የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጃፓን መንግስት የሚደገፈው የግልግል ዳኝነት ይፋ ባደረገው ጥናታዊ ጽሁፍ በአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች በህግ ታራሚዎች አያያዝ እና አስተዳዳር ከፍተኛ ችግሮች አሉባቸው ብሎአል። 31 እስር ቤቶች በእስረኞች  ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትሉም ተገልጿል። ለሰው ልጆች አደገኛ ተብለው ከተለዩት እስር ቤቶች መካከል ደብረ ታቦር፣ ጋይንት፣ አዲስ ዘመን፣ ሃይቅ፣ ደብረ-ብርሃን፣ መሃል …

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሁለቱ ፓርቲዎች የድጋፍ ኮሚቴ አስተባባሪዎች በጋራ በመስራት ሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሳኔ ማሳለፋቸውን ያስታወቁት፣ አንድነት ፓርቲ መንግስት በሚቆጣጠረው ምርጫ ቦርድ አማካኝነት እንዲፈርስ ከተደረገና አባሎቹም ሰማያዊ ፓርቲን ከተቀላቀሉ በሁዋላ ነው። በሌላ ዜና ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ቀድሞ የአንድነት አሁን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ …

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊሄዱ ሲሉ ተያዙ የተባሉት 101 ኢትዮጵያውያን ኬንያ ፍርድ ቤት ቀርበው 50 ሺ የኬንያ ሸልንግ መቀጣታቸውን፣ ቅጣታቸውን ካልከፈሉ ደግሞ በአንድ አመት እስር ተቀጠው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖባቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በምግብ እጥረት የተነሳ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎሳቁለው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተዘግቧል። መንግስት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማግኘቱን …

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶክተር ነጋሦ ጊዳዳ ትላንት እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ The National Endowment For Democracy የተባለው ዓለምአቀፍ የጥናት ተቋም ባመቻቸላቸው መድረክ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

 

ዶክተር ነጋሦ ባቀረቡት በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ያተኮሩት እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር “ሕገ-መንግሥቱ የሁሉንም ብሄረሰቦች ፍላጎት ማንፀባረቅ ያስፈልገዋል” በሚለው ላይ ነው።

 

በኢትዮጵያ የፊታችን ግንቦት ስለሚካሄደው ምርጫ፥ በሀገሪቱ ስለታየው የረዝም ጊዜ መረጋጋትና ልማትም በጽሁፋቸው ዳሰዋል።

 

ሰሎሞን ክፍሌ በስፍራው ነበር። ተከታዩን አዘጋጅቷል።

 

 

ዛሬ ያስቻለዉ የአዉሮጳ ሕብረት ፍርድ ቤት ግን የሺፕሐርድን የጥገኝነት ጥያቄ አልደገፈዉም።ጨርሶም ዉድቅ አላደረገዉም።በፍርድ ቤቱ ዉሳኔ መሠረት ሺፕሐርድ አልዘምትም ለማለቱ ወይም የነበረበትን የጦር ክፍል ለመክዳቱ ያቀረበዉን ምክንያት በመረጃ ማስደገፍ አለበት።

በአዲስ አበባ የደቡብ አፍሪቃ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፤ ሠላዮች፤ ከኢትዮጵያ የመረጃ ሰዎች ጋር ይራኮቱ-ገቡ።ቢያንስ አራት ጠባቂዎች-እሕል ዉሐ ሳይቀምሱ የአፍሪቃ ሕብረት ፅሕፈት ቤትን ሙጥኝ አንዳሉ አራት ቀን ዉለዉ አደሩ።ሴትዮዋም ከግድያ ሴራዉ አመለጡ።

«እኛ ሃገር ባህላዊ ሆነዉ እየተከበሩ ያሉት በዓላት የሐይማኖት በዓላት ናቸዉ። የሐይማኖት በዓላት እድሜ ለአባቶቻችን እና ለእናቶቻችን ከባህላችን ጋር በደንብ አድርገዉ እንደ ጥሩ ስፊት እንደ ጥሩ ስንደዶ ማንም በማያላቅቀዉ ሁኔታ ሰፍተዋቸዋል። የካቲት 12 እኮ ዳቦ አይቆረስለት፤ ቡና አይፈላለት፤ በግ አይታደርለት ጠላ፤ አይጠመቅለት።

በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ሶማሊያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሰዉ ከአልቃይዳ ጋ ትስስር እንዳለዉ የሚነገርለት ፅንፈኛ እስላማዊ ታጣቂ ቡድን አሸባብ በዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ፤ ብሪታኒያ እንዲሁም በሌሎች የምዕራብ ሃገራት በሚገኙ የገበያ ማዕከላት ላይ ጥቃት እንደሚያደርስ መዛቱ ተሰምቷል።

የዐባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት ፣ ወንዙን በጋራ ለልማት የመጠቀም መብታቸውን የሚያስከብር የውል ሰነድ አብዛኞቹ ከፈረሙ ወዲህ የዋናይቱ አፈንጋጭ ግብፅ ወሳኝ አቋም ምን እንደሚሆን ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱ የሚታበል አይደለም። «ግብጻውያን አንዲት

ከአንድ ሰአት በላይ የፈጀውን ጥናታዊ ጵሁፍህን ሰማሁት። ሰምቼ ስጨርስ ደነገጥኩ። ከራሴም ጋር ለሰአታት ሙግት ገጠምኩ ። ኢህአዴግን ለቅቄ የወጣሁት ልቤ የፈቀደውን በነጳነት ለመናገር ነውና የማውቀውን እና የሚሰማኝን መናገር እንዳለብኝ ተሰማኝ…

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን 30 የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች መታሰራቸውን የዞኑ የፓርቲው አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ አስታወቁ፡፡ ከዞኑ አስተባባሪዎች መካከል አቶ ታደመ ፍቃዱ እና ፓርቲውን በመወከል ለተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ…

እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች…

በ  

ከ28 ሚሊየን ብር በላይ እምነት በማጉደል የሙስና ወንጀል ክስ የተመሰረተበት ግለሰብ በ6 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራትና በ7 ሺህ ብር እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ሰሞኑን በዋለው ችሎት ውሳኔ አስተላለፈ። 
    የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በግለሰቡ ላይ የመሰረተው ክስ እንደሚያስረዳው ተስፉ በለጠ የተባለው…


ብዙዎቻችን ሆስፒታልን ስናስብ ከእርሡ ጋር ተያያዥ ሆኖ የሚታየን የህመምና የሞት ስሜት ምቾት የሚሠጥ አይደለም፡፡ ስለዚህ ለአንድ ቀን እንኳ ሆስፒታል ውስጥ መተኛት እንመኝም፡፡ የሃምሳ አምስት ኣመቱ ቻይናዊ ግን ጤንነቱ ተመልሶለት እንኳን ከሆስፒታል ለመውጣት ፈቃደኛ አልሆነም ነበር፡፡ ቼን የተባለው ይህ ቻይናዊ እ.ኤ.አ ነሐሴ 2011 በአደጋ ምክንያት አነስተኛ ጉዳት ገጥሞት ቤይጂንግ ወደሚኘው አንድ ሆስፒታል ለህክምና ሄዶ ነበር፡፡ ህክምና አግኝቶ…

“Ethiopia steams ahead with vision for a modern national rail network “ ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ ጦምረዋል። እኝህ ሰው ምን ያህል በሶሻል ሜዲያ የሚሰጣቸው አስተያየት እንደሚከታተሉ አላወቅም። ለምን ትንሽ ጊዜ ወስደው…

መንግስት ህገ መንግስታዊ መብቶቻችንን በመጣስ ላለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ በደል ሲፈጽምብን ቆይቷል። እኛም እንደህዝብ ድምጻችንን አዋህደን እና በአንድነት ቆመን ሰላማዊ ትግል ስናካሂድ ቆይተናል። ትግላችን እስካሁን አንድም ከሰላማዊነት መርህ ዝንፍ ሳይል…

ነገረ ኢትዮጵያ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸው በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ…

(ራማቶሀራ ዴርቶጋዳ) ፅንፈኛው ወንድሜ! የልቤን ልንገርህ፤ ለዛሬ እንኩዋን ልብ ብለህ አድምጠኝ! ሕመሜ ይመምህ፤ሃሳቤ ያሳስብህ፤ስጋቴ ስጋትህ ይሁን፤ጭንቀቴም ይጭነቅህ፡፡ እባክህንማ አንዴ ዦሮህን ስጠኝ፤ህሊናህን አንዴ ከነጎደበት የማንአለብኝነት፤የትዕቢትና የትምክህት ዓለም ላንዴም ቢሆን ገታ አርገህ መልሰውና እኔን እህትህን ስማኝ፡፡ምናልባት ዛሬ ባትሰማኝ ነገ በሚፈጠረው ሁኔታ ዕድሜ ልክህን ሊፀፅትህ የሚችል ከፍተኛ ችግር ሊከሰት ይችላልና ግድ የለህም ስማኝ! አዎን! እኔም አንተም የአባቶቻችንን ታሪክና አገር እናውቃለን፤ባለፉት ስርዓቶች የኔም ያንተም ወገኖች የደረሰባቸውን ሁሉ እናውቃለን!!! እስኪ ስለዚህ ጉዳይ በግልፅ እናውራ:: ታድያ እኔ መሰረታዊ ናቸው የምላቸውን በገዢ መንግስታት ደረጃ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሱትን ሰብዓዊ ግፎች በወፍ በረር አስቃኝሃለው፤በዚህም ከውስጤ ያለው ቁስል ምን ያህል ያመረቀዘ እንደ ሆነ ላሳይህ እውዳለሁና ከቻልክ አንተም በኔ ቦታ ሆነህ ላፍታም ቢሆን አስበው! የታሪክን ሰበዝ ስንመዝ ግዜ ላለመፍጀት እንዲሁም የዚህ ፅሁፍ ዓላማው የኔን የእህትህን ስሜት በተቻለ መጠን ትጋራ ዘንድ ስንቅ የሚሆንህን መረጃ ማስጨበጥ ነውና ለውይይት ያህል ከሃ/ስላሴ ጀምሮ እስከ ደርግ ድረስ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀሙትን ዘግናኝ መንግስታዊ ግፎችን አንድ ሁለት እያልኩኝ አነሳልሃለው፡፡ ታድያ ወንድሜ! የምፅፈው ከልቤ ነውና አንተም ከልብህ አንብበህ ተረዳኝ፤የምፅፈው ለክርከርና ለሂሳብ ውርርድ አይደለምና! እስኪ ወንድሜ! አንተን በመጠየቅ ልጀምር! እውነት ስለ አፄ ሀ/ስላሴ ያለህን ስሜት ምንድን ነው? በጎ ወይስ መጥፎ? ስለ ደርግስ? እውነቱን እንነጋገርና አንተና መሰሎችህ እኮ ሀ/ስላሴን ሞዓ አምበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ፤መንግሰቱን ደግሞ ጉዋዱ፤ቆራጡ፤አገር ወዳዱ፤ጀግና እያላችሁ የሌላቸውን የዘር ሃረግና መለኮታዊ ስልጣን ሰጥታችሁ ስታወድሱዋቸው ነው የምትኖሩት! ወንድሜ እኔና ወገኖቼ […]

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸው በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርገው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን የትብብሩ ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ዕጩዎቻችን በዝርዝር ሊያሳውቀን አልቻለም፡፡ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ […]

የዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም በአሜሪካ የቢል ቦርድ ሰንጠረዥ ላይ ከመቶዎቹ ምርጥ ዜማዎች መካከል በዚህ ሳምንት ከአንድኛ እስከ አስረኛ ደረጃ የወጡትን ምርጥ ዜማዎች ያካትታል፡፡

በሴት ተከሳሾች የመብት ጥሰት አቤቱታ ላይ “ፍርድ ቤቱ” ሌላ ቀጠሮ ሰጠ
በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙትን ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን እና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬን አያያዝ አስመልክቶ ለዛሬ

Edom Kassaye and Mahilet Fantahun

ተቀጥሮ የነበረው “የፍርድ ቤት” ውሎ የመብት ጥሰቱን አስመልክቶ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ በጽሁፍ ለመስማት ነበር ፡፡ ነገር ግን እስር ቤቱ አስተዳደሮች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው የጽሁፍ ምላሹ ስላልተፈረመበት ማቅረብ አልቻልንም በማለት የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ነኝ ብለው የቀረቡት ዋና ሳጅን ድሪባ ሰበታ ተናግረዋል፡፡

ዋና ሳጅን ድሪባ የእስር ቤቱ የህግ ባለሞያ እና የሴቶች ክፍል ሰራተኛ ነኝ ፍርድ ቤቱ ከፈቀደ በቃል ምላሽ ልስጥ ያሉ ሲሆን አግባብ ያለው የአስተዳደር ሰው አይደሉም በሚል “ፍርድ ቤቱ” ሳይቀበላቸው ቀርቷል፡፡
በዚህም መሰረት “ፍርድ ቤቱ” የቃሊቲ እስር ቤት አስተዳደር መልሱን በጽሁፍ ይዞ እንዲቀርብ ለየካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡( March 4) በተያያዘ ዜና ዓቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ አለኝ ያለውንና ከወንጀል ክሱ ጋር አያይዞ ካቀረበው የማስረጃ ዝርዝር መካከል የሲ.ዲ ማስረጃውን በተመለከተ የተከሳሽ ጠበቆች እስካሁን ስላልደረሳቸው አንዲደርሳቸው በጽሁፍ ጥያቄ አቅርበዋል ፡፡ የጠበቆቸን ጥያቄ ተከትሎ አቃቤ ህግ የሲዲ ማስረጃዎቸቹን ለጠበቆች አንዲያደርስ “ፍርድ ቤቱ” ትዝዛዝ ሰጥቷል፡፡
የዞን9 ማስታወሻ – የሴት እስረኞች መንገላታት በተደጋጋሚ ተገልጾ እና ትእዛዝ ተሰጥቶበት ከመንግሰት በባሰ ጨቋኝ የሆነው “የቃሊቲው መንግሰት” አፈና ያልተሻሻለ አንደሆነ ይታወቃል፡፡ የፓለቲካ እስረኞች አያያዝ የዞን9 ተከሳሾችን ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጋዜጠኛ ርእዬት አለሙን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የሁሉም ጥያቄ መሆኑ መብት ጥሰቱ በተዘዋዋሪ መንግሰት የሚክደውን ፓለቲካ እስረኛ የለም የሚለውን ሃሳብ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠንካራ አርምጃ በመውሰድ በሌሎች ጉዳዬች ላይ ያጣውን እምነት አመኔታ እና ስልጣን ቢያንስ የታራሚዎቸን መብት በማስከበር እንዲያሳየው አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ በዚህ የተገለለ የጭቆና አያያዝ ውስጥ ሆነው አንኳን ፈገግታቸው ለአፍታም ያልተገደበው ሴት እስረኛ እህቶቻችን እንደሆነ ከጭቆናው በላይ መሆናቸውን ካስመሰከሩ ቆይተዋል፡፡
አሁንም ስለሚያገባን እንናገራለን !
ዞን9

የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን […]

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሀትን 40ኛ ዓመት አክብረው ሲመለሱ  እግረ መንገዳቸውን  በ አማራ ክልል የተለያዩ  አካባቢዎችን እየጎበኙ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ  ፤የካቲተ 16 ቀን በወልቃይት ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት የህዝቡን ተቃውሞ በመፍራት መሰረዛቸው ነዋሪውን ክፉኛ አስቆጥቷል። የወልቃይት ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቲት 16 ቀን ወልቃይትን እንዲጎበኙ በአካባቢው ሹመኞች መነገሩን ተከትሎ  …

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሚታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ፋብሪካዎች ስራቸውን በተገቢው መንገድ እንዳያከናውኑ እንቅፋት ፈጥሮባቸዋል። ከዚህ ቀደም ከደንበኞቻቸው ጋር የተለያዩ የስራ ውሎችን ተዋውለው በጊዜው ማድረስ ያልቻሉ ፋብሪካዎች፣ ለደንበኞቻቸው ” በአገራችን በሚታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት በሰአቱ ማድረስ አልቻልንም” በማለት የይቅርታ ደብዳቤዎችን በመጻፍ ላይ ናቸው። በማኑካንቸሪንግና በኮንስትራክሽን ዘርፍ እንዲሁም በአስመጪነት …

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸውን በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርጉ አስበው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፋቸውን የትብብሩን ጸሃፊ አቶ አቶ ግርማ በቀለን ጠቅሶ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ …

ከ2 ዓመት ገደማ በፊት የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ያከበረው የቀድሞው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ፤ ያሁኑ የአፍሪቃ ሕብረት ፣ በቀጣይ 50 ዓመታት ፣ ማለትም እ ጎ አ እስከ 2063 ፣ ክፍለ ዓለሙ አንድነቱን አጠናክሮ ፣ በኤኮኖሚ ዳብሮ ፤

የዚህች ሀገር ባለቤቶች ሁላችንም ካልሆንን በቀር በተናጠል ማንም ባለ ግዛት ሊሆን አይችልም፡፡ ሉሲ አማራ ትሁን ኦሮሞ፣ አፋር ትሁን ሶማሌ፣ ጉሙዝ ትሆን ትግሬ፣ ወላይታ ትሁን ጋሞ የሚያውቅ የለም፡፡ በአኩስምና አካባቢው በተገኙ…

