ይህ የምርጫ ማኒፌስቶም ሀገሪቱ አሁን ካለችበት የኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሚደረግ ሽግግር ወቅት በሀገራችን ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ተወዳድሮ ማሸነፍ ቢችል የሚያከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር የሚተነትን ነው፡፡ ይህ የምርጫ ማኒፌስቶ በዋናነት በሦስት ምዕራፍ የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው የፖለቲካ ሥርዓቱ አደረጃጀት ምን መምሰል እንዳለበት የሚገልፅ ክፍል ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ሰማየዊ ፓርቲ ባለፉት 24 ዓመታት የህወሀት/ኢህአዴግ መራሹ ሥርዓት በሀገራችን ላይ የፈፀማቸውን የተሣሣቱ የፖለቲካ ሂደቶች በዝርዝር የሚያስቃኝ ሲሆን፤ በአንፃሩም ፓርቲው በሥልጣን ላይ ቢቀመጥ በዋነኛነት በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን የፌደራል ሥርዓት በመቀየር መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈርንና፣ ልማትና ሌሎች ማህበራዊ ትስስሮችን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡ በመንግሥት አወቃቀሩ፣ በነፃ-ፕሬስ፣ በመከላከያ ፖሊስና ደህንነቱ አወቃቀር እንዲሁም የውጭ ግንኙነት አማራጭ ፓሊሲውም በዝርዝር በማኒፌስቶው ላይ የተቀመጡ አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡

በሁለተኛዉ ምዕራፍ የማህበራዊ ሥርዓቱን በተመለከተ የተዘረዘሩ ነጥቦችን የያዘ ሲሆን ህወሃት /ኢህአዴግ በሀገራችን ሕዝብ ላይ በማህበራዊ ዕድገቱ ላይ ያስከተለውን ሁለንተናዊ ቀውሰ በማስቃኘት፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሠረታዊ የማህበራዊ ጉዳይ ፍልስፍና የሆነውን ጤነኛና በእውቀት ላይ የተመሠረተ በራሱ የሚተማመን ዜጋን ለመፍጠር ዋነኛ ምሰሶ የሆነውን ትምህርትና ጤና ላይ ያለውን ፖሊሲ በማስቃኘት ጀምሮ በማኅበረሰቡ ውስጥ በዕድሜያቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የዕድሜ አንጋፋዎችና በተፈጥሮና በአደጋ አካላቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸውን የኅብረተሰቡ ክፍሎች የሚሰጠውን ድጋፍ ይተነትናል፡፡ በተጨማሪም ሰማያዊ ፓርቲ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ኪነ-ጥበብ፣ ስፖርት እና መሰል ማኅበራዊ ጉዳዮች የሚመለከትባቸውን እይታዎች ያስቃኛል፡፡

በመጨረሻም በዚህ ማኒፌስቶ በጥልቀት የተገለፀው የፓርቲውን የኢኮኖሚ አማራጭ የሚያሣየው ምዕራፍ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የህወሃት/ኢህአዴግ ሥርዓት እከተለዋለሁ የሚለውን ገጠርን ማዕከል ያደረገ ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ በማስቀድም ልማት የሀገሪቱ መሠረታዊ ጥያቄ ስለሆነ በሚል ለኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ቅንጦት እንደሆነ በመቁጠር ሁሉ ነገራችንን ለልማት በሚል ሰበብ በሀገራችን ኢኮኖሚ ለውጥና ዕድገት ላይ የፈጠረውን ደንቃራ በጥልቀት ይመረምራል፣ ትችቱንም ያቀርባል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ በሕዝብ ተመርጦ የመንግሥትነት ሥልጣኑን ቢይዝ፤ በሀገሪቱ ውስጥ የሚያሰፍነውን የኢኮኖሚ መርህ ያሳያል፡፡ በዚህም መሠረት ሰማያዊ በሀገራችን ተግባራዊ ለማድረግ ያቀዳቸዉን የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማራጮች በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን በዋነኝነትም የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ በተመለከተ አርሶ አደሩን የመሬቱ ባለቤት የሚሆንበትን መብት ማረጋገጥ፤ እንዲሁም ሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች የትኩረት አቅጣጫ ገበያ መር ሆኖ ዜጎች በፈለጉት ሙያ እና የሥራ መስክ ተሰማርተው፣ ሀብት የማፍራት፣ በሕጋዊ መንገድ የንብረት ባለቤት የሚሆኑበት በተጨማሪም በሀገሪቱ በሁሉም አቅጣጫዎች ተሰማርተው የሚሠሩበትን መብት የሚያረጋግጥ እንዲሆን የሚረዳ የፖሊሲ አማራጩን አስቀምጧል፡፡

Feven Tashome is a study in blue. The 21-year-old’s toenails are painted a rich cobalt, her scarf is baby blue and her leather handbag is ultramarine. To ordinary passersby in the Ethiopian capital of Addis Ababa, it’s a fashion statement; to members of Ethiopia’s beleaguered political opposition, it’s a secret handshake.
Feven (Ethiopians go by their first names) is showing her allegiance to an opposition party with an odd name, and an even odder theme song.
The Blue Party is one of Ethiopia’s few remaining opposition parties. Ethiopia is technically a multiparty parliamentary democracy, like Britain, but it is effectively run like a one-party state, with 99.8 percent of parliamentary seats controlled by one ruling party, the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front, or EPRDF.
After the Blue Party was founded three years ago, it organized a peaceful anti-government protest in a country that hadn’t permitted public rallies for a decade. The parade of young Ethiopians demonstrating in jeans and blue T-shirts seemed a sign that the government was relaxing its grip. But with new elections this May, the Blue Party claims that subsequent rallies have been met violently by police. They say hundreds of their delegates have been fired from their jobs or beaten up by thugs.
Blue Party spokesman, 27-year-old Yonatan Tesfaye, says blue is a symbol of two powerful unifying images for Ethiopians: the Blue Nile, and the Red Sea (which is actually turquoise most of the year). Blue is also the color of Twitter and Facebook; social media are one of the last remaining outlets for relatively uncensored expression in the country.
But to the Ethiopian government, “blue” is a symbol of rebellion, like the “Orange Revolution” in Ukraine or the failed “Green Movement” in Iran.
A documentary, the airing of which on Ethiopian state television last year was timed with U.S. Secretary of State John Kerry’s official visit, accused Western human rights groups of trying to instigate the overthrow of the Ethiopian government in what the documentary calls a “color revolution.”
Also timed with Kerry’s visit, the government arrested and imprisoned nine bloggers and journalists critical of the regime. Kerry, who was mainly in Ethiopia to encourage American investment in the skyrocketing Ethiopian economy and to express gratitude for a military partnership (the Ethiopian army is a proxy for intervention in many African hotspots), advised the government to release the journalists and bloggers. He was ignored.
Genenew Assefa, the political adviser to Ethiopia’s minister of communication, is a chain-smoker in a black jacket with a well-thumbed paperback of Hegelian philosophy on his desk.
He dismisses the Blue Party as insignificant (he describes them as “young people running around, screaming around”) but at the same time warns that Westerners do not appreciate how Ethiopia’s “fledgling” 25-year-old democracy is under siege by ethnic separatists and Muslim extremists — some of whom he claims take shelter in the Blue Party.
Ethiopia is majority Christian, “but we have problems with radical Muslims in this country,” Genenew says slowly and deliberately. “And we will suppress. We will not tolerate.”
The Blue Party says it is not Islamist, but secular, with a peaceful and reformist platform: pro-civil rights and anti-corruption.
But the party’s PR strategy is unique in Ethiopian politics. In direct response to the government’s attempt to paint opposition groups as violent and scary, the Blue Party has, from its inception, sought to portray the opposite image.
Even Yonatan, the Blue Party spokesman, says he doesn’t expect his party to win a single parliamentary seat in the upcoming election. The ruling party, while politically repressive, has presided over the fastest growing economy in Ethiopian history. The former high school teacher says he’ll be happy if the Blue Party just becomes an umbrella for people to voice their discontent.
“People are very scared of the politics — they fear the situation,” and become disengaged and apathetic, he says. “So we’re trying to break them out of the fear.”

Source: http://www.npr.org/blogs/parallels/2015/03/10/391917530/ethiopias-blue-p…

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸው በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን የትብብሩ ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ዕጩዎቻችን በዝርዝር ሊያሳውቀን አልቻለም፡፡ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ከምንም በላይ ግን በዕጩዎች ስረዛና ወከባ በርካታ ጊዜ አጥፍቶብናል፡፡›› ሲሉም ሰልፉ የተራዘመበትን ምክንያት ገልጸዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ የትብብሩን አባል ፓርቲዎች ዕጩዎች በዝርዝር ባለማሳወቁ፣ አባል ፓርቲዎቹ ለምርጫ ቦርድ ቅሬታ እያቀረቡ በመሆኑና አሁንም ድረስ ከምርጫ ቦርድ ጋር ያሉት ችግሮች ያልተፈቱ በመሆናቸው ትብብሩ ሰልፉ የሚደረግበትን ቀን ወደፊት ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል፡፡

እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን።

በምርጫ ቦርድ ስም የተወሰነው ህገ-ወጥ ውሣኔ ምክንያት መላ የአንድነትና የመኢአድ አባላት የፖለቲካ እንቅስቃሴአቸው ተገድቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአገራቸው ካላቸው ፅኑ ፍቅር አኳያ ትግሉን ለማስቀጠል ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የአባልነት ፎርም በመሙላት ትግሉን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን! እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡

ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡ በቀጣይም በጋራ የኮሚቴ ውይይቶችን እያደረግን ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡

የሰማያዊና የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበራት

የካቲት 19 2007 ዓ/ም

Eng.Yilkal Getnet

• ‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡

ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል

ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

• ‹‹ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ እንዲቆይ አይፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደተሰረዙበት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ አንድን ዕጩ ለመሰረዝ የሚያበቃ ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ያስመዘገብናቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን በመሰረዝ ከምርጫው ውድድር ውጪ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡

በየክፍለ ሀገሩ የተሰረዙት ዕጩዎች ‹‹ፓርቲው ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርቷል፣ የሌሎች ፓርቲዎች አባላት ናችሁ›› የመሳሰሉ ምክንያቶችና ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን በአንጻሩ በአዲስ አበባ የተሰረዙት ዕጩዎች ከምርጫ አስፈጻሚዎች ምንም አይነት ምክንያትና ደብዳቤ እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዕጩዎቹ ‹‹የተሰረዝንበትን ምክንያት ንገሩን፣ ደብዳቤ ልትሰጡን ይገባል›› ቢሉም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ‹‹እኛ እናንተን ለመመዝገብ ችግር የለብንም፡፡ ግን ከበላይ አካል እንዳንመዘግብ ተነግሮናል፡፡ ደብዳቤም ልንሰጣችሁ አንችልም፡፡›› የሚል መልስ እንደሰጧው ተግልጾአል፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች መሰረዛቸውን ተከትሎ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የቦርዱን ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃናን ለማግኘት ቢጥሩም ‹‹ከከተማ ውጭ ናቸው፡፡ አሁን አታገኟቸውም›› የተባሉ ሲሆን ፕ/ር መርጋ የህወሓትን 40ኛ አመት ለማክበር መቀሌ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በትናንትናው ዕለት በጉዳዩ ላይ ከቦርዱ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፌሳ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን አቶ ነጋ ‹‹ማመልከቻ አስገቡ›› ከማለት ውጭ ዕጩዎቹ ለመሰረዛቸው ተጨባጭ ምክንያት መስጠት እንዳልቻሉ ኢ/ር ይልቃል ገልጸውልናል፡፡

‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ያለ አግባብ የሚሰርዙት ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ ጫና መፍጠር ስለሚችል በሂደቱ እንዲቆ ስለማይፈልጉ ነው›› ያሉት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፤ ሆኖም ይህ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለነጻነት የሚያደርጉትን ትግል ትክክለኛ እንደሆነ እንዳስረገጠላቸው፣ ይህን የነጻነት ትግልም አጠናክረው እንደሚቀጥሉና የካቲት 22 ፓርቲያቸው ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ በ15 ከተሞች የሚያደርገው ሰልፍ የዚሁ የነጻነት ትግል አካል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሁለተኛ ዙር የሠላማዊ ትግል ጥሪውን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላለፈ፡፡ ትብብሩ የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ከተሞች ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በሳምንት አራዝሞ ለየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ማስተላለፉንም አስታውቋል፡፡

ትብብሩ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ገዢው ፓርቲ የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድም የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተለያዩ የህዝብ እንቅስቃሴዎች መገንዘቡን ገልጹዋል፡፡ ትብብሩ ምርጫን በተመለከተ እንዳስታወቀው ኢህአዴግ ስለመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው መሆኑን በዚህ የምርጫ ወቅት በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ እየወሰደ ያለው ህገ-ወጥ እርምጃ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

‹‹ለውጡ የሚመጣባቸው አምባገነኖች ድንገተኛ ከፍተኛ ፍርኃትና ሥጋት በማሳደሩ ህገ-መንግሥቱን በመጨፍለቅ በግልጽና በአደባባይ ህገ-ወጥ ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን ለመውሰድ መገደዳቸው፣ ይህም የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት በማሳደግ ህዝባዊውን ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገሩ የበለጠ ግልጽ ሆኗል›› ብሏል ትብብሩ፡፡

ትብብሩ አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ የአገራችንና ዜጓቿ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሁለት አማራጮች ላይ የተንጠለጠለ ነው ያለው መግለጫው፣ አንድም ያለውን አምባገነናዊ ሥርዓት ተቀብሎ የጭቆና ቀንበር ተሸክሞ በከፋ ውርደት ሥር ሰጥ- ለጥ ብሎ መገዛት፣ አሊያም አምባገነንነትና ጭቆናን ‹‹በቃ›› በማለት በሕዝባዊ የተቀናጀ ሰላማዊ ትግል ለአገራችን ሉዓላዊነትና የዜግነት ክብራችንን ለማስመለስ በህገ መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን ትግላችንን እስከማይቀረው ለውጥ ድል ደጃፍ ድረስ በቆራጥነት መቀጠል ናቸው ብሏል፡፡

በዚህም ትብብሩ ህገ-መንግስታዊ መብትን በመጠቀም በህግና በሥርዓት ትግሉን ለመምራት መዘጋጀቱን በመግለጽ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የትግል ጥሪውን እንዲቀላቀሉት አሳስቧል፡፡ ስለሆነም ትብብሩ ‹‹ኢህአዴግነት ከዜግነት በላይ›› ለሆነባቸው የሥራ ዋስትናቸው፣ ዕድገትም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሙያቸው፣ በልምዳቸው፣ ክህሎታቸው፣ በመሳሰሉት ባልተመሰረተ መልኩ በደል እየደረሰባቸው ላሉ ሁሉ የትግል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

‹‹የህወኃት/ኢህአዴግ ተራ አባላትና ካድሬዎች፤ የፖለቲካ ልዩነት የተለያየ አመለካከትና ሀሳብ ማራመድ ጤናማ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ መገለጫ እንጂ እንደሚነገራችሁ ‹‹ጠላትነት›› ባለመሆኑ፣ ትግላችንም ለሠላማዊና ህጋዊ የሥልጣን ሽግግር እንጂ በናንተ ‹‹መቃብር›› ላይ አዲሱን ሥርዓት የማቆም፣ የነበረውን አጥፍቶ ከዜሮ የመጀመርና እናንተን የማጥፋት ዓላማ እንደሌለው ተረድታችሁ፣ ተቃዋሚዎች እንደናንተው ኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያና ህዝቧ የሚጨነቁ መሆናቸውን በመረዳት ተቃዋሚዎችን እንደ‹‹ ጠላት›› ከመመልከት አስተሳሰብ ራሳችሁን ነጻ እንድታወጡ›› ሲልም ትብብሩ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ወጣቶችና ሴቶች በተለይም የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች፣ መምህራንና ተማሪዎች በተለይም የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የእምነት ነጻነት መብት ጠያቂ የማኅበረሰብ አባላት፣ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፣ የፍትህ አካላት፣ የዴሞክራቲክ ፓርቲዎች አባላት፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ሰላማዊ ታጋዮች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵዊያን/ዲያስፖራዎች እና ሌሎችም ጥሪው የተላለፈላቸው አካላት መሆናቸውን መግለጫው አትቷል፡፡

በመሆኑም፣ ‹‹በምናርገው አገራዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በአንድነትና በቆራጥነት እንድትሰለፉ፤ የካቲት 22/07 በየከተሞቹ በቦታውና በሰዓቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን አበክረን እናቀርባለን›› ብሏል የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር፡፡

• የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ንግድ ቤት ታሽጓል

ምርጫ ቦርድ በሰማያዊ ፓርቲ ምልክትና ስም የተመዘገቡትን ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲታገዱ በየ ክልሉ ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ በላከው ደብዳቤ ገለጸ፡፡ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ክልል የምርጫ ጣቢያ በላከው ደብዳቤ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ትብብር የሚባል መስርቻለሁ፣ እያስተባበርኩ ነው በማለት እንዲሁም ሌሎች የህግ ጥሰቶችን በመፈጸሙ›› በሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው በመግለጽ በፓርቲው ምልክት ሊወዳደሩ የተመዘገቡትን አባላት ህገ ወጥ ናቸው ብሏል፡፡

ምርጫ ቦርድ በደብዳቤው ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ የራሱ አባል ያልሆኑ ፓርቲውን የማይወክሉ ግለሰቦችን ዕጩ አድርጎ በፓርቲው ምልክት በከፍተኛ አመራር ፊርማና ማህተም አረጋግጦ ለምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች አሳውቆ ከሆነ የምርጫ ሂደት የሚያሰናክል የህግ ጥሰት በመሆኑ….›› በሚል እንዳይመዘገቡ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ የሌሎች ፓርቲ አባላት በሰማያዊ ተጠቃልለው ምርጫውን በሰማያዊ ምልክት መወዳራቸውም የሚያስጠይቅ ነው ሲል ገልጾአል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ዞን ሁሉም ወረዳዎች ከሌሎች ፓርቲዎች ወደ ሰማያዊ በመጠቃለል በሰማያዊ ምልክት ለመወዳደር የተመዘገቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ከዕጩነት እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ክልል ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ደብዳቤ መጻፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ከዕጩነት ለመሰረዝ የሚያስተላልፈው ትዕዛዝ ህገወጥና የፖለቲካ ውሳኔ ነው ያሉት የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ‹‹ችግር ካለ በየምርጫ ጣቢያው ይፈታል እንጅ ምርጫ ቦርድ ይህን መዝግብ አትመዝግብ ብሎ ለየምርጫ ጣቢያው ትዕዛዝ ሊሰጥ አይችልም፡፡›› ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ ለየክልል ቅርንጫፎቹ ደብዳቤውን የጻፈው የምዝገባ ጊዜው ካለቀ በኋላ ሲሆን ይህም የሆነው ፓርቲው በአካባቢው ተለዋጭ ዕጩ እንዳይኖረው ታስቦበት ነው ሲሉ ኃላፊው ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የትኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ጠንክሮ እንዳይወጣ የታለመ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ የሌሎች ፓርቲ አባላትን በማሰባሰብ የህዝብን ስልጣን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጠንካራ ትግል ለማደናቀፍ ነው ብሏል፡፡ የህዝብ ግንኙነቱ ኃላፊው አክሎም ‹‹የሌሎች ፓርቲዎች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ መቀላቀላቸውን ተከትሎ ስርዓቱ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥሮበታል፡፡ ይህ የምርጫ ቦርድ ተግባርም ህጋዊ ሳይሆን ከስርዓቱ ፍርሃት የመነጨ የፖለቲካ ውሳኔ ነው›› ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በፓርቲው ላይ እያደረጉ የሚገኘውን ህገ ወጥ ተግባር ሰማያዊ ፓርቲ እንደማይቀበለውና ትግሉን እናዳክማለን ብለው የሚወስዱት ውሳኔ ይበልጡኑ ትግሉን ያጠናክረዋል ብሏል፡፡

በሌላ በኩል በወላይታ ዞን ቦሎሶሶሬ በሚባል ምርጫ ጣቢያ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር በዕጩነት የቀረቡት አቶ ከበደ ካምፔሶ በዕጩነት መቅረባቸውን ተከትሎ የንግድ ቤታቸው መታሸጉ ታውቋል፡፡ ‹‹ዕጩ እንዳልሆን በሰው ለማግባባትና በማስፈራራት ሊያስቆሙኝ ሳይችሉ ሲቀሩ የንግድ ተቋሜን ዘግተዋል፡፡ ጥያቄያቸው ከፓርቲው እንድወጣና ዕጩነቴን እንድተው ነው፡፡›› ሲሉም አቶ ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፓርቲን ለተቀላቀሉትን የቀድሞ የአንድነት አባላት እሁድ የካቲት 8/2007 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፕሮግራሙን ማዘጋጀት ያስፈለገው ምርጫ ቦርድ በአንድነት ላይ በወሰደው እርምጃ ተስፋ ሳይቆርጡ ሰማያዊ ፓርቲን የተቀላቅሉ አባላት ትግሉን ለማጠናከር ያሳዩትን ቆራትነት እና አብሮነት ለማጠናከር እንደሆነ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡

ከጥር 26/2006 ዓ.ም ጀምሮ ፓርቲውን የተቀላቀሉትና አሁንም መቀላቀሉ የሚፈልጉት የቀድሞው የአንድነት አባላት በፕሮግራሙ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረቡት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሁለቱ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ጥላ ስር አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጡ ተስፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ነፃና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል መርሀ ግብር በማዘጋጀት ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እስካሁን ከተደረጉት እንቅስቃሴዎችም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድና የመንግስት አስፈፃሚ ተቋማት በህገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩና የፖለቲካ ምህዳሩም ለሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ፍትኃዊ እሰኪሆን ድረስ የነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ ዘመቻችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች እጩ ተወዳዳሪዎችን ለማስመዝገብ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የምርጫ አካባቢዎች በዕጩ ተወዳዳሪዎቻችን ላይ በገዢው ፓርቲ አባላትና በምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ከፍተኛ እንግልትና እንቅፋት የተፈጠሩባቸው ሲሆን ለአብነት ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡
1. በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እጩ ተመዝጋቢዎች የተወለዱበት ዞን መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን ምስክር አምጡ በማለት እንዳይመዘገቡ ተደርገዋል፡፡
2. በሰሜን ጎንደር ዞን ባሉ ወረዳዎች በሙሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች ፅ/ቤቶችን ዘግተው በመጥፋታቸው ምክንያት መመዝገብ በተደጋጋሚ የሄዱ እጩ ተመዝጋቢዎች ሳይመዘገቡ ጊዜው እንዲያልፍባቸው ተደርገዋል፡፡
3. በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በምርጫ አዋጁ መሰረት 1 እጩ ተመዝጋቢ ቅሬታ እስካልወቀረበበት ድረስ የመመዝገብ መብት እንዳለው እየታወቀ ነገር ግን የምርጫ ፅ/ቤት ሃላፊዎች የሌላ ፓርቲ አባላት ናችሁ ከፓርቲያችሁ መልቀቂያ ካላመጣችሁ በሚል ምክንያት በርካታ የፓርቲያችን እጩዎች ሳይመዘግቡ መልሰዋል፡፡
4. በሰሜን ሸዋ፤ በሲዳማ፤ ጋምቤላ፤ ጋሞጎፋ፤ በምስራቅና በምእራብ ጎጃም አካባቢዎች እጩ ተመዝጋቢዎችን በገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ታጣቂዎች በማስፈራራት፤በአካባቢ ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶች በማሰወገዝ ራሳቸውን ከእጩነት እንዲያገሉ ተፅእኖና ግፊት ተደርጎባቸዋል፡፡
5. በደቡብ ክልል የገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች እጩዎችን ሊያስመዘግቡ የሄዱ ተወካዮችን በማሰርና በእጃቸው የሚገኘውን የእጩዎች ማስመዝገቢያ ደብዳቤዎች በመንጠቅ የምዝገባ ጊዜው እንዲያልፍባቸው ተደርጓል፡፡
6. በሰሜን ጎንደር፤ በሲዳማና በከምባታ ዞኖች የፓርቲው እጩ አባላት በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡
7. በደቡብ ኦሞ ዞን የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልተው የተመዘገቡ የፓርቲያችን እጩዎች በ05/06/07(ማለትም የምዝገባው ጊዜ ካለቀ በኋላ)በደ/ቁ-አ573/ፖአ/ጠ470 ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ክልል ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት በተፃፈ ደብዳቤ 18 የክልል ምክር ቤትና 6የተወካዮች ምክር ቤት በድምሩ24 እጩዎች እንዲሰረዙ ተደርጓል፡፡
እነዚህና ሌሎችም ጥፋቶች የሚፈፀሙት ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ነጻና ፍትሀዊ በሆነ የምርጫ ሜዳ እንዳይሳተፉ በማድረግ የአምባገነናዊን መንግስት የስልጣን ዘመን ለማስረዘም በዕቅድ የተፈፀሙ ድርጊቶች መሆናቸውን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ በእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎችም በማለፍ ፓርቲያችን ለመንግስትነት የሚያበቃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እጩ ተወዳዳሪዎችን በመላ የሐገራችን ክፍሎች አስመዝግቧል፡፡

ገዥው ፓርቲ በስልጣን ለመቆየት እንደ ስልት የያዘው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሕዝብ ዘንድ እምነት እንዲያጡ በብቸኝነት በተቆጣጠራቸው የመንግስት የመገናኛ ዘዴዎች ሥም ማጉደፍና ሕዝብም በምርጫው እምነት እንዲያጣ በማድረግ ከራሱ ደጋፊዎች ውጭ ሌሎች ዜጎች በንቃት እንዳይሳተፉ ማድረግን ነው፡፡ በመሆኑም ሕዝቡ በገዥው ፓርቲ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሳይዘናጋ የፈለገውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ በንቃት እንዲሳተፍና የመራጭነት ካርዱንም እንዲወስድ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ከህገ ወጥ አሰራር እንዲቆጠቡ ፓርቲያችን በአፅንኦት እያሳሰበ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የመሰረተውን ትብብር በማጠናከርና በምርጫውም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ውጤት ለማምጣት ሰማያዊ ፓርቲ ጠንክሮ የሚሰራ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

የካቲት 6 ቀን 2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ

በዘንድሮው ምርጫ ሰማያዊን ወክለው በመቀሌ ለውድድር የቀረቡት አቶ አስገደ ገ/ስላሴ በፖሊስ እየታደኑ መሆኑን ገለጹ፡፡

አቶ አስገደ አሁን ላይ ከቤታቸው ውጭ ከተማ መውጣታቸውን ገልጸው፣ ቤታቸው ሦስት ፖሊሶች ሄደው ‹‹አቶ አስገደ የት ናቸው? ይፈለጋሉ!›› በሚል አሁንም ድረስ ቤታቸው አካባቢ እየፈለጓቸው መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

• በወር 40 ሺህ ብር ኪራይና 250,000 ብር ለ‹‹ኪሳራ›› እንዲከፍል ተጠይቋል

ሰማያዊ ፓርቲ የካ ክ/ከተማ በቀድሞው መጠሪያው ቀበሌ 15 እንዲሁም በአዲሱ መጠሪያው ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 460 የሆነውን ጽ/ቤቱን 25000 ሺህ ብር ቅጣት ከፍሎ እንዲለቅ በአከራዮቹ በኩል ክስ ቀረበበት፡፡ በከሳሽ እነ አቶ ሚስጥረ ሽበሽ የተመሰረተው ክስ ‹‹ቤቱን ለቀው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው …በወር ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ሒሳብ ከጥር 16 ቀን 2007 ጀምሮ ቤቱን ለቀው እስከሚያስረክቡ ድረስ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉን›› ያሉ ሲሆን ‹‹ከሳሽ ቤቱን ለማደስ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በገባነው ውል መሰረት የደረሰብንን 250 ሺህ ብር ኪሳራ እንዲተኩልን›› ሲሉ ከሰዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሚፈልግባቸው ጊዜያት የቀበሌ ካድሬዎች አከራዮቹና ደላሎቹ ለፓርቲው እንዳያከራዩ ሲያስጠነቅቁ የቆዩ ሲሆን በተለይ በጥር ወር 2007 ዓ.ም ይህ ጽ/ቤት እንዳይከራይ ግፊት የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡
በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡

‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡
በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

•‹‹ኢህአዴጎች ለፈለጉት ሰው ቤት-ለቤት እያደሉ ነው››

በምስራቅ ጎጃም ዞን የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጭነት ካርድ የሚያወጡ ዜጎችን ‹‹ካርድ ሰጥተን ጨርሰናል›› በሚል ምክንያት ከሁለት ቃናት በፊት ጀምሮ ብዙ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡
ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን ወረዳ የቦቅላ የምርጫ ክልል በአብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን የገለጹት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ ከፍተኛ ወከባ እየደረሰ ነው ሲሉም አክለው ገልጸዋል፡፡

‹‹አካባቢው ገጠር ነው፤ የምርጫ ጣቢያዎች በአብዛኛው ክፍት ይሆኑ የነበረው እሁድ ነበር፡፡ አሁን ግን እሁድም ዝግ ናቸው፤ ስለዚህ ካርድ መውሰድ አልቻልንም፡፡ ኢህአዴጎች ግን ለራሳቸው ሰው ቤት-ለቤት ካርዱን እያደሉ ናቸው፡፡ ሚሊሻውና ካቢኔው በየቤቱ እየዞረ ለፈለገው ሰው ብቻ ይሰጣል፤ ኢህአዴግን አይመርጥም ብለው ለሚያስቡት ደግሞ ‹የለም› ይላሉ›› ሲሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ዜጎች ካርድ ለመውሰድ ወደ ጣቢያዎች በሄዱበት ወቅት ‹ለምን ቀኑ ሳይደርስ ይዘጋል› ብለው ሲጠይቁ፣ ‹‹ከበላይ አካል የወረደ ትዕዛዝ ነው›› መባላቸውንም ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የስርዓቱን አረመኔያዊ እርምጃ እናወግዛለን!

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አብሮ ስለመስራትና ሌሎቹም ትብብሩን እንዲቀላቀሉ በየጊዜው የሚወተውተው አገራችን በዚህ ዘመን በማይመጥን አምባገነንና የጭካኔ ስርዓት ውስጥ የምትገኝ መሆኑን በመረዳቱ ነው፡፡ ይህ የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነንና ጨካኝ ስርዓት ህዳሩ 27/28 2007 ዓ.ም የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በወጡት አመራሮቻችን፣ አባላቶቻችን፣ ደጋፊዎቻችንና በየጎዳናው የተገኙት ንፁሃን ላይ ከፍተኛ ድብደባና የጅምላ እስር በመፈፀም ስርዓቱን ለመታገል የተነሳነበትን አላማ ትክክለኝነት አረጋግጦልናል፡፡

በዛሬው ዕለትም ገዥው ፓርቲ በፓርቲያቸው የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የሚፈፅመውን ደባ፣ ምርጫ ቦርድንና የህዝብ ሚዲያን ተጠቅሞ ፓርቲውን ለመከፋፈልና አሳንሶ ለማሳየት የሚያደርገውን እኩይ ተግባር በመቃወም ሰልፍ የወጡ የአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎችና የፓርቲው ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው ቤተ ክርስትያን አካባቢ የነበሩ አዛውንት ምዕመናንን ሳይቀር በመደብደብ ጭካኔውን ዳግመኛ አሳይቶናል፡፡ ፖሊስ በትዕዛዝ በአንድነት አባላት ላይ ከፍተኛ የጭካኔ እርምጃ ወስዷል፡፡ አብዛኛዎቹንም በጅምላ አስሯል፡፡

ስርዓቱ በእነዚህ ሰላማዊ ዜጎች ላይ አሁንም የጭካኔ እርምጃውን መድገሙ ስልጣኑን የማጣት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳለ እና ከይስሙላ ያለፈ ለሰላማዊ ትግሉ ዝግጁ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ትብብራችን የስርዓቱን ጨካኝነት እያወቁም ቢሆን በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ በስርዓቱ የማይከበረውን ህገ መንግስታዊ መርህ ተከትለው ሰልፍ ለወጡ ቆራጥ የአንድነት አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች አድናቆቱን መግለጽ ይወዳል፡፡ መስዋዕትነታችሁ ለነገ ድላችን ስንቅ በመሆኑ ይበልጡን ተጠናክራችሁ በጋራ ትግላችን እንደምናጠናክርም እምነታችን ነው፡፡

በተቃራኒው ገዥው ፓርቲ ህግ የማክበርና የማስከበር ሚናውን ረስቶ ፖሊስ፣ ደህንነትንና ሌሎች ተቋማትን ለራሱ ስልጣን ማስጠበቂያ በማዋል በአንድነት አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎች ላይ የፈፀመውን ለዘመኑ የማይመጥንና በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለጠየቁት ኢትዮጵያውያንም የማይገባ የጭካኔ እርምጃ በጥብቅ እናወግዛለን፡፡

ኢትዮጵያውያንን የማስተዳደር አቅምና ሞራል ያጣው ገዥው ፓርቲ የዜጎችን ጥያቄ በኃይል ማዳፈን የማይቻል መሆኑንና አገራችን ወደባሰ ችግር እንደሚከታት ተረድቶ ከዚህ የጭካኔ እርምጃው እንዲቆጠብ፣ እርምጃውን የወሰዱትን አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና የታሰሩትን በአስቸኳይ እንዲፈታ እናሳስባለን፡፡ ፖሊስ፣ ደህንነት፣ መከላከያና ሌሎች ተቋማት ገዥው ፓርቲ አላፊ መሆኑን በመገንዘብና ከገዥው ፓርቲ ታዛዥነት በመውጣት ወገኖቻቸሁ ላይ እንዲህ አይነት የጭካኔና አሳፋሪ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥባችሁ ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡

ያለ መስዋዕትነት ድል የለም!

