የአዲስ አበባ – ፊንፊኔ ዙሪያ እቅድን መቃወም ለምን?
(አዲስ – ከድሬዳዋ) ድሮ ድሮ የአዲስአበባ ዙሪያ ገበሬዎች ራሳቸው መሬታቸውን እየሸጡ ነበር ከተማ የሚስፋፋው፡፡ ከ15 አመት ወዲህ ደግሞ መንግስት ካሳ እየከፈለ መሬታቸውን በሊዝ ለባለሀብት(ቤተሰሪ) ይሰጥ ነበር፡፡ በመጀመሪያዎቹ አመታት ታዲያ ለመሬቱ የሚከፈለው ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ስለነበር የብዙዎችን ህይወት ያበላሸ ነበር፡፡ በ1990ዎቹ አጋማሽ ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ እዚህ ግበ የማይባል ካሳ ተሰትቶት የንግድ ተቋሙን የተነጠቀ ሰው ራሱን እንዳጠፋ መስማቴን አስታውሳለሁ፡፡ ቆይቶ የካሳው መጠንም በሽያጭ የሚገኘውን ያህል ባይሆንም መመሪያ ተዘጋጅቶለት የተሸለ መልክ እየያዘ እንደነበርም አስታውሳለሁ፡፡ እንዲያውም ለልማት የሚፈለግ ቦታ ላይ ተነሺ ሰዎች አስቀድሞ ከ2 አመት በፊት ሁሉ እየተነገራቸው ቅድመ ዝግጅት ያደርጉ እንደነበረና በዚህ መሀል የመሬት ካሳ የተቀበሉ ገበሬዎች መሬቱን በርካሽ ዋጋ አትርፎ መሸጥ ለሚፈልግ የከተማ ስግብግብ ሁለተኛ ዙር ሸጠውለት በፋራ ሙድ ጉድ እንዳደረጉት ሁሉ ሰምቻለሁ፡፡ አሁን ባለፈው አመት የአዲስአበባና አጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች የተቀናጀ እቅድ ሲወጣ የኦሮሚያ ወረዳዎችን ወደአዲስአበባ የሚጠቀልል ነው በሚል ተቃውሞ ሲሰማ ነበር፡፡ መንግስት ደግሞ አዲስአበባና አጎራባች ወረዳዎች በመሰረተልማት፣ በተፋሰስ፣ እና በፕላን የተቀናጁ እንዲሆኑ እንጂ አንዱ ሌላውን እንዲውጥ የታሰበ ነገር የለም ነው የሚለው፡፡ በርግጥም ይህንን የሚያስተባብል ማስረጃ እስከዛሬ አላጋጠመኝም ፡፡ ማንም ተራ ሰው መገመት እንደሚችለው የአዲስአበባ ፕላን ላይ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ቢኖር የዚያ አጎራባች የሆነ የኦሮሚያ ወረዳ በፕላኑ እዚያ አካባቢ የመኖሪያ ሰፈር ሳይሆን የቆሻሻ ማስወገጃ ቢያቅድ ተጠቃሚ ይሆናል፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ አጎራባች ወረዳዎቹ ከአዲስአበባ ጋር የተናበበ እቅድ ካላቸው ብቻ ነው፡፡ በግሌ […]