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ሲመኙት የኖረ፣ የትውልድን ሕልም እውን ያደረገ፣ በዘመናዊ ታሪካችን ውስጥ ሊጠቀስ የሚችል የዚህ ትውልድ ሥራ ነው፡፡ ‹ዓባይን መገደብ› ታላቅ ሐሳብ፣ ታላቅም ውሳኔ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከአካባቢው ሀገራት ጋር የምታደርገውን ውይይት ቋንቋውን የቀየረ፣ የግዮን ምንጩ ከኢትዮጵያ ተራሮች መሆኑን ከብራና አውርዶ መሬት ላይ የጻፈ ነው፡፡ 
 
ስለ ሕዳሴው ግድብ የሚሠሩት ማስታወቂያዎች ግን ፈጽሞ ግድቡን የማይመጥኑ፣ እንኳን ለዓባይ ግድብ ለኛ ቤት አጥርም የማይሆኑ፣ በውስጣቸው ምንም ዓይነት ሀገራዊ ርእይና ፍልስፍና የሌለባቸው፤ ከጠላና እንጀራ የማያልፉ ናቸው፡፡ እንዴው ግድቡ አፍ ስለሌለው እንጂ በስም ማጥፋትና በክብረ ነክ ወንጀል ይከስ ነበር፡፡  የታሪክ ባለሞያዎች፣ የፖለቲካ ጠበብት፣ የኪነ ጥበብ ልሂቃን፣ የእምነትና የባሕል ምሁራን፣ የሥነ ቃል አጥኒዎች፣ የሐሳብ መሪዎችና የሕዳሴ ኮከቦች መነጋገሪያ፣ መከራከሪያ፣ ሐሳብ ማራቀቂያ፣ ትውልድ መቅረጫ፣ ትውልድ ማነሣሻ፣ መሆን የነበረበት የሕዳሴው ግድብ የቀልደኞች ማቧለቻ ሲሆን እንደማየት ያለ የክፍለ ዘመኑ ርግማን የለም፡፡

እኔ እንዲያውም እነዚህ ግድቡን የማይመጥኑ ማስታወቂያዎች በግብጽ ነው እንዴ ስፖንሰር የሚደረጉት? እላለሁ፡፡ ግድቡኮ የግንባታ ሂደት ጉዳይ ነው፡፡ መንግሥት ከአንድ ኮንትራክተር ጋር ተነጋግሮ የሚያጠናቅቀው፡፡ ዋናው ጉዳይ አስተሳሰቡ ነው፡፡ ለምን እንገነባዋለን? የምን ማሳያ ነው? ዓባይን እንገድባለን ስንል ምን ማለታችን ነው? ዓባይ በኢትዮጵያ እምነት፣ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ባሕል ውስጥ ምን ቦታ ነበረው? አሁን ወደየትኛው ቦታ እየወሰድነው ነው? ዓባይን የመገደብ ሂደትና ስኬት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መፍጠሪያ መስፈንጠሪያ እንዲሆን ምን እንድርግ? እነዚህን ነው መተንተን፣ እነዚህን ነው መሥራት፣ እነዚህን ነው የሕዝብ ገንዘቦች ማድረግ፣ በእነዚህ ላይ ነው መግባባት ያለብን፡፡ ግድቡ መሠራት ያለበት በዜጎች ላይ ቀልደን ሳይሆን ዜጎችን በብቃት አሳምነን ነው፡፡  
 
ግድቡ ያልቃል፡፡ ወንዙም ይቀጥላል፡፡ የሚቀረው ታሪክና ሐሳቡ ነው፡፡ አሜሪካውያን በአሪዞናና በኔቫዳ መካከል የሚገኘውን የሁቨር ግድብን የሠሩት(እኤአ ከ1931-36) በችግር ወቅት ነው፡፡ ገንዘባቸው፣ ጉልበታቸውንና ዕውቀታቸው ሠውተው ነው የሠሩት፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ገንቢዎች ሕይወታቸው ከፍለውለታል፡፡ አያሌ አሜሪካውያን ዛሬ ግድቡን ለመጎብኘት ሲሄዱ ከግድቡ በላይ ስለ ግድቡ አሠራር የሚያሳየውን ሙዝየም መጎብኘት ነው የሚያስደስታቸው፡፡ ለምን ተገነባ? የዚያን ዘመን መሪዎችና ሕዝብ ምን ነበር ዓላማቸው? እንዴት ነበር የገነቡት? እነማን ምን ዓይነት መሥዋዕትነት ከፈሉ? ግድቡን ሲገደቡ አሜሪካን የት ማድረስ ነበር ሕልማቸው? ይህን ነው ሙዝየሙ የሚተርከው፡፡ የተሠው ዜጎችን፣ የቀን ራሽን እየተሰጣቸው የገነቡ አሜሪካውያንን፣ በአነስተኛ ክፍያ ለሀገራቸው የሠሩ ባለሞያዎችን ያሳያል ሙዝየሙ፡፡
 
ሁቨር ግድብ ለአሜሪካውያን ግድብ ብቻ አይደለም፡፡ የአልሸነፍ ባይነት መገለጫ፣ ሀገርን ከግል ጥቅምና ከጊዜያዊ ችግር በላይ አድርጎ ማሰቢያ፣ ብንወድቅ እንነሣለን፤ ‹ኢኮኖሚያችን ለጊዜው ቢወድቅም፣ እኛ ሕዝቦች ግን አልወደቅንም› የሚለውን የአሜሪካውያንን የዚያ ዘመን ፍልስፍና ማረጋገጫ ነው፡፡ ጽናታቸውንና የሀገር ፍቅራቸውን ማሳያ ነው፡፡ አስጎብኝዎቹ እንደሚሉትም ‹እንደ ሕዝብ አንወድቅም› የሚለውን ፍልስፍናቸው ማስመስከሪያ ነው፡፡ 
 
የሕዳሴው ግድብ ግን ‹የዚህ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ጎበኙት› ከሚለው ዜና በዘለለ ‹ስለምኑ› የማይወራለት፣ ፍልስፍናው የማይተነተንለት፣ ከግድቡ በላይ፣ ከአሸዋው፣ ከሲሚንቶውና ከብረቱ በላይ፤ ከጠጠሩና ከድንጋዩ ባሻገር ግድቡ ምንድን ነው? የሚለውን መግፍኤ ሐሳብ የሚናገርለት ያጣ ምስኪን ግድብ ነው፡፡ ልጆቻችን ነገ ግድቡን አይደለም የሚጎበኙት፡፡ እንዴት ተሠራ፣ ለምን ታሰበ፣ አባቶቻችን ምን ለውጥ ነበር ሊያመጡ ያሰቡት? የነበሩትን ተግዳሮቶች እንዴት አለፏቸው? የግድቡ መሠራትስ ምን የአስተሳሰብ፣ የአሠራር፣ የኢኮኖሚ፣ የባሕል፣ የዲፕሎማሲና የሀገር ገጽታ ለውጥ አመጣ? የሚለውን መመርመር ነው የሚፈልጉት፡፡ ከግድቡ ጀርባ የነበረውን የኢትዮጵያውያን ፍልስፍናና መንፈስ ነው የሚሹት፡፡  
 
ያ ሁሉ ቀረና፣ ጽድቁ ቀርቶ በወጉ እንኳን የሚኮንነው በማጣት …
 
ጭራሽ ሰሞኑን የምናያቸው ማስታወቂያዎች ደግሞ የግድቡን ሐሳብ አውርደው አውርደው ገንቦ ጠላና የብረት ምጣድ ጥብስ ላይ የሚጥሉ ሆኑ፡፡ ከዚህ በፊት ከጉንጭ የተረፈ ዳቦ በመብላት፣ በጎልማሶች ትምህርት ላይ በማሾፍ የተሠራውን ማስታወቂያ ስንታገሠው አሁን  ደግሞ  ‹ሕዳሴው ወርዶ ወርዶ› የጠላና የጥብስ መጨዋቻ ሆነ፡፡ ፀጉሯ እንኳን ወርዶ ወርዶ ‹ይጠቀለላል እንደ ሰርዶ› ነበር የተባለው፡፡ እንዴው ከዚህ የተሻለ ከፍ ያለ ሐሳብና የመንገሪያ መንገድ አጥተን ነው የግድቡን ሐሳብ በጋን ጠላና በብረት ምጣድ ጥብስ የምናሰቃየው? 
 
አሁን የሦስት ብር የስልክ ሎተሪን ለመግለጥ ‹መቼ ነው መብላት የሚጀመረው?›› ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል? መብላት ከተጀመረ ቆየ አይደለም እንዴ? መብላቱ አስቸግሮ አይደል እንዴ ፀረ ሙስና የሚባል መሥሪያ ቤት የተቋቋመው? አሁንኮ ሰው  መብላትንና መበላትን ለምዶት ‹ምናለ በልተው እንኳን ቢሠሩ› እያለነው፡፡›› የዐጸደ ሕጻናት አማርኛ ማስተማሪያ ይመስል ‹‹ጋን በጠጠር ይደገፋል›› የሚለውን አባባል ለማሳየት ጠላ የሞላ ጋን ማሳየት ያስፈልጋል? ግድቡ አሳዘነኝ፡፡ ‹እብድ የያዘው መልክ አይበረክትም› ማለት ይኼ ነው፡፡ 
 
ልጅቱ የሐር ነዶ የመሰለ ፀጉር ነው ነበራት አሉ፡፡ አልፈለገችውም፡፡ ፀጉር ቤት ገባችና ‹‹ቁረጭኝ›› አለቻት ፀጉር ሠሪዋን፡፡ ከከፈለቻት እርሷ ምን ተዳይዋ ልትመደምዳት ተነሣች፡፡ እዚያ ፀጉር ቤት ልትሠራ ገብታ የነበረች እናት ብትመክራትም ወጣቷ እምቢ አለች፡፡ ሴትዮዋም ‹‹ ይህን የመሰለ ፀጉር ማን እንዲህ ባለ ጭንቅላት ላይ ብቀል ብሎታል› አለች አሉ፡፡  
ሲሆን ‹በባሕል ትክክል ለመሆን› በዚህ ከፊሉ ሕዝብ በሚጾምበት ጊዜ የጥብስ ማስታወቂያ ባይኖር ጥሩ ነበር( የግድ መጠበስ ካለበት ወይም ጥብሱ በስፖንሰር የመጣ ካልሆነ)፡፡ ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው ለገንቦ ጠላ የሚጋደሉ ጠጪዎች ሀገራዊ ለውጥ አምጥተው የሚያውቁት? ‹ዶሮ ብታልም ጥሬዋን› ሆኖ ካልሆነ በቀር፡፡ የሦስት ብር ሎተሪ ለማስቆረጥ በገንቦ ጠላ መጣላት አመልን በቴሌቭዥን መግለጥ ካልሆነ ምን ሊሆን ነው፡፡
 
ወይ ግድቡን ‹የሕዳሴ ግድብ› ብለን መጥራታችንን እናቁም፤ ወይ ማስታወቂያዎቻችን ግድቡን የሚመጥኑ ይሁኑ፡፡ ያን የመሰለ ታላቅ ሐሳብና የትውልድ ሥራ በገንቦ ጠላ፣ በብረት ምጣድ ጥብስ፣ በጉንጭ ሙሉ ዳቦ መቀለጃ አታድርጉት፡፡   

የፊታችን አርብ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል! ‪
‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› —– ረቡእ የካቲት 18/2007 – ድምፃችን ይሰማ
Image
መንግስት ህገ መንግስታዊ መብቶቻችንን በመጣስ ላለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ በደል ሲፈጽምብን ቆይቷል፡፡ እኛም እንደህዝብ ድምጻችንን አዋሕደን እና በአንድነት ቆመን ሰላማዊ ትግል ስናካሂድ ቆይተናል፡፡ ትግላችን እስካሁን አንድም ከሰላማዊነት መርህ ዝንፍ ሳይል የቆጠለ ሲሆን መንግስት ትግሉን ለማስቆም የሚወስዳቸው ግልብ እና አገር አጥፊ እርምጃዎችም ከመርሃችን ሊያዛንፉን እንደማይችሉ በተደጋጋሚ በተግባር ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

ሰሞኑን መንግስት በተለመደው ግፍ መር እርምጃው በርካታ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን በማሰር ዘመቻ ላይ ተጠምዷል፡፡ አንዳችም ጥፋት ያልፈጸሙ ወጣቶችንም የ28 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ በመጠየቅ ወደማጎሪያ ካምፖቹ አስገብቷል፡፡ ይህ ‹‹ሙስሊሞችን በማሰር ከትግላቸው አስቆማለሁ!›› ከሚል መናኛ ቀቢጸ ተስፋ እና ባዶ ምኞት የመነጨ ለመሆኑ እማኝ መጥራት አያሻም – ካሁን ቀደምም መንግስት ሲፈጽመው የቆየው፣ ግና ሊያሳካቸው ያልቻለው ህልሙ ነውና!

አዎን! ደጋግመን ስናሳይ እንደቆየነው ሁሉ ህዝብን ማንገላታት አንጂ ማሸነፍ ፈጽሞ የሚቻል አይደለም! ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው! በአላህ ፈቃድ ያሸንፋልም! ይህን ህገወጥ እና ሊሳካ የማይችል እኩይ የመንግስት ምኞት በተለያዩ ስልቶች መታገል የነፍስ ወከፍ ሐላፊነታችን የሚሆነውም ለዚሁ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ በመሆኑም ከነገ ወዲያ አርብ የካቲት 20/2007 መላው አገሪቱን ያሳተፈ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል፡፡ የተቃውሞውን መርሃ ግብር አስመልክቶ በነገው እለት የምናሳውቅ በመሆኑ እስከዚያው መረጃውን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ ተዘጋጅተን እንጠብቅ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምጻችን ይሰማ! አላሁ አክበር!

‹‹ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል›› የታቦር ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ‹‹አንድ ሕፃን ልጅ ብቻ ሕይወቱ አልፏል›› የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ምክንያቱ በውል ያልታወቀው የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ከምሽቱ…

በዓለማዊው ህይወታችን ሳያዩ ማመን ከባድ ነው፡፡ ባሌ እባብ ሊሆን ይችላል ብሎ መኖርም ከባድ ነው! እርግጥ፤ “አንድ ቀን ቤተ መንግሥት ውስጥ እነቃለሁ” ብሎ ማሰብ ይቻላል፡፡ ግን ድካም አለበት፡፡ በቀስት ተጭሮ እንደመንቃት ቀላል አይደለም፡፡ ቃልኪዳንን መጠበቁን ይጠይቃል፡፡ ለማወቅ ጉጉት ለከት ማበጀትም ይፈታተናል፡፡ በልጦ መገኘትን ጠንቅቆ መቻል እንደው ያለጥረት የሚገኝ፣ ክብሪት እንደመጫርም የቀለለ፣ የዘፈቀደ ነገር አይደለም፡፡ በሀገራችን ተፎካካሪን […]

በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ ነው – ሚኒስትሩ * ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ ይዘረፋል!! የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር…

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ” የአገራችን ህዳሴና የሲቪል ሰርቪስ ሚና” በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሩ ስልጠና ባዘጋጀው ሰነድ ላይ፣ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘው የተማረው ክፍል በኢህአዴግ የመጨረሻው የማይታመነው ክፍል ነው ሲል ገልጾታል። “ይህ የተማረው ሃይል” ይላል ሰነዱ ” አመፅየመምራት፤ኢሳትና ቪኦኤን ከመሳሰሉ አፍራሽ ሚዲያዎች ጋር በመተባበር የቀለም አብዮት ለመምራት ፣ …

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አባይ ጸሃየ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሃይል እንደሚተገበር በድብቅ ሲናገሩ  መደመጣቸው ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አመጽን የሚጋብዝ ብቻ ሳይሆን ፣ ከዚህ ቀደም የደረሰው ደም መፋሰስ ሳይበቃ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዲኖር የሚጋብዝና የሰው ህይወት እንዲጠፋ የሚያደርግ ነው ሲል የሰብአዊ መብት ሊጉ ባወጣው መግለቻ ጠቅሷል። የባለስልጣኑ እብሪት …

የካቲት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የገዳሙ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከወልቃይት ተነስቶ በዋልድባ አብረንታት ገዳም አድርጎ ወደ ማይፀብሪ የሚሰራው መንገድ በ2004ዓ/ም በገዳሙ ፣በአካባቢው ሕብረተሰብ እና  በውጭ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጠንካራ ተቃውሞ የተነሳ ተቋርጦ ቆይቷል። መንግስት ወደ ገዳሙ የሚገባው ለአፈር ምርምር እንጂ መንገድ ለመስራት አይደለም በሚል የመንግስት ካድሬዎችና አንዳንድ መነኮሳትና የቤተክነት ሃላፊዎች …

የካቲት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያ የወንጀል ምርመራ ልዩ ክፍል ሃላፊ ኖሃህ ካቱሞ  100 ኢትዮጵያውያን ኬንያን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም አማርኛ የሚያስተረጉም በመጥፋቱ በማግስቱ መቀጠራቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል። አምና በተመሳሳይ መንገድ 95 ኢትዮጵያውያን ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። አገራቸውን እየለቀቁ ወደ …

በየዓመቱ እጅግ በርካታ የፕላስቲክ ቆሻሻ ባህር ላይ ይጣላል። በጎርጎሪዮሳዊዉ 2010ዓ,ም ብቻ ከ4,8 እስከ 12,7 ሚሊዮን ቶን ፕላስቲክ ዉቅያኖስ ዉስጥ ተጥሎ መገኘቱን የአዉስትራሊያና ዩናይትድ ስቴትስ ተመራማሪዎች መዝግበዉ ይፋ አድርገዋል።