኩላቸው አለ የተባለው የሲዲ ማስረጃ ግልባጭ ስላልተሰጠን አንዲሰጠን ብለው የጠየቁ ሲሆን “ፍርድ ቤቱ” እንዲሰጣቸው ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

የተከሳሾች አያያዝ 

ባለፈው ችሎት ወቅት ጦማሪ አቤል ዋበላ ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ ማረሚያ ቤቱ መልስ አንዲሰጥ መጠየቁ የሚታወስ ሲሆን የጦማሪው ጠበቃ ተከሳሹ ከማረሚያ ቤት አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር ችግሩን ስለፈቱት አቤቱታውን መቅረቱን ለ”ፍርድ ቤቱ” ተናግረዋል፡፡ ጦማሪ አቤልም በበኩሉ ተጨማሪ የመብት ጥሰት አስካልደረሰብኝ ድረስ ባለፈውን አቤቱታዬን ትቼዋለሁ ያለ ሲሆን ባለፈው ተቀምቶ የነበረው የጆሮ ማዳመጫ መሳሪያም ተመልሶለታል ፡፡ ነገር ግን የሴት ተከሳሾች አያያዝ አንደአዲስ አስቸጋሪ እንደሆነ የሚያያቸው ሰው ገደብ እንዳልተነሳ እና አሁንም በጥቂት ሰዎች ብቻ አንደሚጠየቁ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ በማቅረባቸው የእነሱን አያያዝ አስመልክቶ ማረሚያ ቤቱ መልስ አንዲሰጥ ለመጋቢት 18 ጠዋት ቀጠሮ ተሰጥቶ ችሎቱ ተጠናቋል ፡፡

የዞን9 ማስታወሻ 

ሶስት መቶ ቀን እስር እና ከሃያ ቀጠሮ በኋላ የተጀመረው ይህ መደበኛ “የፍርድ ሂደት” እንደተለመደው መጓተቱ ሳያንስ በአንድ ወር በላይ የሚፈጅ ቀጠሮ መሰጠቱ ለክሱ ፓለቲካዊነት አንዱ መገለጫ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ሶስት ወር በፈጀ ምርመራ ሂደት ውስጥ ተገኙ የተባሉትን ማስረጃዎች ለማቅረብ የ40 ቀን መዘጋጃ ጊዜ አንደማያስፈልግ ለማንም ሰው በግልጽ የሚታይ ሃቅ ነው ፡፡ በመሆኑም ባለፈው የቀረበው አቤቱታ ላይ አንደተገለጸው ዳኛውም ሆነ የፍትህ ስርአቱ አላግባብ መታሰራችን እና መከሰሳችን ሳያንስ አንድን “የፍርድ ሂደት” በማራዘም አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት መቀለጃ እየሆነ አንደሆነ እያሳዬን ነው፡፡ የዞን9 ነዋሪያንና አንባቢዎችም ይህ ፍትህ ስርአቱ ስም የሚደረግ ቀልድ አንደማይጠፋቸው አናምናለን ፡፡

የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች በመልካም ጤንነት በጠንካራ ስነልቦና እና በራስ መተማመን ስርአቱን ፊትለፊት እየተገዳደሩ ያሉ ኩሩ ልበ ሙሉ ወጣት ዜጎች ናቸው ፡፡ የተለየ ሃሳብን በሚያራምዱ ጥቂት ወጣቶች የተሸበረውን መንግሰት የምናፍርበት ያህል በጓደኞቻችን አንኮራለን ፡፡

የዞን9 ኩራት ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በድጋሚ መልካም ልደት
ስለሚያገባን እንጦምራለን ፡፡ 

Blogger Befeqadu Hailu drawing by Melody Sundberg

ዞን9
#Ethiopia #FreeZone9Bloggers @FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsmamaw 

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-‹‹ነጻነትለፍትሃዊምርጫ›› በሚልመርህ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓም በ15 ከተሞች እንደሚካሄድ ትብብሩ አስታውቋል። የሙስሊም ማህበረሰቡ ታህሳስ 10፣ 2007 ዓም  በኑር መስጂድ ፣ የካቲት 6፣ 2007 ዓም ደግሞ በአንዋር መስኪድ ያደረገው ተቃውሞ  እንዲሁም የባህርዳር ከተማ ህዝብ ታህሳስ 10፣ 2007 ዓም ያሳየው ህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል በሃይል ሊዳፈን ቢችልም እንደማይጠፋ ትምህርት ሰጥቷል …

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ  (ህወሃት) የትጥቅ ትግል የጀመረበት 40ኛ ኣመት በዓል በስኬት ላይ ብቻ የተመሠረተና ከበሮ ድለቃ የበዛበት የህወሃትን ጉድፎች የተደበቁበት ሆኖ እየተከበረ መሆኑ አሳዛኝ ነው ሲሉ የቀድሞ የድርጅቱታጋይገለጹ፡፡ ስማቸውእንዲገለጽያልፈለጉትየድርጅሩ የቀድሞታጋዮች ለኢሳት በላኩት መልእክትህወሃትየደርግአገዛዝበትጥቅትግል ለማሸነፍከሌሎችየትግልሃይሎችጋርበጣምራናበተናጠልሲታገልመቆየቱናአስከፊውንስርኣትመገርሰሱመልካም ነገር መሆኑ ባይካድም፣  ድርጅቱበሺየሚቆጠሩታጋዮቹን ለሞት ዳርጎ መንግስታዊስልጣን ከተቆናጠጠበሃላየታገለለትዓላማበመርሳትጥቂትሹማምንትራሳቸውንናቤተሰቦቻቸውንየሚያበለጽጉበት፣ቡድናዊ ወገንተኝነትበመመስረትብዙሃኑንያገለለስርዓትእንዲፈጠርአስተዋጽኦአድርጎአልብለዋል፡፡ ህወሃትመንግስታዊስልጣንላይበቆየባቸውባለፉት 23 ኣመታትዴሞክራሲ፣የህግየበላይነትእናየሰብዓዊመብት ጥበቃለማክበርናለማስከበርመታገሉንበመርሳትደጋግሞከሚረግመውየደርግስርዓትባልተናነሰአፋኝስርዓት እየገነባመምጣቱየፓርቲውንመክሸፍቁልጭአድርጎያሳያልሲሉ እነዚሁ ታጋዮች …

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በኮምቦልቻ ከተማ በቡራሮ አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው የተመላሽ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመንግስት ደግፋቸውንና ታማኝነታቸውን እንዲገለጹ በተጠየቁበት ወቅት እስካዘሬ የት እንደወደቅን ሳትጠይቁን፣ አሁን ምን ስለተገኘ ነው በማለት ውድቅ አድርገዋል። ያለፈው አልፏል ለወደፊቱ እንደጋገፍ በሚል ካድሬዎች የማግባባት ስራ ቢሰሩም ፣ የተመላሽ ሰራዊት አባላት ሳይቀበሉት ቀርተዋል። አቶ መለስ ጽፈውታል የተባለውን ማንዋል  ለማስተማር በሚዘጋጁበት ወቅት ፣ …

ማክሰኞ የካቲት ፲፩ ቀን ፪ሺህ፯  ዓ.ም.  ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፲፩ የትግሬ ወያኔ በኃሣብ፣ በዕቅድ እና በተግባር ፀረ-ዐማራ፣ ፀረ-ኢትዮጵያ እና ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆነ ድርጅት መሆኑን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ያረጋገጠው ሃቅ ነው።…

The post ምን እየጠበቅን ነው? «የትግራይ ሪፑብሊክ ድንበር አል-ወሃ ድረስ ነው» -ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

እኛ የታዘዝነውን ነው የፈፀምነው አቶ ታደሰ ሻረው/ የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ፡፡ ዛሬ በቀን 10/06/2007 ዓ.ም በደቡብ ወሎ የሰማያዊ እጩዎን የማፅዳት ዘመቻ አንዱ አካል የሆኑት የኮምቦልቻ ሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች በይፋ ታግደው ያስገቡት ዶክሜንት ተመላሽ ተደርጎላቸዋል፡፡ በትናንትናው እለት በአቶ ትግስቱ አወሉ ተወክያለሁ የምትለው ወ/ሮ ሰብል ይመር የተባለች የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪ በተሰጣት ተልእኮ መሰረት ተወስኖ የመጣላትን ውሳኔ በደቡብ ወሎ […]

ህዝቦች እኩልነት ያልተረጋገጠባት ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰብ መብቶች ለይስሙላ በሚሰበኩባት አገር ዜጎች ህግ ይከበር ብቻ ስላሉ በሌላው አለም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አሸባሪ ተብለው ወህኒ የሚወርዱባት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ምሁራን ከአያት ቅድማያቶቻቸውን የተረከቡትን እምነታቸውን በነጻነት ለማካሄድ ሲሰሩ ታፍሰው ለ እስር የተዳረጉባት አገር ፡ እያለማን ነው እየሰራን ነው በሚል ሽፋን ዘረፋ ላይ እና ዜጎችን ማሳደድ መግደል ማፈን እና ማሰር […]

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ ቀርሳ በተባለ ስፈራ ትላንት ማምሻውን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

አደጋው የደረሰው ትላንት ምሽት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ሲሆን፥ ወደ አዲስ አበባ ይመጣ የነበረ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው…

በሜዴትራንያን ባህር በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ በጉዞ ላይ ህይወታቸው የሚያልፍ ስደተኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት በመጠኑ ቀንሶ ነበር ። ሆኖም ባለፈው ሳምንት ቁጥራቸው ከ300 በላይ የተገመተ ስደተኞች የሜዲቴራንያን ባህር ሲሳይ ሆነዋል ። የቀጠለው የባህር ስደተኞች እልቂትና መላው የዛሬው ትኩረት ነው ።

አፍሪቃ ዉስጥ በየዓመቱ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ልጃገረዶች በዘልማዳዊዉ የአኗኗር ይትበሃል መሠረት የመዋለጃ አካላቸዉ ይተለተላል ወይም ለዚህ ችግር የተጋለጡ መሆናቸዉን የዓለም የጤና ድርጅት ይገልፃል።

የዩሮ ቀውስን ተከትሎ ባለፉት ዓመታት በግሪክ ላይ የተጣለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እና የቁጠባ ርምጃ በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጣው አዲሱ የግሪክ መንግሥት እንደማይቀበል አስታዉቋል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የጀርመን ትምህርት ቤት ትናንት የተመሰረተበትን 60 ዓመት አከበረ። በነዚህ ዓመታት ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እና ጀርመናውያንን አስተምሮ ለከፍተኛ የሥራ ደረጃ እንዳበቃ ተነግሮለታል።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ሃዲድ በተሽከርካሪዎች ጉዳት እየደረሰበት ነው። መንገደኞችም የባቡር መከለያ አጥሮችን በመዝለል መሻገር መጀመራቸው ለተሽከርካሪ እና ባቡር ትራንስፖርቱ ስጋት ሆኗል። በአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ደህንነት ባለሙያ ሁኔታው ትኩረት እንደሚያሻው ተናግረዋል።

