የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘው ክስ መዝገብ የተከሰሱት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 25/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡ በዛሬው ችሎት የተከሳሾቹ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ‹‹ህዳር 12 ለ 13/2007 ዓ.ም አጥቢያ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የተጠርጣሪዎቹ ንብረት ተወስዶባቸዋል፣ የሰብአዊ ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል፣ ድንገተኛ ፍተሻው ህገ ወጥ […]

እሁድ እለተ ሰንበት ቀን ነበር። አምላካቸዉንና ፈጣሪያቸዉን ሊያመሰግኑ ምእመናን የቤተ ክርስቲያኒቱን አዳራሽ አጣበዉታል። በአዳራሹ የነበረዉ ምእመን ፊቱን ወደ መንበረ ታቦቱ አዙሯል። በመንበረ ታቦቱ በቀኝና በግራ በኩል ነጭ የለበሱ ዲያቆናት ቆመዋል።…

The post ሊቀ ጳጳስ ኦስካር ለፍትህ የቆሙ ጳጳስ – ግርማ ካሳ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የወራሪው  የጣሊያን  ሰራዊት  በጦር  አዛዡ  ፊልድ  ማርሻል  ሮዶልፎ  ግራዚያኒ  አማካኝነት 30  ሺህ  ኢትዮጰያውያንን  በግፍ  የጨፈጨፈበት  78ኛ  ዓመት  ዛሬ  በመላው  ኢትዮጰያውያን  ዘንድ  በመተሳብ  ላይ  ነው። በኢትዮጵያና  ከኢትዮጵያ  ውጭ  የሚኖሩ  ዜጎች ፣ የጣሊያን  ወራሪ  ሃይል  በንጹሃን  ኢትዮጵያውያን ላይ  የፈጸመውን  አስከፊ  ጭፍጨፋ የሚያስታውሱ  ጽሁፎችን  በመልቀቅ  እለቱን  ዘክረውታል።

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤተመንግስት ትንሹ አዳራሽ ውስጥ የተካሄደውን የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ግምገማ የሚቃኘው መረጃ እንደሚያሳየው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ የህወሃት ክንፍ እንዲፈጠር ከመከላከያ ኢታማጆር ሹም ሳሞራ የኑስ ጋር ማሴራቸው በሌሎች የኢህአዴግ አባላት ሂስ ቀርቦባቸዋል። አቶ አባይ ወልዱ የቀረበባቸውን ሂስ በደፈናው ተቀብያለሁ፣ አርማለሁ በማለት መመለሳቸውን ሰነዱ ያስረዳል። አቶ አባይ …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ  የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ የተሰረዙበት መሆኑን የገለጸው ፓርቲው፣ የካቲት 22  ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች የሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ  የነጻነት ትግል አካል ነው ብሎአል። የድርጅቱ ሊ/መንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ  እንደገለጹት ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በህገወጥ መንገድ በታገደው የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ  አመራሮች ላይ  ደህንነቶች ዛቻ፣ማስፈራሪያና ማዋከብ እየፈጸሙ ነው። የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት አቶ አስራት አብርሀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ  ባለፈው እሁድ ማታ መናኛ አለባበስ የለበሱ ሁለት ወጣቶች የተከራዩበት ቤት ድረስ በመሄድ  “እንፈልገሃለን”  እንዳሏቸው በመጥቀስ፤ “በዚህ ሰዓት የምትፈልጉኝ እናንተ ደግሞ …

የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በእንጦጦ ማርያም ሙዚየም የወርቅ መስቀሎች ጠፍተዋል መባሉ በምእመናን ዘንድ  ተቃውሞ አስነስቷል። ለርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ከተለያዩ ምዕመናን በስለትና በስጦታ የተሰጡና እስከ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝኑ ይችላሉ የተባሉ ሁለት የወርቅ መስቀሎችና አንድ የወርቅ ሐብል፣ በቅርስነት ከተቀመጡበት ሙዚየም ውሰጥ መጥፋታቸውን …

አረና ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ከ100 በላይ እጩዎቹ ቢመዘገቡም በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰባቸው ጫና ምክንያት በርካቶች ከውድድር መውጣታቸውን ፓርቲው አመልክቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ሳይቀሩ ካርድ የለም ተብለው እንዲመለሱ መደረጉን የፓርቲው የሕዝብ ግኑኙነት ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

በዚሁ ዓለም ዓቀፍ ትርዒት ላይ ከ100 ሃገራት የመጡ ልዩ ልዩ ድርጅቶች ተሳትፈዋል ። በዚሁ የቤት እቃዎችና የጌጣጌጦችና ቅርጻ ቅርጾች ትርዒቱ ላይ 7 የአፍሪቃ ሃገሮች ቢሳተፉም ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ በትርዒቱ ላይ የተወከሉ ድርጅቶች እንዳልነበሩ