ጥር 17/2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለሚያደርገው የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር የአደባባይ ስብሰባ የተላከውን ደብዳቤ ተቀበለ፡፡ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር በአንድ ወር ውስጥ ከሚያደርጋቸው መርሃ ግብሮች መካከል እሁድ ህዳር 72007 ዓ.ም አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሜዳ ወይንም ቤልኤር ሜዳ ላይ የሚደረገውን የመጀመሪያውን የአደባባይ ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲያስተባብር ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን የማሳወቂያ ክፍሉ ደብዳቤውን በዛሬው ዕለት ተቀብሏል፡፡
ትብብሩ እሁድ ህዳር 7 የሚያደርገው የአደባባይ ስብሰባ ፍትሃዊ ምርጫ ስለሚደረግበት ሁኔታ አባላቱንና ደጋፊዎቹን የሚያስተምርበት መሆኑን ለአስተዳደሩ ያስገባው ደብዳቤ ላይ ጠቅሷል፡፡ በስብሰባውም ከ3000 በላይ ህዝብ እንደሚገኝ የስብሰባው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡
የአደባባይ ስብሰባው አስተባባሪዎች ከአሁን ቀደም በተደጋጋሚ ወደ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ያቀኑ ቢሆንም የክፍሉ ሰራተኞች በተደጋጋሚ ‹‹የሉም›› እየተባሉ ሳያገኟቸው ይመለሱ እንደነበር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ትብብሩ በአንድ ወር ውስጥ የሚያደርጋቸውን ሌሎች መርሃ ግብሮች ሰማያዊና ሌሎቹም ፓርቲዎች በየተራ እንደሚያስተባብሯቸው ይጠበቃል፡፡

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተላለፈ አገራዊ የጸሎት ጥሪ

በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ትብብር

አገራችን የክርስትናና እስልምና ኃይማኖቶችን በመቀበል ቀደምት በመሆኗ ብቻ ሳይሆን የኃይማኖቶቹ ተቋማት፣አባቶችና ምዕመናን በመከባበርና መቻቻል አብረው በሠላም በመኖር ለዓለም ህዝብ ተምሳሌት መሆናችን የምንኮራበት ነው፡፡ ለዚህም የቤተ እምነቶቹ አባቶች ለምዕመናኑ ያስተማሩት የሞራልና ሥነ-ምግባር እሴቶችና በአብሮነት ላይ የቆመ የአገር ፍቅር ስሜት፣ እነዚህንም እንዲጠብቋቸውና እንዲያከብሯቸው አርዓያ በመሆን ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

አገራችንና ህዝቧ በተፈጥሮ ሚዛን መዛባት በሚከሰትም ሆነ በአገዛዝ ሥርዓቶች ምክንያት በችግር ውስጥ በሚወድቁበት ጊዜ ሁሉ የእነዚህ ኃይማኖቶች ተቋማትና ምዕመናን መዓቱ እንዲርቅና ምህረቱ እንዲወርድ ፈጣሪያቸውን በጾምና በጸሎት በመለመን/ በመማጸን፣ በሃይማኖታዊ የሞራልና ሥነ ምግባር እሴቶቻቸው መሠረት በመተዛዘን ፣ በመረዳዳትና በመተጋገዝ የተገኘውን በመካፈል በአብሮነት ስሜት በርካታ ክፉ ጊዜያትን መሻገራቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡

ዛሬ ላይ እነዚህ የሞራልና ሥነ-ምግባር እሴቶች እየተናዱ በመሄዳቸው ዜጎች ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ተጋልጠዋል፣ የአገር ፍቅር ስሜት በጥያቄ ውስጥ ወድቋል፡፡ በዚህም በመቻቻል ፋንታ ግጭትና መፈናቀል በአራቱም አቅጣጫ ህዝብን ለሥቃይና ሥጋት ዳርጓል፣ የህግ ‹‹አምላክ›› ክብር እያጣ ፍትህ እየተዛባ ነው፣ ወህኒ ቤቶች በታሳሪዎች ተጨናንቀዋል፣ የምግብ ተረጂውና የጎዳና ላይ ተዳዳሪው ዜጋ ቁጥር ተበራክቷል፣… በአጠቃላይ የህዝባችን ኑሮና ህይወት፣ የአገራችን ሠላምና መረጋጋት ፈታኝና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው፤ የዜጎች ተስፋ በመናመኑ የህይወት ዋጋ በሚጠይቅ ሁኔታ ውስጥ እየተሰደዱ በባዕድ አገር ለአደጋ እየተጋለጡ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በአገራችን ያሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች/ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚዎች/ ተጨባጩን ሁኔታ የሚመለከቱበትና የሚረዱበት መንገድ በሁለት ጫፍ ላይ በመወጠሩ የጋራ መፍትሄ ለማምጣት ያለው ዕድል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ ችግሮቹን እያባባሰ ይገኛል፡፡ ስለዚህ፡-
በአገራችን ውስጥ በተለያየ ምክንያት በሁለት ጠርዝ ላይ የቆሙ ኃይሎች ወደ ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ እንዲመጡ፣ በህዝብ ውስጥ የሚታየው የሞራልና ሥነምግባር ጉድለት እንዲቃናና የመቻቻልና መተሳሰብ ስሜት እንዲያንሰራራ፣ የዜጎች ሥቃይና ሥጋት ተወግዶ በተስፋ እንዲሞላ፣….፤

በአገራችን መረጋጋትና ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን፣ ቀጣይና ዘላቂ ልማት እውን እንዲሆን፣ አብሮነታችንና አንድነታችን እንዲጠናከር፣ የአገር ፍቅር ስሜት እንዲለመልምና ለሉዓላዊነታችን ያለን ቀናዒነት እንዲጠናከር፣….፤

በሰንበትና የጁምኣ ቀናት በጋራ እንዲሁም በየግል የዘወትር ጸሎት ፈጣሪ አምላክን በመለመን ለተያያዝነው አገራዊ ዓላማና የጋራ ጥረት ድጋፋችሁን እንድታደርጉ ለየቤተ እምነት ኃላፊዎች /ቤተ ክርስቲያናትና መስጂዶች/ እና ለምዕመናን በሙሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ፈጣሪ አምላክ አገራችንንና ህዝቧን ከጥፋት ይታደግ ዘንድ በጸሎት እንትጋ!!

ኅዳር 01 ቀን በ2007 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን ጎንደር የዞን ሰብሰቢ አቶ አግባው ሰጠኝ በገዢው ፓርቲ ሀይሎች ታፈነ
ትናንትና ምሽት አካባቢ ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍኖ የተወሰደው የዞኑ አስተባባሪ እስከአሁን ሰዓት ድረስ ያለበትን ቦታ ማወቅ አልተቻለም፡፡ ትናንት ማምሻውን በሲቪል እና መሳሪያ በታጠቁ የገዢው ፓርቲ ሀይሎች ቤቱ ተበርብሮ ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍኖ መወሰዱን በዞኑ ያሉ የፓርቲው አካላት አረጋግጠዋል፡፡
ከሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ዞን አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ በተጨማሪም ወደ ስድስት(6) የሚደርሱ የአንድነት እና መኢአድ ፓርቲ አባላትም ወደ አልታወቀ ቦታ ታፍነው መወሰዳቸው ተረጋግጧል፡፡
በሌላ በኩል በጎንደር ባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ከፍተኛ ክትትልና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሆነ የዞኑ ተጠሪዎች አመልክተዋል፡፡

የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ህዝባዊ ትግል ፕሮግራም የመጀመሪያ ዙር እንቅስቃሴ በፓርቲዎች ትብብር በህዳር ወር ይጀመራል!
ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም ትብብር የመሰረትን ዘጠኝ ፓርቲዎች ስለምስረታችን በሰጠነው መግለጫ የስምምነታችን ‹‹ … ዘላቂ ግብ ማንም ተጎጂ የማይሆንበትና ሁላችንም ተጠቃሚ የምንሆንበትን አቅጣጫ የተከተለ እንደመሆኑ ገዢው ፓርቲ/መንግስት እኔ ከሥልጣን ከለቀቅሁ በቀጣይ በሚመጣው ለውጥ አገር ትበታተናለች በማለት ህዝብን ከሚያስፈራራበት፣ ካድሬዎቹን ፣መከላከያ ሠራዊቱንና የፀጥታና ደህንነት ኃይሉን ተቃዋሚዎች ካሸነፉ አንድም ለወህኒ ካነሰም ‹‹ለልመናና የጎዳና ተዳዳሪነት›› ትዳረጋላችሁ… በሚል ሽብር ከሚነዛበት ፕሮፖጋንዳና አካሄድ እንዲመለስና እንዲታረም ዕድል የሚሠጥ›› መሆኑን ፣ ለትብበሩ አባላት ‹‹ ከምንም እና ከማንም በላይ ቀዳሚው አገርና ህዝብ ›› መሆኑንና በህዝባዊ ሠላማዊ ትግል በምትገነባው ሉዓላዊነቷ የተከበረ ዲሞክራሲዊት ኢትዮጵያ ‹‹ በሁለት ጽንፎች የተወጠረው የአገራችን የአሸናፊ-ተሸናፊ የጠቅላይ ሥልጣን ፖለቲካ ልምድ እንደሚቀየርና በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በህዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት ለመበጣጠስ የተዘራውን አጥፊ ዘር ማድረቅ፣ የተሰራጨውን መርዝ ማርከስ ›› መቻሉን መግለጻችን ይታወሳል፡፡

አካሄዳችንን በሚመለከትም ‹‹…ለጋራ ዓላማችን እውን መሆን ያለፈው አካሄዳችን የትም እንዳላደረሰንና እንደማያደርሰን ከውድቀታችን ልምድ ቀስመን በአዲስ አስተሳሰብና የአመራርና አሰራር ሥርዓት ለማይቀረው ሥር ነቀል ሁለንተናዊ ለውጥ በግልጽነት በተጠያቂነት መርህ በጽናት ለመታገልና ለማታገል የደረስንበትን ስምምነት ስናበስር ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን አገራዊና ህዝባዊ ኃላፊነት በመገንዘብ ›› መሆኑን ገልጸን ለዓላማችን ማስፈጸሚያ ተመጋጋቢና ተደጋጋፊ የአጭርና የረጅም ጊዜ የዕቅድ አቅጣጫ ማስቀመጠችንንም ገልጸን ነበር፡፡ የዛሬው መግለጫችን ዓላማም ባስቀመጥነው የአጭር ጊዜ ዕቅድ – ምርጫ 2007 ላይ ትኩረት ያደረገና ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ፕሮግራም በተከታታይ የሚካሄደውን ህዝባዊ ሠላማዊ ትግል የመጀመሪያውን ዙር የአንድ ወር እንቅስቃሴ መርሀ-ግብር ከባለቤቱ ዘንድ ማድረስ ነው፡፡

በዚህ መግለጫ በአገራችን ነባራዊና ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ማኅበራዊ እውነታዎች ዝርዝር ውስጥ ለመግባት አይሞከርም ፣ በየቤታችን የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚታየውን ፣በአራቱም የአገሪቷ አቅጣጫዎች በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ሥቃይና የሰላምና ፀጥታ ፣የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት… ላይ የደረሰውንና የፈጠረውን ሥጋት ማንሳት ‹‹ ቀባሪን የማርዳት›› ሙከራ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ትኩረታችን በምርጫና በመጪው ምርጫ 2007 ላይ ይሆናል፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው በመጪው ግንቦት ወር አምስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ስለሚጠበቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያዘጋጀውን የጊዜ ሰሌዳ እንደተለመደው ለማወያየት በሚል ለማሳወቅ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስብሰባ መጥራቱ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ስብሰባ አስቀድሞ የዚህ ትብብር አባላትን ጨምሮ አስራ ሁለት ፓርቲዎች ለቦርዱ ጥቅምት 5 ቀን 2005

‹‹ 1ኛ/ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ፤

2ኛ/ ገዢውን ፓርቲና አጋሮቹን ጨምሮ ሁሉም ህጋዊ ፓርቲዎች በጋራ ተገናኝተው በምርጫና የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ላይ የሚወያዩበት የጋራ መድረክ እንዲዘጋጅ ››

የሚሉ የጋራ ጥያቄዎችን በማቅረብ ‹‹የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ማለት ለሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር / የነጻ፣ ፍትሃዊና ተኣማኒና አሳታፊ የምርጫ ውድድር ሥርዓት/ ሠላማዊ ትግል/ ዕድል ከመስጠትና የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ከማረጋገጥ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡ ማለትም በሌሎች አምባገነን መንግስታትና ሥርዓቶች በጦር መሣሪያ ኃይልና በደህንነት አቅም በመመካት በሥልጣን ላይ ለመቆየት ያሳዩትን እምቢተኝነትና ማንአለብኝነት ተከትሎ የተከሰቱ ህዝባዊ እምቢተኝነትና በውጤታቸውም የተከተሉ ቀውሶችን በጋራ በመከላከል ከአሸናፊ/ተሸናፊ ጠቅላይ የፖለቲካ ሥልጣን አስተሳሰብ በመውጣት ለዲሞክርሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረት የመጣልና ለዘላቂ ሠላምና ልማት ዋስትና መስጠት ማለት ነው፡፡ በዚህ ማንም ተጎጂ አይሆንም፡፡›› ብለን ሌላው አማራጭ ደግሞ ‹‹በተቃራኒው እነዚህ ጥያቄዎች ባልተመለሱበት የሚደረግ የምርጫ ተሳትፎ ለኢህገመንግስታዊነትና ኢዲሞክራሲያዊነት ዕውቅና በመስጠት አገሪቷንና ህዝብን ወደባሰ አዘቅት መወርወር በመሆኑ በታሪክና ትውልድ ፊት የሚያስጠይቅ ይሆናል፤በዚህ ማንም ተጠቃሚ አይሆንም፣ በዚህ መተባበርም ከተጠያቂነት አያተርፍም፡፡›› ብለን የእኛ ምርጫ የመጀመሪያው በመሆኑ ቦርዱ ‹‹ ከምርጫ የጊዜ ሰሌዳ በፊት ባለበት አገራዊና ህዝባዊ ኃላፊነት መሠረት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠውና ተገቢ ምላሽ በመስጠት ሚዛናዊነቱን. ከወገንተኝነት የጸዳ፣ በምርጫ ህጉ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሰረት የሚሰራ መሆኑን እንዲያረጋግጥ በድጋሚ አበክረን እንጠይቃለን፡፡›› በማለት አሳውቀናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በስብሰባው ወቅት ( እዚህ ላይ ይህ ዓይነቱ ስብሰባ በ2005 አዳማ ላይ ስለምርጫ 2005 የጊዜ ሰሌዳ ፓርቲዎች በአንድ ላይ ተሰብስበን 33ቱ ‹‹ከጊዜ ሠሌዳው በፊት የፖለቲካ ምህዳሩ ይስተካከል›› የሚል ፔቲሽን ከተፈራረሙ በኋላ ባለው ጊዜ ቦርዱ ፓርቲዎችን በሦስት ቦታ በመከፋፈል እንጂ በአንድ ላይ የማይጠራ መሆኑን ያጤኑኣል) በሦስቱም የስብሰባ ቦታዎች የተገኙ ከኢህአዴግና አጋሮቹ እንዲሁም የኢህአዴግ ቀለብ የሚሰፈርላቸው የ‹‹ስለት›› ልጅ የሆኑ ለአጃቢነት የታጩ ፓርቲዎች በቀር ሁሉም የተቃውሞ ጎራ ፓርቲዎች በተመሳሳይና ተደጋጋፊ መንገድ ከላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች የሚያጠናክሩ ተጨባጭ ማሳያዎችን በማቅረብ፣በማብራራትና የጥያቄዎቹን ምክንያታዊነትና ባልተመለሱበት ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ለቦርዱ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ ቦርዱም እነዚህን ጥያቄዎች በዝርዝር እየመዘገበ መሆኑን በኦዲዮ ቪዥዋል መሳሪያዎችም እየተቀረጹ መሆናቸውን በመግለጽ ለቦርዱ ስብሰባ ቀርበው መልስ እንደሚሰጣቸውና መፍትሄ እንደሚበጅላቸው፣ይህንንም ተገናኝተን እንደምንነጋገር ቃል ገብቶ ስብሰባዎቹ ተጠናቀው ነበር፡፡

