በቡራዩ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል Ethiopia: Car Accident, Fire Kills Twelve in West Addis Abeba
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ ቀርሳ በተባለ ስፈራ ትላንት ማምሻውን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
አደጋው የደረሰው ትላንት ምሽት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ሲሆን፥ ወደ አዲስ አበባ ይመጣ የነበረ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው።
በአደጋው ምክንያት የተነሳው ከባድ የእሳት አደጋም በመኪናው ውስጥ ለነበሩት ሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት እንደሆነም ተጠቅሷል።
በሲኖ ትራኩ ላይ የነበሩት ሹፌር እና ረዳት ከአደጋው መትረፍ የቻሉ ሲሆን የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች ባለስልጣን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እንዲሁም ፌዴራል ፖሊስ በጋራ በመሆን እሳቱን እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰዓት ለመቆጣጠር ተረባርበዋል።
በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ ከ11 የሚበልጡ ሰዎች በተነሳው እሳት ተቃጥለው ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።
አብዛኛዎቹ መሰል አደጋዎችም በከፍተኛ ፍጥነት በማሽከርከር እንዲሁም የመንገድ ደንብን አክብሮ ባለማሽከርከር እየተከሰቱ እንዳሉ መረጃውን ያደረሱን የቡራዩ ከተማ ፖሊስ መምርያ የትራፊክ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ፀጋዬ ባዩ ገልፀዋል።
Receive Ethiopian News and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።