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሁለተኛ ዙር የሠላማዊ ትግል ጥሪውን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላለፈ፡፡ ትብብሩ የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ከተሞች ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በሳምንት አራዝሞ ለየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ማስተላለፉንም አስታውቋል፡፡

ትብብሩ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ገዢው ፓርቲ የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድም የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተለያዩ የህዝብ እንቅስቃሴዎች መገንዘቡን ገልጹዋል፡፡ ትብብሩ ምርጫን በተመለከተ እንዳስታወቀው ኢህአዴግ ስለመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው መሆኑን በዚህ የምርጫ ወቅት በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ እየወሰደ ያለው ህገ-ወጥ እርምጃ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

‹‹ለውጡ የሚመጣባቸው አምባገነኖች ድንገተኛ ከፍተኛ ፍርኃትና ሥጋት በማሳደሩ ህገ-መንግሥቱን በመጨፍለቅ በግልጽና በአደባባይ ህገ-ወጥ ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን ለመውሰድ መገደዳቸው፣ ይህም የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት በማሳደግ ህዝባዊውን ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገሩ የበለጠ ግልጽ ሆኗል›› ብሏል ትብብሩ፡፡

ትብብሩ አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ የአገራችንና ዜጓቿ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሁለት አማራጮች ላይ የተንጠለጠለ ነው ያለው መግለጫው፣ አንድም ያለውን አምባገነናዊ ሥርዓት ተቀብሎ የጭቆና ቀንበር ተሸክሞ በከፋ ውርደት ሥር ሰጥ- ለጥ ብሎ መገዛት፣ አሊያም አምባገነንነትና ጭቆናን ‹‹በቃ›› በማለት በሕዝባዊ የተቀናጀ ሰላማዊ ትግል ለአገራችን ሉዓላዊነትና የዜግነት ክብራችንን ለማስመለስ በህገ መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን ትግላችንን እስከማይቀረው ለውጥ ድል ደጃፍ ድረስ በቆራጥነት መቀጠል ናቸው ብሏል፡፡

በዚህም ትብብሩ ህገ-መንግስታዊ መብትን በመጠቀም በህግና በሥርዓት ትግሉን ለመምራት መዘጋጀቱን በመግለጽ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የትግል ጥሪውን እንዲቀላቀሉት አሳስቧል፡፡ ስለሆነም ትብብሩ ‹‹ኢህአዴግነት ከዜግነት በላይ›› ለሆነባቸው የሥራ ዋስትናቸው፣ ዕድገትም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሙያቸው፣ በልምዳቸው፣ ክህሎታቸው፣ በመሳሰሉት ባልተመሰረተ መልኩ በደል እየደረሰባቸው ላሉ ሁሉ የትግል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

‹‹የህወኃት/ኢህአዴግ ተራ አባላትና ካድሬዎች፤ የፖለቲካ ልዩነት የተለያየ አመለካከትና ሀሳብ ማራመድ ጤናማ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ መገለጫ እንጂ እንደሚነገራችሁ ‹‹ጠላትነት›› ባለመሆኑ፣ ትግላችንም ለሠላማዊና ህጋዊ የሥልጣን ሽግግር እንጂ በናንተ ‹‹መቃብር›› ላይ አዲሱን ሥርዓት የማቆም፣ የነበረውን አጥፍቶ ከዜሮ የመጀመርና እናንተን የማጥፋት ዓላማ እንደሌለው ተረድታችሁ፣ ተቃዋሚዎች እንደናንተው ኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያና ህዝቧ የሚጨነቁ መሆናቸውን በመረዳት ተቃዋሚዎችን እንደ‹‹ ጠላት›› ከመመልከት አስተሳሰብ ራሳችሁን ነጻ እንድታወጡ›› ሲልም ትብብሩ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ወጣቶችና ሴቶች በተለይም የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች፣ መምህራንና ተማሪዎች በተለይም የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የእምነት ነጻነት መብት ጠያቂ የማኅበረሰብ አባላት፣ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፣ የፍትህ አካላት፣ የዴሞክራቲክ ፓርቲዎች አባላት፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ሰላማዊ ታጋዮች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵዊያን/ዲያስፖራዎች እና ሌሎችም ጥሪው የተላለፈላቸው አካላት መሆናቸውን መግለጫው አትቷል፡፡

በመሆኑም፣ ‹‹በምናርገው አገራዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በአንድነትና በቆራጥነት እንድትሰለፉ፤ የካቲት 22/07 በየከተሞቹ በቦታውና በሰዓቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን አበክረን እናቀርባለን›› ብሏል የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር፡፡

የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሁለተኛ ዙር የሠላማዊ ትግል ጥሪውን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላለፈ፡፡ ትብብሩ የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ከተሞች ሊያደርገው አቅዶት…

The post የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር ለየካቲት 22 2007 ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ጠራ:: appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

Image
የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ትግል የሁላችንም ነውና በጋራ እንነሳ!

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ትብብራችን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሠላማዊ ትግል ፕሮግራም ካደረገው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የተከሰቱትን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመገምገም ሁለተኛ ዙር ፕሮግራሙን ነድፎ ለምርጫ ዕጩዎችን የማስመዝገብ ተግባር ጎን ለጎን ለተግባራዊነቱ በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ የዚህ የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ማጠቃለያም የካቲት 15 /2007 በተመረጡ 15 የአገራችን ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ የሚደረጉ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በመነሳት የዛሬው መግለጫ ለየካቲት 15 የታቀደውን በ15 ከተሞች የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ፕሮግራም በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ወደ የካቲት 22/07 መተላለፉን ለማሳወቅና ትብብራችን እስከ ዛሬ ያደረገውን ሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት፣ወቅታዊነትና ትክክለኝነት በተጨባጭ በማረጋገጥ፣የተያያዝነውን ሰላማዊና ህዝባዊ ትግል እንዴት ማስቀጠልና ውጤታማ ማድረግ ስለሚቻልበት የገዢዎቻችንን ከግምት ያለፈ የፍርኃትና ስጋት ደረጃን ያገናዘበ ስልት መቀየሳችንን ፣ የቆምንበትን ህገመንግስታዊነትና ህጋዊነት እንዲሁም የትግሉን ትኩረት የሚመለከቱ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የደረስንበትን ጭብጥ ለህዝባችን በዝርዝርና በስፋት በማቅረብ ለቀጣዩ ትግል ጥሪያችንን ለማቅረብ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት የተደረሰባቸው ጭብጦች፡-
1.ገዢው ፓርቲ/መንግስት የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድ የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ በረቀቀ ስልት እንደሚቀጥል የሙስሊም ማኅበረሰቡ ታህሳስ 10/07 ዓ.ም በኑር መስጂድ፣ የካቲት 06/07 በአንዋር ካሰማውና የትግሉን ቀጣይነት ካረጋገጠበት ፍጹም ሠላማዊ በሆነና አንድም ጉዳት ባልደረሰበት የተሳካ የተቃውሞ ድምጽና ክንዋኔ ተረድተናል፤

2. በታህሳስ 10/2007 ዓ.ም ተመሳሳይ ዕለት የባህር ዳር ከተማ ህዝብ ሃይማኖት፣ ዘርና ሌሎች ልዩነቶችን ወደጎን አድርጎ ፣ገዢው ፓርቲ በዘረጋው የአንድ ለአምስት የደህንነት መዋቅር ሳይጠለፍና ሳይገታ፣ በአንድነት ያሳየው ህዝባዊ እምቢተኝነትም አፈና የቱንም የህዝብ ጥያቄ የማፈን አቅም የሌለው መሆኑን ይልቁንም ትግሉን ወደ ግብታዊነት ሊመራ እንደሚችል ተገንዝበናል፤

3. ገዢው ፓርቲ/መንግስት በመንግስት መዋቅሮችም ሆነ በህዝቡ ማኅበራዊ ግንኙነት እያደረሰ ያለው ጭቆና/የመብት ረገጣው፣ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት…/ እና ከህዝብ የመሸከም አቅም በላይ የሆነው የኑሮ ውድነት፣የመከፋፈልና የጥላቻ ፖለቲካ … የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት እያሳደገው መምጣቱን ፣የተባበረና የተቀናጀ አመራር ካገኘ ህዝቡ ለለውጥ ያለውን ጥማትና ዝግጁነት አስገንዝቦናል፤

እነዚህ ሲጠቃለሉም-ገዢው ፓርቲ/መንግስት ስለመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው በመሆኑ ለዚህ የተቋቋመውን የዲሞክራሲ ተቋም -የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቁጥጥሩ ሥር በማዋል በጠንካራ ፓርቲዎች የውስጥ ጉዳይ በማስገባት ከመጪው ምርጫ ለማግለል ቆርጦ መነሳቱን ፣ ለዚህም አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎችን በሚመለከት በቦርዱ የተላለፈው ፖለቲካዊ ውሳኔና ፍጻሜው ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ለቀጣዩ ምርጫ ዕጩዎችን ለማስመዝገብ በተንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ላይ በተለይ በኦሮሚያ፣በአማራና በደቡብ ኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ያሉት ተመሳሳይ ህገወጥ ተግባራት ነገ ወደ ትብብራችን አባላትና ሌሎች ፓርቲዎች ውስጥ በግልጽና በቀጥታ የማሸጋገር አቅጣጫ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ኢቢሲ ያቀረበው በህገመንግስታዊው የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካዊ ሥርዓት የተቀመጠውን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የመኖር ትርጉም ዋጋ የሚያሳጣው ‹‹መንግስትንና የመንግስት አስፈጻሚዎችን ከተቻችሁ፣ካላከበራችሁ ወይም ጸጥ ለጥ ብላችሁ የምርጫ አጃቢ ካልሆናችሁ እስከ 15 ዓመት ትታሰራላችሁ›› የሚል አንድምታ ያለው በ ‹‹ባለሙያዎች ትንታኔ ›› ሥም የተላከው የማስፈራሪያ መልዕክትና የሌሉ የፈጠራ ክሶችን ለመፈብረክ በአባል ፓርቲዎቻችን ላይ ‹‹የሞተ ጉዳዩን ከመቃብር በመቀስቀስ›› እና በአዲስ መልክ የተጀመረው የሚዲያ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻም በግልጽ ያስተላለፈው ይህንኑ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የትብብራችን አባል ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ወደ ምርጫው በአንድ ምልክት ለመወዳደር በዕጩነት በቀረቡበትና በሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ምዝገባ ላይ በምርጫ ክልል ክስና ቅሬታ ባልቀረበበት ከምርጫ ጋር ከተያያዙ ህጎች፣መመሪያዎችና ደንቦች ውጪ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተፈጠረው ችግር፣እስከ ትናንት ማታ ድረስ ከዕጩዎች ምዝገባ ጋር በተያያዘ የትብብራችንን አባል የሰማያዊ ፓርቲን ሥም ለመጥራት የፈሩበትና እስከዛሬ ትብብራችን የሚጠቀምበትን የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ለማስለቀቅ የተጀመረው የተቀነባበረ ሴራም የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው፡፡

በሌላ በኩል ገዢው ፓርቲ/መንግስት በመንግስት እና በ ‹‹ግልና ነጻ ሚዲያ ሥም ›› በተደራጁ መገናኛ ብዙሃን እያስተላለፈ ካለው ‹‹ማስፈራሪያ›› በተጨማሪ አምስቱን ዓመታት እየሰራ ያለውን የምርጫ ፕሮፖጋንዳ በማጠናከር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከህወኃት ምስረታ 40ኛ ዓመት ጋር አያይዞ ደደቢትን በ‹‹ልማታዊያን›› እያስጎበኘ፣በኢህአዴግ ውስጥ የህወኃትን የበላይነት ጠቅላይ ሚኒስትሩንና አፈ ጉባኤውን ጨምሮ በባለሥልጣናቱ እያስመሰከረ፣እንዲሁም የመሰረተ ልማት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ እያስቀመጠ የምርጫ ቅስቀሳ አጠናክሮ በስፋት በቀጠለበትና በጠንካራ ፓርቲዎች ላይ ፖለቲካዊ ውሳኔ በተላለፈበትም ገዢው ፓርቲ ከጠበቀው ውጤት በተቃራኒ የትብብሩን ትግል ለማጠናከር አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በተለይ የአንድነት አባላትን ከሰላማዊ ትግሉ ያላሸሻቸው ይልቁንም ወደ ትግሉ በተጠናከረ ሞራልና በላቀ ቁርጠኝነት ከትብብራችን አባል ሰማያዊ ፓርቲ መቀላቀላቸው የነጻነት ሰላማዊ ትግሉ በአጠቃላይ፣ የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ፕሮግራማችን በተለይ፣ በተለያየ ፓርቲ የነበሩትን በአጋርነት በማሰባሰብና ለውጡ የምመጣለትን ምልዐተ- ህዝብ ወደ ትብብራችን የበለጠ በመሳብ ለቀጣዩ የጋራ ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ የዚህ በስፋት የመቀጠል ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ ገዢው ፓርቲ/መንግስት /ለውጡ የሚመጣባቸው አምባገነኖች/ ላይ ድንገተኛ ከፍተኛ ፍርኃትና ሥጋት በማሳደሩ ህገመንግሥቱን በመጨፍለቅ በግልጽና በአደባባይ ህገወጥ ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን ለመውሰድ መገደዳቸው፣ ይህም የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት በማሳደግ ህዝባዊውን ትግል ወደ ላቀ/ከፍተኛ ደረጃ ማሸጋገሩ የበለጠ ግልጽ ሆኗል፡፡