በተገባው ቃል መሰረት የሚሰጠውን መልስና የሚበጀውን መፍትሄ በመጠባበቅ ላይ እያለን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች በጥያቄኣችን ላይ ያነሳነውን ለገዢው ፓርቲ ያላቸውን ‹‹ ወገናዊነትና የጉዳይ ፈጻሚነት ሚና›› ፍንትው አድርጎ በሚያሳይ መልኩ የጊዜ ሰሌዳውን ማጽደቅ ብቻ ሣይሆን በምርጫ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የተመሰረቱትን ጥያቄዎቻችንን የቢሮ ጥያቄዎችና አስተዳደራዊ ጉዳዮች በማስመሰል አሳንሶ በማቅረብ ፕሮፖጋንዳ በመስራት በለመደው መንገድ ለመቀጠል መወሰኑን አውጀዋል፡፡ በዚህም ሳያበቃ በትብብር በጋራ ለመስራት በምናደርገው ግንኙነትና በተፈራረምነው ስምምነት መሰረት በቀጣይ ለምንቀሳቀሰውም ቦርዱ በህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር (ከዚህ በፊት ተመሳሳይ መግለጫ ይሰጡ የነበሩት የኢህአዴግ አባልና የደብረ ብርሃን ከተማ ዕጩ የምርጫ ተወዳዳሪ የነበሩ መሆኑን እያስታወስን) በኩል ‹‹ በዚህ ትብብር አማካይነት ነገ ወደ ሥራ ሲገቡ ችግር ቢያጋጥማቸው ቦርዱ ሊቆምላቸው የሚችልበት የሥራ አግባብ የለም ››፣ በዚህም ተጠያቂ ‹‹ እንደግለሰብም ሆነ እንደፓርቲ ራሳቸው ነው የሚሆኑት›› የሚፈጠረው ችግርም ‹‹ከህግ ማክበር ጋር ›› የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ (ሪፖርተር ጥቅምት 29 ቀን 2007) ለማን መሆኑን ባናውቅም (ለኢህአዴግ ይህን መምከር ስድብ ይሆናልና) በማስፈራሪያ መልዕክት የታጀበ የወንጀል ክስ ኃሳብና ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ከላይ የገለጽናቸው ሁሉ በጋራ ትግላችን ላይ ለማሳረፍ የተፈለገውን የፖለቲካ ጫናና አንድምታውን የመረመረው የትብብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ‹‹ ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነነኝ ›› እንዲሉ በህገ መንግስቱና በምርጫ አዋጁ የተቀመጠው መብታችን መጣስ/መጨፍለቅ፣ ቦርዱም ሆነ በሥሩ ያሉት መዋቅሮች ነጻና ገለልተኛ ያለመሆን፣ የምርጫ ሜዳው (የተፎካካሪ ፓርቲዎች በእኩል በህዝብ ውስጥ የመንቀሳቀስ መብት፣የአማራጭ ኃሳብ ማራመጃ ሚዲያ ፣ የመራጩ ህዝብ ዲሞክራሲዊ መብትና ሳይሸማቀቅ በነጻ የመምረጥ መብት፣ የምርጫ አስተዳደሩ፣…) በሚመለከት ለምናቀርባቸው ጥያቄዎች መልስ የማይሰጥ፣ቦርድ በህግ ‹‹ጥፋት›› ለሆነ ድርጊት ከለላ ሊሰጠን እና መከታ ሊሆነን መከጀሉ (መቼ፣ለማን፣እንዴት፣ተደርጎ እንደነበር በጥያቄ ታልፎ) ምጸት መሆኑን ተረድቷል፡፡ የቦርዱም አካሄድ ከተለመደውና በድህረ ምርጫ 2002 ግምገማ ከደረስነው ድምዳሜ ‹‹የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል›› ከሚለው አልፎ ‹‹ ተዘግቷል›› ወደሚል ድምዳሜ የሚያሸጋግር ሆኖ መገኘቱን በተጨባጭ አረጋግጠናል፡፡ ዛሬ ላይ የእምነት ነጻነት ጠያቂዎች፣ጋዜጠኞች፣ጦማሪያን፣የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና አባላት፣ አልፎም ከገዢው ፓርቲ የተለየ ኃሳብ ያላቸው ዜጎች በአፋኝ ህጎች በፈጠራ ወንጀል ተከሰው የት እንደሚገኙ ከእኛ አልፎ የዓለም ህዝብ ያውቀዋል፤ አንድም በወህኒ ያሊያም በስደት፡፡

ስለዚህ ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለማስከፈት ትግሉን የ ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል የፕሮግራም መርህ ለመግፋት ወስኖ የመጀመሪያውን ዙር እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ የአንድ ወር ዕቅድ አዘጋጅቶኣል፡፡ በዕቅድ ዝግጅቱ የፕሮግራሙ የአፈጻጸም ስልት ፣የጊዜ ሰሌዳ፣ የቦታ ሽፋን፣የፋይናንስ ምንጭ፣ ዓላማዎች፣ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮችና መንግስታዊና የህዝብ ክፍሎች፣ዋና ዋና ተግባራት ፣በተጨማሪም በታሳቢነት በአፈጻጸም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች/ደንቃራዎችና ሥጋቶች እንዲሁም ለፕሮግራሙን ስኬት አጋዢ ሁኔታዎች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

በዚህ መሠረት ይህ ዙር የሚያተኩርባቸው ዋና ዋና ተግባራትም–
1. በየቤተ እምነቱ ጸሎት ፕሮግራም እንዲደረግ ጥሪ ማድረግና አባላት እንደየእምነታቸው ተሳትፎ ማድረግ፤
2. በምርጫ ዙሪያ የፓናል ውይይቶችን ማድረግ፤
3. የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረግ፤
4. ለመንግሥታዊ ተቋማት ደብዳቤ ማስገባት፤
5. የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት፤
6. የህዝብ ተሳትፎ ማበረታታትና ድጋፍ ማሰባሰብ፤ ናቸው፡፡

እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው አቢይ ጉዳይ ይህን ዕቅድ ስናዘጋጅ ነጻነታችንና መብታችን ከገዢው ፓርቲ ለምነን የምናገኘው ሣይሆን በእያንዳንዳችን እጅ ውስጥ መሆኑንና በማመን እኛ የዕቅዱ አስተባባሪዎች እንጂ የጉዳዩ ዋነኛ ባለቤት፣ የዕቅዱ ፈጻሚና ዋና ተዋናይ እያንዳንዱ/ዷ ኢትዮጵያዊ/ት ዜጋ ነው/ናት በሚል ሙሉ እምነት ላይ ቆመን መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ለዚህ ዕቅድ ተፈጻሚነት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት በጋራ/በትብብር ከጀመርነው ሠላማዊ ትግል ጎን በመቆም ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ አይኖርምና በምርጫ ሥም ሠላማዊ የነጻነት ትግሉን ማዘናጋት ያብቃ// ማለትና ለዕቅዱ ተፈጻሚነት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ራስን ከባርነት ነጻ የማውጣት፣አገርን ከጥፋት የመታደግ የዜግነት ግዴታ መሆኑ ግልጽ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡

በመጨረሻም ከላይ በገለጽናቸው ተጨባጭ ሁኔታዎች ውስጥ የሚደረግ ምርጫ ገዢው ፓርቲ በጉዳይ ፈጻሚው የምርጫ ቦርድ በኩል በተለመደው መንገድ በምርጫ ሥም ለመሥራት የተያያዘውን ቧልት ራቁቱን በማስቀረት ለ ነጻ፣ፍትሃዊ፣ ተኣማኒና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የምርጫ ሜዳውን እንዲያስተካክል በሠላማዊ ትግል አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማሳረፍ በእኛ በኩል አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈልና እስከ መጨረሻው በጽናት ለመቆም የተዘጋጀን መሆኑን እያረጋገጥን ፡-

1ኛ/ የችግሩ ገፈት ቀማሽና የጉዳዩ ቀዳሚና ዋነኛ ባለቤት የሆናችሁ በአገር ቤት ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ አገራችን ከገባችበት ፈተና ህዝባችን ከሚደርስበት ሥቃይ ለማውጣት የራሳችን የዜግነት ክብር ባለቤት ለመሆን ያለን ምርጫ በጽናትና ቆራጥነት የተባበረና የተቀናጀ ሠላማዊ ትግል ስለሆነ ለዚህ ፕሮግራም ስኬት ሁለንተናዊ የፋይናንስ ፣የማቴሪያል፣የጊዜና ጉልበት፣ የዕውቀትና ሙያ፣ የትግል አስተዋጽኦ (በማድረግ የዜግነት ግዴታችሁን እንድትወጡ) እንድታደርጉና እንቅስቃሴኣችንን በመከታተል የአመራርና አፈጻጸም እገዛችሁ እንዳይለየን ፤

2ኛ/ ከአገዛዝ ሥርዓቶች ጋር የተያያዙ የተለያዩ ችግሮችና ፈተናዎች ለስደት የተዳረጋችሁ፣በውጪ ለመኖር የተገደዳችሁ ባላችሁበት ሆናችሁ የአገራችሁ ጉዳይ እንቅልፍ የሚነሳችሁ ኢትዮጵያዊ የዲያስፖራ አባላት በሙሉ ከላይ የእናንተ ተሳትፎ ከትብብርና ድጋፍ ያለፈ አገራዊ ኃላፊነት የመወጣት ነውና በአገር ቤት ላሉት ካቀረብነው በተጨማሪ ድምጹ ለታፈነውና የሰቆቃ ህይወት ለሚገፋው ወገናችሁ ድምጽ ሆናችሁ የዲፕሎማሲውን ትግል በኃላፊነት ስሜት እንድታከናውኑ፤

3ኛ/በትብብሩ ያልታቀፋችሁ በተለይም በሂደቱ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ተሳትፋችሁ በተለያየ ምክንያት የስምምነቱን ሰነድ ያልፈረማችሁም ሆነ የአገርና ህዝብን ጉዳይ ከፓርቲ ጥቅምና ዓላማ በላይ ስለሆነ በጋራ ለመሥራት ዝግጅቱና ቁርጠኝነቱ ያላችሁ ሌሎች ሠላማዊ የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከጋራ ትግሉ እንድትቀላቀሉ እና/ወይም የፕሮግራሙ አካል እንድትሆኑ፤

4ኛ/ የዓለም አቀፉና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት መንግስታት ተለዋዋጭና ኃላፊ፣ ህዝብ ግን ቋሚ ነውና በግንኙነታችሁ የህዝብ ለህዝብ ዘላቂ ጥቅምንና ታሪካዊና ፖለቲካ አንድምታን ከግምት እንድታስገቡ፤ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በተቀናጀ የጋራ አመራር የተባበረ ህዝባዊ ሠላማዊ ትግል በእኩልነት ላይ የተመሠረተች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንገነባለን//

ጥቅምት 25/2007፣ አዲስ አበባ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን!

ላለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ ስራዬ ብሎ ካዳከማቸውና ጉዳዬ ከማይላቸው ዘርፎች ውስጥ የሚመደበው የትምህርት ስርዓቱ ሲሆን ይህም ከኢህአዴግ ስህተቶች ሁሉ ዋነኛው እና አሳፋሪ ተግባሩ ነው፡፡ ለሁለት አስርት አመታት ትውልዱን በማምከን በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ከገፉት ጉዳዮችም ግንባር ቀደሙ የህወሓት/ኢህአዴግ የተምታታበት የትምህርት ፖሊሲ መሆኑም ይታወቃል፡፡ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑ እየታመነ የትምህርት ስርዓቱ ሆን ተብሎ በንቀት እና በዝርክር አሰራር እንዳያድግና ጥራት እንዳይኖረው ኢህአዴግ እየተጋ አሁን ድረስ ዘልቋል፡፡ በዚህ አይነቱ አጥፊ አካሄድ ምክንያትም ሀገራችን በዓለም ደሃ ሀገራት ተርታ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡

የተማረ እየተገፋ በስራ አጥነት ሲንከራተት እና ለስደት ሲዳረግ በካድሬነት የስርዓቱ አገልጋይ መሆን ደግሞ በተቃራኒው ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግ አባል ካልሆኑም ስራ ሊያገኙ እንደማይችሉ እየተነገራቸው በፍራቻ ለአባልነት የተመዘገቡ ብዙዎች እንደሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በዚህ ሳያበቃ አሁን አሁን ደግሞ የገዢውን ፓርቲ ያረጀና ያፈጀ ኋላቀር አስተሳሰብና ርዕዮተ-ዓለም በተማሪዎች ላይ ለመጫን በየዓመቱ መጀመሪያ ‹ስልጠና› በሚል ፈሊጥ በጀት በጅቶ በግድ ሊግታቸው እየሞከረ ይገኛል፡፡

በዚሁ በያዝነው ወርም በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች እንዲሰበሰቡና ስልጠና እንዲወስዱ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያ አይሉት ማሳሰቢያ በገዢው ፓርቲ በኩል ተላልፏል፡፡ ሌላው አስገራሚ ዜና ደግሞ ተማሪዎቹ በግድ ስልጠናውን እንዲወስዱ መገደዳቸው ሳያንስ ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ተመልሰው መውጣት እንደማይችሉ መሰማቱ ነው፡፡

ይህም ኢህአዴግ ካድሬዎቹን የሚያሰለጥንበት ዝግ የስብሰባ ስልት መሆኑ ጉዳዩን የበለጠ አስገራሚ ያደርገዋል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ይህንን ስልጠና ሲያካሂድም፡-
1. ህግን በጣሰ መልኩ የትምህርት ማዕከላትን የፖለቲካ ማራመጃ እና የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያ አድርጓል፡፡

2. ይህን ፋይዳ ቢስ ስልጠና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎችና ከ800.000 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በሚሰጥበት ወቅት ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እያባከነ ይገኛል፡፡

3. ተማሪዎች የእረፍት ጊዜያቸውን በነፃነት ማሳለፍ ሳይችሉ በአስቸኳይ ወደ ዩኒቨርስቲዎች እንዲመለሱ ተገድደዋል፡፡

4. በሚሰጠው ስልጠናም ላይ በአክራሪነት በብሔርተኝነትና በመሳሰሉት ጉዳዩች ሽፋን በተማሪዎች ዘንድ መርዛማ ጥላቻን እየረጨ ይገኛል፡፡

5. በአጠቃላይ በስልጠናው ወቅት ርካሽ የፕሮፖጋንዳ ስልትን በመጠቀም መጪውን ምርጫ በማምታታት ለማለፍ እየሞከረ ሲሆን ይህም በአምባገነንነቱ ቀጥሎ ህብረተሰቡን አማራጭ ለማሳጣትና ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ አለመረጋጋት ሊወስድ እየሞከረ መሆኑን ያሳያል፡፡ በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዢው ፓርቲ ህገ ወጥ አድራጎት አጥብቆ እያወገዘ ጉዳዩን እየተከታተለም አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑንን ይገልፃል፡፡ ተማሪዎችም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ሳይደናገጡ ያለምንም ፍርሃት ህጋዊ በሆነ መንገድ ይህን ካድሬያዊ ስልጠና በማውገዝ፣ የገዢውን ፓርቲ ድብቅ ሴራ በማጋለጥ እና ለህወሓት/ኢህአዴግ የተለመደ አጥፊ ፕሮፖጋንዳ ባለመታለል ተማሪዎች በአንድነት እንዲቆሙ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ነሀሴ 15/2006 ዓ.ም
ሰማያዊ ፓርቲ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

በአሸባሪነት ተከሰው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተባባሪዎች ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ መከልከላቸውን የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አቶ ሉሉ መሰለ የፓርቲው የዞኑ ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ በፍቃዱ አበበ የዞኑ ምክትል ሰብሳቢ ለዛሬ ነሃሴ 10 ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ተቀጥረው የነበሩ ቢሆንም ፖሊስ ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ ተደርገዋል ሲሉ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ፍርድ ቤት አመራሮችን ለቅዳሜ ነሃሴ በቀጠረበት ወቅት ቅዳሜ ቀን መሆኑን አረጋግጦ እንደቀጠራቸው ቢገለጽም ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታየ ጨረጋ በአካል በሞባይላቸው ላይ በደወልንበት ወቅት ‹‹በአካል ካልተገናኘን መረጃ አልሰጥም፣ ጋዜጠኛ መሆናችሁን በምን ማረጋገጥ እችላለሁ በምርመራ ላይ ያለ ጉዳይ ምን ያደርግላችኋል›› በሚል መረጃ ላለመስጠት ያንገራገሩ ሲሆን በስተመጨረሻ ‹‹ቅዳሜ የስራ ሰዓት ባለመሆኑ ነው ያልቀረቡት ሰኞ ይቀርባሉ፡፡› እንዳልቀረቡ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የታሰሩትን አስተባባሪዎች ለመጎብኘተ ወደ አካባቢው አቅንተው የነበሩት የፓርቲው የአደረጃጀት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ፖሊስ ታሳሪዎቹን እሁድ ቀን ከአስር ሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት እንዳቀረባቸው፣ የአሁኑ ቀጠሮም ቅዳሜ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ያውቅ እንደነበርና በወቅቱ የነበረው ዳኛ አጀንዳ ተመልክተው እንደቀጠሩ እንዳረጋገጡ ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው ጨምረውም ፖሊስ ቅዳሜ የስራ ቀን አይደለም በሚል የሰጠው ምክንያት ታሳሪዎቹን ለማሰቃየት የተደረገ ኢፍትሃዊ ድርጊትና ፖሊስ ከህግ በላይ መሆኑን የሚያሳይ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

ከአሁን ቀደም አራት የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች በሽብርተኝነት ስም መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን እስረኞች ያሉበትን ሁኔታና የዞኑን አደረጃጀት ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ (ከማዕከል) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድና የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ዮናስ ከድር ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት ሲያስተባብሩ የነበሩት አባላት ከማዕከል የሄዱት የፓርቲው አመራሮች ሲመለሱ ለእስር መዳረጋቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡

በመሆኑም አቶ ከሳሁን አየለ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አርባምንጭ አስተባባሪ ከአዲስ አበባ የመጡትን የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የዞኑን አደረጃጀትና በእስር ላይ ያሉትን የፓርቲው አስተባባሪዎች አስጎብኝቷል በሚል መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ሻምበል ካሳ የታሰሩትን ጠይቀሃል በሚል ለእስር መዳረጋቸውንና ነፃነት የተባለው የፓርቲው አስተባባሪ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር እንዳይሰራና በታሰሩት ላይ እንዲመሰክር በማስፈራሪያ መለቀቁ ታውቋል፡፡

በዞኑ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እስራትና መከባ እየደረሰባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ሉሉ መሰለ፣ በፈቃዱ አበበ፣ ካሳሁን አየለ፣ ሻምበል ካሰና ኢ/ር ጌታሁን የተባሉት የፓርቲው አስተባባሪዎችና አባላት በእስር ላይ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል::

ሐምሌ 29 ጠዋት ሜክሲኮ ልደታ ፍርድ ቤት ቀርበው በ5000 ብር ዋስ እንዲወጡ የታዘዘላቸው ወይንሸት፣ አዚዛ እና ኡስታዝ በድብቅ በተካሄደ ይግባኝ ዋሱ ተነስቶ የ7 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ ተፈቅዶለታል፡፡ በእለቱም ከሰዓት በኋላ በድብቅ ፍርድ ቤት ተወስደው የዋስ መብታቸው በይግባኝ ተገፏል፡፡ አሁን በእስር ቤት ይገኛሉ፡፡
እንዲሁም በተያያዘ ዜና ሐምሌ 30 ቀን ኢብራሂም አብዱልሰላም 5000 ብር ደመወዝተኛ ዋስ እንዲለቀቅ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ከ3 ሰዓታት በኋላ ፖሊስ ለይግባኝ ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ አድርጎ ዋስትናው እንዲታገድ በማድረግ በእስር ቤት እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

አርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባሪዎች በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ትናንት ሐምሌ 29 ሌሊት የዞኑ ሊቀመንበር አቶ ሉሉ፣ አቶ ፈቃዱ አበበና አቶ ጌታሁን በየነ ከየ ቤታቸው በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ የተወሰዱ ሲሆን አሁን ያሉበት ቦታ እንደማይታወቅ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
አመራሮቹ በፖሊስ በተያዙበት ወቅት ቤታቸው እንደተበረበረና የፓርቲው አባላት አርባ ምንጭ በሚገኘው የፓርቲው ቢሮ እንዳይገቡ ቢሮውን ከበው የሚገኙ ፖሊሶች እየከለከሉ መሆኑም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል በዞኑ በየ ወረዳው የሚገኙትን የፓርቲው አባላት ከሰማያዊ ፓርቲ እንዲወጡ ጫና እየጠደረገባቸው እንደሚገኝ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ገልጸዋል፡፡

Press Release by Blue Party Ethiopia / Semayawi Party- Ethiopia/
It is a well known fact that TPLF/EPRDF has slaughtered and oppressed Ethiopian citizens since it came to power. In order to oppress the peaceful struggle, especially within the last 10 years, the regime acclaimed several repressive proclamations and laws to legalize its butchery and tyranny. Many politicians, journalists, bloggers, religious leaders and people who raised question against the regime are victims of these proclamations. Since these controversial laws have been applauded by TPLF/EPRDF, the security institutions that serve the regime have put a lot of politicians, journalists, activists and many who issue its power to jails. The regime also tries to label Medias such as ESAT as terrorists’ medium to threaten politicians in relation to terror act which is ridiculous. Blue likes to stress out that no one should not and cannot choose Medias for anyone in regards to freedom of speech and press.

Accordingly, TPLF/EPRDF’s obsession of power and its negligence to accountability is leading the country in a wrong and chaotic situation. Particularly the last four years have been difficult and the arrest of many peaceful citizens made the political atmosphere very constricted. Nevertheless, countless people are struggling peacefully within the rule of law; many flee abroad to over throw the dictatorial government with whatever way they thought is possible. Thus, Blue Party /Semayawi/ finds it very significant to take this firm position due to the above reasons and more that hasn’t been mentioned here:

1- On June 24 2014, the rebel group Ginbot 7’s General Secretary, Andargachew Tsege was detained by the Yemeni intelligence officers in collaboration with Ethiopian intelligence officers. The officials of both countries knowingly violated international conventions. It is not legal or convenient to intervene in eternal matters of a sovereign country whatsoever. Consequently, the act of Yemeni officials will sure distress the upcoming relationships of the countries. Nonetheless, as the regime didn’t let the public and his family know his whereabouts for 16 days, the matter has been viewed suspiciously in our party, in the public at large and in the international community. It is our concern that he could be ill treated and more. Therefore, Blue Party strongly demands that Andargachew Tsege must be treated moderately and that all his rights under custody are respected.

2- The regime also illegally arrested prominent figures of Ethiopian politicians on July 8. The detainees are members and leaders of parties who are engaged in peaceful struggle. In fact it is not surprising to hear such news; however, we have learned that the regime is anxious and is trying to connect the detainees with rebel forces so that it hopes it can crack down the peaceful struggle before the 2015 election for they could be a threat to its power. It is clear that the dictatorial rule wants to stay in power more through spreading fear among the society. Thus its desperation is leading its ego to arrest one of our members and three other party leaders. Blue Party’s National Council Vice Chairperson Mr. Yeshiwas Assefa, Mr Habtamu Ayalew(Head of Public Relations Affairs of UDJ), Mr. Daniel Shibeshi(Vice Chairman of Organizational Affairs of UDJ) and Arana Tigray’s executive committee member and activist Mr. Abraha Desta are detained for activism and peaceful struggle. All these figures have been engaged in promoting peaceful struggle within the rule of law. Their arrest boldly hints that the regime’s final days in power are counted and change is inevitable in the near future. Hence, Blue Party demands an immediate release of the detainees and as well advocate the regime to stop the state terror. We condemn that TPLF/EPRDF comes to its sense and do what’s right for themselves and the country before it’s too late.
Finally we make sure that the act of state terror by TPLF/EPRDF will not hinder us for an inch from the none-violent struggle we are committed to. We have come into the decision that the offensive and atrocious act of TPLF/EPRDF required us to bring the struggle to the next level. Hence, we call upon the Ethiopian people to be ready to a nationwide movement and make sure that Blue Party is fully committed to provide the leadership needed at its unsurpassed. The Party also calls the peaceful parties, international institutes, human right activists, civic societies for all Ethiopian born and Ethiopians to stand together.

Long live Ethiopia
Blue/Semayawi Party Ethiopia
July 10, 2014

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም
የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ፍፁም ሰላማዊ ታጋዮችንና ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው በድፍረት የፃፉ ጋዜጠኞችን ብሎም የእምነት ነፃነታችን ይከበር ብለው የጠየቁ የሀይማኖት መሪዎችን በጠራራ ፀሃይ ያለምንም ወንጀል በዚሁ ህገ ወጥ አዋጅ ‹‹የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል›› በሚባል ማንነቱ በማይታወቅ የጨለማ ቡድን ወደ እስር ቤት እያጋዘ ይገኛል፡፡

ይህን የሚያጋልጡ ሚዲያዎችንም ለማፈን እስር ቤቶችን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እያፈሰሰ የአየር ሞገድ ያውካል፤ በዚህ ሳያበቃ በሀገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ፖለቲከኞችን ለማሸማቀቅ እንደ ኢሳት ያሉ ሚዲያዎችን የአሸባሪ ልሳን ብሎ በመፈረጅ ሚዲያውን የሚጠቀሙትን ደግሞ ከአሸባሪዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አድርጎ መወንጀሉን ቀጥሎበታል፡፡ እንደሰማያዊ እምነት ማንም አካል መልእክት የሚያስተላለፍበትን የሚዲያ ተቋም ሊመርጥለት እንደማይችል መንግስት እንዲገነዘበው ከዚህ በፊት በግልፅ ያሳወቀ ሲሆን አሁንም ፓርቲው በዚሁ የፀና አቋሙ እንደሚቀጥል በድጋሚ ይገልፃል፡፡

ባጠቃለይ የዚህን ገዢ አካል የእውር ድንብር ሀገር የማስተዳደር ጉዞ ለመታገል በርካቶች በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም በህወሓት/ኢህአዲግ ግፍና መከራ ተገፍተው ስርዓቱን በሃይል እናስወግዳለን ብለው ሀገር ጥለው የተሰደዱ ዜጎችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ ማናለብኝነትና የስልጣን ጥመኝነትም በግለሰቦች ላይ ከሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ በላይ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትን አስከትሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ይህ ገዢ ፓርቲ የፈጠረው ስርዓት የሀገሪቷን ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳር በማጥበብ ሀገራችንን ወደ አልተፈለገ አለመረጋጋትና ቀውስ እየመራት ይገኛል፡፡ፓርቲያችንም እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም በቅርቡ እየተፈፀሙ የሚገኙ ህገ ወጥ ድርጊቶች ስላሳሰበው ይህን መግለጫ ለማውጣት ተገዷል:-

1. ሰኔ 16 2006 ዓ.ም የየመን መንግስት የዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎችን በመጣስና በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአማፂ ቡድን ግንቦት ሰባት ዋና ፀሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዟ ይታወሳል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለህወሓት/ ኢህአዴግ ተላልፈው መሰጠታቸውን ከ16 ቀናት በኋላ መታወቁና ይህንንም ሁለቱ ሀይሎች ማመናቸው ተሰምቷል፡፡ ነፃነት በሌለበት ሀገር ዜጎች ሰብዓዊ ክብራቸውን ለማስጠበቅ የሚያደርጉት ጥረት የሌሎች ሀገር መንግስታት የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በዓለም አቀፍ ስምምነቶችም ሆነ በተለይ በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጥላ የሚያጠላ መሆኑን ግንዛቤ አለመወሰዱ እጅግ የሚያሳዝን ድርጊት ነው፡፡ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከተያዙ በኋላ ላለፉት 16 ቀናት በምን አይነት ሁናቴ እንደቆዩ ህዝብና ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁት አለመደረጉ፤ ስለ አያያዛቸው ሁኔታም በማህበረሰቡና በፓርቲያችን ውስጥ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲኖር አድርጓል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሰብዓዊ አያያዝ እያሳሰበው ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ አገዛዝ አያያዛቸውን ግልፅ እንዲያደርግ ሰብዓዊ ክብራቸውም እንዲጠበቅ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
2. በዚሁ ሳምንት ገዢው ፓርቲ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የአምባገነኑን መንግስት ህወሓት/ኢህአዲግን ሲታገሉ የነበሩ ፖለቲከኞችን በስመ አሸባሪ ከያሉበት እየለቀመ ህገ-ወጥ እስራት መፈፀሙ ይታወቃል፡፡ ህወሓት/ኢህአዲግ ይህ ግብታዊ ተግባሩ ምንም እንኳን አዲስ ባይሆንም በአሁኑ ወቅት ለውጥን ለማምጣት በቆራጥነት እየታገሉ ያሉ ሰላማዊ ታጋዮችን ማሰሩ በሀገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ፓርቲዎችን ከአማፂ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው በማስመሰል ሰላማዊ ትግሉን ለማዳከምና መጪውን 2007 ዓ/ም ምርጫ ያለ ተቀናቃኝ ለማለፍ የሚደረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ የፓርቲያችን ብ/ም/ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ በሰላማዊ ትግሉ በቁርጠኝነት እየተሳተፈ ባለበት ሁኔታ ለእስር መዳረጉ፤ የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄን በመፍጠር ላይ ያለው የአረና /ትግራይ/ ፓርቲ አመራር አባል የሆኑትን አቶ አብረሃ ደስታ ለእስር መዳረጋቸው ህወኃት/ኢህአዴግ የመጨረሻው መጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ያረጋግጣል፡፡ በመሆኑም አገዛዙ እያካሄደ ያለውን መንግስታዊ ሽብር አቁሞ ለሀገርም ሆነ ለራሱ የሚበጀውን መንገድ እንዲከተል እያሳሰብን የታሰሩት የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም ፓርቲያችንን መንግስት እያደረገ ያለው ሽብርን የመንዛትና ህግን የመጣስ ተግባሩ መቼም ቢሆን ከሰላማዊ ትግሉ እንደማያቆመውና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በአፅንኦት እየገለፀ እነዚህንና ከላይ የተጠቀሱትን የገዢውን ፓርቲ መርህ አልባነት፣ ህገ-ወጥነት እና የለየለት አምባገነንነትን አሁን ካለው ነባራዊ እውነታ ጋር አጣምሮ የትግል ስልቱን ደረጃ ከፍ ወዳለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንዳለበት አምኗል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ለምናደርጋቸው ሀገር አቀፍ ንቅናቄዎች መላው የሀገሪቱ ህብረተሰብ በንቃት ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ ጥሪውን እያስተላለፈ ለዚህም ቁርጠኛ አመራር ለመስጠት ዝግጁነቱን ለመግለፅ ይወዳል፡፡በዚህ አምባገነንነትን ለመታገል በሚደረገው ንቅናቄም በሀገር ውስጥ የሚገኙ ህጋዊና ሰላማዊ ፓርቲዎች፤አለም አቀፍ ተቋማት፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤ሲቪክ ማህበራት፤መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሰላማዊ ትግሉ ጎን በጋራ እንድንቆም እንጠይቃለን፡፡

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ሰማያዊ ፓርቲ
ሀምሌ 3/2006ዓ/ም

የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 20/2006 ዓ.ም ባደረገው የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በሊቀመንበሩ የቀረበውን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸደቀ ሲሆን ብሄራዊ ምክር ቤቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ውሳኔዎችም ተላልፈዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሊቀመንበሩ የቀረበለትን የስራ አስፈጻሚዎች የቦታ ሽግሽግም ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን በሽግሽጉ መሰረትም አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ጌታነህ ባልቻ የጥናትና ስትራቴጅ ኃላፊ እንዲሁም አቶ እያስፔድ ተስፋዬ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ አጽድቋል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ የግንቦት 20 ልዩ እትም ጋዜጣዋ የግንቦት 20 ‹‹ፍሬዎች›› ተዳሰውባታል፡፡

በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲ ኤፍ ለቀናታል
PDF ያንብቧት!

ታምራት ታረቀኝ የግንቦት 20 ሰለባ የሆኑትንና ሐኪም አጥተው የሞቱትን እውቁን ሐኪም ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያስታውሰናል፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ስለ ግንቦት 20 ፍሬዎች የራሳቸውን እይታ ገልተውባታል፡፡
የመኢአድ ፕሬዝደንት አቶ አበባው መሃሪ፣
የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ስለሽ ፈይሳ፣
የአረና የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ
እንዲሁም የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ሰሎሞን ስዩም ስለ ግንቦት 20 ይናገሩባታል፡፡
አቶ ታዴዎስ ታንቱ የግንቦት 20ን እንክርዳድ ለመመንገል ስለሚያስችለው ስልት ጽፈውባታል፡፡
ሰንደቅ አላማውና ግንቦት 20፣ ግንቦትና ግንቦታውያን፣ ግንቦት 20 የበላቸው ቀሽ ገብሩዎች፣ ግንቦት 20 እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነት….እና በርካታ ጉዳዮች ተዳስሰውበታል፡፡
መልካም ንባብ!

ሰማያዊ ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደረገ ባለው ፖለቲካዊ ትግል በፍርሀት ድባብ ውስጥ ተውጦ የነበረውን ህዝብ የጨለማ ድባብ እየገፈፈው ይገኛል፡፡ በዚህ ስራውም የብዙ ታላላቅ ምሁራንን እና ወጣቶችን ቀልብ መሳብ ችሏል፡፡ በመሆኑም ፓርቲው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ያሳካ ዘንድ ብሎም አሁን ካለበት የተሻለ ተንቀሳቅሶ ተፎካካሪና ተወዳዳሪ ፓርቲ ይሆን ዘንድ ገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡ ገንዘቡን ሊያገኝ የሚችለው ደግሞ ከአበላትና ደጋፊዎች መሆኑ ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም ግንቦት 23 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ ቪው ሆቴል ታላቅ የእራት ግብዣ ፕሮግራም ደግሶ ይጠብቅዎታል፡፡የእራት ግብዣው መግቢያ ካርዶችም የተዘጋጁ ሲሆን እነዚህም ባለ አምስት መቶ ባለ አንድ ሺህ፤ባለ ሶስት ሺህ፤ባለ አምስት ሺኅ እና ባለ አስር ሺህ ብር ናቸው፡፡እርስዎም የእራት ግብዣውን ካርድ በመግዛት ሰማያዊ ፓርቲን እያገዙ ወደ ነጻነት ይጓዙ፡፡ ባለ አስር ሺህ ብር ካርድ በቁጥር ጥቂት ስለሆነ ባለ አምስት ሺህና ሶስት ሺህ አማራጭ መኖሩን እንዳይዘነጉ፡፡ በእራት ግብዣው ላይ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች፤ተጋባዥ እንግዶች፤ታላላቅ ፖለቲከኞች፤ገጣሚያንና ጋዜጠኞች ይገኛሉ፡፡እንዲሁም የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞች፤ጨረታዎችና ታዳሚን ሊያዝናኑ የሚችሉ ለየት ያሉ ጨዎታዎች ይቀርቡበታል፡፡ በዚህ የእራት ግብዣ ላይ በመገኘት እየተዝናኑ፤በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እየተጎራረሱ ስለ ሀገርዎ እጣ ፈንታ በመሶብ ዙሪያ ይነጋገሩ፡፡ የመግቢያ ካርዶችን ከአስተባባሪዎች፤ከአባላትና ከአመራሮች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ወገኖቻችን የመግቢያ ካርዱን ለወዳጅ ዘመድ መግዛት የሚቻል በመሆኑ ይህን በአይነቱ ለየት ያለና ለነጻነት የሚከፈል ውድ ስጦታ ወዳጅ ዘመድዎን እንዲጋብዙ ስንል ጥሪ እናቀርባለን፡፡ አያይዘንም የእራት ግብዣው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ክፍት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-ሰማያዊ ፓርቲ
ስልክ ቁጥር-+251 911 679223
+251 931 153809
+251 11 8 592950
አቢሲኒያ ባንክ አራዳ ቅርንጫፍ የባንክ ሂሳብ ቁጥርC/619
E-mail [email protected]
www.semayawiparty.org

‘መድረክ’ እናመሰግናለን

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በመድረክ ሰልፍ ላይ የመድረክን ጥሪ አክብሮ የተገኘ ሲሆን በሰልፉም ላይ የህዝብን ጥያቄ በማስተጋባት አጋርነቱን አሳይቷል፡፡ ይህን ሰልፍ ላዘጋጀው እና የተቃውሞ ድምፃችንን እንድናሰማ ሁኔታዎችን ላመቻቸው የፓርቲዎች ስብስብ ‘መድረክ’ ምስጋና ልናቀርብ እንወዳለን፡፡

የዜጎችን ጥያቄ በጥይት ማስቆም አይቻልም

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ሰማያዊ ፓርቲ!

May 24, 2014 MEDREK’s demonstration; Blue Party(semayawi) taking part!
Killing citizens in anyway can never be justifiable!

ሰማያዊ ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደረገ ባለው ፖለቲካዊ ትግል በፍርሀት ድባብ ውስጥ ተውጦ የነበረውን ህዝብ የጨለማ ድባብ እየገፈፈው ይገኛል፡፡ በዚህ ስራውም የብዙ ታላላቅ ምሁራንን እና ወጣቶችን ቀልብ መሳብ ችሏል፡፡ በመሆኑም ፓርቲው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ያሳካ ዘንድ ብሎም አሁን ካለበት የተሻለ ተንቀሳቅሶ ተፎካካሪና ተወዳዳሪ ፓርቲ ይሆን ዘንድ ገንዘብ ያስፈልገዋል፡፡ ገንዘቡን ሊያገኝ የሚችለው ደግሞ ከአበላትና ደጋፊዎች መሆኑ ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም ግንቦት 23 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ ቪው ሆቴል ታላቅ የእራት ግብዣ ፕሮግራም ደግሶ ይጠብቅዎታል፡፡የእራት ግብዣው መግቢያ ካርዶችም የተዘጋጁ ሲሆን እነዚህም ባለ አምስት መቶ ባለ አንድ ሺህ፤ባለ ሶስት ሺህ፤ባለ አምስት ሺኅ እና ባለ አስር ሺህ ብር ናቸው፡፡እርስዎም የእራት ግብዣውን ካርድ በመግዛት ሰማያዊ ፓርቲን እያገዙ ወደ ነጻነት ይጓዙ፡፡ ባለ አስር ሺህ ብር ካርድ በቁጥር ጥቂት ስለሆነ ባለ አምስት ሺህና ሶስት ሺህ አማራጭ መኖሩን እንዳይዘነጉ፡፡ በእራት ግብዣው ላይ የተከበሩና ታላላቅ ሰዎች፤ተጋባዥ እንግዶች፤ታላላቅ ፖለቲከኞች፤ገጣሚያንና ጋዜጠኞች ይገኛሉ፡፡እንዲሁም የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞች፤ጨረታዎችና ታዳሚን ሊያዝናኑ የሚችሉ ለየት ያሉ ጨዎታዎች ይቀርቡበታል፡፡ በዚህ የእራት ግብዣ ላይ በመገኘት እየተዝናኑ፤በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እየተጎራረሱ ስለ ሀገርዎ እጣ ፈንታ በመሶብ ዙሪያ ይነጋገሩ፡፡ የመግቢያ ካርዶችን ከአስተባባሪዎች፤ከአባላትና ከአመራሮች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ወገኖቻችን የመግቢያ ካርዱን ለወዳጅ ዘመድ መግዛት የሚቻል በመሆኑ ይህን በአይነቱ ለየት ያለና ለነጻነት የሚከፈል ውድ ስጦታ ወዳጅ ዘመድዎን እንዲጋብዙ ስንል ጥሪ እናቀርባለን፡፡ አያይዘንም የእራት ግብዣው ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ክፍት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-ሰማያዊ ፓርቲ
ስልክ ቁጥር-+251 911 679223
+251 931 153809
+251 11 8 592950
አቢሲኒያ ባንክ አራዳ ቅርንጫፍ የባንክ ሂሳብ ቁጥርC/619
E-mail [email protected]
www.semayawiparty.org

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ ፖሊስ ይዟቸው ላዛሪስ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ድብደባ ደረሰባቸው፡፡
በተለይ ‹‹አንተን የሚጠብቅ ፖሊስ የለንም ተብሎ›› ፈተና እንዳይፈተን የተደረገው ዮናስ ከድር ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ዮናስ ከድር መንቀሳቀስ እንደማይችል አብረውት ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ገልጸውልናል፡፡ ሳምሶን የተባለና ኮድ ሁለት 16321 መኪና የሚይዝ ደህንነት ለምን አትፈታም እንዳለውና ዮናስም ‹‹የታሰርኩበት ምክንያት ህጋዊ ስላልሆነ ህጉ እስክልተከበረ ድረስ አልፈታም›› የሚል መልስ እንደሰጠው ታውቋል፡፡ ደህንነቱም ‹‹እኔ ነኝ እንዳትፈተን ያደረኩህ፡፡ ለእናትህም ደውዬ የነገርኳት እኔ ነኝ፡፡ ስትፈታም ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰህ አትገባም፡፡ ወደ ቤትህ ነው የምትመለሰው›› እንዳለው ታውቋል፡፡
በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላትም ድብደባ እንደረሰባቸው የታወቀ ሲሆን ደህንነቶችና የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ተጨማሪ ድብደባ እንደሚደርስባቸው እያስፈራሩዋቸው መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ለአብነት ያህል በእስር ላይ የምትገኘው እየሩስ ተስፋው እዮኤል የተባለውን የእስር ቤቱ ኃላፊ ‹‹አንተ ነህ የምታስደበድበን›› ባለችው ወቅት ‹‹አሁንም ትደበደባላችሁ፡፡ ወጥታችሁ ተደብድባችሁ መመለስ ብቻ ነው ምንም አታመጡም›› እንዳላት ገልጻለች፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ታሳሪዎቹን ለመጠየቅና ሁኔታውን ለማጣራት ወደ እስር ቤት በሄደበት ወቅትም እስር ቤቱ ውስጥ የሚሰራ አንድ ፖሊስ ‹‹እኔ ነኝ ያስደበደብኩት፡፡ ምንም አታመጡም፡፡ ከፈለጋችሁ በደንብ እዩኝና ክሰሱኝ፡፡ አሁን ከእኔ ጋር መነጋገር አትችሉም ከግቢ ውጡ›› ብሎ እየገፈተረ እንዳስወጣቸው ገልጾአል፡፡ በላዛሪስት ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላለፉት ሁለት ቀናት በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውና በዚህም ምክንያት መዳከማቸው የታወቀ ሲሆን ፖሊስና ደህንነት በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነው እንኳ ከፍተኛ ድብደባ እያደረሱባቸው መሆኑ እንዳሳዘነው አቶ ብርሃኑ ጨምሮ ገልጸአል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የርሃብ አድማ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ 32 የሶማሊያ ስደተኞች ያለ ምንም ምግብ፣ ልብስና ውሃ መታሰራቸውን ገልጸው ችግራቸው እልባት እንዲያገኝ መግለጻቸው ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ መታሰራቸው ህገ ወጥ ሆኖ እያለ 5500 ብር ከፍላቭሁ ውጡ መባላቸውን በመቃወም ‹‹አንፈታም!›› ማለታቸው ይታወሳል፡፡ አቶ ብርሃኑ ‹‹ደህንነትና ፖሊስ ታሳሪዎቹ ላይ ከፍተኛ ድብደባ የሚያደርሱበት ምክንያትም ታሳሪዎቹ ህግን ለማስከበር በሚያደርጉት ጥረት ነው›› ብለዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አንድነት የጠራውን የሰላማዊ ሰልፍ እንደሚቀላቀሉ አስታወቁ
በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው የሰነበቱትና ቀሪዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ዛሬ ባደረጉት ሳምንታዊ የወጣቶች የውይይት ፕሮግራም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) የ‹‹እሪታ ቀን›› በሚል የጠራውን ሰልፍ በግንባር ቀደምነት በመቀላቀል ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ አስታውቀዋል፡፡
ወጣቶቹ ሰልፉን እንደሚቀላቀሉ ያስታወቁት ‹‹ሰላማዊ ሰልፉ ውጤታማ እንዲሆን በምን መልኩ ልናግዝ እንችላለን?›› በሚል አጀንዳ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከውህደት በዘለለ በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በሌሎች የትግል ስልቶች መተባበርና አብሮ መስራት እደግፋለሁ የሚል አቋም እንደሚያራምድ በተለያዩ ሚዲያዎች መግለጹ የሚታወቅ ሲሆን ወጣቶቹ በሰላማዊ ሰልፉ የሚያደርጉት ተሳትፎ ፓርቲው ለትብብር ያለውን አቋም ያሳያል ብለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ለሰላማዊ ሰልፉ ድምቀት የሚያገለግሉ ሜጋ ፎኖች፣ ጥሩምባዎችና ሌሎችም ሰልፉን ለማድመቅ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን ይዘው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

One of this year plans was to awake the public at large into participating in politics without a fear. Of all the methods we engaged in demonstration was one of it. On April 27, 2014, we decided to have the protest. Our enquiries are very clear: TPLF/EPRDF is incapable of ruling so it has to leave power and religious interference by the ruling party has to stop, forcing citizens to leave their neighborhood because of their ethnic group is a crime and that has to stop and forcing citizen to leave and demolishing their houses without any compensation because of ‘development’ is unlawful and negligent. Those are the issues we mainly raised in the protest.
When the day and place first decided, we wrote a letter for Addis Ababa City administration office to let them know about it. Within few hours they sent us a letter that suggests a change of date for a vague reason which is stated as “because there will be international meetings in the city” which is as well far from the truth. Then we had to send another letter to inform them that their reply was unacceptable for it lacks clarity and that conflict with the 1987’s proclamation of public gatherings. While three of the demonstration organizing committee delegates went to give the letter, the officer at desk snubbed and left them at the office with the letter. “He,” they said, “was scared and unconfident to receive the letter. Finally they counted witnesses and left the letter and returned back.
A day, two days . . . passed. According to the 87’s proclamation “unless you’re given an excuse to change because of a vivid reason in 12 working hours it will be considered as officially accepted and known. Therefore in regards to that we started to act; prepared all the flyers to promote the protest, give orientations to members and etc. Monday was the first time we started our promotion. There were 10 teams in all sub cities. Later in late afternoon two teams who went out to Kasanchiz and Gulele got caught by the police and were detained. In the morning they appeared to the court house. Six of them at Arada court house and the other 7 at Mexico court house. The first six were presented and without any dialogue nor argument they were sent back to prison to be brought back in 7 days as requested by the police; those who were presented at Mexico court house were bailed out 1000 birr each.

The next day a letter came from the city office. It issued a filling of a form about the demonstration. Then the organizers thought it was right and went. Yet during the process the officer told them to change the place from Janmeda to other place. They couldn’t accept the change and left the office. It took almost two days to settle the argument about the place. At last the organizing committee and the executive members decided to change the place to Signal Meda(woreda 8 meda) because of a road to Janmeda under construction. Though on Thursday about 14 members counting 2 executives were arrested while distributing flyers and promoting the demo’.
On Friday again police arrested some of our members who went out promoting the demo’. Six members and two cars with all the electronics that were about to be used were detained. When this happened three executive members: the chairman Eng. Yilkal Getnet, Ato Sileshi Feyisa(Vice Chairperson and Demo’ Organizing Committee Assistant Convener) and Ato Brhanu T/Yared(Public Relations Head and Demo’ Organizing Committee Convener) went to discuss the matter with the officials yet as soon as they got out of the office three of them were detained and had to walk to Yeka police station guarded with many polices. The scene looked like some sort of terrorists got caught.
Late at night that evening Eng. Yilkal Getnet was forced to leave the prison separately from the other two comrades. However Yilkal refused to go out and had to go through a long argument with the officials at the station. He insisted not to leave because there was no reason to why he should separately return home while they were caught and had been working together. Nevertheless it was “meaningless and was not productive” so he came back around 09:00pm in the evening.

Consequently supporters, members and leaders of Semayawi(Blue) Party determinedly insisted on keep going and make sure that the demonstration would go as planned even though more than 30 members including 4 executives remained in prison. It was believed at the time that the ruling party was trying to break us down. The regime wanted us to call off the demonstration. In fact not only the regime but also some political personalities didn’t expected Semayawi would execute the event while many of its members and leaders were still in prison.
Conversely on Sunday morning we went out. It was very colorful and loud. All the participants were whistling, blowing ‘turumba’(trumpet), shouting out loud and experience the free breath of fear free environment. The protest went like that until it got to Adwa Square. At the square the police prohibited the crowed from going to the route Semayawi decided to go through. There happened the extraordinary during the confrontation with the police. Unlikely many of the partakers in the protest stood firm and demanded a way through to Balderas which the police debarred. None went back – many joined the push-forward at some point the police could not handle the pushing forward so they were about to start beating then at that point someone at the front told the crowd to kneel down. It was done and the police was confused and couldn’t do a thing. Then when it was calm the confrontation started all over again. While the struggle to pass through the way was going on some assigned representatives of the party were dealing with the police officers. They explained and showed them the form. After a while the route was open and Eng. Yilkal, who were in the middle of the confrontation himself, wave his hand to move forward and all screamed of joy and moved on for all courageously stood for their rights and earned it.
The demonstration was so peaceful and boldly stated all the problems in the country and underlined the incapability of the ruling party to lead this big nation and it need to leave power. Many protesters had been voice of the millions. It was such a symbolic protest that gives lesson to all and motivates many to be brave enough to stand for their rights and to fight for it peacefully yet assertively.
When this report is written about 26 were still arrested and demanding justice because they have been asked a bail about 5000br and an identity card of a person who works for government organizations for 6 prisoners each; 1600br and an ID for 14 prisoners each, and 1000br and an ID for 6 prisoners each in total 58,400br asked for bailing them out. The arrested claimed and argued that they haven’t done anything against the law and they should be freed without any bail or anything like that.
With all the drama, in general, Semayawi (Blue) party executed its second demonstration successfully in regards to its objectives which are mentioned over. It cost the party a lot yet gained even more. Many of us needed to spend a week or two in prison, some are still in jail to motivate and awake the people and make their voice be heard. Many invested out of their pocket yet be happy for all sees hope in the progress.

The change is sure to come and we are ready to carry the load and the burden.

Ethiopia rises and all will be fine!
Semayawi(Blue) Party!

በነገው ስልፍም ይፈቱ ዘንድ ድምጹን ያሰማል!

ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልሳለን›› በሚል ሚያዝያ 19 ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ከምናነሳቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉ ገዥው ፓርቲን ላይ የሠላ ትችት ስለሰነዘሩና ለህዝባቸው መረጃ ስለሰጡ ብቻ የሚደርስባቸውን ህገ ወጥ እርምጃ ያወግዛል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ የህዝብን መብት ለማስመለስ ለጠራነው ሰልፍ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 50 ያህል አመራሮችና አባላት በህገ ወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት የፓርቲያችን ሊቀመንበር (ማታ ተፈትተዋል)፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ ወቅት የዞን ዘጠኝ አክቲቪስቶችና ሌሎች ጋዜጠኞችም ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ሌሎችን ለማሰር ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የገዥው ፓርቲ ከፍርሃት የመነጨ አምባገነናዊ እርምጃ በጽኑ ይቃወማል፡፡ በነገው ዕለትም በእነዚህ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች ላይ የተደረገውን እስር የሚያወግዝ መሆኑን መግለጽ ይወዳል፡፡

ኑ ራሳችን ነጻ በማውጣት የአገራችን እጣ ፈንታ እንወስን!

ቀን 18/08/ 2006 ዓ.ም

ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት፡- ባለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የሚዲያ ነጻነት እንደሚፈቀድ ቢደነግግም በተግባር ግን የራሱን ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛባቸው ሚዲያዎች ውጭ ሌሎቹን ሲዘጋና ሲያሸማቅቅ ኖሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ህዝባችን ከገዥው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ውጭ አማራጭ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ፣ እየተሰደዱ፣ ሚዲያዎች እየተዘጉም ቢሆን የተቻላችሁን ያህል ለህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ለምታደርጉት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር አለን፡፡ የታፈነውን የህዝብ ድምጽ ለማሰማት የምታደርጉትን ጥረትም እናበረታታለን፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በገዥው ፓርቲ አፋኝነት ምክንያት ህዝባችን የሚገባውን መረጃ እያገኘ አይደለም፡፡ እናንተም በሰበብ አስባቡ ጫና እየደረሰባችሁ እንደሆነ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡

ገዥው ፓርቲ ላይ የሰላ ትችት የሚያደርሱ ጋዜጠኞች ‹‹አሸባሪ›› ተብለው ታስረዋል፡፡ ጋዜጦችና መጽሄቶች በስርዓቱ ተዘግተዋል፡፡ በርካታ ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድብደባ፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ደርሶባቸዋል፡፡ እየደረሰባቸውም ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ በሚያደርስባቸው ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ጫና ከገበያ ወጥተዋል፡፡ በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ለህዝባችን አማራጭ መረጃ የሚያደርሱ ሚዲያዎችና የሚዲያው ማህበረሰብ መብቶቻቸውን ተነጥቀው አደጋ ላይ ወድቀዋል፡፡

አማራጭ መረጃ ለዴሞክራሲና ለልማት ቀዳሚውን ሚና እንደሚጫወት የሚያምነው ፓርቲያችን ይህን የመብት ረገጣና አፈና ሲቃወምና ሲታገል ቆይቷል፡፡ አሁንም በጠነከረ መልኩ ይቃወማል፡፡

ፓርቲያችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽን ጨምሮ የተነጠቁትን መብቶቻችን ለማስመለስ በመጣሩ አመራሮቹና አባላቱ በህገ ወጥ መንገደ እስር ቤት በሚገኙበት ተመሳሳይ ወቅት የዞን ዘጠኝ ወጣቶች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ከመቸውም ጊዜ በላይ ጭቆናው እንደመረረ እና ሁሉን ማህበረሰብ ያቀፈ ትግል እንደሚያስፈልግ ዋነኛ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህ የመረረ ጭቆና ህዝባችንን ነጻ ማውጣት የምንችለው እኛ ህዝቡን ማደራጀትና ማንቀሳቀስ የሚዲያ ማህበረሰቡም መደረጃውን ለህዝባችን ማድረስ ሲችል ብቻ ነው፡፡

ፓርቲያችን ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ጨምሮ ገዥው ፓርቲ ከኢትዮጵያውያን የነጠቃቸውን መብቶች ለማስመለስ ተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ የሚዲያው ማህበረሰብ ይህን የተቃውሞ ሰልፍ ሂደት ለህዝብ በማስተላለፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የታመነ ነው፡፡ በመሆኑም መብቶቻችን በህዝብ ትግል ይመለሱ ዘንድ እናንተም የተለመደው የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡

መረጃ ኃይል ነውና በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ የህትመትም ሆነ የብሮድካስት ውጤቶች የተነጠቁትን መብቶቻችን፣ የሰላማዊ ሰልፉን ሂደት፣ በሂደቱ በፓርቲያችንና በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል እና ሰላማዊ ሰልፉን ለህዝብ በማድረስ ግዴታችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን፡፡ በተለይ ሌሎች ሚደያዎች በታፈኑበት በአንጻራዊነት የህዝብ ድምጽ በመሆን ላይ በሚገኘው ፌስ ቡክ በኩል መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ቀላል የማይባል ጫና መፍጠር የሚቻል በመሆኑ አጋጣሚውን በመጠቀም መብታችን ለማስመለስ እንድንታገልና በሰልፉም እንድንገኝ አደራችን እናስተላልፋለን፡፡

ኑ ራሳችን ነጻ በማውጣት የአገራችን እጣ ፈንታ እንወስን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ፖሊስ የሰልፉን ኃላፊነት እንደማይወስድ አስታወቀ የአዲስ አበባ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ በትናንትናው ዕለት ‹‹እንነጋገር!›› ያላቸውን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በዛሬው ቀን ቢሮው በሄዱበት ወቅት ‹‹ሙሉ በሙሉ የሰፉን ኃላፊነት ትውስዳላችሁ!›› እንዳላቸው የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ገልጸዋል፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ በኩል የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑና ምክትል ሰብሳቢው አቶ ስለሽ ፈይሳ የቀረቡ ሲሆን ‹‹እኛ ለፖሊስ ያሳወቅነው በሰልፉ ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን እንዲቆጣጠር ነው፡፡ እኛ ሀላፊነት ልንወስድ የምንችለው ይዛናቸው ለምንወጣው ጽሁፍና ለምናስተላልፈው መልዕክት ብቻ ነው፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ሰልፉን ሊያደናቅፉ የሚመጡ አካላት ቢኖሩ ይህን ኃላፊነት ሊወስድ የሚገባው ፖሊስ ነው›› የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡ አስተባባሪዎቹ ፖሊስ ይህን ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ሰልፉን ለማደናቀፍ ሴራ እየተሸረበ ስለመሆኑ አመላካች ነው ሲልም የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ምክትል ኮሚሽነሩ ‹‹ሰልፉ ከሚካሄድበት 3 ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ አንድ ደቂቃ ቢያልፍ ህገ በህገ ወጥነት እንከሳችኋለን›› እንዳሏቸው ተግልጻል፡፡ በተመሳሳይ የታሰሩት ወጣቶች ‹‹ህገ ወጥ ወረቀት ነው ሲበትኑ የተገኙት፡፡ ህገ ወጥ ወቀረት በመበተናቸውም ሊታሰሩ ይገባቸዋል፡፡›› ማለታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተያዘ ዜና ፖሊስና የደህንነት አባላት የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ አካባቢ የሚገኘውን ህዝብ በር እያንኳኩ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን በድምጽ ብክለት ክሰሱት!›› እያሉ እየቀሰቀሱ ነው፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ የሰፈሩ ነዋሪዎች ‹‹እስካሁን አልረበሹንም፣ ሊረብሹንም አይችሉም፡፡›› እያሏቸው ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እያለ አመራሮቹ ጃን ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ በታሰሩበት ወቅት ፖሊስ ‹‹ህዝቡ ነው የድምጽ ብክለት አድርሰውብናል በሚል›› የከሰሳችሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡

ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ!
የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን!!!
እሁድ ሚያዚያ 19 ቀን ከጠዋቱ 3 – 8 ሰኣት
ቦታ ከፓርቲው ጽ/ቤት ተነስቶ በአዋሬ፣ አድዋ ድልድይ፣ ባልደራስ አድርጎ መድረሻው ወረዳ 8 ሜዳ የካ ሚካኤል ታቦት ማደርያ ይሆናል፡፡
ኑ ራሳችንን ነፃ በማውጣት የሀገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!
ሰማያዊ ፓርቲ

ፖሊስ ቅስቀሳው ላይ ያልነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንም እያሰረ ነው፡፡ በትላንትናው እለት በቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩትን አባላትና ደጋፊዎች ሁኔታ ለማጣራት ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ፖሊስ አስሯቸዋል፡፡
በዛሬው ቀን ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት 1. ብሌን መስፍን 2. አስናቀ በቀለ 3. መስፍን 4. ተስፋዬ አሻግሬ 5. እዮብ ማሞ 6. ኩራባቸው 7. ተዋቸው ዳምጤ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች 1. ፍቅረ ማሪያም አስማማው 2. እያስፔድ ተስፋዬ 3. ጋሻው መርሻ 4. ተስፋዬ መርኔ 5. ሀብታሜ ደመቀ 6. ዘሪሁን ተስፋዬ 7. ጌታነህ ባልቻ 8. ንግስት ወንዲፍራው 9. ሜሪን አለማየሁ ናቸው
(የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ሰልፉ እውቅና እንደተሰጠው የገለጸበት ቅጽ ተያይዟል)

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ለመሆኗ አለም ይመሰክርላታል፡፡ አንቱ የተባሉ ምሁራንን በማፍራት ለዓለም አበርክታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአለም ካሉ ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት እስከ አመራነት ድረስ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህ ምሁራን በተሰማሩበት ስራ መስክ የሚያስመዘግቡት ውጤት እና በስራቸው ተሸላሚ መሆን ላነሳነው ሀሳብ ማጠናከሪያነት ያገለግለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ግን ሀገራችን ከእነዚህ ውድ ልጆቿ ተገቢውን ዋጋ አለማግኘቷ ነው፡፡ ሀገራችን የወላድ መካን እየሆነች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚቀነባበር ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ብትሆንም ቅሉ በተከታታይ ስልጣኑን የጨበጡት ጭፍን አንባገነኖች በሚያራምዱት አግላይ ምሁር ፖሊሲ ምክንያት እውቀታችሁን እና ገንዘባችሁን በምትወዷት ሀገራችሁ ኢንቨስት አድታደርጉ ሁኔታዎች ባለመመቻቸታቸው የስደትን መራራ ጽዋ እንድትጨልጡ ተገዳችኋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለይ ባለፉት 10 አመታት በተቃዋሚዎች መዳከም የሚያታግል ኃይል አጥታችሁ እንደቆያችሁም እናምናለን፡፡

ፓርቲያችን ሰማያዊ እያንዳንዱ ዲያስፖራ ሀገር ቤት ያለውን ዜጋ ያክል የኢትዮጵያዊነት መብት አለው ብሎ ያምናል፡፡ ይህ ይረጋገጥ ዘንድም አጥብቆ ይታገላል፡፡ በተለያየ ሁኔታና ወቅት አንባገነኖችን በሀገር ውስጥ እንደታገላችሁ እናምናለን፡፡ ለዚህ ትግላችሁና ለከፈላችሁት ዋጋም እውቅና እንሰጣለን፡፡ በስርዓቶቹ ጨካኝ ዱላ እና ሰቆቃ ብዛት ውድ ሀገራችሁን ትታችሁ የሥደትን ኑሮ ትገፉ ዘንድ ቢበየንባችሁም ስለ ኢትዮጵያ ከመብሰልሰል እንዳልዳናችሁና ሀሳባችሁ ሀገር ቤት ስለ መሆኑ መስካሪ አያሻም፡፡

ውድ የሀገራችን ልጆች እናንተ የሰው ሀገር በምታለሙበት በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ኢትዮጵያ የጉልበት ሰራተኛ ሳይቀር ከቻይናና ከህንድ በከፍተኛ ክፍያ እያስመጣች ትገኛለች፡፡ ይህ ደግሞ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ስለ መሆኑ ለእናንተ መንገር ለቀባሪ እንደ ማርዳት ያለ ነው፡፡ ይህ በእውነት ለአንድ ሀገር ወዳድ ዜጋ እንደ እግር እሳት ያንገበግባል፡፡ ልማታዊ መንግስት ነኝ በሚል የቃላት ጋጋታ ብቻ ከድሃው ወገናችሁ በሚሰበስበው ገንዘብ የሰከረው ጉልበታም መንግስት ዴሞክራሲና ልማት አንድ ላይ አብረው አይሄዱም በሚል ማሳሳቻ በየ ጊዜው ጉልበቱን እያፈረጠመ የሄደው በአብዛኛው እናንተ ከምትኖሩበት ከምዕራባውያን ሀገራት በሚቀበለው እርዳታ መሆኑ ሀቅ ነው፡፡
ዳያስፖራው በነጻነት መኖር ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ያውቀዋል፡፡ ነጻ ሆኖ መስራት ለሀገር ልማት ግንባታ ያለውን ጠቀሜታም ሀገር ቤት ካለው ህዝብ በተሻለ ሁኔታ ይገነዘባል፡፡ ድህነትና አንባገነንነት ባመጣው ጦስ ኢትዮጵያዊ ክብራችን ተገፎ በየ በረሃው ዜጎቻችን እንደ እንስሳት ሲታረዱ፣ እህቶቻንን በቡድን ሲደፈሩ፣ ወገኖቻችን ልብና ኩላሊታቸው ወጥቶ ለገበያ ሲውል እንደማየት ያለ ዘግናኝ ተግባር ምን አለ?!! ይህ ህገ ወጥ ተግባር ሊፈጸምባቸው አይገባም ብላችሁ ያሳያችሁት ለወገን መቆርቆር ይበል የሚያስብልና ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለን እናምናለን፡፡
በተለይ የሳውዲ መንግስት በዜጎቻችን ላይ የወሰደባቸውን ህገ ወጥ ተግባር ለማውገዝ ያደረጋችሁትን ርብርብና ለሀገራችን በአንድ ሆ ብላችሁ መቆማችንሁን በድጋሚ እያመሰገንን አንባገነኑን ኢህአዴግ ለመታገል በሚደረገው ትግል አጋራነታችሁን ስለምንገነዘብ ከጎናችን በመሆን ለምታሳዩት ውጣ ውረድ እውቅና እንሰጣለን፡፡ ከዚህ በፊት ያሳያችሁትን የትግል ቁርጠኝነት እንደምትደግሙት በማመን ያላችሁን የገንዘብ አቅም፣ የእውቀትና የተሰሚነት ሚና በመጠቀም የአንባገነኑን ስርዓት አፈና በማጋለጥ ከጎናችን እንድትሰለፉ ስንል እንጠይቃለን፡፡ ዳያስፖራው ያለውን የኢኮኖሚ ነጻነት፣ የሚዲያ ነጻነትና፣ ሀገር ቤት ካለው ጋር ሲነጻጸር ያለው የለሻለ የትምህርት ደረጃና ልምድ፣ እንዲሁም በእርዳታ ሰጭ ሀገራት ያለው የተሰሚነት አቅም ተጠቅሞ ሀገር ቤት ያለውን ትግል በማገዝ ነጻ የምንወጣበትን ቀን ሊያፋጥን እንደሚገባ ፓርቲያችን ያምናል፡፡

ፓርቲያችን የህግ የበላይነትን ለማስፈን ሁሉንም የሀገሪቱን ዜጋ ያሳተፈ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ዘርፈ ብዙ ትግል ውስጥ ደግሞ ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልስ›› በሚል መሪ ቃል ታላቅና ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም ይህን ሁሉን አቀፍ የሆነ ሰላማዊ ትግል በሞራል፣ በእውቀትና በምክር፣ እንዲሁም በገንዘብ በማገዝ የትግሉ አጋር ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡

ከአገራችሁ እርቃችሁ የምትኖሩ በመሆናችሁ አዲስ አበባ ውስጥ አብራችሁን ባትቀሰቅሱ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ባትወጡና ባትታሰሩም መረጃውን ለዓለም ህዝብ በማድረስ ከፍተኛ ሚና እየተጫወታችሁ ቆይታችኋል፡፡ በዚህ ሰልፍም አገር ቤት ለሚኖሩ ቤተሰብ፣ ጓደኛ እንዲሁም ሌላው ህዝብ በስልክ፣ በማህበራዊ ድህረ ገጽና የተለያዩ መልዕክት ማስተላለፊያዎች በመጠቀም ህዝቡን የማነቃቃት አቅምና አጋጣሚ ተጠቅማችሁ በትግል ጉዟችን ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ኑ ራሳችንን ነጻ በማውጣት የአገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!

በንግዱ ዓለም ለተሰማራችሁት ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤
በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ሁሉንም የኢኮኖሚ መስክ ጠቅልሎ በመያዙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚገባችሁን አስተዋጽኦ እያደረጋችሁ እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ለይስሙላ ብቻ ነጻ ገበያን ‹‹ፈቅጃለሁ!›› የሚለው ገዥው ፓርቲ ኢኮኖሚውን በራሱ ድርጅቶች ተቆጣጥሮ ለስልጣን መቆያ መሳሪያ አድርጎታል፡፡ የመንግስት ድርጅት የሚባሉትም ቢሆኑ ኢኮኖሚው ጠቅልለው ለተመሳሳይ አላማ መሳሪያ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም አገራችን ነጻ ገበያና የግል ባለሃብቶች የተዳከሙባት ግንባር ቀደም አገር ሆናለች፡፡
ይህ በአንድ ኃይል የተጠቀለለ የኢኮኖሚ ስርዓት እናንተ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በነጻነት እንዳትሰሩ ከማድረጉም ባሻገር ህዝባችን በኑሮ ውድነት እንዲታመስ አንድ ምክንያት ሆኗል፡፡ በተለይ በቅርብ አመታት ከስርዓቱ ጋር አብሮ መሄድ ያልቻለውን የንግዱን ማህበረሰብ ለስርዓቱ እጁን እንዲሰጥ ለማድረግ እንዲመች ከሚሰራው ስራ ጋር የማይመጣጠን ግብር በመጫን ላይ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ ሱቅ በደረቴ የሚሰሩ፤ እንጀራ ጋግረው የሚሸጡ እናቶች፤ የጀበና ቡናና ሌሎቹንም አነስተኛ ስራዎች የሚሰሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ የማይችሉት ግብር ተጨኖባቸዋል፡፡ የንግድ ፈቃድ እድሳት፤ የመስሪያ ቦታና ሌሎችም ነጋዴው በኢትዮጵያዊነቱና ለህዝብ በሚሰጠው ጥቅም ሊያገኛቸው የሚገባቸው መብቶች በሙስና ለፓርቲ ባለው ቅርበትና በሌሎች በዚህ ስርዓት በተሳሳቱ አሰራሮች የንግዱን ማህበረሰብ አስረው ይዘውታል፡፡
ነጋዴውን የሚፈራው ህወሓት/ኢህአዴግ የራሱን ነጋዴዎች ደጋፊ ማህበር አቋቁሟል፡፡ ይህም ነጋዴውን በነጻነት ከመስራት ይልቅ የኢሕአዲግ ተለጣፊ እንዲሆን ካለው ፍላጎት መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በአንጻሩ ሌሎች የንግዱ ማህበረሰብ አካላት የራሳቸውን ነጻ የነጋዴ ማህበር ሲያቋቁሙ አይታዩም፡፡ የመስሪያ ቦታ፤ ግብር እና ሌሎችም ነጋዴው የሚጣልበት ግዴታና የሚገባው መብት ላይ ያለውን ኢፍትሃዊነት ለማስተካከል ጥረት የሚያደርግ የንግዱ ማህበረሰብ አካል አይታይም፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ በሁሉም የኢኮኖሚ መስኮች ሊሳካለት ባለመቻሉ እንዲሁም ነጻ ገበያ ተግባራዊ እንዲሆን አለመፍቀዱ የአገራችን ኢኮኖሚ ከመቸውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ተባብሷል፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያውያን በሰፊው የሚያመርቷቸው ምርቶችም ጭምር ለህዝብ የሚደፈሩ አልሆኑም፡፡ የእነዚህ ምርቶች እጥረት ሲከሰት ጥያቄውን ከእሱ ትከሻ ለማውረድ የሚከሰው የንግዱን ማህበረሰብ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ‹‹ዘይት የደበቀ፣ ስኳር ያልሸጠ፣…›› እየተባለ በሰበብ አስባቡ የስርዓቱ ግፍ ገፈት ቀማሾች ሆናችኋል፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ ድሃ ከሚባሉት አገራት ቀዳሚውን ተርታ መያዟን ለንግዱ ማህበረሰብ ማስረዳት ለቀባሪው አረዱት ይሆናል፡፡ የንግዱ ማህበረሰብ ይህን መሰረታዊ ችግር ከስር ከመሰረቱ ለመፍታት በሚደረገው ትግል የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ ባለመሆኑ አገሪቱን ከገባችበት አረንቋ ለማውጣት የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት መጠቆም ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ይህን ለማድረግም መጀመሪያ የራሱን ነጻነት በማስከበር፣ በመደራጀት የንግዱን ማህበረሰብና ኢትዮጵያውያን አቅርቦቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበትን አጋጣሚ መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ በተለይ የራሱን የፖሊሲ ችግር ተለጣፊ ባልሆኑት የንግዱ ማህበረሰብ አካላት ላይ ለማላከክ የማይታክተውን የገዥውን ፓርቲ ተግባር በማጋለጥ እና ከህዝብ ጎን በመቆም ግዴታችሁን መወጣት ይገባችኋል እንላለን፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም ጃን ሜዳ ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን!›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ መብታችሁን የተነጠቃችሁት የንግዱ ማህበረሰብ አካላትም የራሳችሁንና የቀሪ ኢትዮጵያውያንን መብት ለማስመለስ በሰልፉ ቀዳሚ ተሳታፊ እንድትሆኑ ፓርቲያችን ጥሪውን አቅርቦላችኋል፡፡
ኑ ራሳችንን ነጻ በማውጣት የአገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 9 ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡

በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲ ኤፍ ለቀናታል
PDF ያንብቧት!

ፕ/ር አለማየሁ፣ ፕ/ር መሳይ፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ ግርማ ሞገስ፣ ታምራት ታረቀኝና ሌሎችም ጥልቅ ትንታኔ ሰጥተውባታል፡፡ ጋዜጣዋ በርዕሰ አንቀጽዋ በፋሲካው ስለ ነጻነት፣ ፍትህ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን አስበን እንድንውል ትመክራለች፡፡
በጎንደር የሚፈርሱት 30 ሺህ ቤቶች፣ ኢትዮጵያውያን ዛሬም ‹‹አገራችሁ አይደለም ውጡ!›› እየተባሉ መሆናቸውን፣ አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለ ካሳ መነጠቃቸውንና ሌሎች ትኩስ ወሬዎችን አካትታለች፡፡ ሰለሞን ተሰማ ጂ ለዚህ ትውልድ ‹‹ጥራኝ ጎዳናው፣ ጥራኝ መንገዱ›› እንደሚያስፈልገው ይተነትናል፡፡
በላይ ማናዬ በአገልግሎት እጥረትና በሎሎችም ችግሮች ውስጥ ያለውን ህዝብ ‹‹አይ አንተ ህዝብ ትግስትህ!›› በሚል የችግሩን ጥልቀትና የህዝቡን በዝምታ መገዛት ያስነብበናል፡፡ ጌታቸው ሺፈራው ‹‹የዘመኑ የፖለቲካ ሰማዕታቶች››ን ስለ ፖለቲካው ፋሲካ ቅርበትና ርቀት በአንደበታቸው የሚናገሩትን ጽፏል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ደረጀ መላኩ ስለ ኢትዮጵያ ስትራቴጃዊ ጠቀሜታና ከአሜሪካ ጋር ስላላት ግንኙነት ጥልቅ ትንታኔ ሰጥቶባታል፡፡ ሳሙኤል አበበ ‹‹ማጅራት መችው ፖሊስም የህዝብ ነውን?›› በሚል ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው!›› የሚሉትን ይሞግታል፡፡ ሌሎች ጉዳዮችም ተዳስሰውባታል!

ነገረ ኢትዮጵያ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡
በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ PDF ያንብቧት

– ፕሮፈሰር አለማየሁ፣ ታምራት ታረቀኝ፣ ግርማ ሞገስና ታዲዮስ ታንቱ ጥልቅ ትንታኔዎችን ሰጥተውባታል፡፡
– የተማሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ ማቆም አድማ፣ የአርሶ አደሮች ሰቆቃና ሌሎችም አዲስ ወሬዎች ተካተውባታል፡፡
– በላይ ማናዬ የብሄርፌደራሊዝሙን ቅዝምዝሞሽ ይተነትንልናል፡፡
– ዮናታን ተስፋየ ለምን ፈራን ይለናል፡፡
– እያስፔድ ተስፋዬ የስርዓቱን ሰለባዎች (ከማሞ መዘምር እስከበቀለ ገርባ ዳስሷል፼፡፡ –
– ጌታቸው ሺፈራው ኢህአዴግ ምንም እንደማያሟላ ይሞግታል፡፡
– ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የእስር ቤት ትዝታውን አቅርቦባታል፡፡ ወጣቱ አቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱ ፍትህ ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
– የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስራ አስኪሃጅ በደሎች ተዘርዝረውበታል፡፡

ሰበር ዜና
የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን!!!
የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን በሚል መሪ ቃል ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 እሁድ ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከጠዋቱ 4 ሰአት እስከ 8 ሰኣት ድረስ በጃንሜዳ ያደርጋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ አደረጉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ አስተባባሪነት የተዘጋጀው ይህ ፕሮግራም እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ 9፡ 45 ‹‹በጎ ፍቃደኝነት ለነጻነት›› በሚል መርህ በፓርቲው ጽህፈት ቤት ተከናውኗል፡፡

ዋና ዓላማውን በወሊድ ጊዜ በሚፈጠር የደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰት የእናቶች ሞትን ለመቀነስ መሆኑን የፓርቲው የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ሀና ዋለልኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የለጋሾቹ ምስል በከፊል

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር – 5 ቁልፍ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ እነሆ በ PDF ያንብቧት

– መዝሙረ ኢህአዴግ!
(በላይ ማናዬ)

– የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በተደረገላቸው ግብዣ ወደ አሜሪካ ያመራሉ፡፡ በጉዞው ዓላማና በተለያዩ የአገራችን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

– ኢትዮጵያና የዩክሬኑ ግጥምጥሞሽ
ባለ ቀለሙን አብዮት ማን ይመራዋል?
(በጌታቸው ሺፈራው)

– አዲስ ጠብመንጃ በምንሽር፤
አገዳደሉ ሆድ የሚያሽር፡፡
(በዝክረ ታሪክ አምድ፡- አቶ ታዲዎስ ታንቱ)

– “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ”
(ግርማ ሞገስ)

– ኑሮ ሆነብን እሮሮ
(ጋሻው መርሻ)

– የኢትዮጵያ ፖለቲካና የሴቶች ተሳትፎ
(ኤልሳቤት ወሰኔ)

– ሰላማዊ ትግሉ መሪዎቹን ይሻል
(ታምራት ታረቀኝ)

– ኢትዮጵያዊነት ለእኔ!
(አፈወርቅ በደዊ)

– እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራሞች የሚተዋወቁበት ገጽ አለልዎት

መልካም ንባብ !

የሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ከህዝብ ጀርባ የሚያካሂደውን የኢትዮጵያ – ሱዳን ድንበር ማካለልን በመቃወም በጎንደር ከተማ የጠራውን ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል በእለቱም የፓርቲው አስተባባሪ ለህብረተሰቡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትና አምባገንን ስርዓት ውስጥ ሆናችሁ የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብላችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን በሚል ንግግር ፕሮግራሙን ከፍተው የሰልፉን አላማ አብራርተው የፓርቲውን ሊቀመንበር ወደ መድረክ ጋብዘዋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበርም ለተሰላፊዎቹ ባስተላላፉት መልእክት ለወጣቶች የሀገራቸውን ክብር እንዲያስጠብቁ እራሳቸውንም ከፍርሀት እና ከስጋት በማላቀቅ ለራሳቸውም ለሀገራቸውም አለኝታ እንዲሆኑ፤ እንዲሁም ስርዓቱ ላይ ያሉት አስተዳደሮች ስልጣን ወቅታዊ መሆኑን አውቀው በኢትዮጵያ ድንበር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ደባ እንዲያስቆሙ ከታሪክ ተጠያቂነት እንዲድኑ፤ ለልጆቻቸውም ውርደትን ሳይሆን ክብርን እንዲያወርሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፓርቲውም የጠራውን ሰልፍ እና ማስተላለፍ የፈለገውን መልእክት በተሳካ ሁኔታ አስተላልፎ ፕሮግራሙን አጠናቋል፡፡ ፓርቲውም በአካባቢው የሚገኙ የፓርቲው አስተባባሪዎችን እንዲሁ የጎንደር እና የአካባቢው ህዝብን ለዚህ ሰልፍ መሳካት ላደረጉት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡፡