በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለ16 ተከታታይ ቀናት በጨለማ ክፍል መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ፡፡ ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ (የፓርቲው የጎንደር አደራጅ አቶ አግባው ሰጠኝ)፣ የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች ‹‹መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ›› እያሉ እንደሚደበድቧቸውና በጨለማ […]

ከCNN እስከ FOX የሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ትላልቅ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሰሞኑን እየተቀባበሉ ያራገቡት አዲሱ የአሸባብ ዛቻ-ሚኒሶታን ናይሮቢ-ሞል ኦፍ አሜሪካን-ዌስት ጌት ያደርጋቸዋል የሚል ሥጋት አሳዳሯል።የሥልታዊ እና የዓለም አቀፍ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ ሪቻርድ ዶዉኔ ግን ዛቻዉ አያሰጋቸዉም

ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ አመት የሜድትራኒያን ባህርን በጀልባ ለማቋረጥ ከሞከሩ 218,000 ሰዎች መካከል 3,500 መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታውቋል። በዚህ በተመሳሳይ መንገድ ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር በአሳሳቢ ደረጃ በመጨመር ላይ ነው።

የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አሳወቁ:: ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ ባለመስራቱና የገዢውን ፓርቲ ዓላማና ፍላጎት የሚያስፈጽም ተቋም ሆኖ በምርጫ መወዳደር ለተቋሙ ኢ-ፍትሃዊ ተግባር እውቅና መስጠት ነው ያሉት በአቶ አበባው መሐሪ የሚመራው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ስብስብ የህዝብ ግኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋሁን አለምነው እራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን አስታወቁ፡፡ መኢአድ እንደ ፓርቲ በምርጫው የሚሳተፍ […]


click here for pdf

የዚህች ሀገር ባለቤቶች ሁላችንም ካልሆንን በቀር በተናጠል ማንም ባለ ግዛት ሊሆን አይችልም፡፡ ሉሲ አማራ ትሁን ኦሮሞ፣ አፋር ትሁን ሶማሌ፣ ጉሙዝ ትሆን ትግሬ፣ ወላይታ ትሁን ጋሞ የሚያውቅ የለም፡፡ በአኩስምና አካባቢው በተገኙ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ነገሥታቱ የሚገዙትን ሀገር ሕዝቦች ስም ይዘረዝራሉ፡፡ እጅግ የሚገርመው ግን ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካና የግዛት ይገባኛል ጥያቄ የምንሻኮተው ብዙዎቹ ጎሳዎች/ነገዶች ስማችን የለም፡፡ ሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ከተለያየ ቦታ መጥተን የሠፈርንበት ላይ ረግተን ነው ዛሬ የምንገኘው፡፡ የሕዝብ የሥፍራ ንቅናቄ የታሪኳ አንዱ መገለጫ በሆነቺው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ሌላውን ሀገርህ አይደለም፣ ክልልህ አይደለም፣ መሬትህ አይደለም እንደማለት ያለ ታሪካዊ ኃጢአት የለም፡፡ ትንሽ በታሪክ ወደኋላ ስንጓዝ ዛሬ ክልልና መንደር በመሠረትንበት ቦታ ሌሎች ሲኖሩበት እናገኛለን፡፡ አሁን የያዝነው ቦታ ከምእተ ዓመታት በፊት የሁላችንም አልነበረም፡፡ ሁሉም ሠፋሪ ነው፡፡ ነባር መሬቱ ብቻ ነው፡፡  
ኢትዮጵያ የምታዋጣን የሁላችን እንድትሆን አድርገን ከሠራናት ነው፡፡ እንደ አጥር ሠሪ እንስሳት(territorial animals)  ከዚህ በመለስ ማንም አይገባብኝም፡፡ እኔን ያልመሰለውን በዚህ አካባቢ ላየው አልፈልግም የሚለው ሂደት መጨረሻው መበጣጠስ ነው፡፡ የልዩነትን ያህል ተመሳሳይነት ሰፊ አይደለም፡፡ ተመሳሳይነት እጅግ ጠባብ ነው፡፡ አንድ ነኝ ብሎ በሚያስብ ‹ብሔርም ሆነ ብሔረሰብ› ውስጥ አያሌ ልዩነቶች አሉ፡፡ የጎሳ፣ የቤተሰብ፣ የአካባቢ፣ የእምነት፣ የፍላጎት፣ የርእዮተ ዓለም፣ የጾታ፣ የሀብት ደረጃ፣ የሥልጣን፣ ምኑ ቅጡ፡፡ ሁሉም ተመሳሳዩን ፍለጋ ከሄደ መጨረሻው ግለሰብ ነው፡፡ በሰውነት ክፍላችን እንኳን ተመሳሳያቸውን ከሚያገኙት ይልቅ የማያገኙት ይበልጣሉ፡፡ ሰው እንኳን በግለ ሰብእነት ሕልው የሆነው ልዩነትን በአንድ ኑባሬ ውስጥ በማስተናገድ ችሎታ ነው፡፡ አንድን አካባቢ ‹በተመሳሳይነት ሚዛን› አንድነቱን ጠብቆ ማቆየት አይቻልም፡፡ 

ያማ ቢሆን ኖሮ ሶማልያን የመሰለ ጠንካራና የማይናወጥ መንግሥት አይኖርም ነበር፡፡በእምነትና በቋንቋ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ይሄ ተመሳሳይነታቸው ግን አንድነታቸውን ሊጠብቅላቸው አልቻለም፡፡ ትኩረታቸው ‹ተመሳሳዩን ብቻ ፍለጋ› በሚለው ላይ ስለነበር ወደ ነገድ፣ ወደ ጎሳ፣ ወደ ጎጥ፣ ወደ ቤተሰብ እየወረዱ ነው በጦርነት ሲታመሱ የኖሩት፡፡ ለሶማልያ ችግር መፍትሔው ተመሳሳይን መፈለግ አይደለም ልዩነትን ለማስተናገድ መቻል ነው፡፡ ተመሳሳይነት ጠባብ ነውና፡፡ ጠባብነት ከሚመነጭባቸው ምንጮች አንዱም ‹ተመሳሳይን ብቻ ፍለጋ› ነው፡፡
የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬ በሚታወቅበት ቦታ ላይ ከተገደመ ከ700 ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ በዚያ አካባቢ አያሌ መንግሥታትና ሕዝቦች ተፈራርቀዋል፡፡ ገዳሙ ግን መከራ ሲገጥመው እየቀዘቀዘ፣ መከራውን አሸንፎ ደግሞ እንደ ፍግ እሳት እንደገና እየጋመ ከእኛ ዘመን ደርሷል፡፡ ወደዚያ ገዳም የሚገቡ መነኮሳት ሰማያዊቷን ሀገር የሚናፍቁ፣ ጾምና ጸሎትን ገንዘባቸው ያደረጉ፣ የጻድቁን ቃል ኪዳን የሚጠብቁ ናቸው፡፡ የመነኩሴ ሀገር የለውም፡፡ መነኮሳት እንኳን ከእናትና አባታቸው በተወለዱበት ሀገር ቀርቶ ስማቸውና ታሪካቸው በማይታወቅበት ሀገርም ‹ሀገርህ የት ነው?› አይባሉም፡፡ 
ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ግብጽ ውስጥ ኖረዋል፣ ሊባኖስ ውስጥ ኖረዋል፣ ሶርያ ውስጥ ኖረዋል፤ ግሪክ ውስጥ ኖረዋል፣ ሮም ውስጥ ኖረዋል፡፡ አርመን ውስጥ ኖረዋል፡፡ ‹ሙሳ አል ሐበሽ› ሶርያ ውስጥ የታወቀ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ነው፡፡ የሶርያ ድርሳናት እንደሚነግሩን ሙሳ (ሙሴ) የዐፄ ገብረ መስቀል ልጅ ነው፡፡ ዛሬ ከኢትዮጵያ በላይ ሀገሩ ሶርያ ናት፡፡ በቅርብ ዓመታት የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ገዳም በሊባኖስ ውስጥ በቁፋሮ ተገኝቷል፡፡ ቫቲካን ውስጥ የኢትዮጵያውያን መነኮሳት ማረፊያ ለታሪክ ቆሞ ይታያል፡፡ አርመን ውስጥ ኤቺሚዚን የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ገዳም ዛሬም አለ፡፡ 
እንዲያውም ዛሬ የዝቋላ መነኮሳት እንደገጠማቸው ያለ ‹ሀገርህ አይደለም› የሚል ሰውነት ያልገባው ፈተና ሲገጥማቸው ራሱ ፈጣሪ ነበር ይገሥጽላቸው የነበረው፡፡ በተአምረ ማርያም ላይ የተጻፈውና ኢየሩሳሌም በጦርነት ምክንያት በተዘጋች ጊዜ በ13ኛው መክዘ አካባቢ ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዘው ኢትዮጵያዊ ታሪክ ለዚህ ማሳያ ሆኖ ይኖራል፡፡ ይህ በኢየሩሳሌም ተሳላሚዎች ሁሉ የታወቀውና ዛሬም ድረስ በጎልጎታ መግቢያ በር ላይ ምልክቱን ትቶ ያረፈው ታሪክ እንዲህ ነበር የተፈጸመው፡፡
ከዛሬ 700 ዓመታት በፊት አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛል፡፡ ከአፍሪካ ምድር የሄደ ብቸኛ ሰው ነበር፡፡ የትንሣኤ በዓል ሲከበር የትንሣኤውን መብራት ከመቃብሩ የሚያወጡት ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ያን ጊዜ ግን ብቻውን ስለነበር ማንም ከቁም ነገር አልቆጠረውም፡፡ እንዲያውም  በመልኩ ምክንያት ተንቆ ‹ያለ ሀገርህ ለምን መጣህ፣ ውጣ› ተባለ፡፡ እርሱም ወጥቶ መግቢያው በር ላይ ሲያለቅስ በላዩ ላይ የብርሃን ዓምድ ተተክሎ ታየ፡፡ ተሳላሚው ሁሉ እምነቱንና ታላቅነቱን አደነቀ፡፡ ብርሃኑ የወረደበት ቦታም ተሰንጥቆ እስከ ዛሬ ድረስ ይታያል፡፡ ወደ ጎልጎታ የሚገባም ሁሉ ይሳለመዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በሌሎች ሀገሮች ሄደው በኪደተ እግራቸው የባረኩት ሁሉ ሀገራቸው ሆኖ መኖራቸው ብቻ አይደለም የሚገርመው፡፡ ከመላው ዓለም የመጡ መነኮሳትም በዚህች ሀገር ውስጥ ‹ከየት መጣችሁ? የማንስ ወገን ናችሁ?›› ተብለው ሳይጠየቁ እንደ ሀገሬው ዜጋ ኖረዋል፡፡ አባ መጣዕ(ሊባኖስ)፣ ተሰዓቱ ቅዱሳን፣ አርባ ሐራ፣ አምስቱ የመንዝ ቅዱሳን፣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እጨጌ ዕንባቆም፣ ማኅበረ ጻድቃን፣ እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ መጥተው ኖሩ፡፡ እዚህችም ሀገር ዐረፉ፡፡ ገዳማቸው ገዳማችን፣ ታሪካቸው ታሪካችን ሆነ፡፡ 
ዛሬ ያ ሁሉ ተረስቶ ነው የዝቋላ ገዳም መነኮሳት ዝቋላ ‹ሀገራችሁ አይደለም›› የተባሉት፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያውያን አይደሉምን? እዚህ ቦታኮ ከ700 ዓመታት በላይ ኖረዋል፡፡ እዚህ አካባቢ ከ700 ዓመታት በፊት የነበሩ ዜጎች አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሲመጡ ‹ኦቦ› ብለው ተቀበሏቸው እንጂ ‹ሀገርዎ አይደለም ይውጡ› አላሏቸውም፡፡ ዛሬ በሥልጣን ላይ ካሉትና ገዳሙን በኢሬቻ መተካት ከሚፈልጉት ሰዎች ይልቅ ያኔ የነበሩት ሰዎች ልበ ሰፊዎች፣ አስተዋዮች፣ የሰውነት ክብር የገባቸው፣ የሀገርን ትርጉም የተረዱ፣ ከዘር ይልቅ ለሰውነት ታላቅ ቦታ የሚሰጡ፣ ሰውን በምግባሩ እንጂ በቋንቋውና በቀለሙ፣ በዘሩና በአጥንቱ የማይለኩ ነበሩ፡፡ 
የአንድ ክልል የቱሪዝም ቢሮ አንድን ገዳም ነጥቆ በገዳሙ ሥርዓት የማይፈቀድ ሌላ እምነትን ለመተካት ማነው ሥልጣን የሰጠው? በዚያ ገዳም ክልል ውስጥ ሊከበሩ የሚገባቸው ሃይማኖታዊ በዓላትንስ በምን ቀኖናዊ ሥልጣኑ ነው የሚወስነው? ለምንስ ነው እነዚህን መነኮሳት እየጠራ የሚያስፈራራው? ይኼ ገዳምኮ ዘመናትን ሁሉ ተሻግሮ እዚህ እንዲደርስ ያደረገው በእምነቱ ጽኑ የሆነው የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጅ ነው፡፡ ሕዝቡ እዚያ ገዳም ለጸሎት የተጉ መነኮሳት እንደሚገኙ፣ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቃል ኪዳን ቦታ እንደሆነ የሚያምን ነው፡፡ በየዓመቱ በጥቅምትና በመጋቢት 5 ወደ ቦታው በመሄድ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ከሚያከብረው ሕዝብ አብዛኛው የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጅ ነው፡፡ ታድያ እነዚህ አካላት ይህንን አስተሳሰብ ከየት አመጡት? 
ይኼ ተልዕኮ ሃይማኖታዊ ተልዕኮ አይደለም፡፡ የጠብ ጫሪነት ተልዕኮ ነው፡፡ በሰላም የኖረውን ሕዝብ የማበጣበጥ ተልዕኮ ነው፡፡ መጋቢት 5 ቀን በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓል ‹ኢሬቻን በጠበሉ ቦታ እናከብራለን፣ ሐውልት እናቆማለን› ብሎ በሕዝብ መገናኛ ማወጅ ጠብ ያለሽ በዳቦ እንደማለት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ያጸድቀኛል ብሎ ያሰበው እምነት ሊከተል ይችላል፡፡ ሁለት እምነቶች ግን በአንድ ቤተ መቅደስ ሊመለኩ አይችሉም፡፡ ሁሉም የየራሱን ነው መከተል ያለበት፡፡ ‹ከባልሽ ባሌ ይበልጣልና አልጋሽን ልቀቂለት› የሚለው ብሂል ግን ዛሬ የሚያዋጣ አይመስልም፡፡ የሃያ አንደኛው መክዘ ኢትዮጵያንም በጤና አውሎ አያሳድራትም፡፡ በዝቋላ ገዳም ላይ የተጀመረው ርስትን የመንጠቅ ሥራም በዝቋላ የሚያበቃ አይሆንም፡፡ ‹መንግሥታዊ ሃይማኖት የለም› ከተባለ መንግሥታዊ መዋቅሮች አንድን እምነት ደግፈው ሌላውን እምነት ለመጫን እንዴት ቻሉ? 
ስለዚህም
1.      ቅዱስ ፓትርያርኩ ሁኔታውን በተመለከተ ለሚመለከታቸው ድብዳቤ  መጻፋቸው የሚገባ ቢሆንም ቅዱስ ሲኖዶስ ግን ይህንን ነገር በዕንቁላሉ ለመቅጨት መወሰንና መሥራት ያለበት ጊዜ ዛሬ ነው፡፡ መነኮሳቱና ሀገረ ስብከቱ የጻፏቸው ደብዳቤዎች በገዳሙ ስለደረሰው መከራ ብዙ የሚናገሩት ነገር አለ፡፡ በስብሰባዎች የደረሰባቸው ጫና፣ በየጊዜውም የሚደርስባቸውን እንግልት ገልጠውታል፡፡ ሲኖዶሱ ገዳማትን ከመጠበቅ የሚቀድም ሌላ ኃላፊነት የለውም፡፡  
2.     ምእመናንም ገዳሙን በንቃት መከታተልና በተለይም በመጋቢት 5 ቀን በክብረ በዓሉ በመገኘትና በዓሉን በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት በማክበር ለቅዱሱ ሥፍራ ያለንን ፍቅር፣ ለመነኮሳቱ ያለንን የዓላማ አንድነት፣ ሁላችንንንም ለሚያቅፈው ኢትዮጵያዊነት ያለንንም ክቡር ሥፍራ ማሳየት አለብን

3.     መንግሥትም በጥባጭ ካለ ጥሩ ለመጠጣት አይቻልምና በሚዲያ የተሳተው በሚዲያ፣ በአሠራር የተበላሸውም በአሠራር እንዲታረም ማድረግ ይገባዋል፡፡ 
                  

ነገረ ኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለ16 ተከታታይ ቀናት በጨለማ ክፍል መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ፡፡ ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ…

The post የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በጨለማ ቤት መታሰራቸውን አስታወቁ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ነገረ ኢትዮጵያ ሰማያዊ ፓርቲ በትግራይ ክልል ለክልልና ተወካዮች ምክር ቤቶች ለምርጫ ያቀረባቸው እጩዎች በምርጫ ቦርድ መታገዳቸውን በመቀሌ ከተማ ለክልል ም/ቤት ሰማያዊን ወክለው እጩ ሆነው የቀረቡት አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ለነገረ ኢትዮጵያ…

The post አስገደ ገ/ስላሴን ጨምሮ በትግራይ የሰማያዊ እጩዎች ታገዱ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት…

The post ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ…

The post ሽመልስ ከማል አሜሪካ ጥገኝነት ሊጠይቁ ነው ? – አርአያ ተስፋማሪያም appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የባለስልጣኖች መክዳት የተቃዋሚዎች የትግል ውጤት አንዱ አካል ነው:: በኢትዮጵያ የፍትህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ተባሳ ጥለው ሕዝብን አንገቱን በማስደፋት ለለቅሶ የዳረገው የቀድሞ ዳኛ የዛሬው ባለስልጣን አቶ ሽመልስ ከማል ወደ አሜሪካ በግል ተጉዞ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቅ የሚሉ ጭምጭምታዎች መሰማት ከተጠያቂነት ለመዳን የሚደረግ ሩጫ ,,,, እርግጥ ለትግሉ መረጃ በማሰባሰብ ረገድ ሽመልስ ከማል ሊረዳ ይችል ይሆናል ሆኖም ጎን ለጎን የፍትህ ስርአቱን በማኮላቸት እና በማበላሸት በኮሚኒኬሽን ስራ በሃሰት ሕዝብን ለማዘናጋት በፕሮፓጋንዳ በማጭበርበር ተግባራቸው ከተተያቂነት አይድኑም:: አሜሪካ የምትባል አገር በፈቃዷ የቆሻሾች ማጠራቀሚያ ሆነች?

በእኔ እይታ የባለስልጣኖች መክዳት የተቃዋሚዎች የትግል ውጤት አንዱ አካል ነው::ተቃዋሚዎች የወያኔን አምባገነንነት በገሃድ ማጋለጣቸው ለስር አት መፍረክረክ አስታውጾ አለው::የአቶ ሽመልስ ከማል መክዳት እውነት ሆኖ ከተገኘ ለትግሉ የመረጃ ፍሰውት በጣም ጠቃሚ ነው::እንደ ብስራት አማረ ያሉ ሃገር ቤት የሚመላለሱ የወያኔ ሙቀኞች ወንጀል ሰርተው በወንጀል ታጥበው በአሜሪካ እየኖሩ ነው::ሽመልስ በስርአቱ ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች የሕወሓት ምንጫቸውን ማወቅም አዛዦችንም መለየቱ ለማወቅ አስፈላጊ ሰው ነው::የባለስልጣናት መክዳት የስርአቱን መበስበስ ያመለክታል::ያም ሆነ ያም ዋናው ለትግሉ የሚጠቅሙ መረጃዎችን ማግኘት ነው::ስለዚህ ጉዳዩን በሰከነ መልኩ ማየት ነው:
Image

Image
በአዲስ አበባ ትላንት ለሊቱን በተለያዩ አካባቢዎች ሙስሊሞችን የማሰር ዘመቻውን በመቃወም በራሪ ወረቀቶች ተበትነው እና ተለጥፈው ማደራቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡
ወረቀቶቹ በመንገድ ጋር ግድግዳዎች ላይ፣ በመንገድ ምልክቶች ላይ፣ በመብራት ፖሎች ላይ የተለጠፉ ሲሆን በየመንገዱም መበተናቸው ታውቋል፡፡

ትላንት ሌሊቱን ፒያሳ አምፒር አካባቢ፣ በሜክሲኮ ቄራ መንገድ ላይ፣ በጦር ሃይሎች፣በቦሌ ፒኮክ እና ወሎ ሰፈር፣ በመገናኛ፣ በመካኒሳ፣በቤተል እና በሌሎች ቦታዎች ላይ ወረቀት ተበትነው ማደራቸው ታውቋል፡፡ከተበተኑት እና ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል እስራት ትግላችንን አያስቆመውም፣መስዋትነት የኢስላም መንገድ ነው፣ሺ ሰው ቢታሰር ሺ ሰው ይተካል፣ ለኢስላም መታሰር ክብር ነው፣ ትግላችን ከምረጫው ቡሃላም ይቀጥላል፣ ድምፃችን ይሰማ፣ትግላችን ይቀጥላል የሚሉና ሌሎች በርካታ መልዕክቶችን የያዙ ወረቀቶች በመተናቸው ተገልፆል፡፡

መንግስት በአዲስ አበባ ሙስሊሞች የማሰር ዘመቻውን አጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ህዝበ ሙስሊሙ እስራት መፍትሄ እንደማይሆን በተግባር ያረጋገጠ መልዕክት በትላንትናው ለሊት አስተላልፏል::

ከ2006 እስከ 2009 ዓ.ም የሕዝብ ቁጥር ትንበያዎቹ በክልልና ወረዳዎች ደረጃ በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ድርጅት የተዘጋጀውን (Population projection of Ethiopia for all Regions at Werreda Level from 2014-2017) በጥልቀት ሲመረመር በተለይ የዓማራውን…

The post አማራውና “የብሔራዊ” ሕዝብ ቆጠራውና ትንበያ ትርኢት – ለምን የአዲስ አበባ ሕዝብ ቁጥር ተቀነሰ? appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ…

The post ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብ ውስጥ የነበረው ሽመልስ ከማል አሜሪካ ገባአርአያ ተስፋማሪያም – appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ቁም ነገር መፅሄት 

ሰሞኑን ቴሌን አልታዘባችኋትም ? ‹‹ የምትታለበው ላም›› ቀንዷን እያለሳለሰች ይመስላል፡፡ እያንቆለጳጰሰችን ነው፡፡ ‹‹ወዳጆቼ›› በሚል የእንግሊዘኛ ቃል ታጅባ ብቅ እያለች ነው፡፡

ለእኛ ለደንበኞቿ ያላትን ክብር ለመግለጽ ደፋ ቀና እያለች ነው፡፡

ይህ…

ትላንትና ማታ ለአዋሳ ከተማ ነዋሪዋች ከባድ ቀን ነበረ። ከባድ ብቻ  ሳይሆን አስደንጋጥም ነበረ። በአዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ  ተብሎ የሚጠራው ቦታ የገበያ ማእከሉ ከፍተኛ ንብረት እና በሰው ህይወት ጉዳት ያስከተለ የእሳት…

The post አቃጠሉት አሉ!!! -ከ-ከተማ ዋቅጅራ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በመጭው ግንቦት የሚካሄደው ኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ፤ የመራጮች ምዝገባ ትናንት ተጠናቅቋል። የተፎካካሪ ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል። በዚህ ምርጫ ላይ ከሚሣተፉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ዕጩዎች መካከል የሰማያዊ ፓርቲ…

The post የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ከምርጫው ፉክክር እንዴት ተሠረዙ? “ዕጣ አልወጣላቸውም!” appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በግንቦት ወር በሚካሄደው 5ኛ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰማያዊ ፓርቲ ለማወዳደር ያዘጋጃቸው አንዳንድ ዕጩዎች ዕጣ ስላልደረሳችው በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ፓርቲው ገለፀ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በዌብ ሳይቱ እና በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው ዘገባ ስሞታውን እንደሚከተለው አሰምቷል፡፡ ——— አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡ ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ […]

Highlights: * “አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ሕዝብ የሚሉ ሁሉ ህወሓትን ይጠሉታል።” * “ከአሜሪካንና ከእሥራኤል ጋር ያጣላን ፕሮግራማችን ነው።” * “ተወልደ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር፤ ስዬም የመከላከያ ሚኒስትር እያሉ ኤርትራ ነፃነቷን ስታገኝ የአሰብ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ ነው። ወንበር ፍለጋ ነው እንጂ የኤርትራ ጉዳይ ሰበብ ሊሆን አይችልም።” * “ህወሓት…… ለስድስት ወር ያህል ዝብርቅርቅ ያለ ፕሮግራም ተቀምጦ ነበር። ኢትዮጵያዊነትም አለ። ትግራይነትም አለ። ይሄ ጉዳይ በስድስት ወር ውስጥ እንዲጠራ ተደረገ።” (ጌትነት ምህረቴ) የመምህርነት ሙያቸውን ትተው ነበር በ1967 ዓ.ም ወደ ትግል የተቀላቀሉት። ከህወሓት ነባር ታጋዮች መካከል አንዱ ናቸው፤ አቦይ ስብሃት ነጋ። ህወሓት የተመሠረተበትን 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዝግጅት ክፍላችን በህወሓት አመሠራረት፣ ዓላማና የትግል አግባብ ዙሪያ ከአቦይ ስብሃት ነጋ ጋር ያደረግነውን ቃለ- ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል ይዘን ቀርበናል። አዲስ ዘመን፡- የንጉሡ ሥርዓት ተገርስሶ ወታደራዊ ሥርዓት ሲመጣ የነበረው የፖለቲካ አሰላለፍ ምን ይመስላል? አቦይ ስብሃት፡- የአፄ ኃይለሥላሴን መንግሥት የጣለው ሕዝቡ ነው። የጣለው ደግሞ መውደቅ ስለነበረበት ነው። ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታው የከፋ ነበር። በሌላው ሀገር ኢንዱስትሪው ማቆጥቆጥ ጀምሯል። የአፄው ሥርዓት በጣም ያከረረ ፊውዳል ስለነበር በሀገሪቷ ልማት የሚባል ነገር አልነበረም። ትምህርትም ቢሆን እንደ ጠበል የሚንጠባጠብ በጣም የተወሰነ እንጂ የሰፋ አልነበረም። ሕክምናም እንደዚሁ። ሀገሪቷ ለማንኛውም አደጋ የተጋለጠች ነበረች። ሕዝቡ በረሃብ እየሞተ «ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ናት» ይባል ነበር። ሕዝቡ ኑሮው አስከፊ ሆኖ ሳለ በወቅቱ የሚነገረው ግን ኢትዮጵያ ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ያደገች ናት […]

ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምንነት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ በየዓመቱ የአለም አቀፍ የሴቶችን ወር ምክንያት በማድረግ በመጋቢት ወር ላይ ጉባኤ በማዘጋጀት ሴቶችን በሚመለከቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን እንዲያቀርቡና፣ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲጠቁሙ በማድረግ ማህበረሰባችንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሴቶች በማህበራዊ፣ በኤኮኖሚና በፖለቲካ የሚደርስባቸውን […]

(ምህረት ሞገስ) በመጪው ግንቦት 2007 ዓ.ም በሚካሄደው አምስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ብቻ 25 የፖለቲካ ፓርቲዎች 328 ዕጩ ተወዳዳሪዎችን አስመዝግበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)፣ መላው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት)፣ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አትፓ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ለአዲስ አበባ የምርጫ ክልል ለተዘጋጁ 23 ወንበሮች እያንዳንዳቸው 23 ዕጩዎችን አቅርበዋል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ሃምሳ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከስድስት ሺ በላይ ዕጩዎችን አስመዝግበዋል፡፡ ይሀ ሁኔታ ካለፉት ምርጫዎች አንጻር ሲታይ እንግዳ ነገር ነው። በተሻሻለው የምርጫ ህግ መሰረት በአንድ የምርጫ ክልል ውስጥ መወዳደር የሚችሉት ዕጩዎች ቁጥር 12 ብቻ ናቸው። በተጨባጭ ግን በአሁኑ ወቅት በአንድ የምርጫ ክልል እስከ 19 የሚደርሱ ዕጩዎች መመዝገባቸውን የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ይህ እውነታ ከምርጫ ህጉ አንጻር እንዴት ይታያል? መፍትሄውስ ምን ይሆን? የተመዘገቡት ሁሉ በምርጫው ይወዳደራሉ? ወይንስ ሌላ አማራጭ ይኖራል? በማለት በምርጫ ቦርድ የአገልግሎቶችና ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ዋና ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላን አነጋግረን ቀጣዩን መረጃ ይዘን ቀርበናል፡፡ አዲስ ዘመን፡- ዘንድሮ በሚካሄደው በአምስተኛው አገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ምዝገባ ላይ የተለየ ነገር መከሰቱ ተሰምቷል። ጉዳዩን ቢያስረዱኝ? አቶ ወንድሙ፡- በዘንድሮው ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ማስመዝገብ ላይ የተከሰተውና ለየት ያለው ነግር በምርጫ ክልሎች ዘንድ የዕጩዎች ቁጥር መብዛቱ ነው፡፡ በ1999 ተሻሽሎ በወጣው የምርጫ ሕግ […]

እንደምታውቁት የኢቲዮጰያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት የአድማጭ ተመልካቹን ፍላጎት ለማርካት ዘወትር የተለያዩ ድራማዎችንና አዝናኝ ፕሮግራሞችን እያቀረበ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ከሠሞኑም የዳና ድራማ በቴሌቪዥን ጣቢያችን እንዳይተላለፍ መደረጉን ተከትሎ (በሜሮን ጌትነት የተነሣ ነው)…

The post ዳና ድራማ በመታገዱ ለተከፋችሁ የድራማ አፍቃሪዎች በሙሉ -ከኢቲቪ የተላለፈ መልዕክት appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

(አዲስ – ከድሬዳዋ) ድሮ ድሮ የአዲስአበባ ዙሪያ ገበሬዎች ራሳቸው መሬታቸውን እየሸጡ ነበር ከተማ የሚስፋፋው፡፡ ከ15 አመት ወዲህ ደግሞ መንግስት ካሳ እየከፈለ መሬታቸውን በሊዝ ለባለሀብት(ቤተሰሪ) ይሰጥ ነበር፡፡ በመጀመሪያዎቹ አመታት ታዲያ ለመሬቱ የሚከፈለው ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ስለነበር የብዙዎችን ህይወት ያበላሸ ነበር፡፡ በ1990ዎቹ አጋማሽ ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ እዚህ ግበ የማይባል ካሳ ተሰትቶት የንግድ ተቋሙን የተነጠቀ ሰው ራሱን እንዳጠፋ መስማቴን አስታውሳለሁ፡፡ ቆይቶ የካሳው መጠንም በሽያጭ የሚገኘውን ያህል ባይሆንም መመሪያ ተዘጋጅቶለት የተሸለ መልክ እየያዘ እንደነበርም አስታውሳለሁ፡፡ እንዲያውም ለልማት የሚፈለግ ቦታ ላይ ተነሺ ሰዎች አስቀድሞ ከ2 አመት በፊት ሁሉ እየተነገራቸው ቅድመ ዝግጅት ያደርጉ እንደነበረና በዚህ መሀል የመሬት ካሳ የተቀበሉ ገበሬዎች መሬቱን በርካሽ ዋጋ አትርፎ መሸጥ ለሚፈልግ የከተማ ስግብግብ ሁለተኛ ዙር ሸጠውለት በፋራ ሙድ ጉድ እንዳደረጉት ሁሉ ሰምቻለሁ፡፡ አሁን ባለፈው አመት የአዲስአበባና አጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች የተቀናጀ እቅድ ሲወጣ የኦሮሚያ ወረዳዎችን ወደአዲስአበባ የሚጠቀልል ነው በሚል ተቃውሞ ሲሰማ ነበር፡፡ መንግስት ደግሞ አዲስአበባና አጎራባች ወረዳዎች በመሰረተልማት፣ በተፋሰስ፣ እና በፕላን የተቀናጁ እንዲሆኑ እንጂ አንዱ ሌላውን እንዲውጥ የታሰበ ነገር የለም ነው የሚለው፡፡ በርግጥም ይህንን የሚያስተባብል ማስረጃ እስከዛሬ አላጋጠመኝም ፡፡ ማንም ተራ ሰው መገመት እንደሚችለው የአዲስአበባ ፕላን ላይ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ቢኖር የዚያ አጎራባች የሆነ የኦሮሚያ ወረዳ በፕላኑ እዚያ አካባቢ የመኖሪያ ሰፈር ሳይሆን የቆሻሻ ማስወገጃ ቢያቅድ ተጠቃሚ ይሆናል፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ አጎራባች ወረዳዎቹ ከአዲስአበባ ጋር የተናበበ እቅድ ካላቸው ብቻ ነው፡፡ በግሌ […]

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የምትታተመዋ ዘመን መፅሄት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስን እንግዳ አድርጋ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ይዛ ወጥታለች። ከእነዚህ ነባርና አንጋፋ ታጋዮች መካከልም ጄኔራል ሳሞራ ለመጽሄትዋ ከሰጡት መረጃ የተወሰኑትን በመምረጥ እንዲህ አቅርበነዋል። ዘመን፡- እናመሰግናለን ጄኔራል ሳሞራ እንደሚታወቀው የህወሀት 40ኛ ዓመት መከበር ጀምሯል። እርስዎ ደግሞ በትግሉ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነዎትና እንደ ግለሰብ ትግሉን እንዴት ያስታውሱታል፤ ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት? ጀኔራል ሳሞራ፡- አርባ ዓመት ረጅም ጊዜ ነው። የትግሉ ሂደትም አንድ ዓይነት አልነበረም። የመጀመሪያዎቹ አስራ ሰባት ዓመታት ጨቋኙን ፋሽስት የደርግ ስርዓት ለማስወገድ የተደረገ የትግል ጊዜ ነበር። ይሔ ትግል ደግሞ በርካታ መስዋዕትነት የተከፈለበት ነው። ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት የትግል ሂደት ነው። ደርግ ከተሸነፈ በኋላ ደግሞ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ትግሉ ነው የቀጠለው። እንዳልኩት የመጀመሪያው አስራ ሰባት ዓመት የትግል ዓላማ ጨቋኙን ሥርዓት የማስወገድ ቢሆንም የመጨረሻው ዓላማ ግን ዴሞክራሲን፣ ልማትንና ፍትህን ማረጋገጥ ነበር። እና ትግሉ የመላው ኢትዮጵያ ህዝቦችን ድጋፍ አግኝቶ በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው። በትግሉ ውስጥ ትልቁና ወሳኙ ነገር የደርግን ኃይል መደምሰስ ቢሆንም ከዚያ በመቀጠል ለግጭት፣ ለድህነትና ለሰላም እጦት ይዳርገን የነበረው ሁኔታ በ1987 ዓ.ም በፀደቀው ህገ መንግሥታችን መፍትሔ አግኝቷል። በዚህም ያ የተደመሰሰው ሥርዓት ዳግመኛ እንደማይመለስ እርግጠኛ የተሆነበት ሁኔታ ነበር የነበረው፡፡ ለአሁኑ ልማትና ዴሞክራሲያችን መሰረት የሆነውም ይሄው ህገ መንግስታችን ነውና በትግሉ የደርግ ሥርዓትን መደምሰስ አንዱ ጉዳይ ሆኖ ሁለተኛው ደግሞ ህገ መንግስቱ መጽደቁ ነው፡፡ ከዚህ […]

የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል። የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 […]

የኰሚኒኬሽን ምክትል ሃላፊ የሆነው ሽመልስ ከማል ባለፈው ሳምንት አሜሪካ መግባቱን ምንጮች አስታወቁ። ከሬድዋን ሁሴን ጋር የከረረ ፀብና አለመግባባት ውስጥ የገባው ሽመልስ ለረጅም ሳምንት ከስራ ገበታው ርቆ መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮቹ አሜሪካ የመጣው በግሉ እንደሆነ አስታውቀዋል። በዲሲ ቆይታ ካደረገ በኋላ ኒውዮርክ ወደሚገኘው ወንድሙ ዘንድ ያቀናው ሽመልስ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ አሜሪካ ለመቅረት ሃሳብ እንዳለውና እንደሚፈልግ ምንጮቹ አጋልጠዋል። ሽመልስ […]

ምርጫ አገራችን ወደ ጦርነት እንዳትገባ፣ ዜጎች ያሏቸው ልዩነቶችን ሕዝብ ፊት በማቅረብ በሰላም እንዲፈቱ ለማድረግ የታሰበ ነበር። ምርጫ ባይኖር አንዱ ድርጅት ሌላውን በኃይል ለማሸነፍ ይሞክራል። አመጽና ጦርነት ይኖራል። ያ እንዳይኖር ነበር የምርጫ አስፈላጊነት። ሆኖም ኢትዮጵያ ዉስጥ ግን፣ በምርጫ ሰበብ የዜጎች ደም እየፈሰሰ ነው። በሕዝቡ ላይ ስቃይና መከራ እየጨመረ ነው። ምርጫ በመጣ ቁጥር ሕወሃቶች በደም ይሰክራሉ። ሁሉም […]

በደጋ ዳሞት ወረዳ ሰማያዊን ወክሎ በዕጩነት የቀረበው አቶ ግርማ ቢተው በተመዘገበበት የምርጫ ወረዳ በምርጫ አስፈጻሚነት እንዲሰራ የተመደበው አዱኛ አለማየሁ የተባለ ግሰለሰብ ከዕጩነት እንዲወጣ አማላጅ እንደላከበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ‹‹በምርጫ አስፈጻሚነት የሚሰራው ሰው 97 ላይ የፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ነበር፡፡ ከቅጽ 3 ወደ ቅጽ 4 ለመዘዋወር እፈልግሃለሁ ካለኝ በኋላ ሲያመላልሰኝ ሰነበተ፡፡ አማላጅ ከላከብኝ በኋላ ከዕጩነት እንደማልወጣ በመግለጼ […]

ዓረና-መድረክ ወክልለው ለፌደራል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ሁነው የቀረቡት ኣቶ ወልደገብርኤል ሃይሉ ታሰሩ። የኣፅቢ ወንበርታ ዓቃቤ ህግ ያቀረበላቸው ክስ ታስሮው በመኪና ተጭኖው ወደ ፖሊስ ጣብያ ሲወሰዱ ፖሊሶቹን ደብድበሃል፣ ሰድበሃል የሚል ነው። የክሱ መነሻ በነሃሴ 5 / 12/ 2006 ዓ/ም ማታ 3 ሰዓት ኣከባቢ 9 ፖሊሶችና የወረዳው የፀጥታሃላፊዎች ከቤት ኣስወጥተው እየደበደቡ በመኪና ጭነው ወደ ኣፅቢ ከተማ […]

“ሕዝብ በመንግሥት ላይ አመኔታ ኖሮት የየዕለት ሕይወቱን መምራት ይኖርበታል፡፡ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ የተመሠረተ የሕዝብ ፍላጎት ዘለቄታዊ የሆነ እርካታ እንዲፈጠርለት ሲፈለግ ደግሞ፣ ዋና ዋና የሚባሉ ጉዳዮች መፈተሽ አለባቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንገብጋቢ ተብለው ሊጠቀሱና መፍትሔ ሊፈለግላቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች በአራት ይጠቃለላሉ፡፡” ሲል ሪፖርተር “ሕዝብ የመንግሥትን አመኔታ የሚፈልግባቸው አራት ነጥቦች” ባቀረበው ዘገባ ይዘረዝራቸዋል። ከአራቱ ጉዳዮች አንዱ […]

የካቲት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ  በአለም ባንክ ድጋፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ፣ የባንኩን ፖሊሲ የሚጻረሩ ሆነው መገኘታቸውን የአለም ባንክ የውስጥ የምርመራ ክፍል ማሳወቁን ገልጿል። ይሁን እንጅ የባንኩ ማኔጅመንት በባንኩ የውስጥ የምርመራ ቡድን የቀረበውን ሪፖርት የሚቃረንና ባንኩን ከተጠያቂነት የሚያድን ሌላ ሪፖርት አቅርቧል። …

የካቲት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሕዝበ ሙስሊሙ ፍላጎት ውጪ በ2005 ዓ.ም የተመረጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) አመራሮች የመንግስትን ፍላጎት ማርካት  ባለመቻላቸውና በአመራሮቹ ላይ እምነት በመጥፋቱ በአስቸኩዋይ ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ በማድረግ በምትካቸው ሌሎች ተመርጠዋል። በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ሼህ ኪያር መሐመድ ኢማንን …

ገንዘቤ ዲባባ በአዳራሽ ውስጥ 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች።

እንግሊዛዊ Mo Farah ላለፉት ሰባት ዓመታት በቀነኒሣ በቀለ ተይዞ የቆየውን የሁለት ማየል የቤት ውስጥ ሬኮርድ ሠበረ።

በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ፆታዎች ድል ተቀዳጅተዋል። በዘጠኝ ዓመቱ የቦታው ውድድር ታሪክ ከአንድ ሀገር የመጡ የሁለቱም ፆታዎች አትሌቶች ሲያሸንፉ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

 

 

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባ ብርሃነ የሱስ ፤ ከሁለት ወራት ገደማ በፊት ከሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንስስ ፣ የካርዲናልነት ማዕረግ ማግኘታቸው የሚታወስ ነው።

የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በጥርስ ህክምናው ዘርፍ የተሠማሩ ባለሀብት ሲሆኑ በ2002 ምርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ በፓርላማ ብቸኛ የግል እጩ ሆነዋል፡፡ ዶ/ር አሸብር በፓን አፍሪካ ፓርላማ ውስጥ በም/ፕሬዚዳንትነት እያገለገሉም ይገኛሉ፡፡ በግንቦቱ ምርጫ ዙሪያ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር የሚከተለውን ቆይታ አድርገዋል፡፡ አዲስ አድማስ:- በግንቦቱ ምርጫ በእጩነት ይወዳደራሉ? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- በምርጫው ለመወዳደር ጓደኞቼ ፊርማ አሰባስበውልኝ ለቦርዱ አስገብተናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ተወዳዳሪነቴን የማረጋግጠው የእጩነት ደብተሬን ስወስድ ነው፡፡ ከእኔ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርጌያለሁ፡፡ አዲስ አድማስ:- የት ነው የሚወዳደሩት? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- በከፋ ዞን፣ ቦንጋ ዲንቦ ጓታ ምርጫ ጣቢያ ነው የምወዳደረው፡፡ አዲስ አድማስ:- የግል ተወዳዳሪ የመሆን ጥቅሞችና ፈተናዎች ምንድን ናቸው? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- አብዛኛው ጊዜ ፓርቲዎች ሚዲያ ተጠቅመው ራሳቸውን የማስተዋወቅ እድል አላቸው። ቴሌቪዥን፣ ራዲዮ ይጠቀማሉ፤ ለምርጫው ከመንግስት በጀት ያገኛሉ፡፡ ለግል ተወዳዳሪዎች ግን እነዚህ ሁሉ የሉም፡፡ እኛ የግል ተወዳዳሪዎች በራሳችን ወጪ መቀስቀስ፣ በራሳችን የቅስቀሳ አውታር መጠቀም ስለሚጠበቅብን ብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያለነው፡፡ አንድ ግለሰብ ለመወዳደር ሲፈልግ፣ በዚህ ደረጃ ራሱን ማዘጋጀት አለበት፡፡ አዲስ አድማስ:- ጥቅሞቹስ? ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ:- ራሱ ኢህአዴግን ብትወስድ አባላቱ ከ10 ሚሊዮን አይበልጡም፡፡ ከህዝቡ 70 እና 80 በመቶው የፓርቲ አባል አይደለም ማለት ነው። ስለዚህ ህዝቡ እኛን በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡ ከየትኛውም ፓርቲ ገለልተኛ መሆን ለአስተያየትም ለፍርድም ይጠቅማል፡፡ ብዙ ሰው ወደ ፓርቲ አይጠጋም፤ለዚህም ምክንያቱ ገለልተኛ መሆን ስለሚፈልግ ነው፡፡ የግል ተወዳዳሪ መሆን ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ ግለሰቡ ራሱ በራሱ ነው ወሳኝ የሚሆነው፡፡ […]

የኢትዮጵያውያን ድል እየተደጋገመ ነው። በወንድም በሴትም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ በመሆን በጃፓን የተኪያሄደውን የቶኪዮ ማራቶን ተቆጣጥረውታል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የእግር ኳስ ፍልሚያ ትናንት ሊቨርፑል ሳውዝሐምፕተን ላይ ድል በመቀዳጀት ወደ ዋነኞቹ ተፎካካሪዎች ተርታ ተጠግቷል።

ከጊዜ ወደጊዜ ዕድገት እያሳየ እንደመጣ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ፣ ሁለት አዳዲስ የአይሮፕላን ጭነት (ካርጎ) ማከማቻ ሕንጻዎችን መገንባት መጀመሩ ተገለጠ።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በምስራቅ አፍሪቃ ለአራት ቀናት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀቁ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጀርመናውያን ስለ አፍሪቃ ያላቸው አመለካከት መለወጥ አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

የሕዝቧን መሠረታዊ ፍላጎት አሟልታ በማኖር ከአፍሪቃ አቻ ያልነበራት ሐገር ዛሬ የአሸባሪዎች፤የጎጠኞች፤ የሽፍቶች፤የስደተኛ አስተላላፊዎች፤ የዘራፊዎች መናኸሪያ ሆናለች።ከአራት ዓመት በፊት አንድ መሪ ነበራት።ዛሬ አስራ-ሰባት ሺሕ መሪዎች የሚያዙት አስራ-ሰባት ሺሕ ታጣቂ ቡድናት ይርመሰመሱባታል።

አዲስ አበባ ውስጥ ፣ በአዲስ ከተማ ፤ ወረዳ 5 ፣ መርካቶ አካባቢ ለመወዳደር ተመዝግበው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅኔር ይልቃል ጌትነት፤ በምርጫ ቦርድ ደንብ ከአጩነት መሠረዛቸው ተነገረ።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በምስራቅ አፍሪቃ ለአራት ቀናት ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀቁ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጀርመናውያን ስለ አፍሪቃ ያላቸው አመለካከት መለወጥ አለበት ሲሉ ተናግረዋል።