ስለዚህ ከላይ በተገለጸው አገራዊ ተጨባጭ እውነታ ውስጥ የሚደረግ ሠላማዊና ህጋዊ ትግል በብልሃት/ጥበብና ዲስፕሊን የሚመራ፤ ቆራጥነትን የተላበሰ፣ የተቀናጀና ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚያሳትፍ፣በጠራ ኃሳብ ላይ የቆመ መሆን እንደሚገባው፣ አመራሩም የትግሉን ህጋዊነትና ትኩረት ለይቶ ለህዝብ ግልጽ ማድረግ እንዳለበት ተረድተናል፡፡ ስለሆነም ቀጣዩ ትግላችን ፡-
በመጀመሪያ – ትብብራችን የተከተለው የጋራ ትግል ትናንት፣ዛሬም ሆነ እስከ መጨረሻው ፍጹም ህገ መንግስታዊ፣ ህጋዊና ሰላማዊ፣በአገራችንም ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የተለመደ ነው፡፡ በተለይም ለየካቲት 15 ቀን ስናቅድ ለምርጫ 2007 በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዕውቅና የማይጠየቅበት የፓርቲዎች የቅስቀሳ ወቅት ስለሆነ እንደነበር፣ አሁን በከለስነው ዕቅድም የከተማ አስተዳደሮች ዕውቅና ወይም እነርሱ እንደሚሉት ‹‹ፍቃድ›› የማይጠየቁበት ለገዢው ፓርቲ የማስፈራሪያ ፕሮፖጋንዳ የማይውልና ምልዐተ-ህዝቡ ሰልፉ ተፈቅዷል/አልተፈቀደም ከሚል ጥያቄ ነጻ መሆኑ፣፤
በመቀጠልም – የትግል ጥያቄኣችን ትኩረት ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻነትና ክብር መሆኑ ነው፤ ተጠቃሚዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሁላችን ፣ በትግላችን ስኬታማነት የሚጎዱ ቢኖሩ ከግል ጥቅማቸው የሚነቀሉ፣ በአገርና ህዝብ ላይ በሰሩት ወንጀል ተጠያቂ የሚሆኑ ጥቂት አምባገነኖችና ህገወጥ የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ብቻና ብቻ ናቸው፡፡ ገዢዎቹ እንደሚሉትና እንደሚያስፈራሩበት እንኳን ከእኛ የተለየ የፖለቲካ እምነት ያለው ዜጋ፣ ተራው የህወኃት/ኢህአዴግ አባልና ካድሬ፣ የመንግስት ሠራተኛ፣የፖሊስና መከላከያ አባልም ሆነ የደህንነት ሠራተኛ በምንም መልኩ በሚጠበቀው ለውጥ ተጎጂ እንደማይሆን፤ ለጉዳዩ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት ለመራጩ ህዝብ ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡
በአጠቃላይ ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ የእኛ-የአገራችንና ዜጓቿ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሁለት አማራጮች ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ እነዚህም በአጭር አገላለጽ፡- አንድም –ያለውን አምባገነናዊ ሥርዓት ተቀብለን፣የአገራችን ሉዓላዊነት በጥያቄ ውስጥ ባለበት፣ የጭቆና ቀንበር ተሸክመን በከፋ ውርደት ሥር ሰጥ- ለጥ ብሎ መገዛት፤ ያሊያም– አምባገነንነትና ጭቆናን ‹‹በቃ›› በማለት በሕዝባዊ የተቀናጀ ሰላማዊ ትግል ለአገራችን ሉዓላዊነትና የዜግነት ክብራችንን ለማስመለስ በህገ መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን ትግላችንን እስከማይቀረው ለውጥ/ ድል ደጃፍ ድረስ በቆራጥነት መቀጠል፣ ናቸው፡፡
ለእኛ ሁለተኛው ሁሉንአቀፍ የነጻነትና ክብርን የማስመለስ ሰላማዊ ትግል ብቸኛ አማራጭ ነው፡፡ግባችንም በህገመንግስታዊው የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለአገራችን ሉኣላዊነት፣ዘላቂ ሠላምና ልማት፣ ለነጻነት፣ የዜግነት ክብር፣ እኩልነትና እኩል ተጠቃሚነት መረጋገጥ ነው፡፡ የመጀመሪያው በኃይል ጭቆናን በማክበድ አምባገነንነትን ለማስቀጠል የሚደረገው ሁሉ ለውጡን ያዘገየው፣መስዋዕትነቱንም ያከብደው እንደሆነ እንጂ እንደማያስቀረው ግልጽ በመሆኑ ፣ በውጤቱም ማንም ተጠቃሚ ስለማይሆን ፤በተለይም የገዢው ፓርቲ ‹‹ልዩ ተጠቃሚዎች /አምባገነኖችና ጥቂት ጭፍሮቻቸው/ ›› ተጠያቂነታቸውን የሚያጠናክር፣ህዝባዊ ትግሉም ከማናችንም/ከእነሱም ከእኛም/ ቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሠላምና መረጋጋት ከጥያቄ የሚያስገባ አላስፈላጊ ሁኔታ እንዳይከሰት የመከላከል ሚና ያለው ነው፡፡ማለትም ትግላችን ህገመንግስታዊ መብታችንን በመጠቀም በህግና በሥርዓት የሚመራ ነው፡፡ በመሆኑም፡-
1ኛ/ ምልዐተ ህዝቡ፡- የተባበረን ህዝባዊ ትግል አሸንፎ በሥልጣኑ የዘለቀ አምባገነናዊ ሥርዓት ያለመኖሩን፣ ነጻነት ነጻ ያለመሆኑን፣ የፖለቲካ ትግል በተጨባጩ ዓለም የሚቻለውን ማድረግ ነውና የሰላማዊ ትግሉና የመድብለ ፓርቲ ሥርዓቱ በር ሙሉ በሙሉ እስኪዘጋ ባለው የንፋስ መግቢያ ቀዳዳ በመጠቀም የነጻነት ትግሉን እስከምንችለው ጫፍ ድረስ በጽናትና ቆራጥነት ለመምራት ዝግጁ መሆናችንን ተረድታችሁ፣ በገዢው ፓርቲ የ‹‹ከፋፍለህ ግዛ›› ፖሊሲ ሳትጠለፉ፣በማስፈራሪያ ፕሮፖጋንዳዎች ሳትሸማቀቁ ፣
2ኛ/ ‹‹ኢህአዴግነት ከዜግነት በላይ ›› ሆኖ የሥራ ዋስትናችሁ፣ዕድገትም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሙያችሁ፣ በልምዳችሁ፣ ክህሎታችሁ፣ በጥቅሉም በሥራ ብቃታችሁ ሳይሆን በፓርቲ አባልነት በሚመዝን ሥርዓት የሚደርስባችሁ ሁሉ እንዲገታ፣ የተነጠቃችሁትን በራስ መተማመን መንፈስ ለማስመለስ የምትተጉ፤ ሲቪል የመንግስት ሠራተኞች፣
3ኛ/ የቴለቪዥንና ሬዲዮው ‹‹ሚሊዬነርነት›› ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ የህይወት ለውጥ ያላመጣላችሁ ‹ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ›› የሆነባችሁ፣ የግብርና ግብአቶች ማግኘት የዜግነት መብታችሁ ሆኖ ሳለ ‹‹የፖለቲካ ጉቦ›› የምትጠየቁ በየምክንያቱ ለመፈናቀልና ስደት የተዳረጋችሁና የተጋለጣችሁ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ወገኖች፣
4ኛ/ በአገራችሁ በነጻነት ሰርቶ የማደር መብታችሁን ተነጥቃችሁ ለአድሎኣዊ ውድድርና ለሙሰኞች የተጋለጣችሁ፣ በየትኛውም ጊዜ ከየትም አቅጣጫ ሊመጣ በሚችል ጥቃት በስጋት እየተሰቃያችሁ ያላችሁ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት፣
5ኛ/ የህወኃት/ኢህአዴግ ተራ አባላትና ካድሬዎች፤ የፖለቲካ ልዩነት የተለያየ አመለካከትና ኃሳብ ማራመድ ጤናማ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ መገለጫ እንጂ እንደሚነገራችሁ ‹‹ጠላትነት›› ባለመሆኑ፣ትግላችንም ለሠላማዊና ህጋዊ የሥልጣን ሽግግር እንጂ እንደሚነገራችሁ በናንተ ‹‹መቃብር ›› ላይ አዲሱን ሥርዓት የማቆም፣ የነበረውን አጥፍቶ ከዜሮ የመጀመርና እናንተን የማጥፋት ዓላማ እንደሌለው ተረድታችሁ፣ ተቃዋሚዎች እንደናንተው ኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያና ህዝቧ የሚጨነቁ መሆናቸውን በመረዳት ተቃዋሚዎችን እንደ‹‹ ጠላት›› ከመመልከት አስተሳሰብ ራሳችሁን ነጻ አውጥታችሁ፣
6ኛ/ የፖሊስ፣ መከላከያ ሠራዊትና ደህንነት አባላት፤ ህገመንግስቱና የተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጁ (573/2000) አንቀጽ 58 ከፓርቲ አባልነት/ተጽዕኖ ነጻነታችሁን ስለሚያረጋግጡ፣በኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችሁ ላይ ህገ- ወጥ ትዕዛዝ በመፈጸም ከሚደርስባችሁ ህጋዊና ህሊናዊ ተጠያቂነት ራሳችሁን ጠብቃችሁ፣እንዲሁም የትግላችን ውጤት እኩል ተጠቃሚ መሆናችሁን ተረድታችሁ፣ ራሳችሁን የሚጠበቀው የስርዓት ለውጥ ‹‹ለማኞች ያደርጋችኋል ›› ከሚለው ፕሮፖጋንዳ ሰለባነት ነጻ አውጥታችሁ፣ የአምባገነኖች መጠቀሚያ መሳሪያ ከመሆን እንድትታቀቡና ህዝባዊና ህገ መንግስታዊ ወገኝተኝነታችሁን በማረጋገጥ፤
7ኛ/ ወጣቶችና ሴቶች በተለይም የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች– ማኅበራት/ሊጎች፤በሥራ አጥነት፣ከአቅም በላይ የሆነው የኑሮ ውድነት … በስደት ህይወት ከሚደርስባችሁ ስቃይ ባሻገር በጥቅማ ጥቅም እንድትንበረከኩና የገዢው ፓርቲ አገልጋይ እንድትሆኑ የሚደረገውን ሁሉ በጥሳችሁ ፣በተለይ በመብታችሁ ትግል ስም የተደራጃችሁ የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች- የሚሰጣችሁ ጊዜያዊ ጥቅምና የሚገባላችሁ አማላይ ቃል ኪዳን የምርጫ ሰሞን ማባበያ መሆኑን በተደጋጋሚ ያያችሁት በመሆኑ፣ የሚደረግላችሁም በዜግነት መብታችሁ ማግኘት የሚገባችሁን እንጂ የገዢው ፓርቲ ሥጦታ ባለመሆኑ፤
8ኛ/ መምህራንና ተማሪዎች በተለይም የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፡-በአገራችን የለውጥ ኃይል ማዕከልና ግንባር ቀደም ተሰላፊ የሆናችሁበትን ታሪክ እንድታድሱና ዛሬም እንደ ትናንቱ አገራችሁና ህዝባችሁ ከናንተ ብዙ የሚጠብቁ መሆናችሁን ተረድታችሁ፣
9ኛ/ የእምነት ነጻነት መብት ጠያቂ የማኅበረሰብ አባላት፡- በተለያዩ እምነት ተከታዮች እየቀረቡ ያሉት የእምነት ነጻነት ጥያቄዎች ከሠላማዊውና ህጋዊው የሥርዓት ለውጥና የነጻነት ጥያቄኣችን የማይነጣጠሉ በመሆናቸው በተናጠል መልስ የማያገኙና መፍትሄውም የዘላቂው ሁለንተናዊ ለውጥ አካል መሆኑን ተረድታችሁ፤
10ኛ/ ኢትዮጵያዊ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፡- በአገር ቤትና በውጪ የምትገኙ ነጻና የአገርና ህዝብ ወገንተኛ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፣ በተለይም በተሻለ ኃሳብን በነጻ የመግለጽ መብት በተከበረበት የምትገኙት የህዝብ ጆሮና ዓይን በመሆን የምትሰጡትን አገልግሎት በማጠናከር የተያያዝነውን ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል አማራጭ ኃሳባችንና የትግል ጥሪያችንን ለህዝቡ በማቅረብ የዲሞክራሲ፣ የአገርና ሕዝብ ወገንተኝነታችሁን አጠናክራችሁ በመቀጠል፤
11ኛ/ የፍትህ አካላት፡- በትምህርት ያገነባችሁትና በልምድ ያዳበራችሁት ሙያዊ ቃልኪዳንና የሰብዐዊ ኅሊናችሁ ሚዛን የሚጥልባችሁ ኃላፊነት በጊዚያዊ- የሚያልፍ ጥቅም በአገራችሁና ወገናችሁ ላይ ፍትህን እንዳታጓድሉ ያስገድዳሉና የአምባገነኖች መጠቀሚያ መሳሪያ በመሆን ከመተባበር እንድትቆጠቡ፣
12ኛ/ ሌሎች ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች፡- በአምባገነን ሥርዓቱ በተናጠል የሚደርስብንን አፈና በጋራ ለመመከትና የመድብለ ፓርቲ ትግላችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣በሚያግባቡን የምርጫ ጉዳዮችና የብሄራዊ ውይይትና ዕርቅ ጉዳይ ላይ በአጋርነት በጋራ የመቆም አስፈላጊነት ለነገ የማይባል ነው ስለሆነ፣
13ኛ/ ፓርቲዎቻችሁን የተነጠቃችሁ የነጻነትና የዲሞክራሲ ሰላማዊ ታጋዮች፡- እስካሁን ባለው ጊዜ አፋጣኝና ወሳኝ ፖለቲካዊ ውሳኔ በመስጠት ከትብብሩ አባል ሰማያዊ ፓርቲ የተቀላቀላችሁትን እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን፣ ሌሎቻችሁም የትብብራችን አገራዊ የጋራ ዓላማ ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር በማገናዘብ፣
14ኛ/ በውጪ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵዊያን/ዲያስፖራዎች፡- በተያያዝነው ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል ያላችሁን ሚና በግልጽ ለይታችሁ፣ ተሳትፎኣችሁና ድጋፋችሁ ለትግላችን ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በመገንዘብ ለአገራችሁና ህዝባችሁ ባላችሁ የባለቤትነትና የወገናዊነት ኃላፊነት መሰረት፣
በምናደርገው አገራዊ፣ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በአንድነትና በቆራጥነት እንድትሰለፉ፤ የየካቲት 22/07 ቀጠሮኣችንም የማይቀርበት በመሆኑ በየከተሞቹ በቦታውና በሰዓቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን አበክረን እናቀርባለን፡፡
በተቀናጀ የጋራ አመራር የተባበረ ህዝባዊ ሠላማዊ ትግል በእኩልነት ላይ የተመሠረተች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንደምትገነባ አንጠራጠርም!

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

የካቲት 10/ 2007 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

አራት ክልላዊ ድርጅቶችን ያቀፈው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ አንድነት መድረክ በምን መልክ በምርጫው እንደሚሳተፍና ስለዝግጅቶቹ እንዲሁም ስለሚወዳደርባቸው ነጥቦች እንዲያብራሩልን የድርጅቱ ፕረዚዳንት ፕሮፊሰር በየነ ፄጥሮስን ጋብዘናል። በኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጭ የሚካሄድበት ጊዜ ሶስት ወራት…

The post መድረክ በምርጫ ካሸነፈ የብሄራዊ አንድነት መንግስት እንደሚመሰርት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

Image

Minilik Salsawi በኢትዮጵያዊነቱ እና በሃገር ወዳድነቱ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ የነጻነት እና የመብት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ በአምባገነን መዳፍ ስር ያለው ሕዝብ ነጻ እንዲወጣ ወያኔን ለመጣል በትጥቅ ትግል ላይ የተሰማሩ አፍዴራ ጋድሌ እና አርዱፍ በመዋሃድ የጋራ ግንባር መፍጠራቸው እየተካሄደ ላለው ትግል አንድ እርምጃ መራመድ ትልቅ አስታውጾ ያለው ተግባር ነው::

ፓርቲዎች ባለፉት ዘመናት በተናጠል በመታገል ምንም ውጤት እንዳላገኙ በገሃድ የታየ ጉዳይ ነው::እንዲሁም በሀገር ቤት ያሉ ድርጅቶች ሊዋሃዱ አሊያም ግንባር ሊፈጥሩ በሚፈልጉበት ወቅት የወያኔ አምባገነን ገዢ ደህንነቶቹን አሰማርቶ ከፍተኛ ወከባ በመፍተር ሰርጎ ገቦችን በማስረግ ክፍተኛ መንግስታዊ ሽብርተኝነት እና እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል::በቅርቡ በአስመራ የተካሄደ ውህደት እና አሁንም በአፋር ድርጅቶች መካከል የተደረገው የግንባር ምስረታ ለትግሉ ታላቅ ግብ እና እመርታ ነው::

የግንባሩን መፈጠር ተከትሎ የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ በመድረሳቸው፣ በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ሆነው ለመታገል ወስነዋል።አዲሱ ግንባር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመታገል ፍላጎት እንዳለውም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን ከ”አይ ኤስ ኤስ” እና ”ግልገሎቹ” ለማዳን መፍትሄው ምንድነው? (የጉዳያችን ልዩ ማስታወሻ) ‘አይ ኤስ ኤስ’ ባለፈው ዓመት ያወጣው አዲሱ ካርታ ትናንት የካቲት 8/2007 ዓም እኩለ ሌሊት ላይ ”ሮይተርስ” በሊብያ በ”አይ…

