The story about Ethiopian Hero Ato Andargachew Behonegn, who lost his life while saving 58 people.የ58 ሰዎችን ነፍስ ያተረፈው ብዙም ያልተነገረለት ሰው

The story about Ethiopian Hero Ato Andargachew Behonegn, who lost his life while saving 58 people.
Admas:- የ58 ሰዎችን ነፍስ ያተረፈው ብዙም ያልተነገረለት ሰው! Dying while saving 58 souls – A story of an Ethiopian Mechanic and driver.
ከሰሞኑ በተደጋጋሚ የመኪና አደጋ ከአገር ቤት መስማት እየተለመደ መጥቷል። መኪና ተጋጨ ሁሉም ሞቱ የሚል ዜና በበዛበት በዚህ ወቅት፣ ከሶስት ሳምንት በፊት ራሱ ህይወቱን አጥቶ፣ ግን 58 ሰው ስላተረፈው ሰው ታሪክ ልናካፍላችሁ ወደድን።
_______
ጃንዋሪ 28 /2015 ዓ.ም ስድሳ ሰው የጫነ አውቶቡስ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ይጓዝ ነበር፣ ከቀኑ 12 ሰአት አካባቢም ልክ ከአባይ በረሃ በፊት ያለውና ፍልቅልቂት የሚባለው ቦታ ሲደርሱ ፣ ባልታወቀ ሁኔታ ፍሬኑ አልሰራ ብሎ ሾፌሩ አውቶቡሱን መቆጣጠር ያቅተዋል። On January 28, a Bus with 60 people was traveling from Addis to Bahir Dar. Around 12 pm , when they arrived in an area called Filiklikit, before Abay Desert, the driver lost control of the Bus due to Brake problem.
በዚህ ወቅት ከተሳፋሪዎች መካከል፣ ለመኪና ቅርብ የሆነና ጥሩ ልምድ ያለው መካኒክ አቶ አንዳርጋቸው ቢሆነኝ ነበረበት። አቶ አንዳርጋቸው ወደ ባህር ዳር የሚጓዘውም ፣ እዚያ ተበላሽቶ የቆመ መኪናን አስነስቶ እንዲያመጣለት ጓደኛው ለምኖት ሥራውን ትቶ ቅር እያለው እንደሄደም ባለቤቱ ተናግረዋል። One of the Passengers was Ato Andargatchew Bihonegn. Ato Andargatchew is a driver himself and has a good knowledge of Cars. Seeing the bus driver is unable to control the Bus, he jump into the drivers place and tried to Control, and eventually to stop it somewhere safe, by using the steering wheel, while the driver is still sitting with his belt on.
እናም አቶ አንዳርጋቸው የሾፌሩን መጨነቅና አውቶቡሱን መቆጣጠር እንዳቃተው ሲረዳ፣ ዘልሎ በመጠጋት የሾፌሩን ቦታ ይወስዳል። ሾፌሩ እዚያው ቀበቶውን አስሮ እንደተቀመጠ፣ ፍሬኑ እምቢ ያለውን መኪና አቶ አንዳርጋቸው እንደቆመ መሪውን ብቻ በመያዝ ፣ በከፍተኛ ትግል ለማቆም መታገል ይጀምራል፣ እንደምንም ገደል አካባቢ ከመውደቅ አትርፎትም፣ ከአንድ ቋጥኝ ጋር ተላትሞ እንዲቆም ለማድረግ ሲሞክር ከግጭቱ ሃይል የተነሳ ሾፌሩ እንደተቀመጠ፣ አቶ አንዳርጋቸው ግን በመስኮቱ ተወርውሮ በመውደቅ ህይወቱ አልፏል። የሚገርመው ነገር ከሱ ሌላ አንዲት ሴት ብቻ ህይወቷ ሲያልፍ 58 ቱ ተሳፋሪዎች ግን መትረፍ ችለዋል። የተረፉት ሲናገሩ ፣ በሱ ጥረት ባይሆን ኖሮ ማንም አይተርፍም ነበር። Ato Andargatchew did his best to minimize the danger, he avoided real bad areas and tried to stop the Bus by driving it to the thick Bush. When the Bus slams the Bush and stops, the force throws Ato Andargachew through the window and he died instantly. Another female another passenger also died. But the rest of the passengers, including the Driver survived and they said they believe he gave his life for them. If it was not for Ato Andargatchew, all of them might be dead.
አቶ አንዳርጋቸው ቢሆነኝ የሶስት ልጆች አባት ነበር። ጃንዋሪ 30 ቀን አዲስ አበባ ቤተል ጊዮርጊስ የቀብሩ ሥነ ስርዓት ተፈጽሟል። ብዙም ያልተወራለት የአቶ አንዳርጋቸውን ነፍስ ይማር። Ato Andargatchew is a father of 3 and his body laid to rest at Bethel Giorgis, Addis Abeba on Jan. 30. R.I.P
Source: Admas https://www.facebook.com/dinqmagazine?fref=nf
Receive Ethiopian News and Videos by email. Sign up for Email alerts ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን፣ ጠቃሚ ምክሮችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።