«የኢትዮጵያ ህዝብም ጠመንጃ የታጠቀ ጓደኛ ያገኘው በዚህ ትግል ነው»-ጄኔራል ሳሞራ የኑስ

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የምትታተመዋ ዘመን መፅሄት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስን እንግዳ አድርጋ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ይዛ ወጥታለች። ከእነዚህ ነባርና አንጋፋ ታጋዮች መካከልም ጄኔራል ሳሞራ ለመጽሄትዋ ከሰጡት መረጃ የተወሰኑትን በመምረጥ እንዲህ አቅርበነዋል። ዘመን፡- እናመሰግናለን ጄኔራል ሳሞራ እንደሚታወቀው የህወሀት 40ኛ ዓመት መከበር ጀምሯል። እርስዎ ደግሞ በትግሉ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነዎትና እንደ ግለሰብ ትግሉን እንዴት ያስታውሱታል፤ ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት? ጀኔራል ሳሞራ፡- አርባ ዓመት ረጅም ጊዜ ነው። የትግሉ ሂደትም አንድ ዓይነት አልነበረም። የመጀመሪያዎቹ አስራ ሰባት ዓመታት ጨቋኙን ፋሽስት የደርግ ስርዓት ለማስወገድ የተደረገ የትግል ጊዜ ነበር። ይሔ ትግል ደግሞ በርካታ መስዋዕትነት የተከፈለበት ነው። ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት የትግል ሂደት ነው። ደርግ ከተሸነፈ በኋላ ደግሞ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ትግሉ ነው የቀጠለው። እንዳልኩት የመጀመሪያው አስራ ሰባት ዓመት የትግል ዓላማ ጨቋኙን ሥርዓት የማስወገድ ቢሆንም የመጨረሻው ዓላማ ግን ዴሞክራሲን፣ ልማትንና ፍትህን ማረጋገጥ ነበር። እና ትግሉ የመላው ኢትዮጵያ ህዝቦችን ድጋፍ አግኝቶ በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው። በትግሉ ውስጥ ትልቁና ወሳኙ ነገር የደርግን ኃይል መደምሰስ ቢሆንም ከዚያ በመቀጠል ለግጭት፣ ለድህነትና ለሰላም እጦት ይዳርገን የነበረው ሁኔታ በ1987 ዓ.ም በፀደቀው ህገ መንግሥታችን መፍትሔ አግኝቷል። በዚህም ያ የተደመሰሰው ሥርዓት ዳግመኛ እንደማይመለስ እርግጠኛ የተሆነበት ሁኔታ ነበር የነበረው፡፡ ለአሁኑ ልማትና ዴሞክራሲያችን መሰረት የሆነውም ይሄው ህገ መንግስታችን ነውና በትግሉ የደርግ ሥርዓትን መደምሰስ አንዱ ጉዳይ ሆኖ ሁለተኛው ደግሞ ህገ መንግስቱ መጽደቁ ነው፡፡ ከዚህ […]