The post የትናንቱ የ”አይ ኤስ ኤስ” በግብፅ ክርስቲያኖች ላይ የፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ አንፃር ምን ያመላክተናል? appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በስልጣን ላይ ያለውን የህወሃት /ኢህአዴግ መንግስት በሃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱት ሶስቱ የአፋር ድርጅቶች ማለትም አርዱፍ፣ ጋድሌና የአፍዴራ ታጋዮች የካቲት 8 ቀን 2007 ዓም የጋራ ግንባር ፈጥረዋል። የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ  ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ካድሬዎቹ በደቡብክልል በሲዳማ ዞን በቡርሳ ወረዳ  ስለዕጩዎች ምዝገባና ቀጣይ ድርጅታዊ ሥራዎች ላይ ለመወያየት በወረዳው በሚገኘው የሲአንጽ/ቤት ተሰበስበው በነበሩ የሲአን/መድረክ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ፣በወረዳው የመድረክ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና ሌሎች አባላት ላይ የወረዳው የፖሊሰ ኃይልን በመጠቀም ድብደባ ፈጽመውባቸው እንዲበተኑ ማድረጋቸውን መድረክ ገልጿል፡፡ የቡርሳ ከተማከንቲባበሆኑትበአቶአለማየሁፉንአቴትዕዛዝበተፈጸመውበዚሁድብደባበጽ/ቤቱተሰብስበውበነበሩት 20የሲአንመድረክአባላትላይአካላዊጉዳትእንደደረሰባቸውአስታውቋል፡፡ በዚሁዞን  *በወንሾወረዳበዱባምርጫክልል* የመድረክየክልልምክርቤትዕጩተወዳዳሪየሆኑት አቶበሾላገቢሶበመድረክዕጩነትመቅረባቸውእንደታወቀለብዙጊዜያትሲያርሱየኖሩትንናበአሁኑወቅትምየቡናና የእንሰትተክሎችበብዛትየሚገኙበትንየእርሻመሬትለደንእንፈልገዋለንብለውበመከለልናምልክትበማድረግከዕጩነታቸው እንዲለቁማስፈራሪያእየተደረገባቸውእንደሆነመድረክ ገልጿል።

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በኖርዌ የነበረውን ስነስርአት በተመለከተ ከአቶአበበ ደመቀ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። በአውስትራሊያሜልበርንከተማ  እሁድ  ፈብራሪ 15፣ 2015 ዓ .ምበደማቅሁኔታተከብሯል። ፕሮግራሙ በህሊና ጸሎት ከተጀመረ በኋላ አቶ አንዳርጋቸውን የሚያስታውሱ በቪዲዮ የተቀነባበሩ ስነ ግጥሞች ፣መዝሙሮች እና  ዘጋቢ ፊልሞች ቀርበዋል። የፕሮግራሙአስተባባሪዎች፦  <<የአቶ አንዳርጋቸውን 60ኛ አመት የልደት በአልየምና ከብረው፤  አቶ አንዳርጋቸው የከፈሉትን ዋጋ በመዘከር ፣እርሳቸው እየተሰዉለት ያለውን አላማ …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪና የህወሃት ነባር ታጋይ አባይ ጸሃየ አወዛጋቢው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሃይል ተግባራዊ እንደሚደረግ አዋሳ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ መናገራቸውን የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ገልጿል። አቶ አባይ ጸሃየ የኦሮምያ ልዩ ዞን ሃላፊዎችን በቅድሚያ የወቀሱ ሲሆን፣ ክልሉም እነዚህን ልክ ባለማስገባቱ ሌላው ተጠያቂ መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንደወጣ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች  …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-እጅግ አስደንጋጭ የሆነ የመሬት ሊዝ ዋጋ ንረት እየታየበት የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ባወጣው 13ኛው  የሊዝጨረታ በአዲስ አበባ፤በቦሌእና  በአቃቂቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በድምሩ 238 ቦታዎችን በሊዝለማስተላለፍ አቅርቧል። መንግሥት የመሬትችርቻሮውስጥከመግባቱጋርተያይዞየአንድካሬሜትርባዶቦታዋጋከ 150 እስከ 305 ሺብር  መሰቀሉ መንግሥትን በከፍተኛ ደረጃ ካስተቸው ወዲህ እንዲህ በብዛት ቦታዎች ለጨረታ ሲያቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ በዚህጨረታበቦሌክፍለ ከተማ 116 ቦታዎችለጨረታየቀረቡሲሆንየአንድካሬሜትርመነሻዋጋ …

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በዓለም ባንክ አዲስ መረጃ መሰረት ፤ ከአስሩ የዓለማችን የመጨረሻ ሀገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያነች ። በጥናቱ በድህነት ከ 1 እስከ 10 የተመዘገቡት እንደ ቅደምተከተላቸው ማላዊ ፣ ቡሩንዲ ፣ቻድ ፣ ኒጀር ፣ ላይቤሪያ ፣ ማዳካስካር ፣ ኮንጎ ፣ጋምቢያ ፣ኢትዮጵያና ጊኒናቸው። እንደተለመደው ሁሉ  በዘንድሮውም ጥናት በድህነት ተርታ የተመደቡት አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ሲሆኑ ፤ ከነኚህ …

አራት ክልላዊ ድርጅቶችን ያቀፈው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ አንድነት መድረክ በምን መልክ በምርጫው እንደሚሳተፍና ስለዝግጅቶቹ እንዲሁም ስለሚወዳደርባቸው ነጥቦች እንዲያብራሩልን የድርጅቱ ፕረዚዳንት ፕሮፊሰር በየነ ፄጥሮስን ጋብዘናል።

ሊዮኔል ሜሲ ዳግም ሐትሪክ ሠርቷል፤ ቡድኑ ባርሴሎና ላቫንቴን 5 ለዜሮ በመርታት ከመሪው ሪያል ማድሪድ ጋር ትንቅንቁን አጠናቅሮታል። በቡንደስሊጋው ባየር ሙይንሽን ሐምቡርግን 8 ለባዶ አንኮታኩቷል። አርሰናል በእንግሊዝ FA Cup ድል ቀንቶታል። በጣሊያን ሴሪኣ ዝቅተኛ ነጥብ ያላቸው ኹለት ቡድኖች ኃያላኑን ቡድኖች ተፈታትነው ነጥብ አስጥለዋል።

የሱዳን መንግሥት ጦር ባለፈው ጥቅምት በሀገሪቱ ምዕራባዊ ክፍለ ሃገር በዳርፉር ከተማ በርካታ ሴቶችና ህፃናትን ደፍሯል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩመን ራይትስ ዋች ባለፈው ሳምንት አጋልጧል ።

የዩክሬን መንግስት እና አማጽያን በሳምንቱ መጨረሻ የተፈራረሙት ስምምነት በአንድ ቀን ተጣሰ። የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጄኔፈር ፓሳኪ ሩሲያ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በምስራቅ ዩክሬን አሰማርታለች ሲሉ ከስሰዋል።

-“እጩዎቻችንን ለማስመዝገብ ከቦርዱ አስፈፃሚዎች ተግዳሮት ገጥሞናል” ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ ብሔራዊ በርጫ ቦርድ ወያኔ ሰራሹ አንድነት በአቶ ትዕግስቱ አወሉ እየተመራ ወደ ምርጫ እንዲገባ የወሰነለት እና በአቶ አበባው መሃሪ እንዲመራ የተወሰነው መኢአድ በምርጫው…

The post •“ሠማያዊ ፓርቲ የኔን መዋቅር ተጠቅሞ ነው እጩ ያስመዘገበው” አቶ ትዕግስቱ አወሉ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የኩዌት መንግስት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በህገወጥ መንገድ ወደ አገሪቱ በማስገባት በቤት ሰራተኝነት ያስቀጥራሉ የተባሉ  12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እንዳስታወቀ አረብ…

The post 12 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር በኩዌት ታሰሩ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ዓረና-መድረክ ወክለው በመቐለ ምርጫ ክልል ለፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ኣቶ ገብሩ ኣስራት የመራጭነት ካርድ ተጨርሰዋል በሚል ምክንያት ተከልክለዋል። ይህ የሆነው እሁድ 01 / 06 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ…

The post አቶ ገብሩ ኣስራት የምርጫ ካርድ ተከለከሉ..! appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በአማርኛ ቋንቋ ዕድገትና ብልጸጋ ጎዳና ላይ ከሚገኙት ተግዳሮቶች አንዱ ተገቢ የሆነ፣ ሁሉም የሚቀበለው፣ በቀላሉ የሚገኝና ደረጃውን የጠበቀ የአማርኛ ሥርዓተ ጽሕፈት አለመኖር ነው፡፡ የአጻጻፍ መንገዶችን፣ መልክዐ ፊደልና ሥርዓተ ፊደልን፣ በቃላት አጻጻፍ የሆሄ መረጣን፣ የፊደል መጠንን፣ የስያሜ ቃላት አሰጣጥን፣ የትርጎማ መንገድን፣ ወዘተ የተመለከተ ሥርዓተ ጽሕፈት ያስፈልገናል፡፡ ለዛሬው ግን ብዙዎቻችን የምንስትበትንና የምንምታታበትን የሞክሼ ሆሄያት (ሀ፣ ሐ፣ ኀ፣ ኸ፤ ሠ፣ሰ፣ አ፣ ዐ፤ ጸ፣ ፀ) አጻጻፍን በተመለከተ ታዋቂው ሊቅ ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ(ነፍሳቸውን ይማርና) አዘጋጅተውት ሻማ ቡክስያሳተመውን ‹‹የአማርኛን ሞክሼ ሆሄያት  ጠንቅቆ ያለመጻፍ ችግርና መፍትሔ›› የሚለው መጽሐፍ ላስተዋውቃችሁ፡፡
መጽሐፏ የኪስ መጠን ብትሆንም እስከዛሬ በጉዳዩ ከተዘጋጁት የተሻለች፣ በአመክንዮ የቀረበችና በጥናት ላይ የተመሠረተች ናት፡፡ በተለይም ለደራስያን፣ ለቢሮ ጸሐፊዎች፣ ለፖለቲካ ሰዎች፣ ለጋዜጠኞች፣ ለማስታወቂያ ባለሞያዎች፣ ለአርታዕያን፣ ለፌስ ቡክ ደንበኞችና ለሌሎቻችንም በሞክሼ ቃላት ዙሪያ መመሪያ የምትሆን ናት፡፡ እባካችሁ ነገራችን ወጥ እንዲሆን በሊቁ መንገድ እንሥራ፡፡ ዋጋው 25 ብር ነው ገዝተን በጠረጴዛችን ላይ እናስቀምጥና እንመራባት፡፡
ከምር ሁላችንም ቤትና ቢሮ መጥፋት የሌለባት ናት፡፡

