ዳና ድራማ በመታገዱ ለተከፋችሁ የድራማ አፍቃሪዎች በሙሉ -ከኢቲቪ የተላለፈ መልዕክት
እንደምታውቁት የኢቲዮጰያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት የአድማጭ ተመልካቹን ፍላጎት ለማርካት ዘወትር የተለያዩ ድራማዎችንና አዝናኝ ፕሮግራሞችን እያቀረበ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ከሠሞኑም የዳና ድራማ በቴሌቪዥን ጣቢያችን እንዳይተላለፍ መደረጉን ተከትሎ (በሜሮን ጌትነት የተነሣ ነው) አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅሬታ ማሠማታቸው ይታወቃል ሆኖም ድርጅታችን የኢቲዮጰያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት የተመልላቾቹን ፍላጎት ለማሳካት ካለው ልባዊ ፍላጎት የተነሣ የሚከተለውን መልዕክት ያስተላልፋል፡፡
1. እንደሚታወቀው የዳና ድራማ በእግድ ቢቆምም በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ የምንሠራው ድራማ ግን ይቀጥላል
2. ሜሮን ጌትነት ትወና አቁማ ወደአሜሪካ ብትበርም የገዢውን ፓርቲ ተውኔቶች ለመተወን ዘወትር በዜና ሠዓት እየቀረብን መከተወናችንን የምንቀጥል ሲሆን ድራማው እስከመጨረሻው እንደሚቀጥልም ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
በመጨረሻም ምርት እና አገልግሎታችሁን (ውሸታችሁን) በቴሌቪዥን ጣቢያችን ማስተላለፍ የምትፈልጉ አጋሮቻችን ቢሮ ቁጥር 9 (በረከት ስምኦን ለስብሰባ ካልያዘው) መጥታችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የኢቲዮጰያ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ድርጅት
የኢትዮጵያን ባለስልጣናትን ህዳሴ እናበስራለን
#ሁኔአቢሲኒያ
The post ዳና ድራማ በመታገዱ ለተከፋችሁ የድራማ አፍቃሪዎች በሙሉ -ከኢቲቪ የተላለፈ መልዕክት appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.