የወያኔ የደህንነት አካላት አለመግባባታቸው እየሰፋ መሆኑ ተገለጸ::

ተቃዋሚዎች በሰከነ መንገድ ክፍተቱን መጠቀም እንዳለባቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል::Minilik Salsawi
ለ24 አመታት ያህል ሰራዊቱን እና የደህንነቱን ክፍል በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር ያዋሉት የወያኔ ጁንታ አምባገነኖች መውደቂያቸው መድረሱን ተከትሎ በደህንነት አካላት መካከል ያለው አለመግባባት እየሰፋ መምጣቱን የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል::በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ያሉ ደህንነቶች ላይ እምነት ያጣው የወያነው አምባገነን አዳዲስ የደህንነት አባላት ለቁጥጥር መመደቡ ታውቋል::

በደህንነት ክፍል ውስጥ በመላው ሃገሪቱ የተመደቡ የደህንነት አባላት ላይ እምነት እንዳሌለው የሚናገረው ወያኔ በተለያየ ጊዜ ዝውውር ቢያደርግላቸውም በሃላፊዎች እና በደህንነት አባላቱ መካከል አለመግባባቶች እየሰፉ መነካከስ መቀጠሉን ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ አገላለጽ የደህንነት አባላቱ የጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ቢደረግላቸውም ከሃላፊዎች ጋር አለመግባባቱ እንዲሁም በመካከላቸው ያለ መተማመን መናዱ በግልጽ እየታየ ነው ሲሉ ተናግረዋል::

ተቃዋሚዎች የወያኔን መፈረካከስ እና በሰራዊቱ እንዲሁም በደህንነቱ አካላት ዙሪያ የተነሳዉን ክፍተት ተጠቅመው በሰከነ እና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ለለውጥ በሚደረገው ትግል ጎን ለጎን ያለውን አለመግባባት ክፍተት በመጠቀም የወያኔን ውድቀት ማፋጠን አለባቸው ሲሉ ምንጮቹ አስተያየት ሰጥተዋል::