ተቃዋሚዎች በሰከነ መንገድ ክፍተቱን መጠቀም እንዳለባቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል::Minilik Salsawi
ለ24 አመታት ያህል ሰራዊቱን እና የደህንነቱን ክፍል በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር ያዋሉት የወያኔ ጁንታ አምባገነኖች መውደቂያቸው መድረሱን ተከትሎ በደህንነት አካላት መካከል ያለው አለመግባባት እየሰፋ መምጣቱን የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ያሉ ደህንነቶች ላይ እምነት ያጣው የወያነው አምባገነን አዳዲስ የደህንነት አባላት ለቁጥጥር መመደቡ ታውቋል::

በደህንነት ክፍል ውስጥ በመላው ሃገሪቱ የተመደቡ የደህንነት አባላት ላይ እምነት እንዳሌለው የሚናገረው ወያኔ በተለያየ ጊዜ ዝውውር ቢያደርግላቸውም በሃላፊዎች እና በደህንነት አባላቱ መካከል አለመግባባቶች እየሰፉ መነካከስ መቀጠሉን ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ አገላለጽ የደህንነት አባላቱ የጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ቢደረግላቸውም ከሃላፊዎች ጋር አለመግባባቱ እንዲሁም በመካከላቸው ያለ መተማመን መናዱ በግልጽ እየታየ ነው ሲሉ ተናግረዋል::

ተቃዋሚዎች የወያኔን መፈረካከስ እና በሰራዊቱ እንዲሁም በደህንነቱ አካላት ዙሪያ የተነሳዉን ክፍተት ተጠቅመው በሰከነ እና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ለለውጥ በሚደረገው ትግል ጎን ለጎን ያለውን አለመግባባት ክፍተት በመጠቀም የወያኔን ውድቀት ማፋጠን አለባቸው ሲሉ ምንጮቹ አስተያየት ሰጥተዋል::

ሰሞኑን የህወሃት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመላው ኢትዮጲያ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በቅድሚያ እንኳን ለአርባኛው አመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ እላለሁ ፡፡ በትጥቅ ትግሉም ወቅት ሆነ ከትጥቅ ትግሉ በኋላ ይህን ቀን ለማየት ሳይታደሉ ያለፉ ብዙዎች ናቸውና ምንም ይሁን ምን ለዚህ ቀን መብቃት ትልቅ ነገር እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡ ይህን ፅሁፍ የምፅፈው በተወለድኩባት ባደኩባትና አሁንም እየኖርኩባት ባለችው ኢትዮጲያ ከተመሰረተ ድፍን 40 ዓመት ያስቆጠረ ጎልማሳ የፖለቲካ ድርጅት ላይ እንደአንድ ዜጋ ያለኝን ቅሬታ ለማሳወቅ ነው ፡፡

ሰሞኑን የድርጅቱን 40ኛ ዓመት በዓል በቴሌቪዥን በሬዲዮ እንዲሁም ከመሃበራዊ ድረ ገፆች ላይ ስመለከት እንዲሁም አገሪቱ ላይ ያለውን ተጨባጭ ችግር ስታዘብ ሳልፈልገው አእምሮየ ታሪክ እየመዘዘ ይሞግተኛል ፡፡ ባጭሩ ይህ በዓል በህዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው ብየ ሳስብ ከግራና ቀኝ ከህዝቡ የሚሰነዘረውን ትችት አስተያየትና ምሬት ስመለከት በዓሉን ለብቻችሁ እያከበራችሁት ነው የሚል ስጋት ፈጥሮብኛል ፡፡

ምንም እንኳን የህወሃት የትጥቅ ትግል የዛሬው የህወሃት ቀንደኛ ጠላት ሻእቢያን ጨምሮ በከፈሉት መስዋእትነት ባደረጉት ተጋድሎ አገራችንን ከደርግ አሰቃቂ አገዛዝ የታደጋት መሆኑን ሁሉም ኢትዮጲያዊ ቢያውቅም ከነፃነቱ በኋላ ግን ስርዓቱ በሚከተለው ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስመር ከፍ ያለ ቅሬታ አለው ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ህዝቡ የትም ሂዱ የት ይማረራል … መቸም ይሄ ሁሉ ህዝብ የሚማረረው የኢትዮጲያ ህዝብ ምስጋና የማያውቅ ስለሆነ አይመስለኝም ፡፡ እንደውም ከእግዜር ጀምሮ እስከአምባገነን መሪወቹ ድረስ ራቱን በልቶ ባደረ ቁጥር ከእልፍ ችግሩ ጋር ተጠቅልሎ በሚተኛባት መደብ ‹‹ተመስገን›› ብሎ የሚያድር ህዝብ እንደኢትዮጲያ ህዝብ ያለ አይመስለኝም ፡፡ ግን …… ብሶት ህወሃትን እንደወለደ ሁሉ አሁንም ተማራሪ ህዝብ እየፈለፈለ ምድሩን እየሞላው ነው ፡፡ እናንተም ለህዝብ ብሶትና ጥያቄ ጅራትና ቀንድ እየቀጠላችሁ ተናጋሪውን ሁሉ ባልሆነ መንገድ በመፈረጅ ከማሳቀቃችሁም በላይ የዝሆን ጆሮ ይስጠን እንዳላችሁ ይሄው ድፍን 40 ዓመት ፡፡

በእርግጥ በቴሌቪዥንም ሆነ በአካል ለህዝብ ንግግር ማድረግ ቀላል ነው … ከባዱ ከህዝብ ጋር መነጋገር ነው ፡፡ ይሁንና ንግግር ማድረግም ቢሆን ቀላልነቱ ለሚናገሩባት ቅፅበት እንጅ ሲቆይ ወደሰማይ እንደወረወሩት ድንጋይ ተመልሶ አናት ላይ መስፈሩ አይቀርም ፡፡አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው ፡፡ የተገባው ቃል ሁሉ ስንዝር አልተራመደም ፡፡ በርካታ የልማት ስራዎች ተሰርተዋል መንገድ የጤና እና የትምህርት ተቋማት ግንባታ ግድቦች ዩኒቨርስቲዎች እነዚህ ሁሉ እናተም በተደጋጋሚ እንዲነገርላችሁ የምትፈልጓቸው ስኬቶች ናቸው ፡፡ ይሁንና ህዝብ ያልተሟላለትን ነገር ሲናገር የተሰራለትን እንደካደ አድርጎ ማሰብ ትልቁ የአረዳድ ችግራችሁ ነው ፡፡ ሰው ኑሮ ተወደደብኝ ብሎ ሲያማርር ኑሮ የሚቃለልበት መንገድ ላይ መስራት ብቻ ነው መልሱ ሊሆን የሚችለው ! …‹‹ አይ ኑሮ ቢወደድብህም ዩኒቨርስቲ ግን ሰርተንልሃል›› የሚል ምላሽ መቸም ህዝብን ሊያረካ አይችልም !! አሁን እየሆነ ያለው ግን ይህ ነው ! ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ማስፈራሪያ ዛቻ እንዲሁም የተወሰኑ ሰዎችን ከህዝቡ እየመዘዙ ለብዙሃኑ ችግረኛ እንቆቅልሽ ማለትና የህዝቡን ቅሬታ ማድበስበስ የተለመደ የገዥው ፓርቲ ስራ ሁኗል ፡፡

በተለይም ኢቲቪ (EBC) ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ›› በማለት የሚያቀርባቸው ሰዎች ግራ እያጋቡን ነው ! እስቲ ኑሮ ተወዶብናል ስንል እነዚህ ‹‹አንዳንዶች ›› ኑሮ አልተወደደም የሚል በደፈናው ይዘው ህዝቡን ማበሳጨት ምን ይጠቅማል ?ለማንስ ነው የሚመሰክሩት …መብራት ጠፋብን ስንል አንዳንዶቹ ‹‹ኧረ በጭራሽ›› ይሉናል ፡፡ አንዳንዶች ብዙሃኑን ‹‹ውሸታም ነህ ›› ይሉታል ፡፡ይሄ ህዝብን መናቅ ነው …እንደውም በኑሮ ውድነት ከሚሰቃየው ህዝብ በመሰረተ ልማት አውታሮች እጥረት ፍዳውን ከሚበላው ህዝብ የሚፈጠሩ ህፃናት ወደፊት

‹‹ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ›› ሲባሉ

‹‹ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን መሆን እንፈልጋለን ›› እንዳይሉ እሰጋለሁ ፡፡ ….በአሁኑ ሰዓት ያለምንም ምሬት በተድላ እንደሚኖሩና ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ እንደሆነ የሚመሰክሩ ኢትዮጲያዊያን ቢኖሩ እነዚሁ ‹‹አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች›› ብቻ ናቸውና ምኞቱ እንዲህ ቢሆን አይገርምም ፡፡ ብሄራዊ ቴሌቪዥናችን ‹‹ራበን ›› ብሎ ሰልፍ ለወጣው ህዝብ ‹‹ለምን ኬክ አይበሉም ›› እንዳለችው ልእልት ሁኖብናል ፡፡ ስራ አጣን ስንል ቴሌቪዥናችን ለምን ስራ አትፈጥሩም ይለናል …ኑሮ ለማሻሻል ተሰደድን ስንል …አይ ጥጋብ ፈንቅሏችሁ እንጅ አገራችን ማሩ ወተቱ ይለናል …እንኳን ማርና ወተት የግዜሩንም ውሃ በስንት ጉድ ጥበቃ እንደማንዳረስ ሁሉ !

