ኢትዪጵያን ከፈለክ መጀመርያ እኔን ፈልገኝ!
(ራማቶሀራ ዴርቶጋዳ) ፅንፈኛው ወንድሜ! የልቤን ልንገርህ፤ ለዛሬ እንኩዋን ልብ ብለህ አድምጠኝ! ሕመሜ ይመምህ፤ሃሳቤ ያሳስብህ፤ስጋቴ ስጋትህ ይሁን፤ጭንቀቴም ይጭነቅህ፡፡ እባክህንማ አንዴ ዦሮህን ስጠኝ፤ህሊናህን አንዴ ከነጎደበት የማንአለብኝነት፤የትዕቢትና የትምክህት ዓለም ላንዴም ቢሆን ገታ አርገህ መልሰውና እኔን እህትህን ስማኝ፡፡ምናልባት ዛሬ ባትሰማኝ ነገ በሚፈጠረው ሁኔታ ዕድሜ ልክህን ሊፀፅትህ የሚችል ከፍተኛ ችግር ሊከሰት ይችላልና ግድ የለህም ስማኝ! አዎን! እኔም አንተም የአባቶቻችንን ታሪክና አገር እናውቃለን፤ባለፉት ስርዓቶች የኔም ያንተም ወገኖች የደረሰባቸውን ሁሉ እናውቃለን!!! እስኪ ስለዚህ ጉዳይ በግልፅ እናውራ:: ታድያ እኔ መሰረታዊ ናቸው የምላቸውን በገዢ መንግስታት ደረጃ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሱትን ሰብዓዊ ግፎች በወፍ በረር አስቃኝሃለው፤በዚህም ከውስጤ ያለው ቁስል ምን ያህል ያመረቀዘ እንደ ሆነ ላሳይህ እውዳለሁና ከቻልክ አንተም በኔ ቦታ ሆነህ ላፍታም ቢሆን አስበው! የታሪክን ሰበዝ ስንመዝ ግዜ ላለመፍጀት እንዲሁም የዚህ ፅሁፍ ዓላማው የኔን የእህትህን ስሜት በተቻለ መጠን ትጋራ ዘንድ ስንቅ የሚሆንህን መረጃ ማስጨበጥ ነውና ለውይይት ያህል ከሃ/ስላሴ ጀምሮ እስከ ደርግ ድረስ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀሙትን ዘግናኝ መንግስታዊ ግፎችን አንድ ሁለት እያልኩኝ አነሳልሃለው፡፡ ታድያ ወንድሜ! የምፅፈው ከልቤ ነውና አንተም ከልብህ አንብበህ ተረዳኝ፤የምፅፈው ለክርከርና ለሂሳብ ውርርድ አይደለምና! እስኪ ወንድሜ! አንተን በመጠየቅ ልጀምር! እውነት ስለ አፄ ሀ/ስላሴ ያለህን ስሜት ምንድን ነው? በጎ ወይስ መጥፎ? ስለ ደርግስ? እውነቱን እንነጋገርና አንተና መሰሎችህ እኮ ሀ/ስላሴን ሞዓ አምበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ፤መንግሰቱን ደግሞ ጉዋዱ፤ቆራጡ፤አገር ወዳዱ፤ጀግና እያላችሁ የሌላቸውን የዘር ሃረግና መለኮታዊ ስልጣን ሰጥታችሁ ስታወድሱዋቸው ነው የምትኖሩት! ወንድሜ እኔና ወገኖቼ […]