ጽሑፌን በአንድ ገጠመኜ ልጀምር፡፡ በአንድ ወቅት ከጎንደር አገር ገና በአፍላነት ወጣትነት ዘመኗ ወደ ትግል ከገባች ታጋይና ከእናቷ ጋር ለመገናኘትና በአንድ ምሽትም ውይይታቸውን ለማድመጥ ዕድሉ ገጥሞኝ ነበር፡፡ የትግል ዘመኑ በድል ተጠናቆ፣ አገር ተረጋግቶ በነበረበት ሰዓት ልጃቸውን ለመጠየቅና ለሕክምና ከጎንደር የመጡ እኚህ እናት በወታደራዊ ዩኒፎርምና ማዕረግ ተንቆጥቁጣ ከአጠገባቸው ተቀመጠችውን የትናንትናዋን የበረሃ ፋኖ የዛሬዋን ወታደራዊ መኮንን ልጃቸውን በዛች […]

ትላንት መቀሌ ከተማ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪውን ያለፍላጎቱ በማስገደድ እንዲሰለፍ በተሰጠው መመርያ መሰረት ሁሉም የተሰጠውን ችቦ በመያዝ ቀኑን ሁሉ ከትምህርት ገበታቸው ላይ ተስታጉለው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ያለፍላጎታቸው በማስገደድ በሚደረገው…

The post መቀሌ ከተማ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪውን ያለፍላጎቱ እንዲሰለፍ ተገደዋል። appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ኢሳት ዜና ግምገማው የተካሄደው እንደተለመደው ባለስልጧናቱ በየተራ አስቀድመው ችግራቸውን እንዲናገሩ በማድረግና የራሱን ችግር በተናገረው አመራር ላይ ሌሎቹ ያላቸውን ተጨማሪ ትችት እንዲያቀርቡ በማድረግ ነው። በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በተካሄደው በዚህ ግምገማ…

The post የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቤተመንግስት ተገመገሙ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

Image
ትላንት መቀሌ ከተማ በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪውን ያለፍላጎቱ በማስገደድ እንዲሰለፍ በተሰጠው መመርያ መሰረት ሁሉም የተሰጠውን ችቦ በመያዝ ቀኑን ሁሉ ከትምህርት ገበታቸው ላይ ተስታጉለው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ያለፍላጎታቸው በማስገደድ በሚደረገው ሰልፍ ላይ የህ ወ ሀ ትን የምስረታ 40 ኛ ዐመት በዐል በሚል አላማ ተማሪዎቹ የሚተባበሩ እና የሚያከብሩ በማስመሰል ድራማ ሲያሰሩዋቸው ቆይተዋል።
ምርጫው በተቃረበበት በዚህ ወቅት ገዢው ብድን ወያኔ በተለያዩ መንግስታዊና የግል ተቋማት እንዲሁም የእምነት ቤቶች ውስጥ እጁን በማስገባት ያለ ህዝብ ፈቃድ ዜጎችን ማስፈረም እና በግዳጅ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ማድረጉን በይበልጥ አፋፍሞታል። በትላንትናው ውሎ በተለምዶ የተማሪዎቹ የካፌው አሰራር የቁርስ ግዜያችውን የሚያስተናግደው በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 2፡30 ሲሆን ይህን አሰራር በመቀየር እና በማን አለብኝነት ለሊቱ ወደማብቂያው ገደማ 9፡30 ተጅምሮ 10፡30 ድረስ ለቁርስ ያልተገኘ ተማሪ መመገብ ሳይችል እንደሚቀር ለህዳሴ ካፌው ከባለስልጣናቱ በተላለፈው ማስጠንቀቂያ መሰረት በለሊት ቁርሳቸውን እንዲበሉ ተገደዋል።
ይህም ተማሪዋች ወደ ግዳጅ ሰልፉ ማልደው በቶሎ እንዲዘጋጁ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን ሁሉም በዚህ ጥሪ ላይ የመሳተፍ ግዴታው እንደሆነ በማስጠንቀቂያ መልዕክቱ ተላልፏል። ተማሪው ሳይፈልግ እና የራስ ተነሳሽነት በጎደለው መልኩ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ወያኔዎቹ ይህንን የማን አለብኝነት ትዕዛዝ ሲያስተላልፉ ሀገሬውን እንደፈለጉ በጠመንጃ አፈሙዝ ግድ እንደሚሉት ሁሉም ሊይውቀው ይገባል ።
እንዲህ የሚመሳስሉ መረን የለሽ ግፍ እየተፈጽመበት በአይነ ቁራኛ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ህዝብ በረዥም የጭቆና ሰንሰለት ተሸምቅቆ ከወያኔ ፍላጎት ውጪ በሚያደረገው እንቅስቃሴ ታላቅ አፈና እና ግድያ ፊትለፊቱ ተጋርጦበት የተባለውን ብቻ የሚፈጽም ተደርጓል ።
ስለዚህም በግፍ አገዛዙ በአለም ሁሉ የሚታወቀው አምባገነኑ ወያኔ በሃገራችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፋዊ ስርዐት እና ሃብትን ያለአግባብ መዝረፉን፣ ማስገደዱንም ፣ ግድያውንም በቃኝ ጠግቢያለሁ ስልማይል በተባበረ ህዝባዊ አመጽ በቃህ ሊባል ይገባዋል።
Image
Image
Image

ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኞች አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡ ፍ/ቤቱም የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ካደመጠ በኋላ የሚቀጥለውን ቀጠሮ ለመጋቢት 21-23 ሠጥቶ ተበትኗል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር […]

በዘመነ አፄ ልብነድንግል ጦርነት በመጥፋቱ ንጉሱ ጦርነት አውርድ ተብሎ በየቤተክርስቲያኑ ፀሎት እንዲደረግ ትዕዛዝ አውርዶ ነበር እየተባለ በአፈ ታሪከ ይነገርለታል፤ 24 ዓመት የሞላው የህወሀት/ኢህአዴግ ስርዓትም ጦርነት አውርድ፣ መዓት አውርድ እያለ እንደሚገኝ ከደርጊቶቹ ሁሉ መረዳት የሚቻል ነው። አንድነት ፓርቲ በኃይልና በውንብድና እንዲፈርስ ከተደረገ በኋላ ምንም የማደርገው ነገር ስላነበረ፤ ቤቴ ሄጄ ነው ቁጭ ያልኩት፤ ከፌስቡክም ገለል ለማለት ፈሊጌ […]

ኢትዮጵያውያን በታሪክ በተለያዩ ዘመኖች ከውጭ ወራሪዎች ጋር ተፋልመዋል። ሁሉም የውጭ ወራሪዎች ዘለቄታዊ ግባቸው ተመሣሣይ ነበር፦ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛታቸው አድርገው ሕዝቧን በባርነት ቀንበር ሥር መግዛት። በዚህ ረገድ አረቦች ከ፰ኛው (ስምንተኛው) መቶ…

The post ለመሆኑ ለወደፊቱ የየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ሠማዕታትን የሚዘክር ተተኪትውልድ ይኖረን ይሆን? appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

Minilik Salsawi : ሕዝቡ እየተፈረካከሰ የሚገኘውን ወያኔን በጋራ ታግሎ በማስወገድ ነጻነቱን ማረጋገጥ አለበት::ኢትዮጵያውያን ጨለማን ተገን በማድረግ በታጠቁ በሕወሓት የደህንነት መዋቅር የሚመራ የሽብር ተግባራትን አጥብቆ ስለሚፈራ እና በየጊዜው በሕወሓት ደህንነቶች መሪነት የሚወሰዱ እርምጃዎች በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠራቸው በየእስር ቤቱ የሚካሄዱ ሕገወጥ ጸረ ፍትህ ተግባራት እና የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ሙስና እና ዘረፋ የኢትዮጵያውያን የቀን ተቀን አጀንዳ ሆነው መምጣታቸው ገዢው ፓርቲ ሕዝቡን ምን ያህል እንዳሸበረ ይጠቁማል ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጹ::

የደህንነት ባለስልጣናት እና ጭፍሮቻቸው በከፍተኛ ደረጃ በዘረፋ ላይ መሰማራታቸው ታውቋል:እንደውስጥ አዋቂ ምንጮቹ መረጃ ከሆነ ባለስልጣኖቹ እና ጭፍሮቻቸው የተዘፈቁበት የሙስና ተግባር በተጨማሪ ዘረፋን እና ሴት መድፈርን እንዲሁም የቡድን ወንጀሎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል::በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ባለሃብቶችን በማስፈራራት ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ በማሰር እንዲሁም የሙስና ወንጀል ተገኝቶብሃል ይህን ያህል ገንዘብ አምጣ ካላመጣህ እንገድልሃለን እስከማለት ከመድረሳቸውም በተጨማሪ ይህንን ጉዳይ በየዋህነት ፍትህ ያገኘ መስሎት ለፖሊስ የጠቆመ ባለሃብት በማፈን ንብረቱ በማገድ እና በተለያዩ ስልቶች የተጠየቀውን ገንዘብ እንዲሰጥ በማስገደድ ላይ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል::

በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶችን በመከታተል እና ደህንነት ቢሮ ድረስ በመውሰድ በሙስና ከታሰረው ስም እየተጠቀሰ … ከሚባል ባለስልጣን እንዲሁም ተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት አለህ ማስረጃ ተገኝቶብሃል በማለት በፈጠራ ወንጀል ባለሃብቱን በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበረ እና እንዲሁም የአዲስ አበባን ቆነጃጅት ቢሯቸው ድረስ በግብረአበሮቻቸው አፋኝነት እና አስገዳጅነት በመውሰድ ካለፍላጎታቸው አስገድደው በመድፈር ላይ ናቸው ያሉት ምንጮቹ ተራ የደህንነት አባላት ለዚሁ ተልእኮ ተሰማርተው የሚሰሩት ምንም አይነት ወንጀል በቡድን ሲፈጽሙ የሚጠይቃቸው አለመኖሩን የሕዝቡን በደል የከፋ አድርጎታል::ሕዝቡን በማስተባበር እና በመቀስቀስ የተጫነበትን የአምባገነኖች ብትር በጋራ በመታገል አምባገነኖችን እና ጭፍሮቻቸውን ከስልጣን በማስወገድ ነጻነቱን ማረጋገጥ ያለበት ወስኝ ወቅት ላይ መሆኑን ለመናገር እወዳለሁ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

በከፍተኛ የደህንነት ሃይሎች የሚመራ የእስር ዘመቻ በሙስሊሞች ላይ መከፈቱ ተገለፀ
ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን በአዲስ አበባ ለማሰር ታቅዷል፡፡
የቢላል ሬዲዬ ጋዜጠኛ የነበረው ካሊድ ሙሃመድ በደህንነት ሀያሎች ታፍኖ ተወስዷል።
ህውሃት መራሹ ወያኔ አሁንም ንፁሃን ሙስሊሞችን ከየአካባቢው ማደነኑን ቀጥሏል። በዛሬው እለት በብርጭቆ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ይኖር የነበረው ወንድማችን የሆነው እና የቢላል ሬዲዬ ጋዜጠኛ የነበረው ፣ ከአመት በፊት በረመዳን ወር መግቢያ ላይ በ3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛ ካሊድ ሙሃመድ በዛሬው እለት የፈጅር ሰላቱን ሰግዶ ወደ ቤቱ በሚመለስበት ወቅት በደህንነት ሀያሎች ታፍኖ እየተደበደበ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዷል። ከቤቱ ውስጥም ላፕቶፖችን ጨምሮ በርካታ የሚገለገልባቸውን ንብረቶች እንደተወሰደበት ለማወቅ ተችሏል።

ወንድማችን ካሊድ በአሁኑ ወቅት የ2 ወር ልጅ ያለው ሲሆን በዛሬው እለት የደህነነት ሀይሎች በአራስ ባለቤቱ ላይም ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙ ለማወቅ ተችሏል።
በከፍተኛ የደህንነት ሃይሎች የሚመራ የእስር ዘመቻ በሙስሊሞች ላይ መከፈቱ ተገለፀ

ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን በአዲስ አበባ ለማሰር ታቅዷል፡፡

ፍትህ ራዲዬ /ዕለተ ረቡዕ የካቲት11/2007- በከፍተኛ የኢትዬጲያ መንግስት የደህንነት ሃይሎች የሚመራ ዘመቻ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ መከፈቱን የፍትህ ራዲዬ የውስጥ ምንጮች አስታወቁ፡፡

ዘመቻው የተጀመረው በቀጣይ ሃገራዊ ምርጫ ላይ በህዝበ ሙስሊሙ መካከል ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥሩብናል በሚል የሚሰጓቸውን ሰዎች በማሰር እንደሆነ ታውቋል፡፡

በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የነበሩ ፖለቲካ ፓርቲዎችን እርስ በእርስ እንዲከፋፈሉ በማድረግ የማዳከም ስራ የሰራው መንግስት ፖለቲካ ፓርቲዎቹ በአሁኑ ወቅት ለኢህአዴግ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ብቻ በመንጠላጠል በመሆኑ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የመጨረሻ የማዳከም ዘመቻ ሊከፈትበት እንደሚገባ በማመናቸው አዲስ ዘመቻ በመላው ሃገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ላይ በሚኖሩ በሙስሊሞች ዘመቻው መጀመሩን የፍትህ ራዲዬ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የአሰሳ እና ስምሪት ተግባር እየተካሄደ ሲሆን በአዲስ አበባም በርካታ ሙስሊሞች የማሰሩ ዘመቻ ተጠናክሮ መጀመሩ ታውቋል፡፡ በሙስሊሙ ትግል ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ተብሎ የሚታሰቡ ሰዎችን በሙሉ ወደ እስር ቤት ለማስገባት የተወሰነ ሲሆን ይህንንም ዘመቻ በጅማ እና በአዲስ አበባ እየተተገበረ መሆኑ ታውቋል፡፡

ይህ ዘመቻ የሚመራው በከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአዲስ መልኩ በተዋቀረ ና በተደራጀ ሁኔታ የሙስሊሞችን እንቅስቃሴ በመከታተል ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ ተብሎ የሚታሰቡ ሰዎችን ወደ እስር ቤት የማጎር ዘመቻ እየተካሄደ እንደሚገኝ የፍትህ ራዲዬ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ሃገር አቀፍ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ቁጥራቸው ከ 800 እስከ 1000 የሚደርሱ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ሰዎችን ለማሰር እቅድ የተያዘ ሲሆን ምርጫውን ለማደናቀፍ ከምርጫው በፊት ህዝባዊ አብዬት ለመቀስቀስ ሲንቀሳቀሱ ነበር በማለት ለመወንጀል መታቀዱን ምንጮች ለፍትህ ራዲዬ ገልፀዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በዛሬው ዕለት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች ከያሉበት እየታደኑ እየታሰሩ እንደሚገኙ የፍትህ ራዲዬ ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

የራዲዬ ቢላል ጋዜጠኛ የነበረው ካሊድ መሐመድን ጨምሮ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቀ በርካታ ሙስሊሞች ከያሉበት በደህንነት ሃይሎች እየታፈኑ ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሙስሊሞቹ በተያዙበት አካባቢ በወደሚገኙ የፖሊሰ ጣብያዎች እየታጎሩ ሲሆን የመኖሪያ ቤታቸውም በፖሊሶች እና በደህንነቶች እየተፈተሸ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡በመኖሩያ ቤታቸው የሚገኙ የተለያዩ ላፕቶፕ እና የግል ንብረቶቻቸው በደህንነት ሃሎች በፍተሸው ወቅት ለምርመራ በሚል መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

Image

ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኞች አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ፍ/ቤቱም የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ካደመጠ በኋላ የሚቀጥለውን ቀጠሮ ለመጋቢት 21-23 ሠጥቶ ተበትኗል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ 2006 ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከቆዩ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክስ የተመሰረተባቸው ጥር 28 ቀን 2007 ሲሆን ተከሳሾቹ ለመጀመሪያ ጊዜ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት እድል ያገኙት ግን በዛሬው ዕለት ነው፡፡

በተያያዘ ዜና የመሀል ዳኛው የነበሩት አቶ ሸለመ በቀለ ተከሳሾቹ ይቀየሩልን ባሉት መሰረት ሐሙስ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ራሳቸውን በፈቃደኝነት ከችሎቱ ያገለሉ ቢሆንም በዛሬው ችሎት ላይ ግን ቀርበው እንደነበር በፍርድ ቤት ጉዳዩን የተከታተሉት የተከሳሽ ጓደኞችና ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

Image

ሳውዲ አረቢያ ቢሻ እየተባለ የሚጠራ አነስተኛ ከተማ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በሳውዲያዊ አሰሪዋ ከተተኮሰባት ጥይት ከሞት መትረፏን ምንጮች አረጋገጡ። በዚህች ኢትዮጵያዊት ላይ ስለደረሰው የነፍስ ማጥፋት ጥቃት በኢህአዴግ ተመልምለው የተሰየሙት…

The post በሳውዲ የኢትዮጵያዊቷ የደመወዝ ጥያቄ ሽጉጥ አስመዘዘ «የኢህአዴግ ዲፕሎማቶች መረጃ የላቸውም » appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

በዘመነ አፄ ልብነድንግል ጦርነት በመጥፋቱ ንጉሱ ጦርነት አውርድ ተብሎ በየቤተክርስቲያኑ ፀሎት እንዲደረግ ትዕዛዝ አውርዶ ነበር እየተባለ በአፈ ታሪከ ይነገርለታል፤ 24 ዓመት የሞላው የህወሀት/ኢህአዴግ ስርዓትም ጦርነት አውርድ፣ መዓት አውርድ እያለ እንደሚገኝ…

The post መዓት አውርድ! – አስራት አብርሃም appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግምገማው የተካሄደው እንደተለመደው ባለስልጧናቱ በየተራ አስቀድመው ችግራቸውን እንዲናገሩ በማድረግና የራሱን ችግር በተናገረው አመራር ላይ ሌሎቹ ያላቸውን ተጨማሪ ትችት እንዲያቀርቡ በማድረግ ነው። በአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መሪነት በተካሄደው በዚህ ግምገማ  ከ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ  የተገመገሙት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣”የሀሰት የስራ አፈጻጽመ ታቀርቢያለሽ” የተባሉት የሴቶችና የወጣቶች ሚኒስትር …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባ ዱላ-ገመዳ ከኦሮሚያ ክልል  ፕሬዚዳንት- ከአቶ ሙክታር ከድር ጋር እንደማይግባቡ የተናገሩት፤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራር አባላት በቃኘው ጥልቅ ግምገማ ላይ ነው አፈ-ጉባኤው በግምገማው”የኦሮምያ አባላትን በተለየ ትህትና ታሰተናግዳለህ፣የአፈ ጉባኤነቱን ቦታ በደስታ አልተቀበልከውም፣ በአዲስ አበባ አዲስ ማሰተር ፕላን ጋር ተያይዞ ተል እኮ የማስፈጸም ችግር አለብህ፣ ከማስተር ፕላኑ …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍትሕ ራዲዮ እንደዘገበው፤በአዲስ አበባ ብቻ ከ800 -1000 የሚደርሱ ሰዎችን ለማሰር ታቅዷል፡፡ የሙስሊሙን ማህበረሰብ አካላት  በምክንያት ለማሰር በከፍተኛ የኢትዬጲያ መንግስት የደህንነት ሃይሎች የሚመራ ዘመቻ  መከፈቱን ፍትህ ራዲዬ ዘግቧል። ራዲዮው ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው፤ዘመቻው ያነጣጠረው፤ ከመጪው  ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በህዝበ-ሙስሊሙ መካከል ትልቅ ንቅናቄ ይፈጥሩ ይሆናል የሚል ስጋት ባሳደሩ …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፤ ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች <<ጥፋተኞች አይደለንም>> ብለዋል። የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃል ያደመጠው ፍርድ ቤትም፤ ለፊታችን መጋቢት 21 ቀጠሮ በመስጠት የእለቱን ችሎት  አጠናቋል፡፡ ተከሳሾቹ እጃቸው ከተያዘበት ከሚያዚያ ወር 2006 ዓመተ ምህረት …

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሐት) ውስጥ ፖለቲካዊ ጠባብነትና ትምክህት የሚያራምዱ ወገኖች መኖራቸውንና ሕገመንግስቱም በተሟላ ሁኔታ እየተተገበረ አለመሆኑን አቶ ስብሃት ነጋ የቀድሞ የህወሃት ሊቀመንበር እማኝነታቸውን ሰጡ፡፡ አቶ ስብሃት ነጋ የካቲት 9 እና 10/2007 ዓ.ም ከወጣው አዲስዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በህወሃት ውስጥ ፖለቲካዊ ጠባብነትና ትምክህት መኖሩን አምነዋል፡፡ …

በሊቢያ የግብጽ ተወላጆች የሆኑ 21 ክርስቲያኖች በአሠቃቂ ሁኔታ ከተገደሉና የግብፅ ፕሬዚዳንትም ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ርምጃ እንዲወስድ ካሳሰቡ ወዲህ ፣ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት ጉዳዩ ን አንስቶ መወያያቱ ተገለጠ። ግብፅ በሀገር

በምሥራቅ ዩክሬይን የአውራ ጎዳናና ባቡር ሐዲድ መገናኛ መሥመር ላይ በምትገኘው ዴባልትሴቭ በተሰኘችው ከተማ ፤ የተከበበው የኪቭ መንግሥት ጦር ሠራዊትና የምሥራቅ ዩክሬይን አማጽያን ለሳምንታት ብርቱ ውጊያ ሲያካሄዱ ከቆዩ በኋላ ከተማይቱ በአማጽያኑ ቁጥጥር ሥር መዋሏ ተረጋገጠ።

ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ ፤ የኬንያ መንግሥት የመገናኛ ብዙኀን የሥርጭት አገልግሎትን፣ ከቆየው «አናሎግ» ወደ ዘመናዊው ሥነ ቴክኒክ አያያዝ «ዲጂታል »ማሸጋገሩ ፤ NTV KTN «ሲቲዘን TV» እና QTV በሚሉ ምሕጻረ ቃላት የታወቁትን ዐራት

የካቲት 11፣ 1967 ዓም የተመሠረተው የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ 40ኛ የምሥረታ ዓውዳመት በመቀሌ ከተማ ተከበረ። የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ 40ኛ የምሥረታ ዓመት በተለያዩ ቦታዎች እና ዝግጅቶች ሲከበር ነው የሰነበተው።

ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ሁሉም በተከሰሱባቸው ክሶች ጥፋተኞች አይደለንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡ ፍ/ቤቱም የተከሳሾችን የእምነት ክህደት…

The post ሰበር ዜና – ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ ጥፋተኛ አይደለንም ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ appeared first on ሳተናው (Satenaw) – Latest & Current Ethiopian News, Breaking News,.

ከቀናት በፊት ሬዲዮ ማዳመጥ እስኪሰለቸን ድረስ ሁሉም ጣቢያዎችና ፕሮግራሞች ስለ ‹ቫላንታይን ደይ› ነበር የሚወተውቱን፡፡ ልክ ፍቅር በዚህች ሀገር እንዳልተወለደ፣ ድኾ እንዳላደገ፣ ለወግ ለመዓርግ ደርሶ ጎጆ እንዳልቀለሰ ይመስል ነበር፡፡ ቀይ ልብስ ያልለበሰ፣ አበባ ያልያዘ፣ በምሽት በሚደረጉት ጭፈራዎች ያልተገኘ፣ ማታም ጥንድ ሆኖ አልጋ ያልያዘ ሰው ሁሉ ፍቅርን እንደማያውቅ ተደርጎ ነበር የሚተረክልን፡፡
ዝንጀሮ ጠባቂ ላያድር ያመሻል፣
አፌ ፈራሽ እንጂ ልቤስ ከጅሎሻል፤
ዝንጀሮ ጠባቂ ላያድር ካመሸ
ከፈራህኝማ ነገር ተበላሽ፡፡
                      ተብሎ ያልተገጠመ፤
አቡኪ ወእምኪ ኢይፈቅዱ እንግዳ
ሰዐምኒ ንሑር በሳንቃው ቀዳዳ፤ 

ያልተባለ ይመስል ነበር በዚህች ሀገር፡፡ ‹ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር› አለ ኤፍሬም ሥዩም፡፡ መቼም ፈገግ ካለባቸው አጋጣሚዎች መካከል አንዱ በቀደም ጋዜጠኞቻችን ‹ፍቅር የመጣውኮ ከውጭ ሀገር ነው› ሊሉን ሲደርሱ ሰምቶ መሆን አለበት፡፡

ምዕራባውያን በአንድ ነገር ጎበዞች ናቸው፡፡ ባሕላቸውን ወደ ሸቀጥነት መቀየርና የገበያ ማሟሟቂያ ማድረግ ይችሉበታል፡፡ የካፒታሊስት ሥርዓት አንዱ መገለጫውም ሁሉን ነገር ሸቀጥ ማድረግ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ለእነርሱ ሃይማኖት እንኳን ቢሆን ሲታመንበት ሳይሆን ሸቀጥ ሆኖ ሲሸጥ ነው የሚያዋጣው፡፡ ‹የቫላንታይን ደይ›ን በዓል ከፍቅረኞች በላይ ባለ ሆቴሎችና ባለ ጭፈራ ቤቶች፣ አበባ ሻጮችና የስጦታ ካርድ አምራችና አከፋፋዮች፣ ቸኮሌትና ወይን አምራቾች ይፈልጉታል፡፡ እነርሱ ፍቅርን በእሴትነቱ ሳይሆን በሸቀጥነቱ ነው የሚፈልጉት፡፡ የሚሞቱለት፣ የሚሠዉለት ዓይነት ፍቅር ሳይሆን የሚያተርፉበት ዓይነት ፍቅር፡፡ እንዲያውም አንዳንድ የሚዲያ ባለቤቶች ስለ ቫለንታይን ሂስ ለማቅረብ የሚነሡ የፕሮግራም አዘጋጆችን ‹‹ስፖንሰሮቻችን ይቀየማሉ› በሚል ሲከላከሉ እንደነበር ውስጥ ዐዋቂዎች ይናገራሉ፡፡
ፍቅር እንደ ሸቀጥ ስለታየ ‹ቀይ ልብስ ለብሳችሁ ከመጣችሁ የክብር ሥፍራ አለን፣ ጥንድ ሆናችሁ ከመጣችሁ ቅናሽ እናደርጋለን፣ እኛጋ ጥንድ ሆናችሁ አልጋ ከያዛችሁ ግብዣ ላይ ዋጋ እንቀንሳለን› የሚሉ ዓይነት ማስታወቂያዎች ነበሩ አየሩን የሞሉት፡፡
ኢትዮጵያውያን ከውጭ መልካም ሐሳብ የያዙ በዓሎችን ሲያመጡ ሐሳቡን እንጂ ሙሉ ቅርጽና ይዘቱን አያመጡትም፡፡ ገና ኢትዮጵያዊ መልክ ነው ያለው፤ ግን ዓለም ዐቀፋዊ በዓል ነው፡፡ የጥምቀት በዓል በሌሎችም ክርስቲያን ሕዝቦች ዘንድ አለ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ኢትዮጵያዊ ቁመና፣ መልክና ባሕል አለው፡፡ የደብረ ታቦር በዓል በሌላውም ዓለም ይከበራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ቡሄ ሆኗል፡፡
ይህ መሆኑ በሦስት ነገር ሲጠቅመን ኖሯል፡፡ በአንድ በኩል የራሳችን መገለጫ፣ የማንነታችን ማነጫና መግለጫ ሆኖ እንዲኖር አድርጎታል፡፡ ለዚህ ነውኮ መስቀልን አዲስ አበባ፣ ገናን ላሊበላ፣ ጥምቀትን ጎንደር ላይ ለማየት የአገር ፈረንጅ የሚጎርፈው፡፡ እዚያ የሚሄደው ኢትዮጵያዊውን መልክ ለማየት እንጂ ጌታ መወለዱን፣ መጠመቁንና መስቀሉ ከተቀበረበት መገኘቱን እንደ አዲስ ለመማር አይደለም፡፡ ይህን ሐሳብ ወደ ሕልው ባሕል የቀየርንበትንና ያንንም የጠበቅንበትን መንገድ ለማየት እንጂ፡፡ አንድን ሐሳብ የሕዝብ ባሕል ማድረግ በሰው ልጅ ጉዞ ውስጥ ወሳኙና እጅግ አስፈላጊው የሰብእና ክፍል ነው፡፡ 
በሌላ በኩል ደግሞ ከኢትዮጵያዊ ማንነት ጋር የተዋሐደ በመሆኑ ገጠር ከከተማ፣ ሰሜን ከደቡብ ሳያነቅፈው ተጣጥሞ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ከደኻ እስከ ሀብታም፣ ከማይም እስከ ምሁር፣ ከደቂቅ እስከ ሊቅ እንደ ዐቅሙ ያከብረዋል፡፡ ሦስተኛው ደግሞ በዓሉ ቤተኛ መሆኑ ነው፡፡ ቤተኛ በዓል ማለት ቤተሰብን የሚመለከት፣ ሁሉም የሚሳተፍበት፣ የሀገር ቤቱን ሰው ተሳትፎ የሚጠይቅ ማለት ነው፡፡ ለገና ዳቦ የሚሆነውን እህል፣ በግና ዶሮውን ገበሬ ያመጣል፤ ነጋዴ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን ነገር ያከፋፍላል፡፡ የሴቶች ሞያ በጠላው በዶሮው፣ የወንዶቹ ሞያ በእርዱ በሥጋው ይታያል፡፡ እንኳን አደረሰህ የሚለው ዘመድ አዝማድ መልእክቱን ይልካል፡፡ ከጉልት ገበያ እስከ ‹ሱፐር ማርኬት› አገሩ ሸብ ረብ ይላል፡፡ በዓል መሆኑን አካባቢውም ይናገራል፡፡ ልጅ ዐዋቂው፣ ያገባው ያላገባው፣ ነባሩና አዲስ መሽራው፣ መናኙና ከተሜው፣ ሁሉም ይሳተፋል፡፡ ለዚህ ነው እነዚህ ሀገርኛ በዓላት የመከራ ዘመናትን ሁሉ አልፈው በየጊዜው እየበለጸጉ እዚህ ዘመን የደረሱት፡፡ 
 
እንደ እውነቱ ከሆነ የ‹ቫለንታይን ደይ› ኢትዮጵያኛ ሆኖ ቢሆን ኖሮ በየካቲት አበባዉ ሁሉ ረግፎ ባለቀበት በየካቲት  ወር አልነበረም መከበር የነበረበት፡፡ በጥቅምት እንጂ፡፡ አበባ መስጠት ያለባችሁ የግድ ገዝታችሁ ነው ካልተባልን በቀር፡፡ አገሩ በሙሉ በአበባ የሚያሸበርቅበትን የጥቅምትን ወር አሳልፎ የአበባን በዓል በመከር ጊዜ ማክበር ምን ያህል በዓሉ ኢትዮጵያዊነት እንደሚጎድለውና ተገንጥሎ ብቻውን እንደቆመ የሚሳየን ነው፡፡     
 
ምንም እንኳን ቀይ ሽብር፣ ቀዩ ጦር፣ የቀይ ኮከብ ጥሪ፣ የሚሉ መጥፎ የቀይ ቀለም ትዝታዎች ቢኖሩብንም ያ ሁሉ ቀይ ወይን፣ ቀይ ምንጣፍ፣ ቀይ መብራት፣ ቀይ አበባ፣ ለጦርነት፣ ለሽብርና ለጠብ አይደለም፤ ለፍቅር ነውና ኩነቱን ሳይሆን ምክንያተ ክዋኔውን ተመልክተን ስለ ፍቅር አምላክ ስንል ይሁን ብለን እዚህ ላይ እንለፈው፡፡
 
ግን እስኪ ልክ እንደ ቫላንታይኑ ሁሉ ለራሳችንም ጉዳይ ትኩረት እንስጥ፡፡ አሁን ነገ የካቲት 12 ቀን ለዚህች ሀገር ሕይወታቸውን የገበሩ፣ በፋሽስቶች የተጨፈጨፉ፤ ዛሬ እኛ ዘና ብልን በቀይ ወይንና በቀይ ምንጣፍ የ‹ቫላንታይን ቀንን› እንድናከብር ያደረጉ ሰማዕታት በዓል  ይከበራል፡፡ ከቫለንታይን ይልቅ የካቲት 12 የራሳችን ጉዳይ ነው፡፡ ለዛሬ ማንነታችን ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡ እንዲህ በነጻነት ቀና ብለን እንድንሄድ ዋጋ ከከፈሉ ሰዎች መካከል ናቸው የየካቲት 12 ሰማዕታት፡፡ ይኼው ዛሬ ዋዜማው ነው፡፡ ማንም ግን ስለ ነገው በዓል እየተናገረ አይደለም፡፡ ነገም ከአንዲት ዜና በቀር ማን ስለ ጉዳዩ ጣል እንደማያደርግ እገምታለሁ፡፡  
 
የትናንት ታሪኩን በሚገባ የማያውቅ፣ የማይተነትንና የማይገነዘብ የትናንቱን ስሕተቱን በከፋ መንገድ ለመድገም የተረገመ ነው፡፡ ከትናንት የተሻለ ለመሥራት በትናንቱ መሠረትም ላይ ለመገንባት ትውልድ የተሠራበትን የታሪክ ጡብ ማወቅ አለበት፡፡ በርግጥ እንደ ቫለንታይን ቀን በስፖንሰር አያንበሸብሽም፣ በርግጥም ቀይ ወይንና ቀይ ምንጣፍ የለውም፡፡ አበባ ለመሸጥና ጭፈራ ለመጨፈር አይመችም፡፡ ግን ከቫለንታይን ቀን ይልቅ የካቲት 12 ቀን እኛነታችን ነው፡፡ መነሻ የሌለው መንገድ፣ መንገድ የሌለውም መድረሻ የለም፡፡ ለመንገዱ ዋጋ ነሥቶ፣ ለመድረሻው ተስፋ ማድረግን የመሰለ ዕብደትም የለም፡፡ ለመንገድ ሠሪው ዋጋ ነሥቶ በመንገዱ ላይ ለሚሄደው መኪና ምስጋና ማዥጎድጎድን የመሰለ ክፉ ዐመል የለም፡፡ በትናንቱ ላይ ለመግባባት አለመቻላችን ነው በዛሬውም ላይ ሊያግባባን ያልቻለው፡፡ 
 
እናም እናንት ‹ሚዲያዎች›፣ እናንት በዓለ ሚዲያዎች
የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
እስኪ እንያችሁ
ኢትዮጵያዊ ለሆኑ በዓሎችና ጉዳዮች እንደ ቫለንታይን ቀን ሁሉ አገሩን በሚዲያ ስታውዱት፣ እንደ ቅዱስ ቫለንታይን ሁሉ ስለ የካቲት 12 ሰማዕታት፣ ስለ አድዋ ጀግኖች፣ ስለ ማይጨው ዘማቾች ስትተርኩ እንስማችሁ፡፡ 
 
የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ፣ ባሕሎች ላይ፣ ታሪኮች ላይ፣ በዓሎች ላይ፣ ጀግኖች ላይ፣ ቦታዎች ላይ አጥንታችሁ፣ አንብባችሁ፣  ስታቀርቡ እስኪ እንያችሁ፡፡
ርግጥ ነው ዊኪፒዲያ ላይ አይኖር ይሆናል፣ ኢንተርኔት ላይ በክሊክ አይገኝ ይሆናል፣ ጎልጉል ሲጎለጎል በቀላሉ አይመጣ ይሆናል፡፡ ግን የራሳችን ጉዳይ ነው፡፡ ‹ራሴን በራሴ ካላንቆለጳጰስኩት ማን ያንቆለጳጵስልኛል› ነውና እኛ ለእኛ እንሥራ፡፡ ሌሎችም ስለ ሠሩ ነው ዛሬ ስለ እነርሱ በቀላሉ የትም የምናገኘው፡፡ እኛም ብንሠራ የኛ ጉዳይ በቀላሉ እንዲደረስበት ማድረግ እንችላለን፡፡ 
 
የኢትዮጵያ ነን ካላችሁ
እስኪ እንያችሁ፤