ችግሩ ይሄ ብቻ አይደለም በመልካም አስተዳደር ላይ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግር ውስጥ ነን ፡፡ ሙስና ቁጥር አንድ ጠላታችን ሁኗል …ሙስና ደግሞ በባህሪው ስልጣናቸውን ገንዘብ ላለው ሰው የሚያከራዩ ባለስልጣናትና የስራ ሃላፊዎች ዘንድ የሚፈጠር አደገኛ ተግባር ነው ፡፡ መንግስት ህዝቡን ጠቁም አትጠቁም ጨዋታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ‹‹ደህንነት›› ተብሎ ለአገር ደህንነት ሲባል ጓዳ ጎድጓዳውን እሰልላለሁ እንደሚለው የመንግስት አካል በዚህም ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ‹‹የደህንነት አካል ›› ቢቋቋምና መዘረፋችን ባይቆም እንኳን አሟጠው እንዳይነጥቁን ሃይ ቢባሉ መልካም ነው ፡፡መቸም ሚስኪን ፀሃፊና ጋዜጠኞችን ከማሳደድ ይሄ የተሸለ ስራ ይመስለኛል ፡፡

ሌላው የህወሃት አስጊ ችግር በብሔሮች መሃል የፈጠረውና አሁንም እየፈጠረው ያለው ቁርሾ ነው ፡፡ በተለይ በትግራይ ህዝብና በሌላው ኢትዮጲያዊ መካከል …በተደጋጋሚ ህወሃት በጉድለቶቹ ሲወቀስ የራሱን ችግርና በድርጅቱ ላይ የሚሰነዘረውን ጥላቻም ይሁን ነቀፋ በትግራይ ህዝብ ላይ እንደተሰነዘረ በማስመሰል የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ የሚያደርገው ጥረት በተደጋጋሚ የሚታይ የአደባባይ ሚስጥር ነው !! ይህ ነገር የትግራይን ህዝብ ከእህትና ወንድሞቹ ጋር እያቃቃረው ከስርአቱ ልዩ ተጠቃሚ የሆነ እያስመሰለው ይገኛል ፡፡ የትግራይ ህዝብ በህወሃት የስልጣን ዘመን ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ የተለየ ተጠቃሚ ሁኗል አልሆነም የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ እንደሆነ አለ !!

ይህን ያልኩበት ምክንያት ደግሞ ህወሃት እራሱ እንደሚለው ኢፈርት ወይም ትእምት እጅግ በጣም ግዙፍ እና በኢትዮጲያ ውስጥ( አንዳንዶች እንደውም በአፍሪካም ይላሉ) በሀብት የሚወዳደረው የሌለ የንግድ ተቋም ነው ፡፡ ባለቤትነቱ ደግሞ በተለይ እንደተቀመጠው የትግራይ ህዝብ ነው ! እንግዲህ ይህን የሚያክል ትልቅ ተቋም በስሩ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፋብሪካዎች የማእድን ማውጫወች የኮንስትራክሽን ተቋማት የትራንስፖርት ድርጅቶች የእርሻ ድርጅቶች ያሉት ባለፀጋ ድርጅት ባለቤቱ የትግራይ ህዝብ ነው ከተባለና በትክክል ለትግራይ ህዝብ ገንዘቡ ከዋለ የትግራይ ህዝብ በደንብ ተጠቃሚ ነው ለማለት ያስደፍራል !! ይሁንና እዚሁ ፌስቡክ ላይ የኢፈርት ነገር ላም አለኝ በሰማይ ነው እንደሚሉን በርካታ የትግይ ወንድሞቻችን አባባል ከሆነ ግን የትግራይ ህዝብ በተለይ ከስልጣኑም ከበረከቱም የሌለበት ሚስኪን ነዋሪ ያው እንደሁሉም ኢትዮጲያዊ ነው !!

ዋናው ነገር ተጠቀሙም አልተጠቀሙም አሁን ባለው በርካታ ኢትዮጲያዊ አመለካከት በተለያየ መንገድ እንደምንሰማውም ህወሃትና የትግራይን ህዝብ አዳብሎ የማየት ነገር ጎልቶ ይታያል ፡፡ ህወሃትም ቢሆን የትግራይ ህዝብና ህወሃት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው አይነት ዳርዳርታ ማብዛቱ በቀሪው የኢትዮጲያ ህዝብ ልብ ውስጥ ጥሩ ነገር ይፈጥራል የሚል እምነት የለኝም ! ህወሃት የፖለቲካ ድርጅት ነው ሊጠላም ሊወደስም ይችላል፡፡ እራሱን ችሎ መቆምና ከህዝብ የሚሰነዘርበትን ጥላቻም ሙገሳም ህዝቦችን ሳያነካካ መቀበል ይኖርበታል ፡፡ መልካም አስተዳደር ያሰፈነ ገዥ ፓርቲ የዚህኛው ብሔር የዛንኛው ዘር ነው አይባልም ጥሩ ድርጅት የሚያስተዳድረው ሃገር ድርጅት ነው !! አምባገነን እና ፀረ ህዝብ መንግስት ግን ከማንም ይጠጋ በማንም ይጠለል ህዝባዊ አይደለምና ብሔር የለውም !! አዎ የመላውን የሰው ልጆች ነፃነት ሰበዓዊና ዲሞክራሲ መብት ገፋፊ ከሆነ አምባገነን ብሄር የለውም!!

ይሄ ህወሃትን የነካ የትግራይን ህዝብ ነካ ጨዋታ በ1993 እና 1997 ላይ በተለይ በአዲስ አበባ የተከሰቱትን ተቃውሞች ላይ ነህዝቦች መካከለል አስነስቶ የነበረውን ተገቢ ያልሆነ መዘዝ በማየት ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መታዘብ ይቻላል ፡፡ ያ ጊዜ የዚህ የጥላቻ ዘር ውጤት ፈጦ የታየበት ነበር ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂው ህወሃት ነው !! ለምን ቢባል በህዝቦቹ መካከል ወንድማማችነትን ለማጎልበት በቂ ስራ አልሰራም … (ፍላጎቱም ያለው አይመስልም) በመንግስት ስራ ውስጥም ሆነ በሌሎች ስራዎች የተሰማሩ አንዳንድ የአካባቢው ተወላጆች የትጥቅ ትግሉን ታሪክ የግል ጀብዷቸው ብቻ አድርገው ሲደነፉና ስለታገሉ ብቻ ልዩ ተጠቃሚ የመሆን መብት እንዳላቸው በተለያየ መንገድ ሲጠቅሱ መንግስት መስመር ለማስያዝ ያደረገው ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም !!

አንዳንዴ እኮ ተራ መጠጥ ቤት ውስጥ ሳይቀር በሚነሳ አምባጓሮ ‹‹ደሜን አፍስሸ ባቀናኋት አገር ›› የሚላችሁ እንጩጭ ብሔረተኛ ያጋጥማችኋል ፡፡ እዚህ ፌስቡክ ላይ በፀያፍ ስድብ ታሪክና ታላላቅ ሰዎችን በማጠልሸት ከእኛ በላይ አዋቂ የለም በማለትና አሳዛኝ ድርጊቶችን በመፈፀም የሚታወቁትም ተመሳሳይ ሰዎች ናቸው !! ይህ ከተጋነነ እውቀት ላይ ሳይሆን ትእቢት ላይ ከተመረኮዘ መጥፎ በራስ መተማመን የሚፈጠር በሽታ ከእኔ በላይ ላሳር የሚያስብላቸው እነዚሁ ሰዎች ናቸው !!

ለዚች አገር መሳሪያ አንስቶ የተዋጋው ብቻ ሳይሆን ግንበኛውም ሃኪሙም አስተማሪውም ላቡን አፍስሶላታል !! አበቃ !! ማንም ስለታገለ ደሙን ስላፈሰሰ ለህዝብ ነፃነት በጎ ነገር እንዳደረገ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት እንደተወጣ ያስብ እንጅ ለፈሰሰ ደሙ ከኢትዮጲያ ህዝብ ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳለው ወይም ልዩ ተጠቃሚ የሚደርገው የይለፍ ወረቀት እንደያዘ አድርጎ ማሰብ ነውርም አሳፋሪ አስተሳሰብም ነው !! ሚሊየኖች እየወደቁላት እዚህ የደረሰች አገር ለሟችም ለገዳይም ነፃነትን እንጅ ካሳን የከፈለችበት ዘመን የለም ! ደሜ ለፈሰሰበት ይከፈለኝ የሚል እሳቤ ያለው ዜጋ ቅጥረኛ ወታደር እንጅ በምንም መስፈርት ጀግና ሊባልና ሊሞካሽ አይገባም !! የመስዋእትነት ክፍያው ነፃነት ብቻ ነው !! ነፃነቱም ለሁሉም ህዝብ በእኩልነት !!

መንግስት ለምን የፃፉትን ሁሉ ያስራል .. ለምን በተናገሩት ቁጥር ያኮርፋል … ዜጎቹን አኩርፎ ከውጭ አገር ሽማግሌ እስኪመጣለት አለያም አስሮ የሚያሰቃያቸው ዜጎቹ ያውም በካርዳቸው ድምፃቸውን ሰጡኝ የሚላቸው …ይቅር በለን ብለው እግሩ ስር እስኪወድቁለት የሚጠብቅ ስርዓት ምን አይነት መንግስት ሊወጣው ይችላል …ሁልጊዜ ስለመንገድ አውሩ ሁልጊዜ ስለፋሲካ ብቻ አውሩ የሚል መንግስት እንዴት የህዝብ መንግስት ሊሆን ይችላል ! መፅሄት ላይ ኮሽ ሲል በህዝብ ላብ በህዝብ ግብር በተማሩ ወታደሮችና ደህንነቶች ዜጎቹን የሚያሳፍስ ዘመድ ወዳጅ እንዳይጎበኛቸው የሚከለክል መንግስት ማንን ነው የሚመራው ….

በዚች በአርባኛ አመት በዓል ላይ የሚታየው ሌላው አሳዛኝ ነገር ደግሞ የትግራይን ህዝብ ከሌላው የኢትዮጲያ ህዝብ በላይ ጀግና አድርጎ የማቅረቡ ነገር ነው …እውነታውን ማስቀመጥ ይኖርብናል … ደርግን ለመጣል የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጲያዊያን ወገኖቹ በላይ መስዋእትነት ከፍሏል ይሄ የማይካድ ሃቅ ነው …. ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ከሰማየ ሰማያት የተለየ ጀግንነት ስለተቸረው ሳይሆን የትጥቅ ትግሉ በወቅቱ ለሁሉም ኢትዮጲያዊ በሚመች መልኩ ስላልተደራጀ ነበር ፡፡ እንጅኮ ደርግ ሲወድቅ ከአስራ ስምንት በላይ ብረት ያነሱ ተፋላሚዎች በኢትዮጲያ ነበሩ ! ቀደም ብለን ካየነውም በርካታ ኢትዮጲያዊ ደርግ አፍንጫ ስር ቁሞ በመፋለም ለህወሃት ትጥቅ ትግል መንገድ ከፍቷል …ተማሪዎች ለነፃነት ደማቸውን አፍስሰውላታል … ግለሰቦች ጨካኙን ስርአት ፊት ለፊት ተቃውመው ተሰውተዋል ….

… ደግሞ በህወሃት የትጥቅ ትግል ውስጥ ‹‹አምስት ሁነው ትግሉን ጀመሩ›› የሚለው የታሪክ መነሻ አምስት ሁነው ትግሉን ጨረሱ ማለት አለመሆኑን ማወቅም ተገቢ ይመስለኛል !! ሁሉም ኢትዮጲያ አንጀቱ አሮ በየቤቱ በተቀመጠበት ሰአት እንኳን አምስት አንድ ሰውም ተከተሉኝ ቢል እልፍ ያኮበኮቡ ኢትዮጲያዊያን ስርዓቱን ለመፋለም ዝግጁ ነበሩ …. ነበሩ ብቻ ሳይሆን ከህወሃት በፊት ብረት አንስተው ስርዓቱን እንቢ ያሌ ነበሩ ፡፡ ምሬት ፅዋዋ ሞልቶ ነበር ህዝብ አገዛዙን አክ እትፍ ብሎት ነበር … ህወሃት አሁን ቁጭ ብሎ ማሰብ ያለበት የሚመስለኝ አምስት ሁኖ የትጥቅ ትግሉን መጀመሩን ሳይሆን አሁን የኢትዮጲያ ህዝብ ባጠቃላይ አምስት የሚወዳቸው የሚምናቸው መሪዎች ህወሃት ውስጥ አሉ ወይ የሚለውን ነው !!

በነገራችን ላይ ህወሃት ባለፈበት ጎዳና ሁኑ መላው የኢትዮጲያ ህዝብ ከጎኑ ነበር !! የትግራይ ህዝብ ብቻው ከኢትዮጲያ ህዝብ የተለየ ጀግና ሊሆን አይችልም!! …ከወንድሞቹና ከእህቶቹ በላይ ጀብዱ እንዳለውም ማሰብ አይኖርበትም !! ይሄ እጅግ የተጋነነና የተዛነፈ እሳቤ ነው በኋላ ያልሆኑትን አድርጎ የማይገፉት ተራራ ጋር የሚያጋጨው …ሩቅ ሳንሄድ ሻእቢያ ከእኔ በላይ ጦርነት አዋቂ ከኔ በላይ ተኳሽ ላሳር ብሎ በእብሪት ከወረረን እኮ ገና አስራ አምስት አመት አልሞላውም … ይሁንና የቱንም ያህል ራሱን ጀግና ያድርግ የቱንም ያህል ራሱን ብልህና ጥበበኛ አድርጎ ያስብ ከመላው ኢትዮጲያ እንደአሸዋ የተዘረገፈው ህዝብ ነበር የከፈለውን ያህል መስዋእትነት ከፍሎ አገርን የታደጋት !! እውነቱን እናውራ ከተባለ የሻእቢያን ወረራ የትግራይ ህዝብ ብቻውን ይቋቋመው ነበር ?

መንግስት በቀረው እድሜ ሁሉ በብሔሮች መሃል በሃይማኖቶች መሃል እንዲሁም በፖለቲካ ድርጅቶች መሃል ታየም አልታየም ታወቀበትም አልታወቀበትም ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት ባይኖረው መልካም ነው ፡፡ የፈለገ ቢከፋፈል ቢለያይ ገዥውን የጋራ ጥላት ያደረገ ህዝብ በአንድ ላይ መቆሙና መልሶ ችግር መሆኑ አይቀርም ! ዛሬ 40ኛ አመት በዓሉ ሲከበርም ይሄንኑ ታሳቢ ማድረጉ የሚበጅ ይመስለኛል !

ጉዳየን ስቋጭ እራሱ የህወሃት 40ኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር ላይም ታሪካዊ ጥያቄ በማንሳት ነው …

1965 ዓ/ም የወሎ ህዝብ በእረሃብ ሲረግፍ ከታች ጀምሮ እስከላይ እስከንጉሱ ርሃቡን በመደበቅና በማድበስበስ ስለረሃቡ የተነፈሱትን ሁሉ በማሰር ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ የ80ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ለማክበር አዲስ አበባን በከፍተኛ ወጭ እያሽቆጠቆጧት ነበር ..የዜና አውታሮችም አገር ጥጋብ እንደሆነ ምርትም እንደተትረፈረፈ እየዘገቡ ነበር (እንዳሁኑ EBC) በዓሉም ሃምሌ 1965 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ ተከበረ … ይሄንና ይሄ የታፈነ ግፍና ሌላም የህዝብ በደል ተዳምሮ ንጉሱን በብርሃን ፍጥነት ከነዙፋናቸው አንኮታኮተ ኢትዮጲያንም ለሰሚው ወደሚዘገንን ወታደረዋ አገዛዝና ደም መፋሰስ ዳረጋት !!

ደርግ …በተመሳሳይ በርካታ ኢትዮጲያዊያን በተራቡበትና በእርሃብ በሚረግፉበት ወቅት የፓርቲ ምስረታ ገለመሌ በዓሉን መላዋን አዲስ አበባ በመብራትና በመፎክር አንዎጥቁጦ ሲያከብር ነበር ! ደርግም በተመሳሳይ ‹‹ጠላቶቸ …ሻእቢያ ገንይ ምናምን ከማለት ውጭ ስለውስጥ ችግሩ ትንፍሽ ሳይል ፌሽታውን አከበረ ….ዛሬስ ምን እያደረግን ነው … የእውነት ህዝባችን ፌሽታችንን ህዝባችን በዓላችንን የሚጋራበት የተረጋጋ ኢኮኖሚ ሰላም እና ዲሞክራሲ ላይ ነው …..? እንደኔ እንደኔ አዎ አገራችን በርካታ የልማትና የሰላም እምርታዎችን አስመዝግባለች ግን …በአደገኛ ሁኔታዎች ያሽቆለቆለችባቸው ሁነቶች ይበዛሉ … ስደቱ አሳሳቢ ነው …ከአገር ውጭ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም ክፍለሃገራት ወደአዲስ አበባ የሚፈልሰው ህዝብ ሲታይ ‹‹እድገቱ የፈጠረው›› እያልን ማላገጡ መፍትሄ አይመስለኝም !!

አሁን ያለው የህዝብ ብሶት ቢዘረዘር ማለቂያ የለውም ግን ህወሃትን እንደአንድ ዜጋ የምጠይቀው …ቅን ብልህና ከቂምና በቀል የፀዳ ስርዓት ለመገንባት ይነሳ … በገፍ እየጓፈፈ በየምክንያቱ በየእስር ቤቱ ያጎራቸውን ጋዜጠኞች ጦማሪያን ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት አባላትና የሃይማኖት ሰዎችን ይፍታ ! መንግስት እንኳን ውሃ ቀጠነ ብሎ ያሰራቸውን ንፁሃን ቀርቶ በብዙ ጥፋት ውስጥ ያለፉ የህግ ታራሚዎችን በምህረት መልቀቁ ህዝባዊነት ሰበአዊነት ነው !! አዎ ‹‹ 40ኛ አመት የምስረታ በዓሉ ግማሹን አስሮ ግማሹን አስጨፍሮ ›› ሊሆን አይገባም !! ከየትኛውም ድግስ ከየትኛውም ጭፈራና ንግግር በላይ ሁሉም ኢትዮጲያዊ ከህወሃት ኢህአዴግ የሚጠብቀው መሰረታዊ የአገሪቱ ችግሮች ያለምንም ምክንያት ድርደራ እንዲፈቱለት እንዲሁም ሃሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ የተለያየ ስም ተለጥፎባቸው ያታሰሩ ልጆቹን ጓደኞቹን የስራ ባልደረቦቹንና ወንድምና እህቶቹን እንዲፈታለት ነው !!

ሰላም !!

Image

በየመን የሚኖሩ የቀድሞ ኦነግ አባላት በኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር እየተመለመሉ ነው::በኬንያ ድርድሩ ቀጥሏል::

Minilik Salsawi በኬንያ የተደረገው የምልመላ እና ስብሰባ ጥሪ ሳይሳካ በተቃውሞ ታጅቦ መሰረዙ ታውቋል::በየመን በስደት የሚኖሩ የቀድሞ የኦነግ አባላት በወያኔ አጋዥነት በኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር አስተባባሪነት በሌንጮ ባቲ መሪነት ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ እየተመለመሉ መሆኑን በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገለጹ::ከወያኔ ጋር በኬንያ ድርድር እያካሄደ ያለውና በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር በየመን በመሰረተው ቅርንጫፍ አማካኝነት በወያኔ የደህንነት ሃይሎች እየታገዘ በየመን ለሚመለምላቸው የቀድሞ የኦነግ አባላት ከወያኔ አስፈላጊዉን በጀት እንደተመደበላቸው ለማወቅ ተችሏል::

የወያኔ እና የኦዴግ ዋና ግብ የአንድነት ሃይሎችን አዳክሞ የጎሳ ፌዴራሊዝምን ማስፋፋት እንዲሁም በውጪ ላሉ የጎሳ ድርጅቶች አስፈላጊዉን አሟልቶ ወደ ሃገር ቤት መመለስ ሲሆን የቀድሞ የኦነግ አባላትን አሰባስቦ ወደ ሃገር ቤት ማምጣት ሌላኛው አላማቸው ነው በዚህም መሰረት በአቶ ሌንጮ ባቲ የሚመራ ቡድን በየመን እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ሲታወቅ ወደሰላማዊ ትግል መመለስ እንጂ ወያኔን ከስልጣን የማውረድ ግብ እንዳሌለው ለተመልማዮች ባዘጋጀው ኦረንቴሽን ላይ ገልጿል::

እንዲሁም ላለፉት 40 አመታት የታገልነው የመገንጠል ጥያቄ ምንም ውጤት ስላላመጣ በጋራ ከሕወሓት ጋር በመሆን ኦሮሚያን ማስተዳደር እና በግዴታ የሚጫንን ኢትዮጵያዊነት መቃወም የሚሉ ንግግሮች ለተመልማይ ስደተኞች አስደምጠዋል::ከሕወሓት ጋር አስፈላጊዉን ድርድር እንዳደረጉና ተመልሰው ወደ ሃገር ቤት ለሚገቡ ስደተኞች አስፈላጊ የደህንነት ከለላ እና ስራም እንደሚሰጣቸው እየተሰበከ መሆኑን ከአከባቢው የሚደርሱ መረጃዎች ሲጠቁሙ በኬንያ እየተደረገ ያለውን ድርድር/ንግግር ተከትሎ ለስደተኞች ሊደረግ የታሰበው ሰበካ በሁለቱም ወገን ሳይሳካ ቀርቷል::በኬንያ የቀጠለው ድርድር ከኦሮሞ ተወላጆች ተቃውሞ እየቀረበበት ሲሆን ቀጣዩ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ጉዞ አለየለትም የሚሉ ወገኖች ቢከሰቱም ወደ ሃገር ቤት ለመግባት አስፈላጊዉን ሁሉ ከመስማማቱም በላይ ወደ ሃገር ቤት ለሚመለሱም ወገኖች አስፈላጊዉን ክፍያ ለማድረግ ከወያኔ ገንዘብ እንደተቀበለ ለግንባሩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል::