የለውጥ ሃይል የሆኑት የአፋር ድርጅቶች ግንባር መፍጠር ለትግሉ አንድ እርምጃ መራመድ አስታውጾ አለው::

Minilik Salsawi በኢትዮጵያዊነቱ እና በሃገር ወዳድነቱ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ የነጻነት እና የመብት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ በአምባገነን መዳፍ ስር ያለው ሕዝብ ነጻ እንዲወጣ ወያኔን ለመጣል በትጥቅ ትግል ላይ የተሰማሩ አፍዴራ ጋድሌ እና አርዱፍ በመዋሃድ የጋራ ግንባር መፍጠራቸው እየተካሄደ ላለው ትግል አንድ እርምጃ መራመድ ትልቅ አስታውጾ ያለው ተግባር ነው::
ፓርቲዎች ባለፉት ዘመናት በተናጠል በመታገል ምንም ውጤት እንዳላገኙ በገሃድ የታየ ጉዳይ ነው::እንዲሁም በሀገር ቤት ያሉ ድርጅቶች ሊዋሃዱ አሊያም ግንባር ሊፈጥሩ በሚፈልጉበት ወቅት የወያኔ አምባገነን ገዢ ደህንነቶቹን አሰማርቶ ከፍተኛ ወከባ በመፍተር ሰርጎ ገቦችን በማስረግ ክፍተኛ መንግስታዊ ሽብርተኝነት እና እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል::በቅርቡ በአስመራ የተካሄደ ውህደት እና አሁንም በአፋር ድርጅቶች መካከል የተደረገው የግንባር ምስረታ ለትግሉ ታላቅ ግብ እና እመርታ ነው::
የግንባሩን መፈጠር ተከትሎ የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ በመድረሳቸው፣ በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ሆነው ለመታገል ወስነዋል።አዲሱ ግንባር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመታገል ፍላጎት እንዳለውም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል።