የመን እንደ ሶማሊያ መታመሷ፣ ለኤርትራ መንግስት አመቺ ይሆናል ኤርትራ መንግስት አካባቢውን እየበጠበጠ ስለሆነ በጋራ እንመክተዋለን ያሉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጅቡቲ ፕሬዚዳንት፤ በኤርትራ መንግስት ላይ የተጣለው አለማቀፍ ማዕቀብ እንዲቀጥል የጠየቁ ሲሆን፤…

The post ኢትዮጵያና ጅቡቲ፣ በኤርትራ መንግስት ላይ ማዕቀቡ እንዲቀጥል ጠየቁ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ሐራ ዘተዋሕዶ በምስሉ የሚታዩት የቢራ ማስታወቂያዎችን የያዙ የመጠጥ ግሮሰሪዎች፣ የውበት ሳሎን፣ ባርና ሬስቶራንት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትየቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለምንና የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል አብያተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም፣ ቅጥርና ገረገራ ይዘው…

The post ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅምና በሚያስተች አኳኋን ለሦስተኛ ወገን የሚተላለፉ የአድባራት የንግድ ማዕከላት ኪራይ አሳሳቢ ኾኗል – ሐራ ዘተዋሕዶ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በፌብርዋሪ 14, 2015 አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ  ፌብርዋሪ 14, 2015 በኖርዌይ የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ 3ኛ  እና 4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የሥራ ክንውን ሪፖርት የቀረበበት የተሳካ አጠቃላይ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ…

The post የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

«ለውጥ በማይቆም ተሽከርካሪ የሚጓዝ አይደለም፤ የተከታታይ ትግል ውጤት ነው። ነጻነት የምንፈልግ ሁሉ ጀርባችንን ቀና አድርገን መታገል አለብን። ራሳችን ካልፈቀድንለትና ካልተሸማቀቅን፤ ማንም ሰው እንደ ከብት ሊጋልበን ከቶ አይችልም” ነበር ያሉት ዶር ማርቲን ሉዘር ኪንግ ጁኔር ። በማንኛውም አገር ቢሆን፣ ነጻ የሆነ የዜና አገልግሎት የማያገኝ፤ ተቆርቋሪ የፖለቲካ ወይንም የማህበረሰብ ወይንም የሲቪክ ድርጅት እና በነጻነት የሚንቀሳቀስ የመገናኛ ብዙሃን […]

በምስሉ የሚታዩት የቢራ ማስታወቂያዎችን የያዙ የመጠጥ ግሮሰሪዎች፣ የውበት ሳሎን፣ ባርና ሬስቶራንት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለምንና የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል አብያተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም፣ ቅጥርና ገረገራ ይዘው የሚታዩ የንግድ ማዕከላት ናቸው፡፡ የቦታውን ዋጋ ባገናዘበ አኳኋን በሕጋዊ መንገድ ከአለመከራየታቸውም በላይ በተከራይ አከራይ ለሦስተኛ ወገን በከፍተኛ ጥቅም የተላለፉት እኒኽ የንግድ ማዕከላት፣ በቤተ ክርስቲያን መሳለሚያና መዳረሻ …

ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል! ቃል ኪዳናችንን ማጥበቅ አለብን! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በዛሬው ዕለት ለቀድሞው የአንድነት አመራሮችና አባላት የተዘጋጀው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ላይ ከተናገሩት -ነገረ ኢትዮጵያ: ፓርቲ ጣኦት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ቅንጅትንም አፍርሶታል፡፡ አንድነትንም አልፈረሰም ብለው እንዳይከሱኝ እንጅ አፍርሰውታል ማለት እችላለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰማያዊ ላይም አንድ ነገር ማምጣታቸው የማይቀር ነው፡፡ ያ ማለት ግን […]

«ለውጥ በማይቆም ተሽከርካሪ የሚጓዝ አይደለም፤ የተከታታይ ትግል ውጤት ነው። ነጻነት የምንፈልግ ሁሉ ጀርባችንን ቀና አድርገን መታገል አለብን። ራሳችን ካልፈቀድንለትና ካልተሸማቀቅን፤ ማንም ሰው እንደ ከብት ሊጋልበን ከቶ አይችልም” ነበር ያሉት ዶር…

The post እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ ከፖለቲካ ፣ ሲቪክ ፣ የሃይማኖት ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ኮፕንሐግን በሚገኝ አንድ የአይሁዳዊያን ፀሎት ቤት ፊት ለፊት ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች ቆሰሉ። የዴንማርክ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከቁስለኞቹ መካከል ሁለቱ ፖሊሶች ናቸው። ይህ ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ፖሊስ በእግሩ እንደሸሸ የተነገረውን ተጠርጣሪ ማግኘቱን እና መግደሉን ይፋ አድርጓል።

• ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ…

The post ሰበር ዜና- ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የቡሄ እለት ያበደ ሁሌ ሆ እንዳለ ይኖራል እንዲሉ የአድዋ ድልና የአድዋ ጀግኖች ስም በተጠራ ቁጥር የሚያቃዣቸው በርካቶች ናቸው፤ ስለምንሊክ ለምትጠይቁኝ እኔም እንደገጣሚው እንዲህ እላችኋለው ‹ምኒልክ ማለፉን የምትጠይቁኝ፤ ፊትም አላለፈ ኋላም…

The post የቡሄ እለት ያበደ ሁሌ ሆ እንዳለ ይኖራል እንዲሉ የአድዋ ድልና የአድዋ ጀግኖች ስም በተጠራ ቁጥር appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

• ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ! ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ ቅጽ 4 እንዳታዘዋውሩ›› የሚል መልዕክት ማስተላለፉን እና ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ከመቀነስ ጀምሮ ፓርቲውን ከምርጫው ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ከምርጫ አስፈጻሚዎች መረጃዎች ደርሰውናል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር […]

ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ […]

ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ

• ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ ቅጽ 4 እንዳታዘዋውሩ›› የሚል መልዕክት ማስተላለፉን እና ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ከመቀነስ ጀምሮ ፓርቲውን ከምርጫው ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ከምርጫ አስፈጻሚዎች መረጃዎች ደርሰውናል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፓርቲው ከትግራይ፣ እስከ ሞያሌ ጫፍ ዕጩ ማቅረቡ ለገዥው ፓርቲ ያልተጠበቀና አስደንጋጭ ሆኖበታል ያሉት ኢ/ር ይልቃል በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚደረጉት ጫናዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ ሰይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ 23 ዕጩዎችን አቅርበናል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ዕጩ ያቀረቡ ፓርቲዎች ሳይቀር በሚዲያ ሲነገርላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ የምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት በቴሊቪዥን ቀርበው ‹ሰማያዊ በተደጋጋሚ ብንነግረው አልሰማም፣ በመሆኑም ሰኞ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔ ያስተላልፋል› ብለዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ሰማያዊ በምርጫው እንዳይሳተፍ ችግር መፍጠር እንደሚፈልጉ ነው፡፡›› ሲሉ ፓርቲው ላይ እየተፈጠረበት ያለውን ጫና ገልጸዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በዛሬው ዕለት በኢቢሲ ቀርበው ሰማያዊ ይቅርታ ባለመጠየቁና ማስጠንቀቂያዎችን ባለመቀበሉ ነገ ሰኞ ጥር 9/2007 ዓ.ም ውሳኔ ያስተላልፋል ብለዋል፡፡

ከሌሎች ፓርቲዎች ሰማያዊን በመቀላቀል በፓርቲው ምልክት ለመወዳደር የወሰኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲሰረዙ መደረጉና በሌሎች ዕጩዎች ላይም ከፍተኛ ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

Minilik Salsawi – ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።

ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን።አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::

የሚዲያ ተቋማት እና የድህረገጽ ውጤቶች ሕዝብን በማስተማር ሕዝብን መብቱን እና ነጻነቱን አውቆ ለሌላው እንዲያስተምር በማድረግ ረገድ አስፈላጊውን ወቅታዊ መረጃ እና መነሳሳትን በማስረጽ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። ያለፉ እና የከሰሙ ወሬዎችን እና አሉባልታዎችን ከመርጨት የወያኔ የፈጠራ አደናባሪ እና አዘናጊ አጀንዳዎችን እኝኝ በማለት ከማውራት ብሄር ተኮር ክፋፋይ ሃሳቦችን ከማርከፍከፍ አዛኝ መሳይ መርዝ ሃሳቦችን ከመናገር ተቆጥበን ሕዝቡን ስለመብቱ እና ነጻነቱን በማስተማር ረገድ መትጋት ከተያዘ ለውጥ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። ትችትን እና ሂስን ላለመዋጥ እውነትን ላለመቀበል የሚደረጉ ሩጫዎች ታጥቦ ጭቃ እንጂ የትም እንደማያደርሱ እንዲሁም ፓርቲዎችን እና ሰዎችን መፈረጅ እና መወንጀል ሃሳቦችን ማጣጣል ምንም ለውጥ እንደማያመጣ ካለፈው ተምረናል ። ያሳልፍነው የትግል ሂደት ከጭብጨባ እና ስብሰባ ያለፈ ፋይዳ እንዳሌለው ተገንዝበን የወሬ እና ሆይሆይ ትግል ስለማያዋጣ ጥንካሬን እና ለውጥን የምናመጣበትን የትግል ስልት በመመካከር እና በመወያየት ሃሳብን በማቻቻል መረጃ በመለዋወጥ ሃገራዊ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል እላለሁ።ልዩነትን በማቻቻል በጋራ መታገል ችላ የማይባል ሃገራዊ አጀንዳ ነው።‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

እርጉዝ ነኝ እያለችህ ሴትን ልጅ ሆዷን ረግጠህ ፅንስ አስወረድክ። አሮጊትና ሽማግሌ በጫማ ጥፊ ሳይቀር የሚደበድቡ አሉ። አንድን ሚስኪን ወገን አስርና አስራ አምስት ሆነው ለጉድ ሲቀጠቅጡም በተደጋጋሚ አየን። መፍክር ብቻ በጁ ይዞ የጋራ ለሆነ መብትና በደል ሊያሰማ አደባባይ የወጣ ዜጋ አቅማቸውን ለማሳየት በብዙ ቁጥር ደግሞ ስልጠናችውን የጠቀማሉ። የማጥቂያ እቅድ ይሰጣቸዋል። ቆረጣው፤ ከብባአድርገው፤ አደፍጠው ብቻ ያለ ወታደራዊ […]

እየተከበረ በሚገኘው የ‹‹መከላከያ ሰራዊት ቀን›› በደርግ ወቅት የነበረው የአገራችን ሰራዊት አባላት እንደ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን እንደ ውጭ ወራሪ ተቆጥሮ ሞቱና ቁስለቱ ላይ እየተፎከረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከአሁን ቀደም ዳር ድንበሯን ያስጠበቀ ይጠብቅ፣…

The post የወቅቱ ሰራዊት ‹‹ክብረ በዓል›› ይገባዋልን? – ጌታቸው ሺፈራው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ባለፈው ወር፣ በየፓልቶክ መድረኩ (ለምሳሌ ከረንት አፌር – ዴሞን በዲሞት ፎር እያለች በቀይ ሽብሩ ወቅት የደርግ የነጻ እርምጃ ቀስቃሽና ለፍርድ ልትቀርብ የሚገባት አዛውንት ማለትም ሙያዬ ምሥክርና ሌሎችም) አማካይነት፤ የተለያዩ ራዲዮና…

The post ሰዶ ማሳደድ ያማረው ዶሮን በቆቅ ይለውጣል! – ከአቶ ሰውየው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ሥልጣንን ይዞ ሀገርንና ሕዝብን ለማሥተዳደር ሁለት የትግል አማራጮች አሉ፡፡ በሀገራችን ሁለቱም ዓይነቶች በሚገባ ይታወቃሉ ተሞክረዋልም፡፡  አንደኛው ሕዝብ በሚያደርገው ምርጫ የመንግሥትነት ሥልጣንን መያዝ መሠረቱ ያደረገው ሰላማዊ የትግል…

The post ላልቀረልን ሀገርንና ሕዝብን የመታደግ ትግል ተነሡ! -ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ImageImage
አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን ቆጥሮ በብልጭልጭ ነገር እያባበሉ ማስተኛትን ይመስላል። መጽሀፍ ስለ ሰይጣን ሲናገር እንደ ብርሀን መልዐክ ለመግደልና ለማሳሳት ራሱን ይለውጣል ይላል። ታዲያ ቢያብለጨልጭ ለመግደል ብቻ መሆኑ ደግሞ ሊታሰብበት ይገባል።
ስለ ሶርያ ጥቂት ነገር እናንሳ። ጥንታዊ እና ስልጣኔ የጀመረባት ሀገር እንደነበረች በከብት እርባታ እና በእርሻ ዘመናዊ ሁኔታዎች የበቀሉባት ስለመሆንዋ ተወስቶላታል። ቀደምት ተብላ እንደመጠራቷም ሀገሪቷ ከ100 አመታት በፊት በቱርክ ግዛት ስር ሆና ደማስቆን እና የቤሩትን የወደብ ከተሞች የሚያካልል ሀዲድ ተዘርግቶ የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት ተጠቃሚም ሆናለች። ከዚያም በመነሳት ነጻነቷን አውጃ ራስዋን ማስተዳደር ስትጀምር የዛሬ 60 አመት በፊት 1956 እ.ኤ.አ ሞደርን ሲኤፍኤስ ፓሴንጀር ትሬን በማለት አዲስ መዋቅር አበጅታ እስከ 2012 ተገልግላበታለች።አሁን ያ ያላት መልካም ገጽታ እና ታሪኳ እንዲሁም ከሁሉ በፊት ባብር ነጂ መሆናዋ ከመሰባበር አላዳናትም።

የሶርያ ፕሬዘዳንት ባሻር አል አሳድ በአንባገነንነት ምድሪቷን መግዛት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ከ2011 ዓ.ም ወዲህ አሁን ድረስ መልኩን ቀያይሮ እና የተለያየ ስም ይዞ ታልቅ እልቂት ያስከተለው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ220,000 ንጹሀን ዜጎች በላይ ለህልፈተ ሞት ያበቃ ሲሆን 11 ሺህ 420 ህጻናት መገደላቸው እና ከ2.2 ሚሊዮን በላይ የሆነ ዜጋ ሀገሩን ጥሎ በየጎረቤቱ ጥገኛ እና ስደተኛ ሲሆን የፍትህ የዲሞክራሲ ረሀብ እና ናፍቆት እንጂ መንገድ፣ ፎቅ፣ ባቡርና ሀዲድማ ነበራቸው። ዴሞክራሲ የሰፈነበት አገዛዝ እና ስርዓት ምድሪቷን እስካልተቆጣጠራት ድረስ ሁሉም ነገር ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው።

ስለ ኢትዮጵያ ደግሞ እናንሳ ። በ1895 ዓ.ም አንድ በደረት ላይ የሚንጠለጠል የምድር ባቡር ማሳሰቢያ ባጅ ነበር። በአንዱ ገጽ የአጼ ምኒልክ ምስል በሌላው ደግም 1895 የምድር ባብር ማሳሰቢያ የሚል ተቀርጻበታል። የዛሬ 112 ዓመት በፊት መሆኑ ነው።በአጼ ምኒልክ ውሳኔ የመሰረት ድንጋዩ ተቀምጦ የስዊዝ ተውላጅ በሆኑት ኢንጅነር አልፍሬድ ኢልግ እገዛ መሰረት የሀዲድ መሰመር ግንባታው እኤአ በ1893ተጀምረ። ከ24 ዓመት በኃላ ስራው ተጠናቅቆ በ1917ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ባብር ተነዳ። ይህም የዛሬ 98 ዓመት መሆኑ ነው። እንግዲህ ኢትዮጵያ ምን ያህል ቀደምት የስልጣኔ ከፍታ እንዳላት ያስረዳል።በአፍሪካ ካሉት ቀደምት የባቡር ተጠቃሚዎች መሀል 1ኛ)ግብጽ በ1856 ዓ.ም 2ኛ) ደቡብ አፍሪካ በ1897 ዓ.ም 3ኛ) ሱዳን በ1898ዓ.ም 4ኛ)ኬንያ በ1901ዓ.ም 5ኛ)ታንጋኒካ በ1905 ዓ.ም 6ኛ) ሴራሊዮን 1909ዓ.ም 7ኛ) ናይጄርያ 1912 ዓ.ም 8ኛ) ኢትዮጵያ በ1917 ዓ.ም በሀገራቸው ላይ ባቡርን ለህዝብ ጥቅም ካዋሉት የመጀመራዎቹ ተርታ ትሰለፋለች።

የዛሬው ዘመን ላይ ደርሰን ባቡር እና ሀዲዱ ብርቅ ሆኖ ባብር! ባብር !ባቡር እየተባለ ጡርንበኞች ሲጮሁ መስማት ምን ያህል ከፍትህ እና ከሰላም ይልቅ ግኡዝ ነገር አእምሮአቸውን እንደጨመደደው ልብ ይሏል። በምድሪቷ ላይ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት የተከሰከሰው የአባቶች አጥንት ለባቡር ለፎቅ እና ለመንገድ አልነበረም። ይልቁንም ለፍትህ ለሉዐላዊነት ለነጻነት እና ለአንድነት ነበር። አሁንም ያ አጥንት ትውልዱን ይወቅሳል። ባቡርማ ብርቅ አይደለም! ኢትዮጵያም ነበራት። ሶርያም ኢራቅም ነድታለች ዳሩ የህዝብ ረሀብ ነጻነት ሆነ እንጂ። ሶርያ ያላት ህንጻ፣መንገዷ፣ባብሯ እና ሀዲዷ ከመበታተን ከመሰባበር አላዳናትም።የሀገር ሀብት ዲሞክራሲ የሰፈነበት አገዛዝ የሆነ እንደሆን ብቻ ሀገር ይለማል። ሀብት እና ንብረታችን ነጻነት እና አንድነታችን ነው። የድል ክንዳችን መያያዛችን እና መቀባበላችን ብቻ ነው።

በወያኔ አለንጋ ደንዛዛ እንዲሆን የተመተተብት ትውልድ አፍዝ አደንግዙን ረግጦ ስለኢትዮጵያው ሊነቃ የሚገባበት ዘመን አሁን ነው። ባቡሩና ሀዲዱ መጥፎ ነው ለማለት አይደለም ስላስፈለገም ነው ከ98 ዓመት በፊት የተገነባው። ድሮስ ወያኔ የራሱን ሆድ ሲያጭቅ ድሆች ከፍርፋሪው ባቡር እና ሀዲድ እንደቡችላ ቢወረውርላቸው ምን ይከፋል። ይህ እኮ የወያኔ ካዝና ውድቅዳቂ እና ፍርፋሪ ነው።ፍርፋሪ ደግሞ ሆድ አይሞላም እንዲያውም ቢያስርብ እንጂ።ይህ ማታለያ ወያኔ ሀፍረቱ እንዳይታይበት የለበሰው ብጣቂና ቅዱስ የመሰለበት ማስመሰያው ነው። ተኩላ በበግ ለምድ እንዲከለል ሰይጣንም አውሬነቱን ለመደበቅ ራሱን እንዲከልል ወያኔም ነፍሰ ገዳይነቱን ለመደበቅ አዛኝ መስሎ የማይበስል ቅቤ ያነጉታል። ለኢትዮጵያ እድገት እና ልማት ለሀገሪቷ ፍቅር ያለው መሪ ህዝብን ነጻ ከማድረግ እና የእኩልነት መንፈስ በምድሪቷ ላይ እንዲሰፍን ከመትጋት ይጀምራል ። ነጻነት የሌለው ህዝብ ፎቅ ላይ ቢወጣ በባቡር ቢሳፈር ዳሩ እስረኞቹ ተሳፍረው እየሔዱ ነው ቢባል እንጂ ሌላ የማታለያ መጠርያ ቢሰጠው በመጫኛ መጣል ይሆናል። እንዶሮዋ።

ዳሩ በግኡዛን ቁሳቁስ ብናምር ብንቆጠቆጥ ማን እርሱን ይጠላል። ግን እርሱ ሐብት አይደለም። አንድ ቀን ይከዳል። ምድሪቷ ድንገት ቢያስነጥሳት አሊያም ብትንጠራራ ከበላይዋ በብድር ገንዘብ ያንጋጠጠው ፎቅም በሉት ባቡር አሊያም ሌላ ግኡዝ የፍርስራሽ ቁልል ሁኖ ለመዛቅ ዕዳ ይሆናል። ስለዚህ ስለብልጽግና ስናወራ ስለ ገንዝብ ካወራን ስተናል ማለት ነው። ገንዘብ ኖሮህ ነጻነት ከሌለህ ፎቅ ገንብተህ በየደቂቃው የወያኔ አባት በጣረ ሞት መንፈስ እየመጣ ካስጨነቀህ ከዚህ በላይ ምስኪንነት የለም። ኢትዮጵያ በለጸገች አሊያም ብሩህ ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሎ ወያኔ ራሱን በራሱ ቢያንቆለጳጵስ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የማባበያ እና የማታለያ ባዶ ዲስኩር ፊቱን ሊመልስ እና ሊነቃ ግድ ነው።

የሀገር ሀብት ፍትህ፣አንድነት፣እኩልነት፣ እና ለአንዲት ሀገር በአንድ ክንድ ለሀገር ሉአላዊነት የቆመ አንድ ህዝብ እንጂ ብሩም ወርቁም ነጻ ባልወጣ ሀገር አያምርም! አያደምቅም! የውሸት ነው። በአዲስ አባባ ላይ ብቻ የታየው ብልጭልጭታ ህጻኑ እንዳያለቅስ የተሰጠው ማታለያ ይመስላል። ኢትዮጵያ አዲስ አባባ ብቻ አይደለችም ።

ከቤት እንሰሳት ጋር የውሀ ጥሙን ለመቁረጥ ወደወንዝ የሚርደው ህዝብ፣ ዛፍ ስር በድንጋይ ላይ ተቀምጦ ወጉ እንዳይቀር ሀ ሁ ሂ . . . እያለ ፊደል የሚቆጥረው፣ ለቀዶ ጥገና የ2 አመት ቀጠሮ የሚጠብቁ ታማሚዎች፣በየክፍለሀገራቱ ከልጅነት እስከእውቀት በበጋም በክረምትም መጠለያ ሳይኖራቸው በየጥጋጥጉ ቆሼ ተራ እየተመገቡ ያደጉት ሌላም ቢተረክ ጌዜ የማየበቃው ቁርቁዝና ከሁም በላይ ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ እውነቱን እንዳይናገር የታፈነ እና የተለጎመ የታሰረ አንደበት የተጠራቀመባት ምድር ናት ኢትዮጵያ የሚትባለው። ይህች ናት በወያኔ የተቀረጸችው ኢትዮጵያ። ስለዚህም ነው አሁን የመንቃት ጊዜ እንደሆነ የምንናገረው። ኢትዮጵያውያንን እንደ ህጻን በብልጭልጭ ነገር የማታለል የወያኔ ዘመን ያክትም። ሀብታችን ባቡርና ፎቅ ሳይሆን አንድነት እና እኩልነታችን ነው። በመጀመሪያ ነጻነት!!!

እናቸንፋለን !!!
Biniam Gizaw (Norway)

ዩጋንዳ በሀገሯ የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዓማፅያን ሀገሯን ለቀው እንዲወጡ ከጥቂት ቀናት በፊት ትዕዛዝ አስተላልፋለች። ይኸው የዩጋንዳ ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ የወሰዱት ውሳኔ ከዓማፅያኑ ብርቱ ወቀሳ ተፈራርቆበታል።

ሴራሊዮን መዲና ፍሪታውን ውስጥ 6 ግለሰቦች ላይ እንደ አዲስ የኢቦላ ተሐዋሲ ምልክት በመታየቱ በመዲናዋ የሚገኙ 700 ቤቶች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች መግባት መውጣት መከልከላቸው ተዘገበ።

እኔና ተመስገን – የአቶ ግርማ ሠይፉ ማስታወሻእኔና ተመስገን ጓደኛሞች ነን፡፡ ጓደኝነት ማለት ግን አንድ ማሰብ ማለት አይደለም፡፡ ዘወትር ስንገናኝ ስለዚህች ሀገር የወደፊት ዕጣ ፈንታ እናወጣለን፣ እናወርዳለን፡፡ እጅግ ብዙ ሀሳብ አንለዋወጣለን፡፡…

The post እኔና ተመስገን – የአቶ ግርማ ሠይፉ ማስታወሻ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

አሁን አሁን እጅግ እየከፋ የመጣው የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ፀረ ዴሞክራሲ እና ፀረ ሰላም መሆኑ በይበልጥ ግልጥ እየሆነ ከቀን ወደ ቀን እየተሰፈረ ያለው የግፍ ፅዋ ሞልቶ የመፍሰሱ ጉዳይ አለም ሁሉ የሚያውቀው የወቅቱ ዘገባ ነው። የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ እየጋመ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ መከራና ግፍ እየተቀበለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ወያኔ ባቡር አሳይቶ ህዝብን ለማሳቅ መሞከሩ ትውልድን እንደህጻን […]

በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ምንጮቻችን አስረድተዋል፣ ጥር 24 /2007 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ… ካድሬዎች ተላላኪ የሆነው ይርጋ የተባለ የትግራይ…

The post ወያኔ ከትግራይ ተወላጆች ተቃዉሞ ገጠመዉ፡፡ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

90 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫነ የአየር ሃይል አንቶኖቭ አውሮፕላን ከመጋየት መትረፉን የቅርብ ምንጮች ያደረሱኝ መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ጠዋት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት አቆጣጠር 90 የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪዎችን አሳፍሮ ደቡብ ሱዳን…

The post በአየር ሃይል አውሮፕላን ጥቃት ተሰዘነረ -አርአያ ተስፋማሪያም appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ፓስትር ተከስተ ይህ ትውልድ ሃይል በእጁ ከመያዙም በላይ እውነትን የሚበረብርበት መንሽ በእጁ ስለመኖሩ አያጠያይቅም።በዚህ ሄደት የጉዞ ውጣ ውረድ ውስጥ ስለሚያስፈልገውና ፤ ስለሚፈልገው ነገር እያሰበም እያወራም የመኖሩ ሚስጥር ዛሬ ላይ ስለደረሰበት…

The post የደፈረኝና ፤ የደፈረችኝ እሰጥ አገባ – ከመኳንንት ታዬ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

• የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ንግድ ቤት ታሽጓል

ምርጫ ቦርድ በሰማያዊ ፓርቲ ምልክትና ስም የተመዘገቡትን ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲታገዱ በየ ክልሉ ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ በላከው ደብዳቤ ገለጸ፡፡ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ክልል የምርጫ ጣቢያ በላከው ደብዳቤ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ትብብር የሚባል መስርቻለሁ፣ እያስተባበርኩ ነው በማለት እንዲሁም ሌሎች የህግ ጥሰቶችን በመፈጸሙ›› በሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው በመግለጽ በፓርቲው ምልክት ሊወዳደሩ የተመዘገቡትን አባላት ህገ ወጥ ናቸው ብሏል፡፡

ምርጫ ቦርድ በደብዳቤው ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ የራሱ አባል ያልሆኑ ፓርቲውን የማይወክሉ ግለሰቦችን ዕጩ አድርጎ በፓርቲው ምልክት በከፍተኛ አመራር ፊርማና ማህተም አረጋግጦ ለምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች አሳውቆ ከሆነ የምርጫ ሂደት የሚያሰናክል የህግ ጥሰት በመሆኑ….›› በሚል እንዳይመዘገቡ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ የሌሎች ፓርቲ አባላት በሰማያዊ ተጠቃልለው ምርጫውን በሰማያዊ ምልክት መወዳራቸውም የሚያስጠይቅ ነው ሲል ገልጾአል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ዞን ሁሉም ወረዳዎች ከሌሎች ፓርቲዎች ወደ ሰማያዊ በመጠቃለል በሰማያዊ ምልክት ለመወዳደር የተመዘገቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ከዕጩነት እንዲሰረዙ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ክልል ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ደብዳቤ መጻፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ከዕጩነት ለመሰረዝ የሚያስተላልፈው ትዕዛዝ ህገወጥና የፖለቲካ ውሳኔ ነው ያሉት የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ‹‹ችግር ካለ በየምርጫ ጣቢያው ይፈታል እንጅ ምርጫ ቦርድ ይህን መዝግብ አትመዝግብ ብሎ ለየምርጫ ጣቢያው ትዕዛዝ ሊሰጥ አይችልም፡፡›› ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ ለየክልል ቅርንጫፎቹ ደብዳቤውን የጻፈው የምዝገባ ጊዜው ካለቀ በኋላ ሲሆን ይህም የሆነው ፓርቲው በአካባቢው ተለዋጭ ዕጩ እንዳይኖረው ታስቦበት ነው ሲሉ ኃላፊው ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ የትኛውም የተቃዋሚ ፓርቲ ጠንክሮ እንዳይወጣ የታለመ በተለይ ሰማያዊ ፓርቲ የሌሎች ፓርቲ አባላትን በማሰባሰብ የህዝብን ስልጣን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጠንካራ ትግል ለማደናቀፍ ነው ብሏል፡፡ የህዝብ ግንኙነቱ ኃላፊው አክሎም ‹‹የሌሎች ፓርቲዎች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ መቀላቀላቸውን ተከትሎ ስርዓቱ ከፍተኛ ስጋት ተፈጥሮበታል፡፡ ይህ የምርጫ ቦርድ ተግባርም ህጋዊ ሳይሆን ከስርዓቱ ፍርሃት የመነጨ የፖለቲካ ውሳኔ ነው›› ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በፓርቲው ላይ እያደረጉ የሚገኘውን ህገ ወጥ ተግባር ሰማያዊ ፓርቲ እንደማይቀበለውና ትግሉን እናዳክማለን ብለው የሚወስዱት ውሳኔ ይበልጡኑ ትግሉን ያጠናክረዋል ብሏል፡፡

በሌላ በኩል በወላይታ ዞን ቦሎሶሶሬ በሚባል ምርጫ ጣቢያ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር በዕጩነት የቀረቡት አቶ ከበደ ካምፔሶ በዕጩነት መቅረባቸውን ተከትሎ የንግድ ቤታቸው መታሸጉ ታውቋል፡፡ ‹‹ዕጩ እንዳልሆን በሰው ለማግባባትና በማስፈራራት ሊያስቆሙኝ ሳይችሉ ሲቀሩ የንግድ ተቋሜን ዘግተዋል፡፡ ጥያቄያቸው ከፓርቲው እንድወጣና ዕጩነቴን እንድተው ነው፡፡›› ሲሉም አቶ ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ጥር 7 በባህርዳር በሚካሄደው የመከላከያ ቀን ላይ ነዋሪው በስፋት እንዲወጣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ስም እየመዘገቡና በበአሉ ላይ ካልተገኙ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እያስፈራሩ መሆኑን የከልሉ…

The post የኢህአዴግ ካድሬዎች የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ለመከላከያ ቀን እንዲወጣበማስፈራትላይ ናቸው appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፓርቲን ለተቀላቀሉትን የቀድሞ የአንድነት አባላት እሁድ የካቲት 8/2007 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፕሮግራሙን ማዘጋጀት ያስፈለገው ምርጫ ቦርድ በአንድነት ላይ በወሰደው እርምጃ ተስፋ ሳይቆርጡ ሰማያዊ ፓርቲን የተቀላቅሉ አባላት ትግሉን ለማጠናከር ያሳዩትን ቆራትነት እና አብሮነት ለማጠናከር እንደሆነ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡

ከጥር 26/2006 ዓ.ም ጀምሮ ፓርቲውን የተቀላቀሉትና አሁንም መቀላቀሉ የሚፈልጉት የቀድሞው የአንድነት አባላት በፕሮግራሙ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረቡት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሁለቱ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ጥላ ስር አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጡ ተስፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ነፃና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል መርሀ ግብር በማዘጋጀት ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እስካሁን ከተደረጉት እንቅስቃሴዎችም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድና የመንግስት አስፈፃሚ ተቋማት በህገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩና የፖለቲካ ምህዳሩም ለሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ፍትኃዊ እሰኪሆን ድረስ የነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ ዘመቻችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች እጩ ተወዳዳሪዎችን ለማስመዝገብ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የምርጫ አካባቢዎች በዕጩ ተወዳዳሪዎቻችን ላይ በገዢው ፓርቲ አባላትና በምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ከፍተኛ እንግልትና እንቅፋት የተፈጠሩባቸው ሲሆን ለአብነት ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡
1. በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እጩ ተመዝጋቢዎች የተወለዱበት ዞን መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን ምስክር አምጡ በማለት እንዳይመዘገቡ ተደርገዋል፡፡
2. በሰሜን ጎንደር ዞን ባሉ ወረዳዎች በሙሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች ፅ/ቤቶችን ዘግተው በመጥፋታቸው ምክንያት መመዝገብ በተደጋጋሚ የሄዱ እጩ ተመዝጋቢዎች ሳይመዘገቡ ጊዜው እንዲያልፍባቸው ተደርገዋል፡፡
3. በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በምርጫ አዋጁ መሰረት 1 እጩ ተመዝጋቢ ቅሬታ እስካልወቀረበበት ድረስ የመመዝገብ መብት እንዳለው እየታወቀ ነገር ግን የምርጫ ፅ/ቤት ሃላፊዎች የሌላ ፓርቲ አባላት ናችሁ ከፓርቲያችሁ መልቀቂያ ካላመጣችሁ በሚል ምክንያት በርካታ የፓርቲያችን እጩዎች ሳይመዘግቡ መልሰዋል፡፡
4. በሰሜን ሸዋ፤ በሲዳማ፤ ጋምቤላ፤ ጋሞጎፋ፤ በምስራቅና በምእራብ ጎጃም አካባቢዎች እጩ ተመዝጋቢዎችን በገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ታጣቂዎች በማስፈራራት፤በአካባቢ ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶች በማሰወገዝ ራሳቸውን ከእጩነት እንዲያገሉ ተፅእኖና ግፊት ተደርጎባቸዋል፡፡
5. በደቡብ ክልል የገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች እጩዎችን ሊያስመዘግቡ የሄዱ ተወካዮችን በማሰርና በእጃቸው የሚገኘውን የእጩዎች ማስመዝገቢያ ደብዳቤዎች በመንጠቅ የምዝገባ ጊዜው እንዲያልፍባቸው ተደርጓል፡፡
6. በሰሜን ጎንደር፤ በሲዳማና በከምባታ ዞኖች የፓርቲው እጩ አባላት በታጣቂዎች ከፍተኛ ድብደባ ደርሶባቸዋል፡፡
7. በደቡብ ኦሞ ዞን የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልተው የተመዘገቡ የፓርቲያችን እጩዎች በ05/06/07(ማለትም የምዝገባው ጊዜ ካለቀ በኋላ)በደ/ቁ-አ573/ፖአ/ጠ470 ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ክልል ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት በተፃፈ ደብዳቤ 18 የክልል ምክር ቤትና 6የተወካዮች ምክር ቤት በድምሩ24 እጩዎች እንዲሰረዙ ተደርጓል፡፡
እነዚህና ሌሎችም ጥፋቶች የሚፈፀሙት ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ነጻና ፍትሀዊ በሆነ የምርጫ ሜዳ እንዳይሳተፉ በማድረግ የአምባገነናዊን መንግስት የስልጣን ዘመን ለማስረዘም በዕቅድ የተፈፀሙ ድርጊቶች መሆናቸውን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ በእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎችም በማለፍ ፓርቲያችን ለመንግስትነት የሚያበቃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው እጩ ተወዳዳሪዎችን በመላ የሐገራችን ክፍሎች አስመዝግቧል፡፡

ገዥው ፓርቲ በስልጣን ለመቆየት እንደ ስልት የያዘው ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሕዝብ ዘንድ እምነት እንዲያጡ በብቸኝነት በተቆጣጠራቸው የመንግስት የመገናኛ ዘዴዎች ሥም ማጉደፍና ሕዝብም በምርጫው እምነት እንዲያጣ በማድረግ ከራሱ ደጋፊዎች ውጭ ሌሎች ዜጎች በንቃት እንዳይሳተፉ ማድረግን ነው፡፡ በመሆኑም ሕዝቡ በገዥው ፓርቲ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሳይዘናጋ የፈለገውን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥ በንቃት እንዲሳተፍና የመራጭነት ካርዱንም እንዲወስድ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ ከህገ ወጥ አሰራር እንዲቆጠቡ ፓርቲያችን በአፅንኦት እያሳሰበ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የመሰረተውን ትብብር በማጠናከርና በምርጫውም ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ውጤት ለማምጣት ሰማያዊ ፓርቲ ጠንክሮ የሚሰራ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

የካቲት 6 ቀን 2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ

በዘንድሮው ምርጫ ሰማያዊን ወክለው በመቀሌ ለውድድር የቀረቡት አቶ አስገደ ገ/ስላሴ በፖሊስ እየታደኑ መሆኑን ገለጹ፡፡

አቶ አስገደ አሁን ላይ ከቤታቸው ውጭ ከተማ መውጣታቸውን ገልጸው፣ ቤታቸው ሦስት ፖሊሶች ሄደው ‹‹አቶ አስገደ የት ናቸው? ይፈለጋሉ!›› በሚል አሁንም ድረስ ቤታቸው አካባቢ እየፈለጓቸው መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

• በወር 40 ሺህ ብር ኪራይና 250,000 ብር ለ‹‹ኪሳራ›› እንዲከፍል ተጠይቋል

ሰማያዊ ፓርቲ የካ ክ/ከተማ በቀድሞው መጠሪያው ቀበሌ 15 እንዲሁም በአዲሱ መጠሪያው ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 460 የሆነውን ጽ/ቤቱን 25000 ሺህ ብር ቅጣት ከፍሎ እንዲለቅ በአከራዮቹ በኩል ክስ ቀረበበት፡፡ በከሳሽ እነ አቶ ሚስጥረ ሽበሽ የተመሰረተው ክስ ‹‹ቤቱን ለቀው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው …በወር ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ሒሳብ ከጥር 16 ቀን 2007 ጀምሮ ቤቱን ለቀው እስከሚያስረክቡ ድረስ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉን›› ያሉ ሲሆን ‹‹ከሳሽ ቤቱን ለማደስ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በገባነው ውል መሰረት የደረሰብንን 250 ሺህ ብር ኪሳራ እንዲተኩልን›› ሲሉ ከሰዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሚፈልግባቸው ጊዜያት የቀበሌ ካድሬዎች አከራዮቹና ደላሎቹ ለፓርቲው እንዳያከራዩ ሲያስጠነቅቁ የቆዩ ሲሆን በተለይ በጥር ወር 2007 ዓ.ም ይህ ጽ/ቤት እንዳይከራይ ግፊት የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡
በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡

‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡
በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ – ኮምቦልቻ በደቡብ ወሎ የቃሉ ወረዳ የክልልና የፌደራል እጩዎች ለምርጫ ቦርድ ማስረጃቸውን ሊያስገቡና ለማሳወቅ ወደ ምርጫ ቦርድ በሄዱበት ወቅት የመታወቂያ እድሳት እንደሚያስፈልጋቸው በተገለፀላቸው መሰረት ወደሚኖሩበት ሀርቡ ከተማ 01 ቀበሌ በመሄድ መታወቂያቸውን አሳድሰው ይመለሳሉ፡፡ ይህ በተደረገ በሁለተኛው ቀን መታወቂያውን ያደሰውን ቴድሮስ የተባለ የቀበሌው ስራ አስኪያጅ በቀበሌው ካድሬዎች ተጠርቶ ‹‹መታወቂያ ለተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች […]

ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፓርቲን ለተቀላቀሉትን የቀድሞ የአንድነት አባላት እሁድ የካቲት 8/2007 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፕሮግራሙን ማዘጋጀት ያስፈለገው ምርጫ ቦርድ በአንድነት ላይ በወሰደው እርምጃ ተስፋ ሳይቆርጡ ሰማያዊ ፓርቲን የተቀላቅሉ አባላት ትግሉን ለማጠናከር ያሳዩትን ቆራትነት እና […]

ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ነፃና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል መርሀ ግብር በማዘጋጀት ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እስካሁን ከተደረጉት እንቅስቃሴዎችም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድና […]

ምርጫ ቦርድ በሰማያዊ ፓርቲ ምልክትና ስም የተመዘገቡትን ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲታገዱ በየ ክልሉ ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ በላከው ደብዳቤ ገለጸ፡፡ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ክልል የምርጫ ጣቢያ በላከው ደብዳቤ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ትብብር የሚባል መስርቻለሁ፣ እያስተባበርኩ ነው በማለት እንዲሁም ሌሎች የህግ ጥሰቶችን በመፈጸሙ›› በሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው በመግለጽ በፓርቲው ምልክት ሊወዳደሩ የተመዘገቡትን አባላት ህገ ወጥ ናቸው ብሏል፡፡ ምርጫ ቦርድ […]

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ባለፈው የክረምት ወር ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሰጠውን የፖለቲካ ስልጠና ለከምባ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ ቢቆይም፣ ሰራተኞች ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ አልተሰጠንም በሚል ፣ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ አስተያየት አንስጠም በማለታቸው ስብሰባው መተናቀቁን በስብሰባው የተገኙ ተስብሳቢዎች ተናግረዋል። “በደቡብና በጋምቤላ ክልሎች መካከል ያለው የእርሻ ቦታ  ለኢህአዴግ አባላት ኢንቨስተሮች ለምን ተሰጠ? ኢትዮጵያ እየተበደረቸው ያለው …

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊመንበር አቶ ታምሩ አበበ ለኢሳት እንደገለጹት አንዳንድ ነዋሪዎች በውጭ አገራት ነዋሪዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ 6 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና ከ300 ያላነሱት ደግሞ ንብረታቸውን መዘረፋቸውን ተናግረዋል። ድርጊቱን ለማውገዝ የደቡብ አፍሪካ ሰራተኞች ማህበርና የተለያዩ የኮሚኒቲ አባላት ድርጊቱን አውግዘዋል።

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በአቡነ ግንደበረት ወረዳ በመንዲዳ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ባልቻ፣ በፌደራል ፖሊሶች በግፍ የተገደለባቸውን ደሜ ባልቻ የተባለውን ልጃቸውን የሙት አመት በመዘከራቸው፣ ለምን ይህን አደረጉ በሚል እርሳቸውና ሌሎች 10 ወጣቶች ባለፈው ሰኞ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል። አቶ ባልቻ የልጃቸው ገዳዮች እንዲያዙ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቢቆዩም አልተሳካላቸውም። የልጃቸውን ፎቶ …

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  እረገብብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ከጁማ ጸሎት በሁዋላ በአንዋር መስጊድ ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ በቅርቡ መንግስት በመጅሊስ ውስጥ ያካሄደውን ሹም ሽር ተከትሎ ነጻ መጅሊስ እንዲኖር ጠይቀዋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎችን አሳይተዋል። የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ህዝበ ሙስሊሙ ያነሳውን የነጻ መጅሊስ ጥያቄ መርታችሁዋል በሚል ታስረው እንደሚገኙ ይታወቃል።

የካቲት ፮(ስድስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ጥር 7 በባህርዳር በሚካሄደው የመከላከያ ቀን ላይ ነዋሪው በስፋት እንዲወጣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ስም እየመዘገቡና በበአሉ ላይ ካልተገኙ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው እያስፈራሩ መሆኑን የከልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች። ሰሞኑን በየመንገዱ ላይ የተለያየ የሙዚቃ ትርኢት በማሳየት ህብረተሰቡን ለመቀስቀስ ቢሞክሩም የህዝቡን ትኩረት ለማግኘት ያልቻሉት የመከላከያ አመራሮች፣  መንገዱን በየ50 ሜትር በታጠቁ ወታደሮችና የፌደራል ፖሊሶች …